የተለያዩ መሪዎች የተለያዩ የአመራር ስልቶችን ይመርጣሉ ። ለዚህ ምክንያቱ በአንድ በኩል የመሪዎቹ የራሳቸው ግላዊ ባህሪ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሁኔታዎች አስገዳጅነት
ነው ። አንዳንድ መሪዎች በአምባገነንነት
መምራትን ይመርጣሉ ፣ ሌሎች ደግሞ በዲሞክራትነት
መምራትን ይመርጣሉ። አንዳንዶች በውይይትና በድርድር ሲያምኑ ፣ ሌሎች ደግሞ በፈላጭ ቆራጭነት ያስተዳድራሉ
። በሰላም ወቅት በአምባገነናዊነት
መንገድ አገርን መምራት አግባብነት አይኖረውም ፣ በጦርነት ወቅት ግን አምባነገነናዊ
አገዛዝን (Dictatorship)
ማስፈን የበለጠ ቀላል ነው ። አንዳንድ ጊዜ መሪዎች በሽብር ጭምር ለመግዛት የሚሞክሩበት
ወቅት ጊዜ አለ ። ይህ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው ። ለምሳሌ አንድ ሀገር በወጪ ወራሪ በምትወረርበት
ወቅት ወረራውን ለመመከትና ራሷን ከውጪ ወራሪ ለመከላከል አስፈላጊ የሆነውን እርምጃ በፍጥነት መውሰድ መቻል ሲኖርባት በሰላም ወቅት ግን ተመሳሳይ የሆነ የአመራር ስልት ውጤቱ ያልተጠበቀ ሊሆን ይችላል ።
የጥንት ሮማውያን በውጪ ወራሪ በሚወረሩበት
ወቅት ለጊዜው ወረራውን ለመግታት እንዲያስችላቸው
መንግስታቸው
ይመራበት ከነበረው ሪፐብሊክ ይልቅ ከመሀከላቸው
መርጠው አንድ እንደ አምባገነን የሚሰራ ሰውን ይመርጡ ፣ ችግሩ እንስከሚያልፍ
ድረስ በእርሱ ይመሩ ነበረ ። ይህም
ዲክታተር የሚለው ቃልም የመጣው ከዚሁ ከሮማውያን ነው ። ነገር ግን የሮማውያን
ዲሞክራሲያዊ
ስርአት መጨረሻ ላይ የፈረሰው በእነዚሁ አምባገነን ብለው በሾሟቸው ሰዎች አማካይነት ቀድሞ ለሴኔቱ ይገዙ የነበሩት የጦር ጄኔራሎች ጁልዬስ ቄሳርን ጨምሮ ውሎ አድሮ ወደ ነገስታትነት
በመለወጥ የሪብሊካዊ ስርአቱን አፈራርሰውታል
።
አንድ ኩባንያም ራሱን አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሲያገኘው እንዲሁ አጣዳፊ የነፍስ አድን እርምጃዎችን
ወስዶ ህልውናውን ማስጠበቅ መቻል አለበት ። ነገር ግን በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ወቅትም የሚደረጉ ነገሮች ከመሪው ቁጥጥር ውጩ የወጡና ነገሮች ከተረጋጉ በኋላ መሪውን የሚያሳጣ ወይንም የሚያስጠይቁ
መሆን አይኖባቸውም
።
የአመራር ይትበሀል እሚነሳው ከመሪው ብቻ ሳይሆን ከባህሉ ፣ ከአስተሳሰቡና
ርእዮ - አለሙም ጭምር ነው ። ለምሳሌ እንደ ቻይና ፣ራሺያ ፣ ኢትዮጲያ ባሉ ሀገራት በአንድ ጠንካራ መሪ (Strong Man)
ዙሪያ ሁሉም ነገር የሚሰባሰብ ሲሆን ፣ ይህም መሪው በፍፁም ትክክለኝነት
ነው የሚመራው በሚል ከደጋፊዎቹ ድጋፍን ያገኛል ። በአንፃሩ ግን ከምእራቡ አለም አሜሪካንን ፣ እንግሊዝን ፣ ጀርመንን ብንወሰድ መሪዎች ለትናንሽ ስህተታቸው ሳይቀር ያለምህረት በሚዲያው በተቃዋሚዎቻቸውና
በተለያዩ ጉዳዩ በሚመለከታቸው
