Friday, February 6, 2015

ፍትሀ ነገስትና ዘመናዊ የኢትዮጲያ ህግ



ፍትሀ ነገስት ለሃገራች ህግ መሰረት ሲሆን ይሄው ፍትሀ ነገስት መሰረት የሚያደርገው መፅሐፍ ቅዱስን ነው ፡፡ ከቅዱሳን መፅሀፍት ለህግ ልዩ ትኩረትን ይሰጣሉ ፡፡ ማንኛውም ሃይማኖት አንዱ ክፍል የሚሆነው ህግ ነው ፡፡ ለምሳሌ በክርስትና ሃይማኖት በሃገራችን ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የፍትሀ ነገስት የህግ መፅሀፍ ሲሆን በእስልምና ሃይማኖትም የሸሪአ ህግና ይህንንንም ለመተርጎም የሸሪአ ፍርድ ቤቶች አሉ ፡፡ በሃገራችን ከሳሽና ተከሳሽ ከተስማሙ ጉዳያቸው በሸሪአ ህግ እንዲታይ መፍቀድ ይችላሉ ካልተስማሙ ግን ወደ መደበኛው ፍርደፍ ቤት ሄደው እንደሚዳኙ የሃገራችን ህግ ይደነግጋል ፡፡
እግዝአብሄር አዳምንና ሄዋንን ከፈጠረ በኋላ መጀመሪያ የሰጣቸው ነገር ህግ ነው እርሱም ከዚያ ከተከለከለችዋ የበለስ ፍሬ እንዳትበሉ የሚል ነበረ ፡፡ አዳምና ሄዋንም ይህንን ህግ በመጣሳቸው ግን ከገነት እንደተባረሩ እና ለምድር ስቃይ እንደተዳረጉ እንረዳለን ፡፡ ፍትህ እጅግ ከባድ ነገር በመሆኗ ስጋ ለባሽ ሊያመጣት እንደማይችል መፅህፍ ቅዱስ ‹‹ከመሀከላቸው አንድስ እንኳን ፃድቅ የለም›› ስለዚህ ያ ፍፁም ፍትህ ሊመጣ የሚችለው ከምድር ስጋ ለባሽ ነገስታት ሳይሆን ከእግዝአብሄር ነው ፡፡ እየሱስ ክርስቶስም በእውነት ለመፍረድ ተመልሶ እንደሚመጣና የፍትህና የሰላም አለቃ እንደሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ያስረዳል ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ለፍትህ ትልቅ ቦታን ይሰጣል ‹‹እውነትና ፍትህ የዙፋንህ መሰረት ናቸው›› መዝሙር ዳዊት ላይ ሲል ፍትሀ ነገስትም ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 44 ምእራፍ 4 ላይ ‹‹በወገኖቹ መሐከል በእውነት መፍረድ ይገባዋል›› ይላል፡፡ ያም ሆኖ ግን ፍትህ የነገስታት የዙፋንና የአንድ ህዝብ ውስጣዊ ሰላም መሰረት በመሆኗ ሰው በሚችለው አቅም ከትክክለኛው ፍትህ ማፈንገጥ እንደሌለበትና እንደ እግዝአብሄር ፍፁም ፍትህን ማስፈን ባይችልም የሰው ልጅ ከትክክለኛው የፍትህ መሰረት መውጣት እንደሌለበት ያስገነዝባል ፡፡
