Friday, February 6, 2015

የአሁንነት ሀይል



ኤክሀርት ቶሌ የተባለው የአሁንት ሀይል ‹‹The Power of Now›› የተሰኘና ሌሎች በርካታ መሀፍትን ያበረከተው የዘመናችን እውቁ ረቂቅ መንፈሳዊ አዋቂ ‹‹ሚስቲክ›› መሆኑ የሚነገርለት ይህ መንፈሳዊ መምህር እንደሚለው ብዙ ሰዎች አሁንን ረስተው የሚያስቡት ገና ስላልደረሱበትና ወደፊት ስለሚመጣው ወይም ሊመጣ ስለሚችለው ነገር ነው ፡፡ አሁን የሚያደርጉት ነገር በሙሉ ወደፊቱ ለሚሰጠው ውጤት ብለው ሲሆን ፣ የአሁንን ጊዜ ለወደፊቱ መሸጋሪያ ብቻ አድርገው ይወስዱታል ፡፡ ነገር ግን ያ ወደፊት የሚሉት ነገር ወይም ሁኔታ ላይመጣም ፣ ላይኖርም፣ ላይከሰትም ይችላል ፡፡ በዚያን ወቅት እነርሱም ያንን ነገር ለማየትም ሆነ ለመመልከት በዚያ ቦታ ላይገኙም ፣ ላይኖሩም ይችላሉ ፣ ነገር ግን ልክ በወደፊቱ ጊዜ እንደሚኖሩ እርግጠኛ በመሆን ላልደረሱበት ጊዜ አሁን የሚያደርጉትን የወደፊቱ እነርሱ ይመጣል ለሚሉት ነገር መሰረት እየጣሉ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ ፡፡
በኤክሀርት አባባል ሰዎች ደስታ ወደፊት ርቆ ያለ እና ገና ወደፊት እሚደረስበት ነገር መሆኑን አድርገው ያስባሉ ፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ከዚህም አልፈው የአሁን ወቅት የወደፊቱ ፣ የሚመጣው እንቅፋት እደሆነ አድርገው ያስባሉ ፣ ለአሁኑ ወቅት ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረትና ጥቃቄን ፣መደረግ ያለበትንም ነገር በአግባቡ ሳያደርጉ ይቀራሉ ፡፡ የዚህ አይነት ሰዎች የአሁንን ወቅት በአግባቡ ሳይጠቀሙበት የሚቀሩት እነሱው ሲሆኑ ፣ ነገር ግን ለራሳቸው የሚስቡት የአሁኑን ወቅት በትክክል እየተጠቀሙበት እንዳሉ ነው ፡፡ በዚህም በእጃቸው ያለውን የአሁኑን ወቅት በአግባቡ ሳይጠቀሙበት ይቀራሉ ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ የሚያደርገው ነገርና የሰው ልጅ ቆይታም በጊዜ ሂደት ውስጥ ያለ ነገር እንደመሆኑ የአሁኑ ወቅት አመለጠው ማለት በህይወት ጉዞው ውስጥ ‹‹ህይወቱ አመለጠው›› ማለት መሆኑን ኤክሀርት አበክሮ ያስረዳል ፡፡  
ኤክሀርት እንደሚያክለው ‹‹በሆነ ወቅት ስኬታማ እሆናለሁ ብላችሁ አታስቡ እናም ወደፊት በአንድ ወቅት እንደዚህ እሆናለሁ ብላችሁ አትጠብቁ ፣ ከአሁኑ ወቅት ጋራ ስኬታማ የሆነና የሚመቻሁን ግንኙነት ውህደትና መስተጋብርን ፍጠሩ እንዲሁም አሁን በምትሰሩት ማንኛውም ነገር ምሉእነትና እርካታ ይሰማችሁ›› ይላል ፡፡ ብዙ ሰዎች እነሱ ለማይኖሩበት ዘመንና ለማይገኙበት ወቅት ሲዘጋጁ ማየትና መስማት የተለመደ ነው ፡፡ 
በእርግጥ እዚህ ጋር የሰው ልጅ በእቅድ የሚመራ እንደመሆኑ መጠን እቅድን አያውጣ ፣ ለወደፊቱ መሰረትን አይጣል ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው ፡፡ ሰዎችን ትተን አገራትም ጭምር የአምስት ፣ የአስር አመት እቅድን ያወጣሉ ግብ እና ራእይ ያስቀምጣሉ ፡፡ አሁን እምናደርገው ነገር ለወደፊቱ መሰረት መሆኑን አሁን በትክክል ያላደረግነው ነገር አድሮ መልካም ውጤትን እንደማያስገኝልን የምናውቀው ሀቅ ነው ፡፡ አሁን መልካም ነገርን ካደረግን ግን የዚያን ውጤነትን እንደምናጭድ ፣ አሁን ባልጣልነው መሰረት ላይ ወደፊት እንደማንገነባ የታወቀ ሲሆን ፣ ታላቁ መጽሀፍም ‹‹ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው›› ይለናል ፡፡
ኤክህርት ግን ይህንን ቀላል ሀቅ በመዘንጋት ሳይሆን ሰዎች ግላዊ ህይወታቸውን በዚህ ምድር ላይ በሚኖሩበት ወቅት የዚህ ምድር ቆይታችን አጭር እንደመሆኑ መጠን በዚህ በተወሰነ እድሜ ልናደርግ የምንፈልገውን ነገር ገና ለገና ወደፊት ላልመጣው ዘመን ማድረግ የምንፈልገውን ነገር ሳናደርግ በመዘጋጀት ብቻ እንዳንጨርሰው ለመጠቆም መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
‘time isn’t precious at all , because it is an illusion’ Eckhart Tolle
መፅሀፍ ቅዲስ ትንቢተ ኢየሳያስ ‹‹ሃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ አመዳይ ብትሆን እንደ ሸማ ትነጣታለች›› ይላል ‹‹ኑና እንዋቀስ›› ያለፈውን እርሱንና ስለአሁኑ ብቻ አስቡ ፡፡ በአሁኑ ውስጣችሁ ከተለወጠ ፡፡ ስለ አለፈው ሃጢአታችንም ሆነ ስለ መጪው ስኬታችን አብዝተን መተማመን የለብንም ፡፡ ይህ በቅዱሳን መፅፍት ውስጥም የሰፈረ ነው ፡፡

