Friday, February 6, 2015

ሰውና ተፈጥሮው



‹‹ ማንም ሰው በሁሉም ጊዜ ጥሩ ለመሆን የሚሞክር ቁጥራቸው በርካታ በሆኑት ጥሩ ባልሆኑ ሰዎች ይገፈተራል ፤ ስለዚህ አንድ ስልጣኑን መጠበቅ የሚፈልግ መስፍን ጥሩ አለመሆንን መማር አለበት ፣ ይህንንም እውቀቱን ሁኔታው እንደሚጠይቀው መጠቀም ወይም አለመጠቀም ይኖርበታል ››
ይህ የማክያቬሊ አባባል በአጭሩ ሲገለፅ ‹‹ሁልግዜ ጥሩ የምትሆን ከሆነ የመጥፎ ሰዎች መጫወቻ ትሆናለህ ›› ማለቱ ነው ፡፡
        ኒኮሎ ማክያቬሊ (መስፍኑ)
‹‹በእግራቸውም እንዳይረጋግጡት ፣ ተመልሰውም እንዳይነክሷችሁ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ፣ እንቁዎቻችሁንም በእርያዎች ፊት አትጣሉ፡፡ ››
         (እየሱስ ክርስቶስ የማቲዎስ ወንጌል ም፣7፡ ቁጥር 6)
ከላይ በተቀመጡት በሁለቱ አባባል መሀከል ተመሳሳይነት እንዳለ ልብ ማለት ይቻላል ፡፡ የማክያቬሊ ፅንሰ ሃሳብ ቀድሞ ሰዎች ሁሉንም ነገር እግዝአብሄር እንዳለ ይሉ የነበረ ቢሆንም ይህን ከላይ ወደ ታች ማለትም ከእዝአብሄር ወደ ሰዎች የነበረን ግንኙነት በመለወጥ ሰዎች የራሳቸውን እጣ ፈንታ ራሳቸው መወሰን ወይንም ቅርፅ ማስያዝ ይችላሉ ፡፡ ከላይ ወደ ተች ታች (Vertical) የነበረውን ግንኙነት ማክያቬሊ ወደ ጎን (Horizontal) ዘረጋው ፡፡  ከእርሱ ቀድሞ ፖለቲካና ቤተክርስትያን በእጅጉ የተቆራኙና አንዱን ከአንዱ መለየት የማይቻልበትና ፖለቲካ ሃይማኖታዊ በሆኑ አስተሳሰቦች የሚመራና የሚቃኝ ነበረ ፡፡ ይህም ይህ ማ ዓለም ባለቤትና ሁሉን ያደረገ አንድ ላእላይ መንፈሳዊ ህላዌ (Being) አለው የተቀመጠ ህግና ስርአት አለው የሚለውን የፕሌቶን በኋላም የክርስትናን የሌሎችን ሃይማኖቶችን አስተሳሰብ የሚገዳደር ነው ፡፡ 
 በማክያቬሊ አስተሳሰብ ግን ሀይማኖትና የተለያዩ ሲሆኑ ምድራዊ የሆነው ፖለቲካ ራሱን ከሀይማኖት መለየት አለበት የሚል አቋም አለው ፡፡ ሰው ራሱ በሚያርገው ማንኛውም ነገር የራሱን እጣ ፈንታ መወሰንና ቅርፅ ማስያዝ ይችላል የሚል ነው የማክያቬሊ ፍልስፍናዊ መርሁ ራሳቸው የኢጣሊያ ምሁራን የፖለቲካ ሳይንስ አባት ተደርጎ የሚቆጠረው ማክያቬሊ በታሪክ በፖለቲካው መስክ ያበረከተው ፍልስፍና ይሄው መሆኑን ይገልፃሉ ፡፡
ነገር ግን ማክያቬሊ በታሪክ እጅግ አወዛጋቢ ከሆነ ሰዎች አንዱ ሲሆን ፣ ዘ ካውንት ኦፍ ሞንቴ ክሪስቴ (The Count of Monte Cristie) በአማርኛ ‹‹እፎይታ›› ተብሎ የተተረጎመው አበጀ ጎሹ ያሳተመውና የተረጎመው መፅሀፍ ደራሲ ማለትም አሌክሳንደር ዱማስ በፃፈው ፅሁፍ ላይ ማክያቬሊ ዋና ገፀ ባህሪ አድርጎታል ተብሎ እሚታመነውን ቄሳር ቦርጂያን ‹‹ከአባቱ የባሰ እጅግ ስግብግብና ጨካን ነበረ›› ሲለው ህመም ባይጥለው ኖሮ እጅግ ስኬታማ ይሆን ነበረ ብሎ ማክያቬሊ የሚቆጭለት ይኸው በወጣትነቱ የሞተው መስፍን በዛን ዘመን ተበታትና የነበረችውን ጣሊያንን አንድ ያደርግ ነበረ የሚል ስሜት ስለነበረው ለመስፍኑ የበዛ አድናቆት እንደነበረው መገመት ይቻላል ፡፡ ነገር ግን ይህን ሰው ማክቬሊ የመስፍኑ መፅፍ ዋና ገጸ ባህሪ ማድረጉ ግን ማክያቬሊን ክፉኛ ያስተቸውንና በታሪክ አወዛጋቢ አድርጎት አልፏል ፡፡
