Friday, February 6, 2015

Global Migration & Poverty



ዓለም አቀፉ የህዝቦች እንቅስቃሴና ፍለሰት (Migration)

በአሁኑ ወቅት ስደት ዋነኛ የህዝቦች መንቀሳቀሻ ነው ፡፡ በአረቡ ዓለም ያለው የህዝቦች መንቀሳቀስ ጦርነትን በመሸሽ እንዲሁም በላቲን አሜሪካ ያለውን የቡድን ግድያና ለአደንዛዥ እፅ የሚደረገውን ጦርነት በመሸሽ ምክንያት በአለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የአዳዲስ ህዝቦች እንቅስቃሴና ፍልሰት ይታያል ፡፡
አውሮፓ ህዝቡ እያረጀ በመሆኑ የተሟ የጤና እንክብካቤን ለማግኘት ለታዳጊጉ አገራት ወጣት ወደ አውሮፓ መምጣት እንዳለባቸው ይረዳሉ ፣ ነገር ግን በአብዛኛው ስለ ስደት ያለው አመለካከት አሉታዊ ጎኑ የሚበዛበት ሲሆን እንደ አሜሪካ ያሉ ሃገራት በስደተኞች የተቋቋሙ ናቸው ፡፡ ስደት የህዘብች ስብጥርንና የተለያዩ ህዝቦችን ወደ አንድ ሃገር በመግባት የሃገርን ገጽታ በበጎ ጎኑ የመለወጥ አቅም አለው ፡፡

ድህነት (Poverty)

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የተነበሩት ሊንደን ቢ ጆንሰን እ.አ.አ. በጥር 8 ቀን በ1964 ዓ.ም. በድህነት ላይ ለኮንግሬሳቸው ባሰሙት አመታዊ ንግግር ላይ ‹‹ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በድህነት ላይ ጦርነትን አውጃለሁ›› ብለው አስታወቁ ፡፡ ጆንሰን በታሪክ የመጀመሪያውን ጦርነት በድህነት ላይ ያወጁ ፕሬዝደንት ናቸው ፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ የዓለማችን መሪዎች እንዲሁም አለም አቀፋዊ ተቋማት እንደ የተባበሩት መንግስታትና አለም ባንክንና የአለም የገንዘብ ድርጅትን ጨምሮ ድህነት ላይ ጦርነትን አውጀናል ሲሉ በተደጋጋሚ ይሰማሉ ፡፡ የፕሬዝዳንቱ አላማ ‹‹የድህነትን ምልክቶችን ለማስታገስ ብቻ ሳይሆን፣ ለማዳንና ለመከላከልም›› ጭምር ነበረ፡፡ ከዚያ ወዲህ የአሜሪካ የፌደራል መንግስት ድህነትን ለመዋጋት ከ19 ትሪሊየን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል ፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁሉ ገንዘብ ምን ውጤት ተገኘ ተብሎ ቢጠየቅ ተገቢነት አለው ፡፡ ከዚህ ይልቅ አንዳንድ ባለሙያዎች በግል እርዳታን የሚያደርጉ እና የግል ኩባንያዎችና ሃብታም ደግ ግለሰቦች የሚሰጡት በመንግስት ከሚደጎመው የማህበራዊ ዋስትና ይልቅ ውጤታማ ሊሆን ይችላል ወይ ብለው ጠይቀዋል ፡፡ ከማህበራዊ ከመንግስት ይልቅ ውጤታማ ናቸው ወይ ብለው እስከ መጠየቅም ደርሰዋል ፡፡
በተመሳሳይም በአፍሪካ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ የአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለአፍሪካ አገራት ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ለግሰዋል ፡፡ ነገር ግን አፍሪካ ከድህነት ፈጽሞ በዚህ የእርዳታ ገንዘብ ከድህነት ያልተላቀቀች ሲሆን አፍሪካ ለውጥ ማምጣትና መነቃቃት የጀመረችው ኢንቨስትመንት ስታገኝና ከእርዳታው ይልቅ የንግድ ትስስርን በተለይም ከሩቅ ምስራቅ አገራት እንደ ቻይናና ህንድ ካሉ አገራት ጋር መፍጠር  በጀመረችበት ወቅት እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ በእርግጥ አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣችበት ባቸው ከ1960ዎቹ እስከ 90ዎቹ ድረስ መረጋጋት ርቋት መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በተበላሸ ወታደራዊ አገዛዝ በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ነግሶ መቆየቱና ይህን ተከትም የእርስ በእርስ ጦርነቶች በበርካታ የአፍሪካ አገራት መቀስቀሱ እንዲሁም አፍሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት የጦርነት አውድማ መሆኗ ለአፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ውድቀት አንዱ ሰበብ ሆኖ መቆየቱ አሌ አይባልም ፡፡ ይህ ጉዳይ አከራካሪ ሲሆን በርከታ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየትን ይሰጣሉ ፡፡

No comments:

Post a Comment