ታላላቅ ሰዎችና ስራዎቻቸው



በዓለም ታሪክ ውስጥ ግለሰብ ሰዎች ለዓለም ያደረጉት አበርክቶ ለክፍለ ዘመናት ህልውና ከነበራቸው ታላላቅ ኢምፓየሮችና ነገስታት ካደረጉት በብዙ እጥፍ ይበልጣል ፡፡ ለምሳሌ ከግሪክ ስልጣኔ እና ኢምፓየር ይልቅ ታላላቆቹ የግሪክ ፈላስፎች በዘመናቸው ለሰው ልጅ ያበረከቱት ይልቃል ፡፡ ግሪክን ከሚያክል ስልጣኔ ይልቅ በተደጋጋሚ ስማቸው የሚነሳው ፕሌቶ፣አሪስቶትል እና ሶቅራጥስ እና መሰል የግሪክ ፈላፋዎች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡
በዚህም በአንድ ዘመን ወይም በጥቂት ክፍለ ዘመናት ውስጥ ተነስተው ገነው ከዚያም ከሚደበዝዙት ኢምፓየሮችና ማንም የሚያስታውሳቸው ከማይኖረው ነገስታት እና ስልጣኔዎች ይልቅ ዘመንና ጊዜን ትውልድን ቋንቋን መሻገር የሚችለው እውቀትና ሃሳብ እንዲሁም የዚሁ እውቀት ጥበብና ሃሳብ ባለቤቶች ፈላፎችና ገጣሚዎች፣ደራሲዎች፣ሰአሊዎች ይበልጣሉ ፡፡ ለምሳሌ የጥንት ሮማውያንን ብንወስድ ኦቪድን የመሰለ ገጣሚን አፍርተዋል፡፡ ሜታሞርፎሲስንና (Metamorphosis) የፍቅር ጥበብ (The Art of Love) የመሳሰሉ ፅሁፎችን በቅኔ የፃፈው ይህ ባለቅኔ ገጣሚና ፈላስፋ የጥንት ሮማውያን ለመቶዎች አመታት በዓለም ላይ በሀያልነት ሲቆዩ ካፈሯቸው በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ታላላቅ ሰዎች ሆኖ በታሪክ ሲሰፍር ፅሁፎቹ አሁንም ድረስ እንደ አዲስ ይነበባሉ ፡፡ ይህ ገጣሚ፣ በአብዛኛው ስማቸው በደግ ከማይነሳው እንደ ኔሮና ካሊጉላን ከመሳሰሉት ሮማውያን ነገስታት ይልቅ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል ፡፡ 
ሰአሊዎችንም ብንወስድ ለምሳሌ ፓብሎ ፒካሶ ስራዎች ሰአሊው ካለፈ በኋላ፤ አሁንም ድረስ በዋጋም ሆነ በተወዳጅት የላቁ ሲሆን የእርሱ ስራዎች ዋጋም የአክስዮን ገበያዎችን የሚበልጥ የዋጋ እድገትና ዋስትና ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል ፡፡ ሊኦናርዶ ዳቬንቺም እንዲሁ ከጣልያን የህዳሴው ዘመን ሰአሊና ፈላስፋዎች አንዱ ሆኖ ሁለገብ እና ተወዳጅ አርቲስት ሆኖ በታሪክ ሲሰፍር እርሱ የኖረበት ዘመን የጣልያን መሳፍንትና መኳንንት እነማን እንደነበሩም ማንም ትዝ አይለውም ፡፡
የዓለም ቱጃሮችን ታሪክን ብንመለከት ከነገስታቱ ብዙም የተለየ አይደለም ፡፡ የአለም ህተ ሀብታሞችም እንደ ነገስታቱ በቀላሉ የሚረሱ ሲሆን በጣም ደግና ለጋስ ካልሆኑ በስተቀርማ ስማቸውን ማንም አያነሳውም ፡፡ ለምሳሌ አሜሪካዊው ቱጃር ሮክፌለርን ብንወስድ ተወዳዳሪዎቹን ከገበያ በማስወጣት የሚታወቀው ይሄው የንግድ ሰው ተፎካካሪዎቹን አግባብ ባልሆነ መንገድ ከገበያ በማሰወጣት ሲታወቅ እርሱ በመሀል ኒውዮርክ ያሰራው የኢምፓየር ስቴት ህንፃ አሁንም ድረስ በኒውዮርክ ከተማ ሲገኝ ለስሙ መታሰቢያ ቢሆነውም እና የአሁኖቹን የአሜሪካንን የነዳጅ ኩባንያዎች መሰረት ጥሏል ቢባልም ሌላ እምብዛም የሚታወስበት ነገር የለም፡፡
ከዚህ እምንረዳው በታሪክ ለሰው ልጅ አንድ እርምጃ አስተዋፅኦን ያበረከቱ ሰዎች የበለጠ ዋጋ እንደሚሰጣቸው ሲሆን ፣ ምንም እንኳን ብዙዎቹ በዘመናቸው የማይወደዱና ተሰሚነት ያልነበራቸው ፣ ወይም የተረሱና የተገለሉ የነበሩ ሊሆኑ ቢችሉም ካለፉ በኋላ ግን የስራቸውን ጥቅም በማየት በመጪዎቹ ትውልዶች የሚከበሩና ዋጋ የሚሰጣቸው ይሆናሉ ፡፡ ከምእራቡ ዓለም አዳዲስ ቴክኖሎጂን በመፍጠር እንደ ቶማስ ኤዲሰን ፣ስቲቭ ጆብስ ፣ ቢል ጌትስን የመሳሰሉት ሰዎች በታሪክ ስፍራ የሚሰጣው ናቸው ፡፡ 
ይህ በአፍሪካ የባሰ ሲሆን አፍሪካ ውስጥ ከእውቀት ሰው ይልቅ አሁን በስልጣን ወይም በሀብት ማማ ላይ ያሉ ሰዎች የበለጠ ዋጋና አክብሮት የሚሰጣቸው ሲሆን ለጥበበኞችና ፣ ለደራሲዎች ፣ ለሰአሊዎችና ለመሳሰሉ አሁን በህይወት እያሉ የሚሰጠው ክብር እጅግ ዝቅ ያለ ነው ምናልባት ካለፉ ከጊዜ በኋላ ሊሆን ይችላል የተሻለ ክብርንና መታወስን ሊያገኙ የሚችሉት ፡፡

