በተለያዩ ማህበረሰቦች አንድ ዘንድ ፣ ሞት የተለያየ ስያሜና ትርጓሜ ያለው ነገር ነው ። አንዳንዶች ሞት ፀጥታ ነው ፤ ሞት ትርጉም የለሽ የሆነ ነገር ነው ፤ ሞት ወደ መንፈሳዊው አለም መሸጋገሪያ ነው ፣ ሞት ወደ ሌላ ህይወት ወዳለው አካል መቀየሪያ ነው ፤ ለምሳሌ በሂንዱዎች አንድ ሰው ወደ ተለያዩ ህይወት ወዳላቸው አካላት ይለወጣል ብለው ያምናሉ ። አንድ ሰው ከነበረ ወደ ሌላ አንድ አይነት እንሰሳ ይለወጣል ሲሞት ተብሎ ይታመናል ።ሞት አገላለፁ ራሱ የተለያየ ነው ። ለምሳሌ አረፈ ፣ ነፍሱ ከስጋው ተለየች ፣ በሞት ተለየ ወዘተ የመሳሰሉ አገላለፆች አሉት ። ለምሳሌ በእንግሊዝኛው ብንወስድ (Passed Away , deceased) ፣ የመሳሰሉትን አገላለፆችን ይጠቀማል ።
ቀደምቱ ሰው ማሰብ ከቻለበት ጊዜ ጀምሮ ማን እንደፈጠረው ሲያስብና ሲጠይቅና ሲመራመር ኖሯል። የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በትላልቅ አውሬዎች፣በወንዞች ፣በፀሀይ፣በጨረቃ ፣በዛፍና ሌሎችም ከእርሱ አቅም በላይ ናቸው ብሎ በሚያስባቸው ነገሮች በሙሉ ሲያመልክ ኖሯል።
ሞት የተገለጠ መፅሀፍ ነው የሚያነበው የለም እንጂ ይላል መፅሀፍ ቅዱስ ይህም ሞት ለማንም ሰው የማይቀርና የታወቀ ነገር ቢሆንም ሰው ግን ይዘነጋዋል ማለት እንደ ማለት ነው ። ሀይማኖቶች በሰው ልጅ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖን የሚያሳድሩ ናቸዉ። የሰዉ ልጅ አምላኩ ትዝ እሚለዉ ከሞት ጋር ሲጋፈጥ ነው ። ሞት በራሱ ወይንም በሚወዳቸዉ ሌሎች ሰዎች ላይ ሲመጣ ወይም ራሱ ሞትን ሲጋፈጥ አምላኩን ያስታውሳል ። መፅሀፍ ቅዱስ «ሞት የተገለጠ መፅሀፍ ነው ፣ የሚያነበው የለም እንጂ» ይላል ። መፅሀፍ ቅዱስ ሞትን ከሀጢአት ጋርም ያያይዘዋል ። «የሀጢአት ደሞዙ ሞት ነው» ይላል ። ሞት በሐጢአት አማካይነት የሚከሰት ነገር አድርጎ ይገልፀዋል ። ይህም ለሁላችንም ሞት ከፊታችን የተደቀነ ነገር ይሁን እንጂ ስለሞት ረስተን ዘላለማዊ እንደሆንን አድርገን ነው እምንኖረው ።
ነገር ግን ሞት ለታላላቅ ሰዎችም አይቀሬ ነው ። ሊኦናርዶ ዳቬንቺ «ጊዜ የመልካም ነገሮች እኩይ አጥፊ ነው» ይለዋል ። ይሄውም ጊዜ በሰዎች ላይ ሞትን የሚያስከትል ነገር መሆኑን ሲገልፅ ሲሆን ይህ ብቻም ሳይሆን ጊዜ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ህንፃዎችንም ጭምር ያፈራርሳል ።
