Saturday, July 6, 2019

Sidama ክልል

የሲዳማን ክልልነት ጥያቄ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥት በድርድር እንዲፈታው ዐለም ዐቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን አሳስቧል፡፡ ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ #ICG ከናይሮቢ ቢሮው ባወጣው ወቅታዊ ሪፖርታዥ መፍትሄው የሕዝበ ውሳኔውን ቀን በቶሎ ቆርጦ ማሳወቅ ነው ብሏል፡፡ ዞኑ በተናጥል ክልልነቱን ካወጀ ደሞ እንደ ሀዋሳ ያሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች እስኪፈቱ የመንግሥት ምስረታውን እንዲያዘገየው መክሯል፡፡ ጉዳዩ በጥንቃቄ ካልተያዘ ደቡብ ክልል በሞላ ብጥብጥ ውስጥ ሊገባ ይችላል፤ ሕገ መንግሥታዊ ዝግጅት ሳይደረግ መንግሥት የሲዳማን ክልልነት ከተቀበለም ያው ግጭት ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ሕዝበ ውሳኔው በጊዜ ገደቡ ካልተካሄደ በመጭው የፈረንጆች ሐምሌ 18 የሲዳማ ክልልን በተናጥል ለማወጅ ሲዳማ ዞን በያዘው አቋም እንደጸና ነው፡፡ በተያያዘ ዜና የሲዳማ እጀቶዎች ዛሬ ሃዋሳ ላይ ባደረጉት ስብሰባ የትኛውንም ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ውሳኔ ላለመቀበል መወሰናቸውን የሲዳማ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

No comments:

Post a Comment