Friday, February 6, 2015

The Prophet



ነቢይ


የአሲሪያውያና ዋና ከተማ የነበረችው ነነዌ ከታሪክ ገጽ እንደምጥትጠፋ በመጽሃፍ ቅዱስ ተንብዮአል ፡፡ የነነዌ አሸናፊዎች እነ ልክ እነርሱ እንዳደረጓቸው ያደርጓቸው ፡፡አሲሪያ እን አንድ አገርን ስትማርክ ህዝቡን ታሰቃይና ደማቸውን ታንዠቀዥቅ ነበረ ፡፡ ደማቸው በሜዳውና በወንዙ ይፈስ ነበረ ፡፡ ነነነዌ በጎርፍ ፣ በእሳትና በጦር ትሸነፋለች ብሏል ፡፡ እኛ የዓለም ሃያካነብላን ነን ማን ያሸንፈናል ፡፡ 1500 የግንብ አጥሮች በርካታ ከተሞች ፣ በርካታ ከተሞች ብርከታ መቤተመፅሀፍት ፣ ምሽጎች ለሃያ አመታት የሚያዋጋ ምሽግን አዘጋጅተው የነበረ ሲሆን ፡፡ በጎርፍ ወራት የጎፉን አወራደረድ የቀየሩት ሲሆን በክሮኒክል መፅሀፍ ላይ አለ ፡፡ ንጉሱን ከእነ እቁባቶቹ ህዝቡ ሲያቃትላቸው እንዳይማርኩ አቃጥሏቸዋል፡፡ ‹‹ክፉም ቢሆን ወደ ፍርድ ያመጣዋል›› መክ 12፣14

የነነዌ ውድቀት አይቀሬ ነው ብሏቸዋል ፡፡ ትንቢተ ናሆም 612 ቢሲ 1824 በአርኪዎሎጂ እስሚገኙ ድረስ ተቀብረው ቆይተዋል ፡፡

ማህተመ ጋንዲ ‹‹ልክ ነገ እንደምትሞት ተደሰት ፣ ዘላለም እንደምትኖር እውቀትን ፈልግ›› ፡፡ ይሁን እጂ ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹የዚህ አለም ጥበብ በእግዝአብሄር ፊት ሞኝነት ነው›› 1ኛ ቆሮንጦስ ምእራፍ 3፣ ቁ 19፣20 ፡፡

  ነቢይ በሃገሩ አይከበርም የማርቆስ ወንጌል ምእራፍ 6 ላይ ‹‹ይህ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሃገሩ መጣ ደቀመዛሙርቱም ተከተሉት ፤ ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኩራብ ያስተምር ጀመር ብዙዎቹ ሰምተው ተገረሙና ፡- እነዚህን ነገሮች ይህ ከየት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት ? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው ? ይህስ ፀራቢው የማርያም ልጅ የያእቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምኦን ወንድም አይደለምን ? እህቶቹስ በዚህ በኛ ዘንድ አይደሉምን ? አሉ ይሰናከሉበትም ነበር ፡፡ እየሱስም መልሶ ፡- ነቢይ ከገዛ ሃገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው ፡፡ በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር ፣ ተአምር ሊያደርግ አልቻለም፡፡ ስለአለማመናቸውም ተደነቀ ›› በዚሁ ምእራፍ በቁጥር 10 - 12 ድረስ ደግሞ የሚከተለውን ይላል ፣
‹‹በማናቸውም ስፍራ ወደ ቤት ብትገቡ ከዚያ እስከተክትወጡ ድረስ በዚያው ተቀመጡ ፡፡ ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባችው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ፡፡ እውነት እላችኋለሁ ፣ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል አላቸው ››

