የትግራይ #ሁለተኛ ሰልፎች፣# ፖለቲካ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ |
ትግራይ # ሰልፏን አካሂዳለች፡፡ መቐለ ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ ተሰልፋለች፡፡ ከአሁን በፊት ሐምሌ ላይ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ በያኔው ሰልፍ ኢንጂነር ስመኘውን የልማት አርበኛና የኢትዮጵያ ባለውለታ መሆኑን ዘክሮ፣ #ሕግና መርህ ይከበር የሚል መፈክር በብዛት አስተጋብቶ፣ ከኤርትራ ጋር የተደረገውን እርቅ አወድሶ ሰው ወደቤቱ ተመልሷል፡፡ የዛሬው ለየት የሚለው የፌደራሉ ባንዲራ፣ የሌሎች ሰንደቅ ዓላማና የሕወሓት አርማ በብዛት በመውጣቱ ነው፡፡
ሰልፍ ሐሳብን መግለጫ መንገድ ነው፡፡ አንድ ሰውም ሰልፍ ሊወጣ ይችላል፡፡# አቤ# ጉበኛ የተሰኘው ዝነኛ ደራሲ፣ #የአቡነጴ ጥሮስን ሀውልት እየዞረ ሶሻሊዝምን አውግዞ የገባበት ጊዜ እንደነበር #ጋዜጣ ላይ አንብቤያለሁ፡፡ ሰልፍ ሐሳብን መግለጫ መንገድ እንጂ መንግሥትን የሚቀይር መድረክ አይደለም፡፡ ትራምፕ ተመርጦ ሲገባ የሂላሪ ደጋፊዎች ወዲያው ነበር ሰልፍ የወጡት፡፡ ሆኖም ተመራጩን ሰው ከዋይታወስ አላወጣቸውም፤# የትራምፕም ደጋፊዎች የሂላሪን ደጋፊዎች አላንጓጠጡም፣ አላጣጣሉም፡፡ ይሕ አንዱ የዴሞክራሲ መገለጫ ነው፡፡
እኛ ዴሞክራሲን የማናውቅ ኢትዮጵያዊያን ግን ሰው ሐሳቡን በነፃነት እንዲገልጽ እድል ሲያገኝ፣ መንጨርጨር እናስቀድማለን፡፡ስሪታችንም፣ እድገታችንም፣ መንግስታችንም አምባገነን ስለሆነ ከእኛ ሐሳብ ውጭ የሆነን ጉዳይ ስንሰማ እና ስናይ ያንገበግበናል፡፡ይህ ዴሞክራሲ ነው!! የትግራዩን ሰልፍ በዚህ መነጽር ማየት ይበጃል፡፡
ይሁን እንጂ ለመነጋገሪያ የሚሆኑ ጉዳዮች አይጠፉም፡፡ #ለአብነት የዛሬውን #የመቐለ ሰልፍ በዋናነት ያስተባበረው፣ #የትግራይ መንግሥት ሳይሆን እራሱ ሕወሓት #እንደሆነ የሚያሳዩ ነገሮች አሉ፡፡ #ይህ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊዎቹንና አባሎቹን አጀንዳውን እንዲያስተጋቡለት ወደ አደባባይ መጥራቱ ነውር የለውም፡፡ ችግሩ፣‹‹የትግራይ ሕዝብ #መርህና ሕግ ይከበር ብሎ ጠየቀ›› ብሎ ዜና ሲሰራና ሲያሰራ ነው፡፡ እነዚህ የሕወሓት አባላትም ሆኑ እራሱ ሕወሓት #ስድስት #ሚሊዮኑን የትግራይ ሕዝብ ሊወክሉ አይችሉምና፡፡
ሬኔ ላፎርት# Ethiopia _Climbing_ Uncertain _Mountain የሚል ትንተና ከአንድ ወር በፊት አስነብቦ ነበር፡፡ #በዚያ ጽሁፉ ላይ ‹‹#ሕወሓት #የትግራይ ሕዝብን ተከብበሃል በሚል ከፍተኛ ድጋፍ አሰባስቧል››ይላል፡፡ በጊዜያዊነትም ቢሆን አሁን ሕወሓትን መከላከያው አድርጎ የሚያስብ #ትግራዋይ ቁጥሩ እየበዛ መሆኑንም ይህ አውሮጳዊ ጸሐፊ ይገልፃል፡፡