መስፍኑ የተባለው መጽሀፍም የመጨረሻ ምእራፉ ጣሊያንን አንድ ሊያደርግ የሚመጣ ማንኛውም መስፍ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚመክር ነው ፡፡ ስለዚህ ማክያቬሊ ይህን መፅሀፍ የፃፈው የጣሊያንን አንድነት ለማስከበር ሊመጣ ይችላል ብሎ ለሚያምነው መሪ እንደ ምክር እንዲሆን ነው እንጂ ለወደፊቱ ዘመን ለሚመጣው የፖለቲካ ሳይንስን አዲስ አስተሳብን ፈር ለመቅደድ አይመስልም ፣ ነገር ግን በፃፈው በዚህ ወጣ ባለና ከዘመኑ እጅግ የቀደመና ያፈነገጠ መፅሀፍ ሰበብ ከሰው ተገልሎ፣ ከስራው ተባሮና ተግዞ በብቸኝነት በገጠር ርስቱ ቁጭ ብሎ የፃፈው ይሄው አስተሳሰቡ የዘመናዊው የፖለቲካ አስተዳደር መሰረታዊ ፍልስፍናን የሚወክል መፅሀፍ ሊወጣው በቅቷል፡፡
መፅሀፉ የአርትኦት ስራ ያልተሰራበትና በአንድ ሰው በመገለል ለብቻ ሁኖ ተጽፎ  የተሰራጨ ነው ፡፡ ከጨረሰውም በኋላ አንዱን መታሰቢ ላደረገለት ሎሬንዞ ለተባለው ለሜዲቺ መስፍን የተቀሩትንም ጥቂት ኮፒዎችን ለጓደኞቹ ከበተነ በኋላ ሽልማትንና ወደ ስራው መመለስንና ምስጋናን የጠበቀው ማክያቬሊ ያልጠበቀውን ስድብንና ነቀፋን ሲያስተናግድ ከመገለልና ወደ የልኡላኑን ፊት ለማግኘት ሳይታደል በዚያው ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ አልፏል ፡፡ የካቶሊኩ ፖፕ በተለይም አንድ አዲስ መስፍን የቀድሞውን መስፍን ቤተሰቡን ጭምር አብሮ ነው ማጥፋት ያለበት ማለቱን ክፉኛ ሲተቹት ፣ በዘመኑ የነበሩ የጣሊያን የፖለቲካ መሪዎችም መታሰቢያ የተደረገለት ሎሬንዞም ጭምር እምብዛም አልወደዱትም ፡፡
ከዚያ በኋላ የእርሱ ስራ በእንግሊዝና በፈረንሳይ ፀሀፍት እየተተረጎመ ለተቀረው አለም ሊተዋወቅ በቅቷል ፡፡ አሁን ከአለማችን አንድ መቶ ተፅእኖ አሳዳሪ ከሚባሉ መፅሀፍት ይሄው ‹‹መስፍኑ›› የተባለው መፅሀፍ ነው ፡፡
ለነገሩ እርሱ ሌሎች በርካታ ስራዎችንም የሰራ ሰው ሲሆን ለምሳሌ የፍሎሬንስን ሪፐብሊክ በተመለከተ ምን መምሰል እንዳለበት ፣ እንዲሁም ስለ ጦርነት ጥበብ የፃፋቸው ፅሁፎች በታሪክ ሁነኛ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው ፡፡ በተለይም ስለ ፍሎሬንስ ሪፐብሊክ ፅሁፉ ለዘመናዊ የመንግስት አስተዳደርና ፣ ለህገመንግስት ቅርፅ ተፅእኖ አሳዳሪ ስራው ነው ፡፡ በኋላ ላይ ወደ አውሮፓ የመጡትና የፈላጭ ቆራጭ የዘውዳዊ ስርአትን በሪፐብሊካዊ አስተዳደር ለመተካት ለሚፈልኩ ወጣት ፖለቲከኞች የእርሱ ሪፐብሊክ ስራው መሰረት ተደርጎ ይቆጠራል በኋላ ላይም የሩስያ አብዮተኞች የእርሱን የሪፐብሊክ ፍልስፍና ወስደው ስራ ላይ አውለውታል ፡፡