Ethiopian chritianity in History



ክርስትያኖች ስነ - ፅሁፍን ፣ ሳይንስን ሂሳብን በመሳሰለው ክርስትያኖች አረቦችን አግዘዋል ፡፡ ማንኛውም ስልጣኔ ከእርሱ ቀደም ከነበረ ስልጣኔ ላይ ተመስርቶ ነው እንጂ እንደ አዲስ መስሎ የሚቆመው ከእርሱ በፊት በነበረ ስልጣኔ ላይ በመመስረት ነው የሚመሰረተው፡፡ ክመንት አሌክሳንደር (Clement Alexander) በበኩሉ የግሪክ ፍልስፍና ግሪካውያንን ወደ ክርስትና ለማድረስ አግዟል:: የግሪክ ፈላስፎች እንደ ሀይማኖት የለሽ አይደሉም ፡፡ እነ ፕሌቶ በመንፈስ ቅዱስ መንፈስ ተመርቶ የተፈላሰፈው የተገለፀበት ነው እስከመባል ተደርሷል፡፡ 
አካላዊና ዝቅ አድርጎ ማየትና መንፈሳዊውን እጅግ አግዝፎ ማየት አሁን ላለንበት ግዴለሽ እንድትሆን ፣ በዚህም ምክንያት ከምርምርና ከጥናትና ከሳይንስ እንድትርቅ ሲያደርግ ከዚህ አንፃር በጣም የጨለማ ዘመን ከሮማውያን ስልጣኔ መውደቅ በኋላ እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ነበረ ፡፡ የነበረውም ትምህርት እጅግ አነስተኛ ነው ፡፡ በዚህ ግዜ በአንፃሩ የእስልምናው ዘርፍ ሊነሳ በቅቷል አረቦች በፍልስፍና ፣ በሳይንስ ፣ በሀሳብ ለአረቡ ዓለም እሚታወቅበት ዘመን ሊሆን በቅቷል፡፡ አውሮፓ በጭለማው ዘመን በሚገኝበት ዘመን መሆኑ ነው ፡፡ ከ11ኛው ክፍል ዘመን በኋላ ግን አውሮፓ መረጋጋትና የትምህርት ተቋማት መቋቋም ሲጀምሩ የመፅሀፍ ቅዱስ ምሁራን መፈጠር ሲጀምሩ በስነ - መለኮት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ምሁራን ሊፈጠሩ በቅተዋል ፡፡
አውሮፓውያን በስፔን አማካይነት ከአረቦች ጋር መገናኘት መጀመራቸው ጠፍተው የነበሩና የት እንደገቡ የማይታወቁ የነበሩ በተለይም የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ስራዎችን ከአረቦች ማግኘት ችለዋል ፡፡ በሰሜን አውሮፓ ተደብቀው የነበሩ የግሪክ ፈላስፎች ስራዎችም ተገኝተው በቅተዋል ፡፡ በ12ኛው ክፍለ ዘመን የአሪስቶትል ስራ መገኘት ፡፡ አሪስቶትል እውነትን በመመርመር በማጥናት የሚገኝ ነው ማለቱ ከፕሌቶ በተቃራኒው ፕሌቶ ዋናው ሰማያዊው ነው የሚለውን የፕሌቶን አቋም ፈትኗል ፡፡ ቶማስ አኳዬንስ የአሪስቶትልን ስራዎችን በመውሰድ አዳብሮታል፡፡ አመክንዮ ስለ ፍጥረታዊው ዓለም  ፡፡
ኮንሲታንቶንፕል በኦቶማን እጅ መውደቅ የግሪክ ወደ ፈላስፎች ወደ ምእራብ አውሮፓ እንዲፈልሱና እውቀታቸውን ይዘው ወደ አውሮፓ እንዲፈልሱ አግዟል ፡፡ ኤራስመስ ኦፍ ሮተርዳም የተባለው የግሪክ መፅሀፍ ቅዱስ መተርጎም እና የአውሮፓ ወደ ሬኔሳንስ ዘመን ማበብና መፍለቅ ነው ፡፡
