Sunday, November 18, 2018

privatisation in ethiopia public enterprises

privatization ወይም የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወር ሂደት ምን መምሰል አለበት ? ፦

የኣለም ባንክ ተወካይ እንዳስታወቁት "የተደረገው ጉዳይ የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል የማዛወሩ ተግባር ቢሆንም፣ ይህም በራሱ በጣም የሚያበረታታ ለውጥ ነው፡፡ ይሁንና በእኛ ምልከታ ኢትዮጵያ ከፕራይቬታይዜሽን የበለጠ ተጠቃሚ የምትሆነው በእነዚህ ዘርፎች ውስጥ ተወዳዳሪነትን ማስፈን ስትችል ነው፤ እንደሚገባኝም የመንግሥት ዓላማም በዚህ አቅጣጫ መጓዝ ነው፤›› በማለት ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2011 በሰጡት መግለጫ ኣስታውቀዋል

ሲጀመር ያክስዮን ግብይትን እሚያቀላጥፍ ተቁዋም በሌለበት ሁኔታ ምንም እንኩዋን የምርት ገበያ ባለስልጣን የምርት ገበያ ባለስልጣን ecx ያክስዮን ግብይት እንዲያካሂድ የተሻሻለው አዋጅ ቢፈቅድለትም እና  የህግ ምእቀፍ ቢዘጋጅለትም ማገበያየት አልጀምረም ፥ ዝግጅት እያደረገ እንዳለ ገመገለጹ በስተቀረ ። ያክስዮን ግብይት የሚዛወሩትን የልማት ድርጅቶችን የሚከታተሉ በርካታ ቦርዶች ቢቁዋቁዋሙም ነገረ ግን የንግድና ኢኮኖሚውን ዘርፍ በሙያም በልምድም ከሚያውቁት ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ቦርድ አልተሾሙም ብዙዎቹ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ ስዎች ሲሆኑ እነኝህም በየዘርፉ ባለሙያዎች አለመሆናቸው ይታወቃል ባለሙያዎች አይደሉም ነገር ግን እንደ ታዛቢ እንዲሆኑ ሊሆን ይችላል  ቦርድ ላይ የተሰየሙት።  

ካክስዮን ገበያ መቁዋቁዋምና ስራ መጀመር በሁዋላ ያክስዮን ግብይት ተቆጣጣሪ መ /ቤት መቃዋቃዋም አለበት ፥ ባሁኑ ሰአት ያክስዮን ግብይትን የሚያጸድቁት ባለአክስዮኖች ባመታዊ ስብሰባ ወቅት ሲሆን መንግስት ግን ያክስዮን ግብይትን ወይም ዝውውርን የሚከታተልበት ተቁዋምም ሆነ ከ60 አመት በፊት የወጣው የንግድ ህግ አሁን ላለው ያክስዮን ግብይት መጠንና ዝውውር በቂ ስላልሆነ ሳይሻሻል እንዳለ ነው። የንግድ ህጉ ከዛሬ ነገ ይሻሻላል ቢባልም እስካሁን ድረስ ተሻሽሎ አልወጣም።
ዶ/ር አብይ ከመጡ ወዲህ የዚህ አይነት ዘመን ያለፈባቸው እና ለአሰራር አመቺ ያልሆኑ ህጎች ይሻሻላሉ ቢባልም በሚፈለገው ፍጥነት እየተሻሻሉ አለመሂናቸው አሳሳቢ ነው።
ይሁንና ግን የፖለቲካ መሪዎቹ ይህንን ዝውውር ለመፈፀም የሚያስችል አቅም ያላቸው አይመስልም አማካሪ ካልቀጠሩ በስተቀረ።