በአሁኑ ዘመን ውድድር የከፋበት ዘመን የሆነው ነገር ግን ይህንን ዘመን ሊገልፅ የሚችለው የዝግመተ - ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ነው ፡፡ አንድ አዞን ብንወስድ አድርጎ ትልቅ እስሚሆን ድረስ ትላልቆቹ አዞዎች በሚኖሩበት አካባቢ የማይገኝ ሲሆን ጥልቀት ወደ ሌላውና ትላልቆቹ ወደ ማያዘወትሩት አካባቢ ራሱን ያሸሻል ፡፡
በአሁኑ ወቅት በዝርያዎች መሀከል ያለው ውድድር ከፍተኛ ሲሆን በዝግመተ ለውጥ ንድፈ - ሃሳብ መሰረት አንድ ዝርያ በጣም ከተባዛ በኋላ እርስ በእርሱ የከፋ ውድድርን ማደግ ይጀምራል ፡፡ ቀድሞ ለምሳሌ የኒያንደርጋትታልና የሆሞ ሳፒያንስ (Neandertal Homo Sapians) ዝርያዎች የነበሩ ቢሆንም ኒያንደርታል በወረርሽኝ በሽታ ወይንም ከሆሞ ሳፒያንስ በመጣ ተፅእኖ እንደጠፋ ወይንም ምንነቱ በማይታወቅ ምክንያት እንደጠፋ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ ፡፡ የአንጎላቸው መጠን ከአሁኑ የሰው ዘር ወይንም ከሆሞ ሳፒያንስ ያንስ የነበረውና ነገር ግን እንደ ሰው ቆመው ይራመዱ የነበሩትና በራሳቸው ቋንቋ ይግባቡ የነበሩትና ተወዳዳሪ የነበሩት የኒያንድርታል ዝርያዎች ጠፍተው በምትካቸው በሳይንሳዊ ስሙ ሆሞ ሳፒያን ወይንም ዘመነኛው የሰው ልጅ የዚህ ምድር ወራሽና ባለቤት ሊሆን በቅቷል ፡፡
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የአየር ንብረት ለውጥ በአገራት በተለይም በታዳጊ አገራት ላይ ከባድ ጉዳትን እያደረሰ የሚገኝበት ፣ ለክፍለ ዘመናት ህዝቦችንና ማህበረሰቦችን በሰላም አስተሳስሮ ያኖረው የሃይማኖት መፋለስ የሚታይት ፣ የእርሻ መሬት ወደ ከተማነት እየተቀየረ ያለበት ፣ ለምግብ ሰብል አመቺ የነበረ መሬት ወደ ጠፍ መሬትነት እየተቀየረ ያለበት እንዲሁም ወንዞችን ጨምሮ የውሀ አካላትና ውቅያኖሶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተበከሉ ያሉበትና ፣ የአለም ሙቀት መጨመር ለሰው ልጅ ካንሰርን ጨምሮ የበሽታ ስጋት የደቀነበት ፣ የአለም ሰሜናዊና ደቡባዊ ንቀፍ ክበባት በረዶ እየቀለጠ የሚገኝበትና የውሀ አካላትና ደሴቶች እየሰመጡ የሚገኙበት ዘመን ነው ፡፡
ስፒኖዛ መልካም እጅግ በጣም ጥቂት ስለሆነ መልካም ያልሆኑ ነገሮች ይበዛሉ ሲል ፣ መፅሀፍ ቅዱስም ‹‹የሰው ልብ እጅግ ክፉ ነው›› ይላል ፡፡
None of you is a believer, until what you love for yourself loves for your brother. Prophet Mohamed
በራስህ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ እንዲደረግ አታድርግ የሚለው አባባል በበርካታ ሃይማኖቶችና ፍልስፍናዎች ውስጥ ያለ ነው ፡፡
ጠቢቡ ሰለሞን ስለ ሰው ልጅ ሲናገር መፅሃፈ መክብብ ምእራፍ 6፣15 ላይ ‹‹ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ ሃጥእም በክፋቱ እጅግ ዘመን ሲኖር ፣ ይህን ሁሉ ከንቱ በሆነ ዘመኔ አየሁ ፡፡ እጅግ ጻድቅ አትሁን ፣እጅግ ጠቢብም አትሁን ፣ እንዳትጠፋ ፡፡ እጅግ ክፉ አትሁን፣እልከኛም አትሁን ጊዜህ ሳይደርስ እንዳትሞት›› ላይ ይላል ፡፡ ብዙ ሰዎች አውነት ሊሆን የማይችለውን ነገር እውነት ነው ብለው ያምናሉ ፡፡