በዚህም ግን ስነ መለኮት አል ተብሎ መሄድም ነበረ በተለይም ሂውማኒዝም የሚባለው አስተሳሰብ ከስነ - መለኮት ጋር የተፋታ ነበረ ይሄም አንድ የሀይማኖት ፈተና ሆኖ ከዚያን ዘመን ጀምሮ  ቀጥሏል ፡፡ 
ከተሃድሶ ወይንም ‹‹ከሪፎርሜሽን›› ጋር ተያይዞ የመጣው በሰሜን አውሮፓ የመጣውና ነፃነትና ለምርምር ሰፊ ነፃትን በመስጠቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ግስጋሴ በርን ከፍተዋል ፡፡ ነገር ግን ሂውማዝም በሳይንስና በአዳዲስ ግኝቶቹ አማካይነት በመደገፍ ጉልበት እያገኘ ሲሄድ ስነ - መለኮትን መዋጥና መገዳደር ከጀመረ ወዲህ በአውሮፓውያን አእምሮ ውስጥ እግዝአብሄር ምንም ጣልቃ የማይገባት ዝግ የሆነ ዓለም አድርጎ ወደ ማሰብ እንዲሄድ አድርጓል ፡፡
ኢማኑኤል ካንት ያሉት በአመክንዮ መመራት አለብን አመክንዮ ፊት ተፈትሾ ያላለቀ ነገር ተቀባይነት እንዳይኖረው አመክንዮ ፊት ቀዳሚ የሆነበትና እግዝአብሄርን አንፈልግም እስከማለት ተደርሷል ፡፡ በ17ኛው እና በ18ኛው ክፍል ዘመናት ተአምራትና ፈውሶች ሁሉ ተቀባይታቸውን እዲያጡና ፡፡
ብሎም ከትምህርት ሰርአቱም ጭምር በመገፋት የትምህርት ሁሉ ንግስት ነው የሚባለው የስነ - መለኮት ትምህርት አንድ ፀሀፊ የስነ - መለኮት ትምህርት በስደት ላይ ነች እስኪል ድረስ ስነ - ለመለኮት እጅጉን እየተገፋ መጣ ፡፡ በስደት ላይ ያለውን ስነ - መለኮት ትምህርት ሊሆን በቅቷል ፡፡ 
የዳርዊን ዝግመተ ለውጥ ፅንሰ - ሃሳብ ደግሞ እግዝአብሄር የለም እስከመባል የተደረሰበት ነው፡፡ ስነ መለኮት በዘመናዊው ትምህርት ውስጥ በዘመናዊው ትምህርት ምንም ቦታ የሌለውና ተደርጎ ተወስዷል ፡፡
መፅሀፍ ቅዱስ ከአይሁዳውያን ለአለም ካላቸው እይታ አንፃር መፃፉ እርግጥ ነው ለምሳሌ በዮሀንስ ራእይ ላይ አረቦች ሩስያን በማሰለፍ ከቻይና ጋር ሆነው እየሩሳሌምን ለመያዝ እስራኤል ላይ ወረራን ያደርጋሉ የሚለው ትንታኑ ይን አይሁን ለማወቅ አወዛጋቢ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በዋነኝነት መፅሀፍ ቅዱስ የመንፈሳዊ መፅሀፍ መሆኑና የታሪክ መፅሀፍነቱ ሁለተኛ እንጂ መጀመሪያ አለመሆኑ ግልፅ ነው ፣ አንዳንድ አይሁዳውያን ራሳቸው መፅሀፍ ቅዱስን ጊዜ ያለፈበትና እንደ ታሪክ መፅሀፍ ሊቆጠር ይችላል ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን መንፈሳዊ መፅሀፍ እንደመሆኑ መጠን ግን መንፈሳዊ መፅሀፍነቱን ሊያጣ እንደማይችል ግልፅ ነው ፡፡
በብሉይ ኪዳን መፅሀፍ ‹‹ሙሴ በቤተመንግስት የግብፃያውያንን ጥበብ እየተማረ አደገ›› የሚል ሲሆን ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ግን ሁሉንም የእግዝአብሄርን ጥበብ አይሁዳውያን በእንዳፈለቁትና እንደደረሱበት አድርገው ፅፈውታል ፡፡ብሌይዝ ፓስካል በበኩሉ መፅሀፍ ቅዱስን አትናቁት ይላል ፡፡

