አንዳንድ መሪዎች ችግሮችን መፍታት ሲያቅታቸው ወይንም ችግሩን ለመፍታት የሚያስፈልገውን ለውጥ ወይንም ጥገናዊ ለውጥ (Reform) ማድረግ ሳይፈልጉ ሲቀሩ የተከታዮቻቸውን ወይንም የህዝባቸውን የአትኩሮት አቅጣጫውን ለማስቀየር የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋሉ ። ይሁን እንጂ አንድ ችግር ወይንም መሻሻል ያለበት ነገር በመሰረታዊነት መስመር ካልያዘ ወይንም ካልተፈታ ችግሩ ለጊዜው ተድበስብሶ እንዲቀርና በረጅም ጊዜግን የከፋ መዘዝ የሚያስከትል ሆኖ ብቅ እንዲል ብቻ ነው እሚያደርገው ።
ሀላፊነትን በትክክል አለመወጣት አንዱ የአመራር ወይንም የመሪነት ድክመት ነው ። አንድ መሪ ተሳስቶ ይሁን ወይንም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አግባብነት የሌለው ውሳኔን ከወሰነና የሚመራውን ተቋም ወይንም ድርጅት ፣ ሀገር ላይ ጉዳትን ካመጣ ብዙ ጊዜ ያንን ቦታውን እንዲያጣ ይደረጋል። በተለይም በምእራቡ አለም መሪዎች ከተሳሳቱና ውሳኔያቸው ጉዳትን ካስከተለ በቶሎ ከዛ ቦታ እንዲነሱ ይደረጋል።ይሄም ተገቢ አሰራር ሲሆን ለዚህም ያ ሰው እዛ ቦታ ለረጅም ጊዜ ከቆየ የሚያስከትለውን ጉዳት በመገመትና በመረዳት ነው። ለዚህም በምእራቡ አለም ጠንካራ የመገናናኛ ብዙሀኖች ስላሏቸው በዛ አማካኝነት ከህዝብ ቢደበቅ እንኳን ይፋ ስለሚያደርጉት የህዝብ ግፊት ስለሚያይል ነገሩን በቶሎ ለማስተካከል ይረዳቸዋል።ይህ አሰራር በተለይም ቀድሞ ብዙም ተጠያቂነት ባልነበረባቸው በትላልቆቹ ኮርፖሬሽኖችና ባንኮችም ጭምር ውስጥ ተግባራዊ እየሆነ ሲሆን ፣ ኩባንያው የህዝብን አመኔታን እንዲያጣ ያደረጉ የግዙፍ ኮርፖሬሽኖች ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው እንዲለቁ ሲደረጉ በተደጋጋሚ ተስተውሏል ።
ለውጥ ከሁለት አቅጣጫ የሚመጣ ሲሆን ፤ ከላይ ወደታች (Top Down) እና (Bottom Up) ወይም ከላይ ወደታች ነው ። ከላይ ወደ ታች እሚመጣው የለውጥ አይነት በመሪዎች የራስ ተነሳሽነት የህዝቡ ግፊት ቢኖርም ባይኖርም ራሳቸው መሪዎቹ አምነውበት የሚገፉት የለውጥ አይነት ሲሆን ፣ ሁለተኛው
አይነት ከለውጥ ደግሞ ከራሱ ከህዝቡ በራሱ ግፊት የሚመጣና ሀገሩ የምትሄድበትን
አወቅጣጫ ራሱ እሚመራበትና
እሚጠቁምበት
ነው ። ብዙ ጊዜ ከታች የሚመጣን የለውጥ ግፊት ከላይ ያሉ መሪዎች በማይቀበሉ ከሆነ ከብዙ ትችግስት በኋላ የለውጥ እንንቅስቃሴዎች
ብሎም አብዮቶች ሁሉ ሊካሄዱ ይችላሉ ።
ስለዚህ ምንግዜም ቢሆን መሪው የለውጡን አቅጣጫና አካሄድ አስቀድሞ መገመትና መጠበቅ መቻል ሲኖርበት ፣ በአንደ በኩል የለውጡን ጥቅም ማየት ከቻለ ምንም እንኳን የራሱን ግላዊ ስልጣን እሚቀንስና እሚያሳጣ ሆኖ ቢገኝ ነገር ግን በታሪክ የሚኖረውን ስፍራውን በመልካም ለማስፈርና አይቀሬም ከሆነም ያንን ለውጥ ለማገዝ መደገፍ አንድ አማራጭ ሲሆን ፣ ነገር ግን የለውጡ ፍላጎት የብዙዎች ሆኖ እሱ ብቻውን ለማስቆምና ለመግታት ከሞከረ ግን በታሪክ የሚኖረውን ቦታ ማበላሸት ብቻ ም ሳይሆን መሪነቱን ፍፁም ጥላሸት ሊቀባው ፣ እና ቀድሞ የሰራቸውን ጥሩ ስራዎች ሊጋርድበትና
ይችላል ።
ሌላው ደግሞ አንድ መሪ ውድድሩን ካጠፋ ፣ የራሱን የሚመራውን ተቋም እድገት ያቀጭጨዋል ። ለተቋሙ ወይም ለሀገሪቱ የፖለቲካ እድገት እገዛን ሊያደርግ ይችል የነበረውን ፣ እንዲሁም ለወደፊቱ ሽግግር ወቅት ሲመጣ ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖር የሚያስችለውን