Gorfu Contra Nietzsche



ኒች ዛርቱስትራን የፃፈው በዘረኝነት በመሳሳት መሆኑ አጠያያቂ ነው በእርግጥ ሶቅራጥስን አፍንጫው ደፍጣጣ ፣ መላጣ እና ከአውሮፓዊነት ይልቅ አፍሪካዊ መልክ እንዳለው ታሪኩ የተፃፈ ሲሆን ይህም ዘረኝነትን ማለትም ኒች ሶቅራጥስን ሲያቃልለው መልኩን በመመልከት ይህ ሰው አውሮፓዊ ወይንም ግሪካዊ ሳይሆን አፍሪካዊ ነው በሚል ነው ፡፡ ለዚህም የኒቼን ታሪክ የፃፉ ሰዎች እንደሚስማሙበት ኒች ዘረኝት የሚነካካው ሰው እንዳልነበረና ከራ ጀርመናዊያንን ይልቅ ፈረንሳውያንን ይበልጥ ያደንቅ የነበረ ሰው እንደነበረና በዘመኑ በጀርመን አገር ተንሰራፍቶ ከነበረው የፀረ - ሴማዊነትንም ፈፅሞ የማይካካው ሰው እንደነበረ ስለ እርሱ የተፃፉ ድርሳናት ያመለክታሉ ፡፡ በራሱ ወገኖች በሆኑ ጀርመናዊውያን ፀረ - ሴማዊነት ከት ብሎ ይስቅ እንደበረ ባገሩ ሰዎች ከንቱ ዘረንነኝነት የሚስቅ ሰው ችአ እንደነበረ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት [1]፡፡
የኒችን ስራ ከሳይንስ አንፃር ለመመርመር መነሳት ወደ መስመሩን ወደ መሳት ሊያመራ ሲችል ፣ ምክንያቱም ይሄ ዛርቱስትራ (Thus Spoke Zarathustra) ይናገራል የሚለው የኒች ስራ ላይ ዛርቱስትራ እንደ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን እንደሚናገረው ቃና ነው የሚናገረው ፡፡ ይህ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው እንጂ ሳይንስን ወይንም የምናልባት ንድፈ - ሓሳብን (Probability Theory) ፣ የአቶሚክ ፊዚክስን በመጠቀም ለማብራራት ፣መነሳት ሀይማኖትን በሳይንስ አመክንዮ ለመርታት እንደ መነሳት እና ወደ ግዙፉና መሰረታዊ ወደ ሆነው የሳይንስና የሀይማኖት ክርክር የሚመራ ነው ፡፡ በሳይንስና ሀይማኖት ክፍለ ዘመናትን ባስቆጠረው ክርክር ውስጥ አንዱ የአንዱን አመክንዮ እንደማይቀበለው የታወቀ ሲሆን ሳይንስ ሀይማኖት የሚያምንበትን ራእይ ፣ መገለጥን ፣ ተአምራትና ገድሎችንና ፈውስን ሳይንስ ፈፅሞ የማይቀበላቸው ሲሆን በአንፃሩም ሀይማኖት በበኩሉ የኢ - አማንያን (Atheists) መሰረታዊ ንድፈ ሃሳብ የሆነውን የሳይንስን ዝግመተ - ለውጥ ወይንም (Evolution) ‹ኢቮሉሽን›ን ፣ ወይንም የቁስ አካላዊ ፍልስፍናንና ንፅርዮተ - ዓለምን ‹‹World View›› ወይም ‹‹ወርልድ ቪው› ፈፅሞ እንደማይቀበላቸው የታወቀ ነው ፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ማለትም ሀይማኖትን ሳይንስ የሚጠቀሙባቸው መሰረታዊ አስተሳሰቦች ሃራምባና ቆቦ ስለሆኑ ሁለቱን ማስታረቅ አስቸጋሪ ሲሆን በዘመናትም መራራቃቸው እየሰፋ ነው የሄደው ፡፡ 
