Thursday, May 2, 2013

ፕሬዝዳንት ኦባማና አፍሪካ




ፕሬዝዳንት ኦባማ በመጀመሪያ ተመርጠው ወደ ስልጣን ሲመጡ በርካቶች የአፍሪካን አህጉር ትኩረት ያደርጋሉ ብለው ተስፋን ሰንቀው የነበረ ቢሆንም የኦባማ ትኩረት ግን አሜሪካ ላይ ሆኖ ቀርቷል አሜሪካ 1930 ዎቹ ወዲህ በታሪኳ ከታላቁ የምጣኔ-ሀብት አዘቅት ለመጀመሪያ ጊዜ የገባች ሲሆን ይህም ኦባማን ትኩረታቸውን በአሜሪካ የውስጥ ጉዳይ ላይ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል

በአንድ በኩል አሜሪካ ራሷ በገጠማት ከባድ ምጣኔ-ሀብታዊ ቀውስና የመካከለኛው ምስራቅ ማለትም በኢራቅና በአፍጋኒስታን ባካሄደቻቸው ወታደራዊ ዘመቻዎች ሳቢያ የኦባማ አስተዳደር ትኩረቱን ወደ ውስጥ ለማድረግ ተገዷል    

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ኦባማ በተመረጡ ሰሞን ወደ ጋና ብቅ ብለው ለአፍሪካ አምባገነኖች ምንም አይነት ቸልተኝነት እንደማይኖር ገልፀው የነበሩ ቢሆንም በተግባር ግን የአሜሪካ ፖሊሲ ከአፍሪካ ዲሞክራሲ ይልቅ ለራሷ ብሄራዊ ጥቅም ሆኖ ዘልቋል ። « ጥቅም እንጂ ወዳጅ የላትም» የምትባለው አሜሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነት መርሆዋ ብሄራዊ ጥቅሟን ማስከበርን ያስቀደመ እንደሆነ አለም ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል ።

No comments:

Post a Comment