ተቋማዊና ፣ እውቀትና የሰው ሀይል እድገት እንዲቀጭጭ ነው እሚያደርገው
። የጤናማ ውድድር መኖር ለተቋማትም ሆነ ለመንግስታት
እድገት አስፈላጊ ነው ። በውድድር ባለበት አለም ውስጥ የመጨረሻ አሸናፊና ተሸናፊ እሚባል ነገር የሌለ ሲሆን በየትኛውም ውድድር ምንግዜም ጊዜያዊ ተሸናፊና ጊዜያዊ አሸናፊ ናቸውረ ያሉት ።
ስፖርትን እንኳን ብንወስድ አንድ ቡድን በአንድ ውድድር ቢያሸንፍ በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ ሌላው ያልተጠበቀው
ቡድን ያሸንፋል ፣ስፖርትን በውድድሩ ወቅት ካለው ትእይንት በተጨማሪ አጓጊ የሚያደርገው
ይሄው ያልተጠበቀው
ማሸነፍና መሸመፍ ናቸው ። በመሪነት ውስጥም ያልተጠበቀው
ፓርቲ ተመርጦ ወደ ስልጣን ሊመጣ ሲችል ፣ የተጠበቀው ፓርቲ ደግሞ ሊሸነፍ ይችላል ። ስለዚህ ሽንፈትን እንደ መጨረሻ መወሰድ የሌለበት ሲሆን ማሸነፍም እንዲሁ ዘላለማዊ አይደለም ። አሁን ያሸነፈ ፓርቲ ከጥቂት አመታት በኋላ ተሸናፊ ሆኖ እሚገኘው እሱ ይሆናል ፤ ተሸናፊውም በሚቀጥለው ጊዜ ድሉ የእርሱ ይሆናል ።
የሌሎች ሰዎችን የማሰብና የማወቅ ችሎታን አሳንሶ የሚገምት መሪ መጨረሻ ላይ በርካታ ያልጠበቃቸውን ፈተናዎችን ይጋፈጣል ። እኔ እማውቀውን ሌሎች ሰዎች አያውቁትም ብሎ ማሰብ ወይንም ሌሎች ተወዳዳሪዎቹንም ሆነ አጋሮቹን ጭምር የራሳቸውን ጉዳይ በትክክል መፈጸም አይችሉም ብሎ ማሰብ በተለይ ለመሪ ትልቅ ስህተት ነው ።አንድ መሪ ሊፈጽማቸው ከሚችላቸው ስህተቶችም ትልቁና ዋነኛው ይሄው ነው ። የሰው ልጅ አእምሮ የማሰብ፣ የማወቅና የማገናዘብ ችሎታ ያለው በመሆኑ ብዙ ጊዜ ተመጣጣኝ የሆነ ነገሮችን የመረዳት ችሎታ በብዙ ሰዎች ዘንድ አለ ።
ሌላው ደግሞ መሪው ራሱን እንደ አይበገሬ (Invincible) አድርጎ መመልከት የለበትም ። ከዚያ ይልቅ ሌሎች ተወዳዳሪዎቹም ቢሆኑ ሊያደርሱበት የሚችሉትን ፣ እንዲሁም እርሱ እራሱ ነገሮችን ቢያበላሽ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ መገመት መቻል አለበት ።
መሪዎች ለረጅም አመታት በአንድ የስልጣን ወንበር ላይ ሲቀመጡ በዛ ቦታ ላይ (Burn Out) መድከምና መሰላቸት ሊያደርጉ ይችላሉ ። በተለይም የአገር መሪዎች ለረጅም አመታት ሲቀመጡ የመታከትና የመሰላቸት ፣ የመዛል (Burn Out) የማድረግ እድላቸው ሰፊ ነው ። አንዳንድ የስፖርት በተለይም የእግር ኳስ አሰልጣኞች ቡድናቸው ከፍተኛ ስኬትን በሚያስመዘግብበት
ወቅት በድንገት ከአሰልጣኝነት
ስራቸው ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ አግልለው የሚቆዩበትም
ይኀው ምክንያት ነው ።ህጉ ራሱም ስለማይፈቅድላቸው
፣ ዲሞክራሲ ባለባቸው ሀገራት ውስጥመሪዎች
ከተወሰኑ አመታት በላይ በስልጣን ወንበር ላይ ስለማይቀመጡ
በርን አውት የማያደርጉ ሲሆን ፣በአንፃራዊነት
በስልጣን ላይ የሚቆዩበት አመታት አጭር በመሆናቸው ነው ፣ በአንፃሩ ግን ዲሞክራሲ ባልዳበረባቸው
ሀገራት ውስጥመሪዎች
ለረጅም አመታት በስልጣን ወንበር ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ ። የኩባንያ መሪዎችም ሊሰላቹ ይችላሉ ። አንዳንድ መሪዎች በነበሩበት ስኬትን ካመጡ በኋላ አዲስ ጀብድን በመፈለግ ወይም አዲስ ችግርን ለመፍታት በመፈለግ ከነበሩበት ትተው ወደ አዲስ ኩባንያ ለማምራት ሲፈልጉ በምእራባውያን
ኩባንያዎች ታይቷል ። አዲስ የሚፈቱት ችግር (Adventure) መፈለግም መሪው ቀድሞ የነበረውን ቦታ ትቶ ወደ ሌላ እንዲሄድ ሊገፋፋው ይችላል ።