እግዝአብሄር ዋናው ማእከሉ ነው ፡፡ እንጂ የሰው ተግባር እግርዝአብሄርን ማሞገስና ማወደስ ነው ፡፡ የግል ፣ ሃገራዊ፣ አለምአቀፋዊ ፣ ማህበረሰባዊ እና የቤተሰብ ችግሮች ማንም ሰው በህይወቱ ውስጥ የሚያጋጥሙት የችግር አይነቶች ናቸው ፡፡ እግዝአብሄር እስረኤላውያንን ከግብጽ ባርነት ቀንበር እንዳዳናቸው ለሚምኑት ለፍጥረቶቹ መድህን አዳኝ ነው ፡፡

እግዝአብሄር የእስራኤላውያንን አዳኝ ነው ፡፡ ባርያን ከቀንበሩ ማላቀቅ የማዳን ስራ ነው፡፡ ክርስቶስ ከሰይጣን ፣ ከሀጢአት ያዳነን ነው ፡፡ ድህነት የእግዝአብሄር ስራ ነው ፡፡ እግዝአብሄር ዓለሙን የወደደ እንደመሆኑ ድህነትን ለፍጡራኑ ያበረክታል ፡፡ ‹‹ሀብትህ ባለበት ገንዘብህ ባለበት ልብህ አለ›› ክርስቶስ ‹‹ልብህ የሚሆነው መዝገብጀህ ባለበት ጥሪትህ ባለበት በዚያ ነው››