መፍረድ እጅግ ከባድ የሆነ ነገር ነው ፡፡ በሃዲስ ኪዳን መፅፍ አንዲት ሴት ዝሙትን ፈጽማለች ብለው አይሁዳውያን ለእየሱስ ክርስቶስ በድንጋይ ተወግራ እንድትገደል ዘንድ  እንዲፈርድባት ለእየሱስ ክርስቶስ ያመጡለታል ፡፡ አይሁዳውያኑም የተለመደው ፍርድ በድንጋይ ተወግራ መገደል ነው እንደዛም ብሎ ይፈርዳል በሚል ድንጋይ ከምረው በእጃቸው እያነጠሩ ውገሯት እስከሚል ድረስ ይጠብቃሉ ፡፡ እየሱስ ግን የጠየቃቸው ከእናንተ መሀል ንፁህ የሆነ ሃጢአት የሌለባት ይውገራት ብሎ ፈታኝ ጥያቄ አቀረበላቸው ነገር ግን ከእነርሱ አንዳቸውም እጃቸውን በእርሷ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆን አንድ በአንድ ጥለው ሄዱ፡፡ ‹‹አትፍረድ ይፈረድብሃል›› የሚለው የመፅሀፍ ቅዱስ አባባልም የሚያስረዳው ይሄንን ነው ፡፡   
ሃዋርያው ጳውሎስ በኦሪት ዘመን የታወቀ የህግ መምህር በነበረው በገማልያ እግር ስር ሆኖ ህግን ያጠና ሲሆን የኦሪትንም ሆነ የሙሴን የአይሁዳውያን እንደ ብርቅና አይነኬ አድርገው የሚያዩዋቸውን ህግጋት የተማረና ያጠና ሰው ነበረ ፡፡ ለሮሜ ሰዎች በላከው መልእከት ላይም ሮሜ ምእራፍ 2 ፣ ቁጥር 12 - 16 ላይ እንዲህ ይላል ፡፡
‹‹ያለህግ ሃጢአትን ያደረጉ ያለህግ ይጠፋሉ፣ ህግም ስላላቸው ሃጢአት ያደረጉ ሁሉ በህግ ይፈረድባቸዋል ፣ በእግዝአብሄር ፊት ህግን የሚደርጉት ይፀድቃሉ እንጂ ህግን የሚሰሙ ፃድቃን አይደሉምና ›› 
ከዚህ አባባል የምንረዳው ያለህግ ስልጣኑን ተመክቶ ሃጢአትን የሚሰራ እርሱም በተራው ሌሎች ከእርሱ የበለጠ ስልጣን በእጃቸው ሲገባ እርሱ ያደረገባቸውን መልሰው ያደርጉበታል ሲሆን ህግ አለኝ ብሎ ህግ በኔ ወገን ነው በሚል ትምክህት ራሱ ያወጣውም ለራሱ እንዲመቸው አድርጎ ራሱ ባወጣው ህግ ሌሎችን ሲዳኝ ፣ ሲቀጣ ራሱ በሰራው እስር ቤት ሲያጉር ኖሮ እርሱም በተራው ሲሻር ህጉ የህጉ ስልጣንና ሃይል በሌሎች እጅ ሲገባ እርሱ ህጉን ጠቅሶ ሌሎች ላይ ያደረገውን ሌሎችም ያንን ህግ መልሰው ጠቅሰው እርሱ ላይ መልሰው ይቀጡታል ፣ ይህ በዓለምና በሃገራችን ታሪክ በተደጋጋሚ የታየ ሃቅ ነው ፡፡ ትክክለኛውን  ህግ በእግዝአብሄር ፊት የሚያደርግ ግን ይፀድቃል ፣ የተመሰገነ ይሆናል ፡፡   
እግዝአብሄር ህዝቡ ‹‹ከጠላቶቻቸው ስቃይና መከራ ሲደርስባቸው›› አምላክ እንዳዘነ መሳፍንት 2፣18 እንዲሁም ‹‹ንፁህ ደም ያፈሰሱ እጆች›› ምሳሌ 6፣16 ፣17 ላይ በአምላክ ዘንድ የተጠሉ እንደሆኑ መጽሀፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡

የክስ አቀራረብና ስነ - ስርአት



አንድ ሰው ፍርድ ቤት ሲሄድ በክስ ማመልከቻው ላይ በሚያቀርብበት ወቅት በግልፅ ችሎቱ የማየት ስልጣን አለው ስለዚህም ፣ ይፈረድብኝ ወይንም ይፈረድልኝ ብሎ ምሎ ነው ፡፡ የክስ ማመልከቻውን በሚያቀርብበትም ጊዜ መጀመሪያ የሚለው ይህ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን አለው በሚል አረፍተ ነገር ነው ፡፡ ይህን አካሄድ ሳይከተልም ማንኛውንም ክስም ሆነ አቤቱታን ማቅረብ አይቻልም ፡፡
አንዳንድ ጊዜ ህግ ሲወጣ ወይም አንድ አዋጅ ሲታወጅ ሆነ ተብሎ የሚተው ክፍተት እና አሻሚ የሆኑ ቃላቶች ስራ ላይ ሊውሉ ይችላሉ ፤ ይሄውም በተከራካሪ ወገኖች ብርታት እንዲሞላና አንደኛው ተከራካሪ ወገን ሌላ ወገን ተከራካሪ ወገን በማይኖርበት ወይንም ጠያቂ የማይኖርበት ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ያለውን ክፍተት እንዲጠቀምበት እና ጉዳዮችና እና ንብረቶች ባለቤቶች እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ፡፡ ባለቤት የሌላቸው ንብረቶች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ አንድ ንብረት ሌላ ተከራካሪ ከሌለው የኔ ነው ለሚል ወገን ሊፈረድለት ይችላል ፡፡
ሌላው በወንጀል ህጉም ሆነ በፍትሐ ብሄር የስነ ስርአት ህጉ ላይ በግልፅ አስን እንደተነደነገገው ፅጥቅነሙን ለማስከበር ክዶ መከራከር ይችላል ፡፡ ነገር ግን ከሳሽ ወይም ተከሳሽ ሳይሆን በሐሰት ለሌላ ሰው ጥቅምን ለማስገኘት ወይንም ሌላውን ሰው ለማሳሰር ቢዋሽ ወይንም በሀሰት መረጃ ቢያቀርብ ግን በህግ ተጠያቂ እደሚሆን በግልፅ ተደንግጓል ፤ አንዳንድ ሰዎች ከሳሽ ወይንም ተከሳሽ በሚሆኑበት ወቅት ክዶ መከራከር ጥቅማቸውን ሎያስከብር እንደሚችል ከፍ ግምት ውስጥ ባለማስገባት ወይም ባለማወቅ ወይንም የህግ አማካሪን ባለመያዝ ሲጎዱና በባላጋራቸው የበለጠ ጉዳት ሲደርስባቸው ይስተዋላል ፡፡ ራሱ ሰበር ሰሚው በወሰናቸው ውሳኔዎች ላይም በግልፅ እንደሚተነትነው ተክዶ ቢከራከሩ ኖሮ እንደዚህ ይሆን ነበረ ነገር ግን ስላልተካደ እሚወሰነው እንደዚህ ነው በማለት ትንታኔ ሲሰጥ ይስተዋላል ፡፡  
በአንድ የሰበር መዝገብ ላይ በተደረገ ክርክር የቤት ሽያጩ መደረጉ ሳይካድ ነገር ግን የአፃፃፍ ፎርሙን አልጠበቀም በሚል ሽያጩ ይፍረስልኝ የሚል ክስ ተቀባይነት እንደሌለው ሰበር በሰጠው ውሳኔ ላይ ማየት ይቻላል ፡፡ በማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ጋር በተገናኘ ውል መኖሩን በማመን ነገር ግን