Friday, February 6, 2015

Ethiopia Queen of Sheba ንግስተ ሳባ በአረብ ታሪክ ጸሀፍት



‹‹ለሰብአ በመኖሪያቸው በአውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው ፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሯቸው) ፡፡ ከጌታሁ ሲሳይ ብሉ ፣ ለእርሱም አመስግኑ (አገራችሁ) ውብ ናት ፡፡ (ጌታችሁ) መሀሪ ጌታም ነው (ተባሉ) ፡፡ (ከማመስገን) ዞሩም ፡፡ በእርሱም ላይ የግድቡን ጎርደፍ ለቀቅንባቸው ፡፡ በአትክልቶቻቸውም ሁለትን አትክልቶች ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለ ጠደቻና ቆርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው ፡፡›› ሰብአ 15-16
      የዓረብ ታሪክ ፀሀፍት ይህ በቅዱስ ቁርአን ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ለየመን እንደተፃፈ አድርገው ይረጉሙታል ፡፡ ነገር ግን ከአፃፃፉ መረዳት እንደሚቻለው አገራችሁ  ‹‹ከጌታሁ ሲሳይ ብሉ ፣ ለእርሱም አመስግኑ (አገራችሁ) ውብ ናት›› ሲል በተፈጥሯዊ አቀማመጧ፣በወንዞቿ፣በተራሮቿ ውበትን የተጎናፀፈችውና የበርካታ እፅዋትና እንሰሶች መኖሪያ ለሆነችው ለአቢሲኒያ ወይንም ለአሁኑ ኢትዮጲያ እንጂ ለየመን እንዳልተነገረ መረዳት ይቻላል ፣ በአካባቢው ያለች ውብ ሀገር ኢትዮጲያ መሆኗንም ማንም አይስተውም ፡፡
      የአረብ ታሪክ ጸሀፊዎች በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ጠቢቡን ሰለሞንን በእየሩሳሌም ልትጎበኝ የሄደችውንና ስመ ገናናዋን ንግስተ ሳባን ወይንም በአረብኛው አጠራር ንግስት ቢልቂስ የየመን ንግስት አድርገው ያቀርቧታል ፡፡ እንደ አረብ የታሪክ ጸሀፍት ንግስተ ሳባን የኢትዮጶያ ንግስት ሆና በታሪክ የሰፈረችው በግብፅ ኮፕቲክ ቀሳውስት ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚል ርእስ ባዘጋጁት መፅሀፍ አማካይት የኮፕቲክ የታሪክ ፀሀፊዎች በየመንና በአቢሲኒያ መሀከል የነበረውን የሰላምና የጦርነት ግንኙነትን ወደ አፈ ታሪክ በመለወጥ ንግስቲቷን ሆነ ብለው ታሪክን በማዛባት የአቢሲያ ንግስት አድርገው አቅርበዋታል ባይ ናቸው ፡፡  
እንደ አረብ ታሪክ ጸሀፍት አባባል የግብፅ ኮፕቲክ ቀሳውስት ይህንን ያደረጉበት ምክንያት በወቅቱ በነበረው በምእራባዊቷ ሮማ ካቶሊካዊትና በምስራቅ አብያተ ክርስትያናት መሀከል በተነሳው የእምነት ልዩነት ምክንያት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ወደ ሮማ ካቶሊክ እንዳታዘነብል ለማባበል ሲሉ ያደረጉት ነው የሚል ነው ፡፡ 
በአረብ ታሪክ ፀሀፍት ከዚህም አልፈው ንግስት ሰባና በጠቢቡ ሰለሞን መሀከል ተፈጠረ የተባለውን ወሲባዊ ግንኙነት እና ምንሊክ የተባለ ንጉስ ተወለደ የሚለውን ክብር ነገስት ላይ የሰፈረውንም ጭምር ሀሰት ነው፣ ነቢዩ ሰለሞን ከሳባ ጋር ዝሙት ፈጸመ መባሉን ፈጣሪ ይቅር ይበለን ሲሉ ይተቻሉ፡፡
ይህ በንግስት ሳባና በንጉስ ሰለሞን መሀከል የተፈጠረው የደምና የስጋ ቁርኝት በኋላ ላይ የሰለሞናዊው ስርወ መንግስ በቀዳማዊ ሀይለስላሴ በ1966ቱ ዓብዮት ከስልጣን እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ አልፎ አልፎ በዮዲት ጉዲትና በዛጉዌ ስርወ መንግስት ፣ እንዲሁም  በግራኝ ጦርነት ወቅት በአንዳንዶች ግዛቶች አካባቢ የሰለሞናዊው ስርወ መንግስት አገዛዝ ለተወሰኑ ጊዜያት ከመቋረጡ በስተቀር ለሺህዎች አመታት ኢትዮጲያን ሲገዛ ለበርካታ ክፍለ ዘመናት በህዝቡ ዘንድ ተቀባይት ያለው ህጋዊ የስልጣን ምንጭ (Legitimacy) በመሆን አገልግሏል፡፡
‹‹ክብረ ነገስት›› የተባለው መፅሀፍ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው እ.ኤ.አ በ1932 ዓ.ም. በኦክስፎርድ ምሁር ሰር ዋሊስ በጅ ሲሆን ይህን የተፈጠረ የስጋና የደም ትስስር በንግስናና በፖለቲካው ዓለም ብቻ ሳይወሰን በኋላ ንጉሰ ምንሊክ ወደ እየሩሳሌም እንደሄደና የእስራኤላውያንን ኦሪት ፅላትንና ካህናትን ይዞ ወደ አቢሲኒያ በመምጣት በኢትዮጲያ የኦሪት ሀይማኖትን እንደመሰረተ ይናገራል[1] ፡፡


[1] የቅርቢቱ ዓለም እውነታዎች ፣በሃሩን የህያ ፣ ትርጉም አህመድ ሁሴን (አቡ ቢላል)፣ ጥር 2002 ነጃሺ ማተሚያ ቤት፣አዲስ አበባ

No comments:

Post a Comment