#Activism #Strategy ፥
#አክቲቪዝም ከወሬ ነጋሪነት ወደ #tink tank ወይም #ፖሊሲ ቀራጭነትና መለስተኛ #ጥናትንና ንባብን በማድረግ ወደ ፖሊሲ ለመቅረጽ የሚረዱ ሃሳቦች አመንጪነት ምስደግ አለበት ። ፖሊሲ አውጭዎች ያንብቡትም አያንብቡትም በማንኛውም ዘርፍ አዲስ እውቀት ካለ በ#online በድረ ገጾች በማህበራዊ ሚዲያ ቢለቀቅ አይከፋም።
* * *
ባሁን #በፌስ ቡክ ዘመን እንዲሁም በርካታ #የቴሌቭዥን #ጣብያዎች ባሉበት ሰአት ዜናዎችና ፎቶግራፎች በአንድ ግዜ ይሰራጫሉ። ስለዚህ #ዜናዎችን #ፎቶግራፍ አሰራጭ ከመሆን ይልቅ ጥናታዊ የሆኑ ነገሮች /መረጃዎች ይመረጣሉ።
ሌላው ያገርን ስምና ጥቅምን የሚጎዱ መረጃዎች ቢገኙ እንኩዋን አለመለጠፍ። እርስ በእርስ መናበብና #ወቅታዊ ጉዳዪችን በሚገባ መረዳት ያሻል።
* * *
ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ሙያዎች። #specialise ማድረግ ። በተለይም #የማህበራዊ #ሳይንስ ዘርፎች #በታሪክ ፥ #በኢኮኖሚክስ #በህግ በውጭ ግንኙነት .. ወዘተ ዘርፎች #ሙያዊ #ምልከታን ማድረግ እንዲሁም ከአካዳሚ ተቁዋማትና #ከዩንቨርስቲ #ምሁራን ጋር መወያየት መቀራረብና በጉዳዩ ላይ ምሁራዊና ሙያዊ እይታን መያዝ ይገባል።
* * * *
ሰሞኑን መንግስት የጥላቻ ንግግሮችን #hate speech ለመግታት #ፖሊሲን ሊያወጣ እንድሆነ ተነግራል። ይህ ህግ ሁኖ ሲወጣ #ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትን እንዳይገድብ ጥንቃቄን ማድረግ ያሻል። #ድንበሩ የት ድረስ ነው #ሃሳብን በነጻነት መግለጽና #የጥላቻ ንግግር እሚባለው የቱ ነው ? እሚለው በአንክሮ መታየት አለበት።
No comments:
Post a Comment