Ethiopia Queen of Sheba ንግስተ ሳባ በአረብ ታሪክ ጸሀፍት



‹‹ለሰብአ በመኖሪያቸው በአውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው ፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች (ነበሯቸው) ፡፡ ከጌታሁ ሲሳይ ብሉ ፣ ለእርሱም አመስግኑ (አገራችሁ) ውብ ናት ፡፡ (ጌታችሁ) መሀሪ ጌታም ነው (ተባሉ) ፡፡ (ከማመስገን) ዞሩም ፡፡ በእርሱም ላይ የግድቡን ጎርደፍ ለቀቅንባቸው ፡፡ በአትክልቶቻቸውም ሁለትን አትክልቶች ባለ መርጋጋ ፍሬዎችን ባለ ጠደቻና ቆርቁራም ባለ ጥቂት ዛፎችን ለወጥናቸው ፡፡›› ሰብአ 15-16
      የዓረብ ታሪክ ፀሀፍት ይህ በቅዱስ ቁርአን ላይ የሰፈረውን ፅሁፍ ለየመን እንደተፃፈ አድርገው ይረጉሙታል ፡፡ ነገር ግን ከአፃፃፉ መረዳት እንደሚቻለው አገራችሁ  ‹‹ከጌታሁ ሲሳይ ብሉ ፣ ለእርሱም አመስግኑ (አገራችሁ) ውብ ናት›› ሲል በተፈጥሯዊ አቀማመጧ፣በወንዞቿ፣በተራሮቿ ውበትን የተጎናፀፈችውና የበርካታ እፅዋትና እንሰሶች መኖሪያ ለሆነችው ለአቢሲኒያ ወይንም ለአሁኑ ኢትዮጲያ እንጂ ለየመን እንዳልተነገረ መረዳት ይቻላል ፣ በአካባቢው ያለች ውብ ሀገር ኢትዮጲያ መሆኗንም ማንም አይስተውም ፡፡
      የአረብ ታሪክ ጸሀፊዎች በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ጠቢቡን ሰለሞንን በእየሩሳሌም ልትጎበኝ የሄደችውንና ስመ ገናናዋን ንግስተ ሳባን ወይንም በአረብኛው አጠራር ንግስት ቢልቂስ የየመን ንግስት አድርገው ያቀርቧታል ፡፡ እንደ አረብ የታሪክ ጸሀፍት ንግስተ ሳባን የኢትዮጶያ ንግስት ሆና በታሪክ የሰፈረችው በግብፅ ኮፕቲክ ቀሳውስት ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚል ርእስ ባዘጋጁት መፅሀፍ አማካይት የኮፕቲክ የታሪክ ፀሀፊዎች በየመንና በአቢሲኒያ መሀከል የነበረውን የሰላምና የጦርነት ግንኙነትን ወደ አፈ ታሪክ በመለወጥ ንግስቲቷን ሆነ ብለው ታሪክን በማዛባት የአቢሲያ ንግስት አድርገው አቅርበዋታል ባይ ናቸው ፡፡  
እንደ አረብ ታሪክ ጸሀፍት አባባል የግብፅ ኮፕቲክ ቀሳውስት ይህንን ያደረጉበት ምክንያት በወቅቱ በነበረው በምእራባዊቷ ሮማ ካቶሊካዊትና በምስራቅ አብያተ ክርስትያናት መሀከል በተነሳው የእምነት ልዩነት ምክንያት የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ወደ ሮማ ካቶሊክ እንዳታዘነብል ለማባበል ሲሉ ያደረጉት ነው የሚል ነው ፡፡ 
በአረብ ታሪክ ፀሀፍት ከዚህም አልፈው ንግስት ሰባና በጠቢቡ ሰለሞን መሀከል ተፈጠረ የተባለውን ወሲባዊ ግንኙነት እና ምንሊክ የተባለ ንጉስ ተወለደ የሚለውን ክብር ነገስት ላይ የሰፈረውንም ጭምር ሀሰት ነው፣ ነቢዩ ሰለሞን ከሳባ ጋር ዝሙት ፈጸመ መባሉን ፈጣሪ ይቅር ይበለን ሲሉ ይተቻሉ፡፡
ይህ በንግስት ሳባና በንጉስ ሰለሞን መሀከል የተፈጠረው የደምና የስጋ ቁርኝት በኋላ ላይ የሰለሞናዊው ስርወ መንግስ በቀዳማዊ ሀይለስላሴ በ1966ቱ ዓብዮት ከስልጣን እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ አልፎ አልፎ በዮዲት ጉዲትና በዛጉዌ ስርወ መንግስት ፣ እንዲሁም  በግራኝ ጦርነት ወቅት በአንዳንዶች ግዛቶች አካባቢ የሰለሞናዊው ስርወ መንግስት አገዛዝ ለተወሰኑ ጊዜያት ከመቋረጡ በስተቀር ለሺህዎች አመታት ኢትዮጲያን ሲገዛ ለበርካታ ክፍለ ዘመናት በህዝቡ ዘንድ ተቀባይት ያለው ህጋዊ የስልጣን ምንጭ (Legitimacy) በመሆን አገልግሏል፡፡
‹‹ክብረ ነገስት›› የተባለው መፅሀፍ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተተረጎመው እ.ኤ.አ በ1932 ዓ.ም. በኦክስፎርድ ምሁር ሰር ዋሊስ በጅ ሲሆን ይህን የተፈጠረ የስጋና የደም ትስስር በንግስናና በፖለቲካው ዓለም ብቻ ሳይወሰን በኋላ ንጉሰ ምንሊክ ወደ እየሩሳሌም እንደሄደና የእስራኤላውያንን ኦሪት ፅላትንና ካህናትን ይዞ ወደ አቢሲኒያ በመምጣት በኢትዮጲያ የኦሪት ሀይማኖትን እንደመሰረተ ይናገራል[1] ፡፡