በርግጥ #የትግራይ የፖለቲካ #ልሂቃንና የመሀል አገር ፖለቲከኛ የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደዚያ ዓይነት ስሜት ይፈጥራል፡፡ በብሽሽቅ የተሞላ የሚመስለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ ትግራይን የሚያይበት መነጽር ትግራዋይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያን አካሄድ በጥርጣሬ እንዲያይ የሚያደርገው ይመስላል፡፡ አቶ #ኢሳያስ #አፈወርቂ ሲመጡ፣‹‹ሕወሓትን አጥፋልን›› የሚል መፈክር ሲወጣ፣ ከተለያዩ አካባቢዎች ትግራዋይን ማዕከል ያደረገ ጥቃት ሲፈጸም፤ እነዚሁ ዜጎች ወደ ጎረቤት ሐገራት ሲሰደዱ፣ በየቅዳሜው አዲስ አበባ ላይ የሚታተሙ# መጽሔቶችና ጋዜጦች ‹‹ትግራይ ልትገነጠል ነው›› የሚል ፈጠራ ሲጽፉ ወዘተ፣ የትግራይ ሕዝብ አማራጬ ሕወሓት ብቻ ነው ብሎ እንዲያስብ ሆኗል፡፡
#የአረናው #ሊቀመንበር #አብርሃ ደስታም፣ ሰሞኑን # ቴሌቭዥ #በዋልታን በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንዳረጋገጡት፣ በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ክልል መንግሥት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ# ታክቲካሊ (#በስልት) መደገፍን መርጠዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ #ብአዴን #(አዴፓ) የክልላችንን ሕዝብ ለመከፋፈልና ለማዋከብ እየሰራ በመሆኑ፣ ሕዝቡ #ጠብመንጃ ወዳለው ሕወሓት ተጠግቷል ባይ ናቸው አቶ አብርሃ፡፡
እንዲያም ሆኖ ትግራይ ላይ የተካሄዱት ሰልፎች ማንንም የማይሳደቡ፣ ጎረቤት ሐገራትን ለሀገር ውስጥ አጀንዳዎች ትብብር የማይጠይቁ፣ ብሔሮችን፣ ድርጅቶችን፣ ቡድኖችንና ግለሰቦችን የማያጣጥሉ ሆነው የተካሄዱ መሆናቸውን ባለፈው ሳምንት የታተመችው #የተመስገን ደሳለኝ #ፍትሕ #መጽሔት አስነብባለች፡፡
#ጠቅላይ _ሚኒስትር #ዓቢይና ትግራይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ወደ #መቐለ የተጓዙት #ከጅግጅጋው የመጀመሪያ ጉዟቸው በኋላ ነበር፡፡ በወቅቱ በትግራይ ክልል ከፍተኛ ድጋፍ እንዳላቸው ያረጋገጡበት ነበር፡፡ #ሰማዕታት አዳራሽ በተካሄደው ውይይት ላይም ከክልሉ ሰዎች ጋር ጥሩ መግባባት እንደነበራቸው ታይቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ እና #ትግራይ የተኳረፉት #በአሜሪካ #ጉዟቸው ወቅት እንደሆነ የሚያምኑ ብዙ ናቸው፡፡ #በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች #ከዳያስፖራዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት የተናገሯቸው ንግግሮች ብዙዎችን እንዳስከፋ ይገመታል፡፡
በወቅቱ ዳያስፖራዎቹ ጥያቄ ሲጠይቁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አካባቢያቸውን እየጠቀሱ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን የገለጹ ሰዎች የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ሲያጣጥሉ ከመታየታቸውም በዘለለ የመለሱበት መንገድ ትግራይንና ሕዝቡ ጀግናዬ ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች አንኳስሷል ብሎ የሚያስብ ሰው ጥቂት አይደለም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ አሜሪካ የሄዱት ከሰኔ 16ቱ የግድያ ሙከራ በኋላ ስለነበር ፣‹‹ያንን ጥቃት