በሌላ ሃገር ቢሆን አማካሪዎችን በዘርፉ መቅጠር አማራጭ ነው የውጭም ሆነ ያገር ውስጥ አማካሪዎችን ቀጥሮ ማሰራት አስፈላጊ ነው ። ሌላው ( policy flexibility) አስፈላጊ ሲሆን የዚህን ያህል ግዝፈትና ኣይነት ያለውን ሪፎርም ለማድረግ የተሙዋልስ ወይም።ምሉዕ የሆነ የፖሊሲ ማሻሻያ ማእቀፍን መዘርጋት ያስፈልጋል ግማሹን አሻሽዬ ግማሹን አላሻሽልም ማለት አይቻልም።  ከፊል አሻሽላለሁኝ ከፊሉን ደግሞ በነበረው አስቀጥላለሁ የሚለው የመንግስት ፖሊሲ የሚያስኬድ አይመስልም። ለዚህም ይመስላል ትላልቆቹን የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል አዛውራለሁ ቢልም መንግስት ቀጣይ በምን መንገድ ነው እሚዛወሩት ? ዝውውር ከመጀመሩ በፊትስ የሚያስፈልጉት አዳዲስ ተቆጣጣሪ ተቁዋማት እነማን ናቸው ? መሻሻል ወይም እንደ አዲስ መውጣት ያለባቸው የህግ ማእቀፍስ ምን መምሰል አለበት እሚለው ፍኖተ ካርታ roadmap ያለው አይመስልም።

ያም ሆኖ ግን ወደ ግል የተዛወረ ሁሉ ስኬትን ያመጣል  አይደለም። ልምሳሌ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ በካናዳና ዩ ኤስ አሜሪካ ሲሳካ በታላቁዋ ብሪታንያ ግን አልሰራም።  በአውሮፓም የሰራባቸው አሉ ያልሰራባቸውም አሉ። 
የግል ባለሃብቶችም እነኝህን ትላልቅ ኩባንያዎችን ሲያስተድስድሩ የሚያገኙትን ትርፍ ወደ ውጭ እሚያሸሹት ከሆነና ድርጅቶቹን።በትክክል እማያስተዳድሩዋቸው ከሆነ ጉዳት ነው። ቀድሞ ልግል ባልሃብት ተሽጠው ከስረው የቀሩ ወይም የተዘጉ ድርጅቶች አሉ። ድርጅቶቹን ልምግዛት ወይም ለማስፋፋት በሚል የባንክ ብድር ወስደው ብድራችውን ሳይከፍሉ አገር ጥለው የጠፉ  አሉ።
ባሀገረ አሜሪካ ቱጃር አላሙዱ የሆኑ ግለሰቦችዋ ትርፋቸውን ወደ ስዊዝ ባንክ እያሸሹባት ነው።  ያሜሪካ መንግስት የስዊዝ ባንኮችን እስከመክሰስ የደረሰበት ግዜ አለ። እነ UBS እና ሌሎችም የስዊዝ ባንኮች የሃብታም ግለሰቦችን መረጃ ስጥ ኣልሰጥም በሚል የገቡበትን ውጥንቅጥ ማየት ይቻላል። 

"የስራ ፈጠራ "፦

መንግስት የስራ ፈጠራ ኮሚሽን አቁዋቁማል ይህ መልካም ሲሆን ስራ ፈጠራ በትእዛዝ እሚፈጠር ሳይሆን የፖሊሲ መሳሪያዎችን ( policiy) instruments መጠቀምን ይጠይቃል። በተለይም እብዛኛው የሃገሪቱ ሃብት በመንግስት የልማት ድርጅቶች በተያዘበት ሁኔታ እንዲሁም እንደ መብራት ሃይል ያሉት ከመንግስት ባንኮች ከፍተኛ ብድርን በወሰዱበት ሁኔታ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን  crowed out ከገበያው ውጭ በማድረጋቸው ወይንም ከውድድሩ ውጭ ማድረጋቸው የግሉ ዘርፍ በበቂ ሳያድግ ለዘመናት እንዲቀጭጭ አድርጎአል።
ያገራችን በተለይም የስራ አጥነት ከፍተኛ ምጣኔ ላይ ነው ያለው ለምሳሌ የተሻለች የበለፀገችና ትልቅ በምትባለዋ አዲስ አበባ ከተማ የስራ አጥነት ምጣኔው በመቶኛ ከ27 እስከ 30 በመቶ ድረስ ይደርሳል።

No comments:

Post a Comment