[1] የቅርቢቱ ዓለም እውነታዎች ፣በሃሩን የህያ ፣ ትርጉም አህመድ ሁሴን (አቡ ቢላል)፣ ጥር 2002 ነጃሺ ማተሚያ ቤት፣አዲስ አበባ

ሰይጣንንና ሃጢአት



ሰዎችን የሚሳስተው ሁለት ነው አንደኛው ራሱ ሰይጣን መንፈሱ ሲሆን ፣ ሌላኛው ግን መፈታተን ወይም ስጋ የሚባለው ነገር ነው ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሄዋን የተከለከለውን ፍሬ የበላችው እርቧት ወይም የሚበላ ሞልቶ በተረፈበት ገነት ውስጥ የምትበላው አጥታ ሳይሆን የሰይጣን መንፈስ ስላሳሳታት ነው፡፡ አለምነህ ፍልስፍን በሚለው መፅሀፉ ላይ የኢ - አማንያንን (Atheists) ሓሳብ በመውሰድ ሰይጣን የሚባል ነገር እንደሌለና የሰው ልጅ ውስጡ መሆኑን ይገልፃል ፡፡
‹‹ሰኮናህን ይነክስሃል አንተም ራስ ራሱን ትቀጠቅጣለህ››፤ተብሎ እግዝአብሄር እንደረገመው ሁሉ ፡፡
ሰዎች ሀጢአትን የሚሰሩበት ሁለት ምክንያቶች አሉ ፣ አንደኛው ለስጋው በማድላታቸው ወይንም ያንን ነገር ለማድረግ ሲፈታተናቸው ሲሆን ሌላኛው ግን በቀጥታ በራሱ በሰይጣን መንፈስ በመነዳት ወይንም በሰይጣን መንፈስ ቁጥጥር ስር በመሆን ነው ፡፡ ሰይጣን ራሱ የመፈታተን ውጤት ሲሆን ከእግዝአብሄር ጋር በስልጣንና በመፎካከሩና የበለጠ ሀይልንና ገናናነትን ለማግኘት በመሞከሩ ከሰማየ ሰማያት እንደተባረረ በቅዱሳን መፅሀፍት የተገለጸ ነው ፡፡
ሰይጣን እንደ መንፈስ ህልውና የለውም ብሎ መካድ በተዘዋዋሪ መንገድ እግዝአብሄርም የለም እንደማለት ነው ፡፡ ምክንያቱንም የእግዝአብሄር ተቃራኒና በተፃራሪው የቆመ ሰይጣን በመሆኑ ማንኛውም ነገር ተቃራኒ እንዳለው ሁሉ የእግዝአብሄርም ተቃራኒ ሰይጣን ነው ፣ የመልካም ተቃራኒ ክፉ ፣ የወንድ ተቃራኒ ሴት፣ የጥቁር ተቃራኒ ነጭ ወዘተ … እያለ መሄድ ማንኛውንም ነገር የምንመለከትበት ነው ፡፡ ነገር ግን የዚህ ክርክር ድክመት ምንድነው ቢባል አንድ ነው ይሄውም የአንድ ነገር ተመጣጣኝ ተቃራኒ ነገር ካለው ሰይጣንና እግዝአብሄር ተቃራኒ መሆናቸው አከራካሪ ባይሆንም ፣ ነገር ግን ሀይላቸው ግን ተመጣጣኝ ሊሆን አይችልም ፣ምክንያቱም አሸናፊው እና ሀያሉ እግዝአብሄር ስለሆነ ነው ፡፡ ስለዚህ ሰይጣንና እግዝአብሄር ተቃራኒ መሆናቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ተመጣጣኝ ሀይል እንደሌላቸው ግን አከራካሪ አይደለም ፡፡ 
እየሱስ ክስርቶስ ሲናገር ‹‹ገሀነም ለሰይጣንና ለመናፍስቱ ተዘጋጅቷል›› ሲኦል እንደሚባለው በእሳት የተሞላ አይደለም ለዚያም ምክንያቱ ሰይጣንም ሆነ አጃቢዎቹ መናፍስቶች ናቸው እንጂ የሚቃጠል ቁስ አካል አይደሉም ይልቅ ግን ሰይጣንና መናፍስቱ መንፈሶች እንደመሆናቸው ቁሳዊ ነገር ማጥፋት የሚችለው እሳት መንፈስን ሊያጠፋ አይችልም ፡፡ በዮሀንስ ራእይ ላይ ‹‹ይህም የእሳት ባህር ሁለተኛ ሞት ነው ፣ በህይወት መፅሀፍ ተፅፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣለ ›› ራእይ 20፣15 ‹‹መላእክት መጥተው ሃጢአተኞችን ከፃቃንም መሀከል ይለዩአቸዋል ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል ፣ በዚያ ጥርስ ማፋጨትና ልቅሶ ይሆናል ›› ማቴ 13፣49-50
