የፍትህ ሥርአት ማሻሻያ አንዳንድ ሃሳቦች " ፦
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፍትህ ስርአት ማሻሻያ እንደተጀመረ ጠ/ፍ ቤት አመራሮችን በመተካት ተጀምረዋል። እርምጃው የዘገየ ቢሆንም ለውጡ ግን አዋጆችን በማሻሻል መታገዝ አለበት በተለይም የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ሳይውል ሳያድር ሊሻሻል ይገባዋል። ይህ ጥፋተኛ ዳኞችን ያለተጠያቂነት የሚሸኘው አዋጅ ይሻሻላል "ጥፋትን የፈፀሙ ዳኞችን እስከ ወንጀል ድረስ ለመጠየቅ የሚያስችል ነው" ተብሎ የነበረ ቢሆንም የት እንደደረሰ አይታወቅም አዋጁ። እዚህ አገር ላይ ጥፋተኞችን ሳይጠየቁ መሸኝት የተለመደ ሲሆን ፥ ህጎቹ ራሱ በርካታ ክፍተቶች( legal loopholes ) በርካታ ናቸው ከእነኚህም በፍትህ ስርአቱ ያለው ዋነኛው ነው።
አመራር በመለወጥ ብቻ ሳይወሰን ለ60 አመታት ያህል የቆዪትን የፍትሃ ብሄርና የስ/ስ/ህጉ እንዲሁም የወንጀለኛ መቅጫ የስ/ስ/ህጉ መሻሻል የሚገባቸው ሲሆን አዳዲስ መውጣት ያለባቸውም ማውጣት ለፍትህ አሰጣጥ አመቺ ያልሆኑ ነባር ህጎችን መፈተሽ ያስፈልጋል። እንዲሁም ያመራር ለውጡ ወደ ታችኛው የ ፍ /ቤቶች አመራሮች ማለትም የመ/ ድረጃና ከፍተኛ ፍ/ቤት አመራሮች በነካ እጃቸው ይለወጡ።
ጠ/ሚር ዶ/ር አብይ በነካ እጃቸው ወደ ታች ያለው የስር ፍርድ ቤት አመራሮችን ማንሳት ይገባቸዋል። የፍርድ ቤቶች ዳኝነት ተበላሽቶ የከፋ ደረጃ የደረሰው ባቶ ተገኔ ጌታነህ የጠ/ፍ ቤት ፕ/ት በነበሩበት ወቅት ሲሆን በእርሳቸው የፕ/ትነት ዘመን በርካታ ፍርደ ገምድል ውሳኔዎች ተወስነዋል ብዙዎች አእምሮቸው የተነካበት ፥ ኑራቸው የተቃወሰበት ፤ በርካቶችም በሙስና የተነካኩበትና ተጠያቂነት የጠፋበት ሁኔታ ነበረ። ከእርሳቸው በሁዋላ የተሾሙት አቶ ዳኜ መላኩም ጠ/ፍ ቤቱን ለማሻሻል ጥረትን አድርገዋል ፥ በጠ/ፍ/ቤቱ በርካታ የባለጉዳይ መስኮቶችን በመክፈት በዲጂታል ወረፋ እንዲያዝ በማድረግ ፥ የቀጠሮ ግዜን በማማጠር ፥ የፋይል ክምችትን መቀነስ ችለው ነበረ ግን መሰረታዊ ችግሮቹ ግን ቀጥለው ቆይተዋል።
የጠ/ፍ ቤቱ ፕሬዝዳንቶቹ ጥቅማ ጥቅምም እጅጉን ተሻሽሎአል ይሁን እንጂ አቶ ዳኜ በርካታ ቅሬታ የሚቀርብባቸውን የስር ፍ/ቤት አመራሮችን አልነኩም ፤ ስለዚህ የእርሳቸው ጥረት የሚፈለገውን ለውጥ ሳያመጣ ቀርቶአል። የአሁኑዋ ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊም በቶሎ የስር ፍ/ቤት አመራሮችን በማንሳት ስራቸውን መጀመር አለባቸው አለበለዝያ ከላይ የእርሳቸው ጥረት ብቻውን ለውጥን አያመጣም። አዋጆችን ማሻሻል በእጅጉ አስፈላጊ ሲሆን ይሻሻላሉ የተባሉ አዋጆችም በፍጥነት መሻሻል አለባቸው።
No comments:
Post a Comment