ውሉ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1723 መሰረት የተከናወነ አይደለም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተቀባይት የሌለው ስለመሆኑ እንዲሁም 1723 (1) መሰረት የሚደረግ ምዝገባ ዓማላማ በተዋዋይ ወገኖች መሀከል ውል መኖሩን ለማስረዳት መሆኑን በፍ/ብ/ቁ 1723 (1) ፣ እና በፍ/ብ/ህ/ ቁ 2878 መሰረት አድርጎ በ13ኛው ቅፅ 2004 ዓ.ም. በሰ/መ/ ቁጥር 36887 ላይ ትንታኔን ሰጥቶበታል ፡፡
  ዞሮ ዞሮ በቃልም ይሁን በፅሁፍ ይደረግ ሁለቱ ወገኖች ውል አለን ብለው እስካመኑ ድረስ ውሉ የሚፀና ነው የሚሆነው ውል የለንም ብለው ሁለቱም ወይም አንደኛው እስካልካደ ድረስ ፣ የውል አፃፃፍ ፎርሙን አልጠበቀም በሚል ብቻ የታመነ ውል ሊፈርስ እንደማይችል መረዳት ይቻላል ፡፡ አንዱ ውል አለን ቢልና አንደኛው ቢክድ እንኳን በውልና ማስረጃ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት የተረደረገ ውል እስከሌላቸው ድረስ አንደኛው ወገን  ያልተረጋገጠን ወይንም በማስረጃ ሊረጋገጥ የማይችልን ውል እንዲፈፅም አይገደድም ፡፡   
በወንጀል ህጉ አንቀፅ 252 ላይ እንደተመለከተው በቁጥ 1 እስከ 3 ላይ ሲመለከት ሐሰተኛ ቃል ቢሰጥ እንዲሁም ፣ ዳኝነት ነክ ስልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ በሚወሰን ጭብጥ ላይ እያወቀ አግባብነት ያላቸውን ፍሬ ነገሮችን እያወቀ ሐሰተኛ ቃሉን የሰጠ እንደሆነ ከ3 እስ 5 አመት ሊደርስ በሚችል ፅኑ እስራት ሊቀጣ እንደሚችል ሲደነግግ በዚሁ አንቀፅ በቁጥር 3 ላይ ግን ይህንን ያደረገው ተከተራካሪው ወገን ጥቅሙን ለማስከበር ሲል ለሚያቀርበው ትክክኛ ያልሆነ ከክርክር እነዚህ ከላይ የተመለከቱት አንቀፆች ተፈፃሚ እንደማይሆኑ ይደነግጋል ፡፡
በተመሳሳይም በ1958 ዓ.ም. የወጣው የፍትሀ ብሄር የስነ - ስርአት ህጉ አንደውም ተከራካሪው ወገን ሊክድ የፈለገውን ግልጥ አድርጎ መካድ እንዳለበት ይደነግጋል ፡፡ በስ/ስ/ቁጥር 83 ላይ ተከሳሹ የቀረቡትን ነገሮች ሁሉ በዝርዝር እና በግልፅ ክዶ በመቃወም ነው ፡፡ እንደዚሁም ከሳሹ ተሰከሳሽ ሆኖ መልስ በሚሰጥበት ጊዜ የቀረበበትን ክስ በዝርዝርና በግልፅ መካድ አለበት ፡፡ ስለ ካሳ ጥያቄ የቀረበውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ካልሆነ በስተቀር በክሱ ላይ የቀረበውን ነገር በግልፅና በዝርዝር ያለመካድ ያልተካደውን ነገር በከፊል ሆነ በሙሉ አምኖ እንደመቀበል ያስቆጥራል ይላል ፡፡