ሃጢአት በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ሀጢአት የምትሰራ ነፍስ ሁሉ እርስዋ ትሞታለች›› ህዝ 18፣4 ላይ ሲል ሮሜ 3፣23 ላይ ደግሞ ‹‹ሁሉ ሀጢአትን ሰርተዋል የእግዝአብሄር ክብር ጎድሎቸአቸዋል››‹‹የሀጢአት ደሞዝ የዘላለም ሞት
(በገሀነም መቃጠል) ነው›› ሮሜ 6፣23 ይላል ፡፡ ‹‹በሃጢአታችን ብንናዘዝ ሃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ፃድቅ ነው››
‹‹ከዓለም እንድታወጣቸው አለምንህንም ፣ እንድትጠብቃቸው እንጂ›› የዚህ አለም ገዢ በሆነው በሰይጣን በሚገዛ አለም ውስጥ የሰው ልጅ በዚህ ምድርር ላይ እስካለ ድረስ ማውጣት አይቻልም ፣ነገር ግን ጠብቃቸው ነው ያለው ፡፡
ዜኖ የጠርጣራዎች አባት በጥንት ግሪካውያን ‹‹ብልህ ሰዎች ከስሜት ነፃ መሆን አለባቸው ፣ ስሜት ማሳየት የለባቸውም የደስታም ሆነ የሀዘን ከደስታም ሆነ ከሀዘን አሳዛኙ ነገር ግን ፣ የዚህ አይነት ሰዎችም ቢሆኑ ራሳቸውን ለተፈጥሮ ህግ ማስገዛት ግዴታ አለባቸው - ያም እጣ ፈንታ ነው፡፡›› አለ ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ፡፡ የሃይማኖት ሰዎች እየሱስ ክርሰቶ በውሀ ላይ ሲራመድ እንዴት ለተፈጥሮ ህግ አልተገዛም ፣ በውሀ ላይ ሲሄድ ተኝቶ ነበረ ማእበል ጀልባዋን ሲያናጋት ፣ እረ ጌታ ሆይ እረ ጠፋን ሲሉት ለምን እምነት የላችሁም ብሎ ጠየቃቸው ፡፡ በመንፈስ ግን ሰዎች ምንም ገደብ የለባቸውም ነፃ ናቸው፡፡ ክርስቶስ ነፃነትን ከህመም ፣ ከማንኛውም እስራት ነፃ አውጥቶናል ፣ እረኛችን ነው አንፈራም ፡፡ 
እየሱስ ለድሆች ነው የመጣሁት ሲል በሃጢአት ለተዘፈቁና በሃጢአት ቀንበር ውስጥ ለታሰሩ እንጂ ለገንዘብ ድሆች ማለቱ ወይንም ሃብታሞችን በሚመለከት አልመጣሁም ማለቱ አይደለም ፡፡ ክርስትስ ወደዚህ ምድር በመጣበት ወቅት በርካታ ከስነ - ፣ምግባር ያፈነገጢ ድርጊቶች በዘመኑ በሮማውያን ቄሳሮች በምትገዛው እየሩሳሎምም ሆነ በሌች ግዛቶች የተንሰራፋ ነበረ ፡፡ በጎችን ያለጠባቂ ስለተመለከተ ነው ለእነኚህ በጎች የመጣው ፡፡ የድሆች ሰቆቃ ከምንድነው የመጣው ቢባል ከሰይጣን ፣ ከማህበረሰበና ከሃጢአት ነው ፡፡ አደንዛዥ እፅና አልኮሆል የሃጢአት ሰዎችን በባርነት የሚሰብር ሲሆን የሰዎችም ህይወቶችም ይበላሻሉ ፡፡
በምእራቡ አለም ሰዎች የሚያረጋጋ ስነ - ልቦናን የሚረጋጉ ፣ ድብርነትን የሚያባርሩ በሚልና በሌሎችም ስም በርካታ የመድሀኒቶች አይነቶች በሀኪሞች ለህመምተኞች ይታዘዛሉ ነገር ግን ዋናው የዚህ ሰበቡ የሰዎች መነጠል ይህም መነጠል መንፈሳዊ መነጠል (Spritual Alination) ሲሆን ይህም ከሃጢአትና ሰዎች በሃጢአት ከመዘፈቃቸው የሚመነጭ ነው ፡፡