በእርግጥ ሀይማትኖት የሳይንስን አንዳንድ የተቀበላቸው አስተሳሰቦች አሉ ፣ ለምሳሌ ጋሊሊዮ ጋሊሊን በዘመኑ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብታወግዘውም ከብዙ ክፍለ ዘመናት በኋላ ግን ከቤተርስትያን አስተምህሮ ጋር ግጭትን እንደማይፈጥር በመረዳት ለጋሊሊዮ ስራ እውቅናን ሰጥታዋለች ፡፡ በኋላም ላይ ስለ ጠፈር ምርምር እንዲሁ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እውቅናን ስትሰጥ ሃይማኖት በተወሰነ መልኩ ሳይንስ ከሀይማኖት አስተምህሮ ጋር ግጭት እንደሌለው በመረዳት የሀይማኖት ሰዎች ለሳይንስ ክርክር ማድመጥና ምላሽን መስጠት ጀምረዋል ፡፡ ይሁን እንጂ ሀይማኖት እና ሳይንስ ተቀራርበዋል ፣ ታርቀዋል ማለት አይደለም ፡፡ በመሰረቱ ሳይንስ ከሀይማኖት አንፃር በጣም እንጭጭና ጨቅላ ነው ፣ ነገር ግን ብዙዎቹ ሳይንቲስቶች ይህንን ለማመንም ሆነ ለማወቅ ዝግጁ አይደሉም ፡፡
የአንፃራዊ ንድፈ ሃሳብን አልበርት አንስታይን ሲያቀርብ አንዷ የዚህን ንድፈ ሀሳብ ተቃዋሚ የነበረችው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ስትሆን ፖፑም አንስታይንን ተችተውታል ታላቁ ፈላስፋ ኒቼ ከአልበርት አንስታይን የአንፃራዊነትን ንድፈ ሃሳብ ከማግኘቱ በፊት በፃፋቸው ፅሁፍ ላይ ‹‹No Truths Only Interpretations›› የሚል አባባልን የተጠቀመ ሲሆን ይህም ‹‹እውነት የሚባል ነገር የለም የእውነት ትርጓሜዎች እንጂ›› ሲል ይህም እውነት በተለያየ መንገድ ከተለያየ ማእዘን በአንፃራዊነት በበርካታ እርስ በእርሳቸው በማይመሳሰሉ ትርጓሜዎች ሊሰጣት ይችላል - እዚህ ላይ ኒችና አንስታይን ይስማማሉ ማለት ነው ፡፡


[1] Nietzsche , Wikipedia.com

ሃሳባዊነትና ቁስ-አካላዊነት



ካርል ማርክስ የሀሳብን ሚና ዝቅ በማድግ የቁስ አካልን ሚና ከፍ በማድረጉ ምክንያት ታላቁ የፍልስፍና ክህደት በመባል ይታወቃል ፡፡ ከአለማችን ፈላስፎች ለምሳሌ ታላቁን ፕሌቶን ብንወስድ የሀሳብን ቀዳነሚነትን ያስቀደመ ሲሆን በዚህም እጅግ የሚደነቅበትና የክርትና ሀይማኖት ሳይቀር ከፕሌቶ ብዙ ሀሳቦችን ወስዷል እስከ መባል ደርሷል ፡፡ የማርክስ ፍልስፍና የወደቀበት ምክንያት የሰው ልጅን የራስ ወዳድነት ተፈጥሯዊ ባህሪን (Individualism) ባለመቀበሉ ፣
የካርል ማርክስ ሀሳብን የፍራንሲስ ፉኩያማ የታሪክ ፍፃሜ (The End of History) የሚለው አስተሳሰብ ሁለቱ ፅንፍና ፅንፍ ያሉ ሓሳቦች ናቸው ፡፡ በፉኩማያ አስተሳሰብ መሰረት የታሪክ ፍፃሜው የሚሆነውና ዓለም የምታመራው ወደ ሊበራል ዲሞክራሲ ስርአት ነው በአንፃሩ ለካርል ማርክስ ግን የታሪክ ሂደቱ ገና ያላበቃ ሲሆን የሚሄደውም ወደ ኮሚኒዝም ነው ፡፡ የሁለቱም አስተሳሰብ ግን የየራሱ ድክመቶች አሉበት ፍራንሲስ ፉኩያማ መጀመሪያ ያፈለቀውን ሃሳቡን ከዚያ በኋላ እያሻሻለ የመጣ ሲሆን በእርሱ አስተሳሰብ መሰረት የዓለም ታሪክ የሚያመራው ወደ ሊበራል ዲሞክራሲ ስርአት ሲሆን ይህም በርካታ የምእራባውያን የሚዲያ ጋዜጠኞች የሊበራሊዝም ስርአት ትክክለኛ ነው ለማለት የሚጠቅሱት ነው ፡፡