ሞት ለሰዉ ልጆች ሁሉ የሚቀር ነገር ባለመሆኑ ለማንም ሰዉ ጊዜዉን ጠብቆ ይሞታል። ከሞትና ከዉልደት ስናነፃፅር ሞት የተሻለ ፍትሀዊ የሆነ ነገር ሲሆን ዉልደት ግን እንደሞት ፍትሀዊ አይደለም ። አንድ ሰዉ ከመጥፎ እድል ፣ ከድህነት ፣ ወይንም ወይንም ከማንኛዉም ጥሩ ካልሆነ ጉድለት ጋር ሊወለድ ሲችል ፣ ሌላዉ ደግሞ ከሀብታም ቤተሰብ ወይንም ከንጉሳዉያን ቤተሰብ ሊወለድ ሲችል በውልደቱ ብቻ ከሀብትና ከፀጋ ጋር ሊወለድ ይችላል። በአንፃሩ ሞት ግን አንድ ሰው ሀብታም ሆነ ፣ ደሀ ሆነ ከነገስታት ተወለደ ፣ ምሁር ሆነ መሀይም ሆነ ፣ ፕሬዝዳንት ሆነ ሞት አይቀሬ ነው ።
ሞት ባይኖር ኖሮ አለማችን ምን ትመስል ነበረ? ሞት አዲስ ነገር እንዲፈጠር በሩን የሚከፍተዉ ሞት ሲሆን በሞት አሮጌዉ ተወግዶ ወይም ጠፍቶ አዲሱ የመተካትን እድልን ያገኛል።በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ መሞት የሌለባቸው ሰዎች ያለጊዜአቸው ሲሞቱ እጅግ አሳዛኝ ቢሆንም አዲስ ነገር የመፈጠር እድልን አያገኝም። ለምሳሌ ከመቶዎች አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች አሁን ድረስ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ ምን ይመስሉ ነበረ ብለን አስበን እናውቃለን ? ።
ይሁን እንጂ ሞት ከሰዉ ልጆች ጋር ዘላለማዊ የሆነ ነገር ቢሆንም ህይወትን ከማስቀጠል በላይ የሚያረካና የሚያስደስት ምንም ነገር የለም።ስዩም ወልዴ ራምሴ «የህይወት ጀልባ የምትቀዝፈው በመልካም ሰዎች በጎ ክንድነት ነው» ይላል፣ ይህም መልካም ሰዎች በሚሰሩት መልካም ስራ ነው የ ህይወት እምትቀጥቀለው ።
መሞትንና መኖርን ብናነፃፅር በህይወት ከመኖር ይልቅ መሞት ቀላል ነው ፤ ለዚህም ምክንያቱ አንድ ሰው ለመሞት ከፈለገ ኮረንቲ መጨበጥ ወይንም የሚበር መኪና ውስጥ ገብቶ ህይወቱን ማሳጠር ሲችል ፣ በአንፃሩ ግን ለመኖር አንድ ሰው መኖሪያውን ፣ የሚመገበውን ምግብ ፣ ለመኖር የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ነገር ማሟላት ይኖርበታል ፤ መኖር ይበልጥ ፈታኝና ትግልን የሚጠይቅ ሲሆን በአንፃሩ ግን መሞት መፍረስ ማለት እንደመሆኑ በጣም ቀላል ሆኖ ይገኛል ።
አንድ ሰው ከሞተ በኋላ ቢከሰስም ራሱን መከላከልም ሆነ ምክንያትን ማቅረብ አይችልም ። ስለዚህ የሞተን ሰው መክሰስ ከባድ የሚሆነው ። አንድ ሰው በዚህ ምድር ላይ ሊያደርግ የሚችለው ማንኛውም ነገር በህይወት እስካለ ድረስ ብቻ ሲሆን ፣ የሰራውን ስህተትን ጭምር በህይወት እስካለ ድረስ ማስተካከል የሚችል ሲሆን ፣ እንዲሁም ህይወቱን ወደ ሚለፈልገው አቅጣጫ መምራት ይችላል ። ከሞተ ግን እነኚህን ሁሉ ማድረግ አይችልም ። በህግም ጭምር አንድ ሰው እንደሞተ ህጋዊ መብቱን እንደሚያጣ የየሀገራት ህግጋት ደንግገዋል ።