የሚተቹበትና
ሲሆን ፣ ጥፋትን ከሰሩ ስራቸውን እስከመልቀቅ
፣ ብሎም እስከመከሰስ
ድረስ ተጠያቂ ይሆናሉ ። የቀድሞው የአሜሪካ
ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን በወቅቱ ታቃዋሚ ፓርቲ የነበረው በዋተርጌት ሆቴል ውስጥ ይገኝ የነበረው የዲሞክራቲክ
ፓርቲው ቢሮዎች እንዲጠሉፉና
እንዲሰለሉ በማድረጋቸው
፣ ህገ - መንግስቱን በመጣሳቸው ከስልጣናቸው
እንዲለቁ ተደርገዋል ። ነገር ግን ይሄ ክስተት ዲሞክራሲ ባልተጠናከረበት
ሀገር ቢሆን ፣ እንደ ቀላል ጥፋት ታይቶ መሪው በስራው ላይ ሊቀጥል እንደሚችል መገመት ይቻላል ፣ እንደውም ተቃዋሚዎቹን
ለማፈን ይሄንን ስልት እንደ ህጋዊ መንገድ ሊጠቀምበት ይችላል ።
በአንፃሩ ቻይናን ብንወስድ ቻይናም በአንድ ጠንካራ መሪ አገዛዝ ስትመራ የቆየች ሀገር ስትሆን በአንፃሩ ግን የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ፣ ከማኦ የአመራር ክስረት ማለትም በ1950ዎቹ
የባህል አብዮት ተካሂዶ በነበረበት ወቅት ለፓሪውም ሆነ ለሀገሪቱ ክስረትን ካስከተለ ወዲህ የአንድ ሰው አገዛዝን አደጋ በመረዳት ፣ ምንም እንኳን ቻይና በአንድ ፓርቲ የምትምራ መራ ሀገር ብትሆንም በፓርቲው
ውስጥ ግን የጋለ ክርክርና ውይይት የሚካሄድበት
ቡድናዊ ወደ ሆነ የአመራር ስልት ራሱን ለመለወጥችሏል
ይህም ከቀድሞው በተሻለ ሁኔታአመራር
ለመስጠት አስችሎታል ። በእርግጥ ቡድኑ ራሱ ምን ያህል ዲሞክራ ሲያዊ ነው ፣ አገርን የሚመራ እንደመሆኑ መጠን ምን አይነት የህዝብ ውክልና አለው የሚለው ሊያከራክር ይችላል ።
መሪው የሚመራበት መንገድ መሪው ስለአለም ካለው ግንዛቤ ይነሳል ። ለምሳሌ አንድ መሪ ሰዎችን መጥፎና ፣ ታማኞች ያልሆኑ ብሎ የሚያስብ ከሆነ አመራሩም ያንን ለመቋቋም በሆነ መንገድ ሲያደርግ ። የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት መሪ የነበረው ስታሊን ሰዎች መጥፎ ናቸው ብሎ የሚያስብ ሲሆን ለዛም በርካታ ሰዎችን ህይወትን የበላውን የአመራሩን ውጤት መረዳት ይቻላል። በአንፃሩ ደግሞ መሪው ለሰዎች በጎ አመለካከት ያለው ከሆነ ብዙም ሌሎችን በሚጎዳ መንገድ አይንቀሳቀስም
፣ በአንፃሩ የሌሎችን ስሜት በመጠበቅና በመረዳት ይሄዳል ።
ከዚህ ውስጥ ሁለት አይነት አስተሳሰቦችን
መመልከት ይቻላል ፣ ይህም በተዘዋዋሪ መንገድ አለምን እንዳለችው መረዳትና ፣ አለም እንደዚህ መሆን አለባት ብሎ ማለት ነው ።
ሌላው ደግሞ ውክልናን መስጠት ሲሆን ፣ አንዳንድ መሪዎች ለሌሎች ውክልናን በመስጠት የሚመሩ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ ሁሉንም ነገር ራሳቸው አይተው ወስነው ፣ ተቆጣጥረው የሚመሩ አሉ ። ሙሴ ዳኝነትን ለመስጠት ላይ ታች በሚልበት ወቅት ላባ መፅሀፍ ቅዱስን ተመልከት ፣ ሽማግሌዎችን
እንዲወክልና