የሰው ልጅ እንደ አንድ ብቸኛ ዝርያ የሚቃለል አይደለም በአለም ላይ በርካታ አጥቢዎች ወፎች ፣ አሶች ፣ ተሳቢዎች ሳቢዎች ወዘተ… ቢሞሉም የሰው ልጅ ህሊና ስላለውና ህሊናዊ - ንቃትን ስለሚጎናፀፍ የተለየ ፍጡር ነው ፡፡ እንደ አንድ ተራ ዝርያ ወይ እንሰሳ  የሚታይ አይደለም ሰው ፡፡
የካርል ማርክስ ኮሚኒዝም እጅግ የበዛ ተምኔታዊ ወይም ሃሳባዊነት (Utopia) ‹‹ዩቶፒያ›› የሚጎላበት እና ተግባራዊ ለመሆንም ከሰው ልጅ ባህሪና ተፈጥሮ አንፃር ብዙ መቃኘትን የሚሻ አስተሳሰብ ነው ፡፡ የመንፈስንም ሆነ የሃሳብን መሪነት ጨርሶ የማይቀበለው ማርክሲዝም ውድቀቱ ይሄው ቁስ አካልን ከሃሳብና ከመንፈስ ማስቀደሙ ሲሆን ሊበራሊዝምም ቢሆን ከላይ እንደሚታየው ሁሉንም ሰው ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ይምሰል እንጂ ፣ በነፃነትና በሊበራሊዝም ስም ከልክ ያለፈ ነፃነትን በመስጠት የሰው ልጅ ተፈጥሮን አስከመገዳደር የሚደርሰው ይሄው የሊበራል ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው ፡፡   
ማንም ሰው እንደሚረዳው ሁለት አይነት አለሞች እንዳሉ ነው እነሱም ፣ መንፈሳዊውና ቁሳዊው እንዲሁም የሚታየውና የማይታየው በመባል ይታወቃሉ ፡፡ ብዙውን ግዜ ሰዎች የሚታየውን ወይንም ቁሳዊው የሆነውን ዓለም በቀላሉ ሲረዱትን በዚህም ዓለም ውስጥ ስኬታማ ለመሆንና የሚያስፈልገን የሚሉትን ቁሳዊም ሆነ የገንዘብ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲጥሩ ማየት የተለመደ ሲሆን ነገር ግን ከዚያም ባለፈ ሚስት ከማግባትና ልጅ ከመውለድ ፣ መኪና ከመግዛት ፣ ሀብት ከማፍራት ፣ ገንዘብ ከማከማቸት ፣ በስልጣን ላይ ስልጣን መደራረብ ፣ በትምህርትና በስራ ከመግፋት ባለፈ ስላለው ስለማይታየው ዓለም ለብዙ ሰዎች ግልፅ አይደለም ፡፡
ጠቢቡ ሰለሞን የመንፈስን ሃያልነትንና ምንም ነገር እንደማይገድበው ሲገልፅ በመፅሀፈ መክብብ ምእራፍ 8 ፣ቁጥር 8  ላይ ‹‹መንፈስን ለማስቀረት በመንፈስ ላይ ስልጣን ያለው ሰው የለም›› ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለወገኖቹ ለእብራውያን ባስተላለፈው መልእክት እብራውያን ምእራፍ 14 ፣ ቁ 1-3 ‹‹አለሞች በእግዝአብሄር ቃል እንደተዘጋጁ ፣ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታየው እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን›› የማይታየውን ነገር የተረዱ በእምነት  1 ቆሮ ምእራፍ 2 ፣ ቁጥር 14 ላይ ‹‹ለፍጥረታዊው ሰው የእግዝአብሄር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም ፣ በመንፈስም የሚመረምር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም ፡፡ መንፈሳዊው ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም ››