ሰይጣን አንድ ራሱን የቻለ ሰው ነው ፡፡ ሰዎችን የሚማርክ እንደ ጦር እስረኛ ማርኮ የሚያስቀር ነው ፡፡ ሰይጣን በማታለል ፣ በዝሙት ፣ በመተት በመማረክ ሰዎችን ከፍትህ እንዲያፈነግጡ ሰብአዊነታቸውን ረስተው የውሸት ስብእናን እንዲላበሱ ያደርጋል ፤የጤና ፣የገንዘብ ችግሮች የማህረሰቡ መገለል ፣ ስነ - ልቦናዊ ቀውስ ፣ የምግብ እጥረት ፣ የጤና መቃወስ እንዲከተልና ከቤተሰብ ጀምሮ የማህበረሰብ መፈራረስንና ህልውናው አደጋ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል ፡፡
የዚህ ዓለም ገዢ ብሎ እየሱስ ክርስቶስ የጠራው ሰይጣን እየሡስ ክርቶስን ለማሳሳት በአንድ ገደል ጫፍ ላይ ወስዶ የዓለም ነገስታትን ክብር በማሳየት ‹‹ለኔ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› ሲል ፈትኖታል ፡፡ ሰይጣን የጋለ ምኞቱ በምድር ላይ ብቻም የተወሰነ አይደለም በኢያሳያስ 16፣ ቁጥር 12 ላይ
‹‹አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮኮብ ሆይ ፤እንዴት ከሰማይ ወደቅህ ! አህዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ ፣ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ ! አንተም በልብህ ፡-ወደ ሰማይ አርጋለሁ ፣ ዙፋኔንም ከእግዝአብሄር ክዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ፣ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ፤ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ ፣በልኡልም እመሰላለሁ አልህ ፡፡ ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓድ ጥልቅ ትወርዳለህ ››  
ነገር ግን ማንም ሰው ሁሉንም ክፋትንና መከራን በሰይጣን ማላከክ እንደማይችል መፅሃፍ ቅዱስ ራሱ ይናገራል ፡፡ ያእቆብ 1፣13 ላይ ‹‹በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ፣ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የህይወትን አክሊል ይቀበላልና ፡፡ ማንም ሲፈተን ፡-በእግዝአብሄር እፈተናለሁ አይበል፡፡ እግዝአብሄር በክፉ አይፈትንምና እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፡፡ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ሃጢአትን ትወልዳለች፣ሃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች ›› ይላል፡፡
የዪሀንስ ወንጌል ምእራፍ 8 ላይ ‹‹እናንተ ከአባታችሁ ከዲያቦሎስ ናችሁ እርሱ ያደረገውን ማድረግ ትፈልጋላችሁ››