የህግ መሰረትነት



ለአንድ ማህበረሰብ ውስጣዊ ሰላም ዋነኛው መሰረት ህግ ነው ፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንደሚለው ‹‹የትም ቦታ ያለ ኢ - ፍትሀዊነት ፣በሌላ ሁሉም ቦታ ላለ ፍትሀዊነት አደጋ አለው››፡፡ የውጭ ወራሪ ቢመጣ መንግስት የራሱ መከላከያ ወታደራዊ ሃይል አለው ይመክተዋል ፣ ይህም መንግስት በሚሰበስበው ግብርና ብድር የራሱ ባጀት የሚመደብለት እንዲሁም መንግስት የራሱ የውጭ ግንኙነትና የዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ውስጥ ባለው የዲፕሎማሲ ልኡካንን በመላክም ይሁን እዚህ ያሉትን ተወካዮቻውን ጠርቶ በማነጋገር ፣ ደህንነት እና የመሳሰሉት ተቋማትን በመጠቀም መንግስት የአንድ አገርን ብሄራዊ ጥቅም ያስጠብቃል ፡፡ የዜጎች መብት ግን በእንደዚህ አይት መንገድ አይከበርም ፡፡ የዜጎች መብት የሚከበረው በህግ የበላይትና በህግ ልእልና መሳሪያነት ነው ፡፡ 

የህግ ምሁራን እንደሚናገሩት ለአንድ ማህበረሰብ ውስጣዊ ሰላም ህግ መሰረት ነው ፡፡ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንደሚለው ‹‹የትም ቦታ ያለ ኢ - ፍትሀዊነት ፣በሁሉም ቦታ ላለ ፍትሀዊነት አደጋ አለው››፡፡ የውጭ ወራሪ ቢመጣ መንግስት የራሱ መከላከያ ወታደራዊ ሃይል አለው ይመክተዋል ፣ ይህም የራሱ ባጀት የሚመደብለት እንዲሁም መንግስት የራሱ የውጭ ግንኙነት ፣ ደህንነት እና የመሳሰሉት ተቋማትን በመጠቀም መንግስት የአንድ አገርን ብሄራዊ ጥቅም ያስጠብቃል ፡፡ የዜጎች መብት ግን በእንደዚህ አይት መንገድ አይከበርም ፡፡ የዜጎች መብት የሚከበረው በህግ የበላይትና በህግ ልእልና መሳሪያነት ነው ፡፡   

ሰበር ችሎት ምንነት



የዳኝነት አካሉ የዜጎች በህግ ፊት እኩል የመሆንን ፣እንዲሁም ፍትህ የማግኘት መብት በህገ መንግስቱ የተረጋገጡትን ለማስፈፀም የተቋቋመ አካል መሆኑ በህገ መንግስቱ እውቅና የተሰጠው መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ የሰበር ስርአት አላማው ወጥ የሆነ የህግ አተረጓጎም እና አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል ነው ፡፡ የሰበር ስርአት የህግ የበላይነትን ለማረጋጥ የተቋቋመ እና ማረጋገጫ ዘዴ ነው ፡፡ የውሳኔዎች ወጥነትና ትክክለኝነት የሚረጋገጠው በዳኝነት አካሉ የመጨረሻ አካል በሆነው በሰበር ሰሚ ችሎት ነው ፡፡ የህግ ስህተት ያለበትን ውሳኔ ፀንቶ እንዲቆይ ማድረግ የዳኝነት አካሉ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ተአማኒነትና ከበሬታን ይጎዳል ፡፡ይህንንም ለማስተካከል ይህ የዳኝነት አካል ስልጣን ተሰጥቶታል ፡፡ ከዚህ በኋላ የዳኝት ስርአቱን እርከኖችን ከጨረሰ በኋላ አንድ ሰው ሊሄድ የሚችለው ወደ ህገ - መንግስታዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወደሚገኘው ተቋም ይሆናል ፡፡ አንዳንድ ግዜ ህግ ሲተረጎም የግለሰቦችን ወይንም የተቋማትን የማይገሰሱ ህገ - መንግስታዊ መብቶችን ሊጥስ ይችላል ይህን ለማስተካከል ደግሞ የህገ መንግስዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሊያያቸው እንደሚችል ተደንግጓል ፡፡   
ይህ ስርአት ከቀድው የግርማዊ ንጉሰ ነገስት የዙፋን ችሎት የነበረና በኤፌደሪ ህገ መንግስት በ1987 ዓም በወጣው በአንቀትፅ 83 ስር የሚገኝ ሲሆን ዝርዝር በአዋጅ ቁጥር 25 / 1988 እና አዋጅ ቁጥር 454 /97 የተደነገገ ስርአት ነው፡፡ ይህ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች የሚሰየሙበት ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም ራሱ በሌላ ጊዜ እስካለወጠው ድረስ በየትኛውም ደረጃ ለሚገኝ የዳኝነት አካል አስገዳጅ ሃይል (ፕሪሲደንስ) ያለው ስለመሆኑ በአንቀፅ 2 (4) ተቀምጧል፡፡  በዚህም መሰረት ሰበር ችሎቱ የቀድሞውን ውሳኔ በአዋጅ ቁጥር 454 / 1997 አንቀፅ 2(4) መሰረት መለወጥ እንደሚችል ተደንግጓል ፡፡