እንዲመራ ሲመክረው ዋና ዋና የሆኑ ጉዳዮች ብቻ ወደሱ እንዲመጡለት
እንዲያደርግ
መክሮታል ። ይሁን እንጂ አይሁዳውያን
ከትክክለኛው
መንገድ ሲያፈነግጡ ፣ ከመንገዳቸው
እንዳይወጡ በመቅጣትም በማስተማርም
ጭምር ለመመለስ የሚጥር መሪ ነበር ። ሙሴ መንፈሳዊ መሪም ርእሰ - ብሄርም ጭምር ነበረ ። እንዲሁም አይሁዳውያን
ከባድ ችግር እንደሚገጥማቸው
ነግሯቸዋል «ክፉዎች ስለሆናችሁና
ስለማትታዘዙ
ወደፊት ከባድ ችግር ይገጥማችሀል
» ብሎ ነግሯቸዋል ።
በታሪክ መድረክ በተደጋጋሚ እንደታየው መሪዎች ሁሉ ተመሳሳይ ፍፃሜ አይኖራቸውም
። አንዳንዶች በስልጣን ዘመናቸውን ጨርሰው ተከብረው የቀረውን ህይወታቸውን
በሰላም ያሳልፋሉ ፣ አንዳንዶች የቀረውን ዘመናቸውን በእስር ፣ ሌሎች ከስራቸው በመባረር ፣ በእስር ፣ ሌሎች ደግሞ በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን
ሊያጡ ይችላሉ ፣ ሌሎች በህመም ከስራቸው ህይወታቸውን
በማጣት ሊሰናበቱ ይችላሉ ። ስለዚህ መሪው ሌሎች ፍፃሜያቸው በዚህ አይነት መንገድ ስለሆነ የኔም እንደነሱ ይሆናል ማለት የለበትም ፣ ከዚህ ይልቅ የማንኛውም ሰው እጣ ፈንታ ከሌላው በእጅጉ የተለየ እንደሆነው ሁሉ የመሪዎችም እጣ ፈንታ
በጣም የተለያየና ፣ ያልተጠበቁ ነገሮች የሚከሰቱበት
ነው ።
በአለም ላይ ጥሩ ነገርን ካደረጉ መሪዎች ብንወስድ ጥሩ ነገርን ያደረጉ ነገር ግን ህይወታቸውን
ያጡ መሪዎች አሉ ። ለምሳሌ ማርቲን ሉተር ኪንግንና ማህተመ ጋንዲን ብንወስድ ምንም እንኳን እነኚህ ሁለት መሪዎች ለህዝባቸው ጥሩ ብርሀንን የቀደዱና መልካም ያደረጉ ቢሆንም ህይወታቸውን
በሰው እጅ በመገደል ሊያጡ ችለዋል ። በአንፃሩ አንዳንድ መሪዎች ወንጀልን ቢሰሩም ጥሩ ነገርን ባያደርጉም ከህግ አምልጠው የቀረውን ህይወታቸውን
በሰላምና ያሳለፉም አሉባቸው ለዚህ አይነተኛ ምሳሌዎች የሚሆኑት የኢንዶኔዢያ
ፕሬዝዳንት የሆኑት ሱሀርቶ ምንም እንኳን በዘመናቸው በመቶ ሺዎች ዜጎችን ቢያስጨፈጭፉም
ከህግ አምልጠው የቀረውን ህይወታቸውን
መኖር ችለው ከዚህ አለም ተለይተዋል ፣ እንዲሁም የቺሊ ወታደራዊ መሪ የነበሩት አውግስቶ ፒኖቼም እንዲሁ በህግ ተጠያቂ ሳይሆኑ ቀርተው እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህግ ተጠያቂ ሳይሆኑ ቀርተዋል ።
ስለዚህ
መጥፎ ያደረጉም መሪዎች ከህግም ሆነ ከቅጣት ተጠያቂ ሳይሆኑ በሰላም ቀሪ ህይወታቸውን
ማሳለፍ የቻሉ ናቸው ። ብዙዎች ግን በወንጀል የተዘፈቁ ለስራቸው ዋጋ ከባድ ዋጋንና ውርደትንተከናንበዋል
። ለምሳሌ የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት በአለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የሀምሳ አለመታት እስር ሲፈረድባቸው
፣ እንደ ሙሀመድ ጋዳፉ ያሉት በጠላቶቻቸው
እጅ ሲገደሉ ፣ሳዳም ሁሴን ያሉት በጠላቶቻች እጅ ገብተው በሞት ተቀጥተዋል ።