መላእክት ጀርባ የሚታየው የብርሀን ድባብ ከቀደምቱ ጥንታዊው ሰው የፀሀይ - አምልኮ ስርአት የተወሰደ ሲሆን በጥንት ሳንቲሞች ላይ ይሄ በግልፅ ይታያል ። ለምሳሌ የመጀመሪያዎቹ የሳንቲም ገንዘብ ያሳተሙት በጥንት አክሱማውያንን ሳንቲሞች ብንመለከት በአንድ ገፁ የፀሀይ ወይንም የጨረቃ ምስል ይገኛል ። ግሪካውያንም ሆነ ሮማውያን የፀሀይ - አምልኮት ስርአትን የሚከተሉ ነበሩ ። በአሁኑ ጊዜ የመልአክትን ወይንም የቅዱሳንን ምስል ብንመለከት ከበስተጀርባው የፀሀይ ብርሀን ድባብን እናያለን ይሄም ከጥንቱ ሰው የፀሀይ አምልኮ ስርአት የተወሰደ ነው ።
አሁን በአለም ላይ የምናየው የማንኛውም ነገር አደራደርና አሰላለፍ ፣ ቀደም ባሉ በርካታ አስርት ፣ መቶ እና ሺ አመታት በተጣሉ መሰረቶች ላይ የተገነባ ነው ። በአለም ላይ ያለው የምጣኔ - ሀብት ፣ የሀይማኖት፣ የማንኛውም ነገር በገናናነትና ሀይል ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአለም ላይ በአሁኑ ሰአት የምናየውና የምንሰማው ፉክክር በአንድ በኩል የነበረውን የበላይነት አስጠብቆ ለመቀጠል ፣ በሌላ በኩል ደግሞያንን ሁኔታ ለመቀየርና አዲስ ነባራዊ ሁኔታን ለመፍጠር የሚደረግ ትግል በአለም ላይ ማየት የተለመደ ነው ።
ሞት እፎይታን «Relief»ን የሚሰጥ ነገር ሲሆን ፣ አንድ ሰው ለምሳሌ በማይድን በሽታ ቢሰቃይ ወይንም ቢያረጅ በህይወት ለመቆየት ከእርሱ ይልቅ እሱን የሚያስታምሙ ሌሎች ሊሰቀቃዩ ይችላሉ ፣ ሌላው ደግሞ እርጅና አንድ ሰውን ለመኖር አስቸጋሪ ሁኔታን ሊፈጥርበት ይችላል ፣ ስለዚህ ሞት እፎይታን የሚሰጥ ነገር ነው ። ይህ ብቻም ሳይሆን አዲሱ እንዲጀምር እድልን የሚሰጥ ነው ። ዝግተመ - ለውጥ ንድፈ ሀሳቦች እንደሚነግሩን አንድ ህይወት ያለው ፍጡር ተፈጥሮ እንክብካቤ የሚያደርግለት ራሱን እስከሚተካ ድረስ ብቻ ነው ። እራሱን ከተካ በኋላ ማለትም ራሱን የሚተካበት እድሜ ማለትም የወጣትነት እድሜው እያለፈ በሄደ ቁጥር ካለፈ በኋላ ግን ተፈጥሮ ፊቷን ታዞርበታለች ። ሰውነቱ ማርጀት ይጀምራል ፣ ህመም ይደራረብበታል ፣ አካላዊ መስህብነቱ እየጠፋ ይሄዳል ፣ ወዘተ …. ።
አንዳንድ ታላላቅ ሰዎች በህይወት ዘመናቸው የሚሸሹ ፣ የሚጠሉ እንዲሁም ማህበረሱ የሚፀየፋቸው ሊሆኑ ይችላሉ ። ነገር ግን ሲሞቱ በአንድ ጊዜ ተወዳጅ ሰዎች ይሆናሉ ። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ ። በአንድ በኩል የላቀ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ እነሱ ብቻ አሸናፊ መሆናቸው በብዙ ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ አይሆንም ፣ ሌላው ሰዎቹ ራሳቸው ባላቸው ከፍተኛ ችሎታ ወይም ስልጣን በመጠቀም ሰዎችን የማያስደስት ነገርን ሲያደርጉ ነው ። እነኚህ ሰዎች ካለፉ በኋላ ነው ማህበረሱ ትክክለኛ ዋጋቸውን የሚረዳው ።
No comments:
Post a Comment