አፍሪካ



አፍሪኮም በሰሜን ማግሬብንና በደቡብ የሳህራ በረሃንነና የማግሬብ ክልልን ለመቆጣጠር ነው ፡፡ አሜሪካ በስፔን ወታደራዊ የጦር ሰፈር የከፈተች ሲሆን ከዚህም በመነሳት በምእራብ አፍሪካ የሚሆነውን ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅምንና ቅርበትን ይፈጥርላታል ፡፡
አፍሪኮም ትልቁ ወታደራዊ መደብ ነው አሜሪካ በአፍሪካ ያላት ፡፡ የአሜሪካ የአፍሪካ ኮማንድ ሲሆን የአሜሪካን ጥቅም  በተፈጥሮ ሀብት በሃይልና በአሸባሪነት ያላትን ለመቆጣጠር ነው ፡፡ ከመስከረሙ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ አሜሪካ በአፍሪካ የዚህ አይነት ወታደራዊ እዝ መደቦችን ስትፈጥር ነው ፡፡ ትኩረቱም በሰሃራና በማግሬብ ክልል አካባቢ ነው የአሜሪካ የዚህ የጦር መደብ ትኩረት ፡፡
      ነገር ግን ይህ የአሜሪካን ጥቅምን መሰረት በማድረግ ቢሆንም ነገር ግን ይህ የአፍሪካ  ህዝብ ጥቅምን ይወክላል ወይ ነው ጥያቄው ፡፡
ነገር ግን አሜሪካ ወደ አፍሪካ ዘግይታ ሲሆን የመጣችው በአብዛኛውም እርዳታን ላይ ትኩረትን የሚያደርገው የአፍሪካ አሜሪካ ፖሊሲ አፍሪኮምን በማቋቋም ከአፍሪካ ጋር ግንኙነትን ቢመሰርትም ውሎ አድሮ ግን ከቻይና ጋር የተፈጠረው የንግድና የምጣኔ ሐብት ግንኙነት ለአፍሪካም ለቻይናም የበለጠ ውጤታማ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው ፡፡
እንደ ህንድ ባሉ አገራት የንፋስና የጸሀይ ሀይል የበለጠ ጥቅምን አስገኝቷል የሚሉ ተቺዎች አሉ ፡፡ ከትላልቅ የሃይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶች ይልቅ ፡፡
የአፍሪካ ዲያስፖራና በአፍሪካ ያሉ መንግስታት እርስ በእርስ መናበብ የሚጎድላቸው  ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ዲያስፖራው በሃገሩ ካሉ መንግስታት የመረረ ጥላላቻ ስለሚኖረው በአገሩ ካሉ መንግስታት ጋር ተቀናጅቶ የመስራት ገዳይ ከሌሎች ዲያስፖራዎች ለምሳሌ ከቻይናም ሆነ ከህንድ ዲያስፖራ በተለየ መልኩ የአፍሪካ ዲያስፖራ የሚፈለገውን አቅም ቢኖረውም ለአህጉሩ ሊያበረክት እንዳልቻለ መገመት ይቻላል ፡፡