ያደረሱት ሰዎች ለምን በስም አይገለጹም›› ተብለው ከአንዲት ትግራዋይ ጥያቄ ሲቀርብላቸው ‹‹ከደሙ ንጹህ ነን ልትሉ ከሆነ አይደላችሁም፤ ገና ማን ፋይናንስ እንዳደረገ፣ እንዳሰለጠነና እንዳሰማራ እየተጣራ ነው›› ብለው ተናገሩ፡፡ የዚህን ንግግር አሽሙር ‹‹ከጥቃቱ ጀርባ የትግራይ ሰዎችም አሉበት›› የሚል ነው ብለው የተረጎሙት ብዙዎች ናቸው፡፡ እስካሁንም ፍርድቤትም ሆነ አቃቤሕግ በዚህ ጉዳይ ላይ የወነጀለው ትግራዋይ ግን አልተገኘም፡፡
‹‹ብንሞትም አረቄ #ቤት አንሞትም›› የሚለው መልሳቸውንም አሽሙር አድርገው የወሰዱት ከጥቂት በላይ ናቸው፡፡‹‹#ሐየሎም አርዐያን ሰደበብን›› ብለው የተቆጡ #የትግራይ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡
‹‹በወቅቱ #ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሰው ዝመት እና ተዋጋ ሲሉኝ እኔ ዘምቻለሁ፤ አሁንም ቢሆን# ከኤርትራ ጋር ስላለው ጉዳይ ሕዝቡ አያገባውም እኔ ያልኩትን #ተቀብሎ መፈጸም አለበት›› ብለው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በአብዛኛው የትግራይ ኤሊት ዘንድ ንግግራቸው አልተወደደላቸውም፡፡ በአንድ በኩል ጦርነቱን መዋጋት የለብንም ይሉ የነበሩትን መለስ# ዜናዊን #ጦረኛ አድርገዋቸዋል የሚል ቅሬታ ሲሰማ፣ በሌላ በኩል በራሳችን ጉዳይ እንዴት አያገባችሁም እንባላለን የሚል ጥያቄም ያለው ትግራዋይ እንዲበዛ ሰበብ ሆኗል፡፡
‹‹ያለፉት 27 ዓመታት ቆሻሻ ናቸው›› የሚለው ንግግራቸውም፣ በሕወሓት ዙሪያ ያለውን የፖለቲካ ኃይል ይጎረብጣል፤ በሕወሓት የበላይነት ተመርቷል የሚል ትርክት ላለው ፖለቲካ ይህ የእርሳቸው ንግግር በሕወሓት ዙሪያ ላለው ትግራዋይ ምቾት አልሰጠም፡፡ጥፋቱም #ልማቱም በልክ መቅረብ አለበት ብለው የተከራከሩ ሰዎች ብዙ ነበሩ-በወቅቱ፡፡
አቶ መለስን #የርዕዮተዓለምና #የፖለቲካ #ሊቅ፣ #ሐየሎም #አርዐያን የጀግንነት ቁንጮ አድርጎ ለሚያምነው ለእያንዳንዱ ትግራዋይ ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ የአሜሪካ ንግግር ምቾት የሚሰጥ አይደለም፡፡ ስለ ቲም ለማ ሲያወሩም፣‹‹#ቲም ለማ ማለት #ደመቀ ነው፤ ሙፍሪያት ናት፣…››እያሉ ሲዘረዝሩ፣‹‹አምባቸው ሰላም ብሏችኋል፣ገዱ ሰላም ብሏችኋል…›› እያሉም የባለሥልጣናትን ሥም# ከየብሔሩ ሲጠሩ፣ ከ#ትግራይ አንድም ሰው አልጠቀሱም፡፡ ይህ ደግሞ የትግራይ ልሂቃን ‹#‹ከጠራኋቸው ውጭ ያሉት እንደ እኛ አይደሉም›› አሉ ብሎ ትርጉም እንዲሰጠው አድርጓል፡፡
በዚህና በመሰል ጉዳዮች #በፌደራሉ መንግሥትና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያኮረፈ ይመስለኛል፡፡ ለዚያም ነው በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ በከፊል እንደታየው የጠቅላይ ሚኒስትሩን #ንግግሮችና ፎቶዎች በትግራይ ሰልፎች ላይ ያልታዩት፡፡ #ሆኖም ግን አንድም ጊዜ በየትኛውም ሰልፍ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶዎች ሲቃጠሉ አልተስተዋለም፤ እርሳቸውን የሚቃወሙ #መፈክሮችም አልታዩም፡፡
No comments:
Post a Comment