ከሳይንሱም አንፃር ብንመለከት ማንኛውም ቁሳዊ የሆነ ነገር በጊዜና በቦታ የተገደበ ሲሆን ጊዜና ቦታ (ታይም ስፔስ) አጥረው የማይገድቡት ምንም አይነት ቁሳዊ የሆነ ነገር የለም ፡፡ ጊዜን ብንወስድ ቁሳዊ የሆነ ነገር እንዲያረጅና እንዲሰባበርና አንዲሞት ያደርገዋል ፣ ቦታንም ብንወስድ አንድ ቁሳዊ የሆነ ነገር ህልውና የሚኖረው በቦታ ውስጥ ሲሆን ቦታ ከሌለው ግን ነገርየው በየትኛው ቦታ መኖር ስለማይችል ህልውናው ይጠፋል ፡፡ይሁንና መንፈስ ቁሳዊ ከመሆን ጋር ግንኙነት የሌለው ነገር በመሆኑ በጊዜም ሆነ በቦታ አይገደብም ፡፡ ለዚህም ነው አንድ መንፈስ አማኞችና ተከታዮች ካሉት ሺህዎችን አመታት ለሚጠሩት ሰዎች እየተገለጠ የሚኖረው ፡፡
የዓለማችን ታላላቅ ሀይማኖት መስራቾች ራሳቸውን ከዓለም አግልለው ስለ ዓለም ብዙ ብዙ አስበዋል፣ ተጨንቀዋል ፡፡ ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት እየሱስ ክርስቶስና ነቢዩ መሀመድ ሲሆኑ እየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከፆመና ከፀለየ በኋላ በዚያውም ሰይጣን ሲፈታተነውም ስለ ዓለም ነገስታት ክብርንና በማሳየት ሲሆን የዓለም ነገስታትን እሰጥሀለሁ ያለው ሲሆን ክርስቶስም ባለመቀበል መልሶለታል ይህም የሚያሳየው ሀይማኖት ዓላማው ከዚህ ምድር ካለው ማንኛውም ክብርና ሀብት በላይ መሆኑን ሲሆን ቡድሀንም ብንወስድ የንጉስ ልጅ የነበረና ልኡል የነበረ ሲሆን ያን ሁሉ ክብርንና ሀብትን ትቶ እንደመነነና ለ49 ቀናት እንደ በተመስጦ ውስጥ እንደቆየ ኒርቫናን (Nirvana) ወይንም አብርሆትን በመጎናፀፍ ዛሬ የዓለማችን አንዱና ታላቅ የሚባለውን ሀይማኖት እንደመሰረተ የታወቀ ነው ፡፡
ከሃገራችን ፈላስፎች ይህንን አብዝተው ያሰቡበት እጓላ ዮሃንስ ሳሆኑ አይቀሩም ፡፡ 
የሃሳብን  ወይም የመንፈስን ቀዳሚነት መካድ ትልቁ ክህደት ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡ የመንፈስን ቀዳሚነት መካድ የመንፈስን መሪነትን ማጣትን ያስከትላል የመንፈስንና የሃሳብን ቀዳሚነት አለመቀበል ፣ ይህም ክህደት ትልቅ ሽንፈትን አስከትሏል በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ፡፡ ለዚህ አይነተኛው ምሳሌ የሚሆነው ማርክሲዝም ሲሆን የመንፈስን ህልውናም ሆነ ከቁስ አካል በፊት የሀሳብን ቀዳሚነትን የካደው ማርክሲዝም አይሸነፉ ሽንፈትን ተሸንፎ በታሪክ አብቅቶለት ከመድረኩ ተወግዷል ፡፡ ይሁን እንጂ በአለም ታሪክ የአሁኑን ዘመንን ያህል መንፈሳዊነት ወይንም ሃይማኖታዊነት አስፈላጊ የሆነበት ዘመን የለም ይቻላል፡፡ ነገር ግን በአንፃሩ ወቅቱ ቁሳዊ ዘመን በመሆኑ ምክንያት መንፈሳዊነት የተዘነጋበትና ቦታ የማይሰጠው ዘመን ነው ፡፡