የቅጂና ተዛማጅ መብት



አንዳንደ አገራት እንደ ጃፓን ያሉ አገራት የፓተንት ህግ ያላቸው ሲሆን አንድ ሰራተኛ በሚሰራበት ኩባንያ ውስጥ አዲስ ነገርን ፈልስፎ ቢገኝ ቀድሞ ኩባንያዎች በጣም ትንሽ ገንዘብን ይከፍሉና ምርቱን ግን በመቸብቸብ እጅግ ትርፋማ ይሆኑ የነበረ ሲሆን በአንፃሩ ግን ፈጠራውን ላመነጨው ሰው ግን ምንም ሳይከፍሉ እነሱ የፈጠራው ባለቤት ይሆኑ ነበረ ፡፡ ነገር ግን ጃፓናውያን ይህን በመመልከት ሰራተኛው ለሚፈጥረው ፈጠራ ግን ከድርጅቱ ትርፍ መካፈል እንደሚችልና ወቅታዊ የሆነ ለክፍያን እንደሚያገኝ ደንግገዋል ፡፡
ይህን ህግ በማሻሻል ይበልጥ ሰራተኛው ቋሚ ተከፋይና ባለቤት እንደሆነ ደንግገዋል በዚህም የሰራተኞችን የፈጠራ በማበራታታት ላይ ይገኛሉ  ፡፡ ነገር ግን የዚህ ችግሩ አንድምታ ለምሳሌ 500 ፓተንቶችን ሊጠመቀም ይችላል ስለዚህ እነኚህን ሁሉ ፓተንቶች ባለቤቶችን መክፈልና ምን ያህል ሊደርሳቸው ይባል ገባል የሚለከውን ኮሚቴዎችን በማቋቋም ይወስናሉ ፡፡ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የኤክትሮኒክስ ምርቶች እስከ አስር ሺህ ፓተንቶችን ሲጠቀሙ ለእነኛ ሁሉ ማከፋፈሉና ክፍያውን መወሰኑ ይበልጥ ፈታኝ ስሆነባቸው ማበረታቻ ወይንም እንደ ቦነስ ያለ ክፍያን ለመክፈል በማሰብ ላይ ናቸው ፡፡
የፓተንትና የቅጂና ተዛማጅ መብቶች (Patent & Copyright) በአለም ላይ ውስብስብ ለአሰራር አስቸጋሪ ከሆኑ ህጎች አንዱና ዋነኛው ነው ፡፡