Monday, March 11, 2013

የተፈጥሮ ገፀ - በረከትና የልማት ፈተና



አንዱ የተፈጥሮ በረከት የባህር በር ወይም ወደብ መኖር ነው ነገር ግን የባህር በር ሳይኖሯቸው እጅግ ሀብታም የሆኑ ሀገራት አሉ ለምሳሌ ከአውሮፓ ስዊዘርላንድንና ኦስትርያን ብንወስድ የባህር በር ባይኖራቸውም በአለም ላይ ካሉ እጅግ ሀብታም ሀገራት የሚመደቡ ሲሆን፣ የህዝባቸው የኑሮ ደረጃም በአለም ላይ ካሉት በግንባር ቀደምትነት እሚጠቀስ ነው በጣም ትናንሽ የሆኑትን የአውሮፓ ሀገራትን ላግዘምበርግን ብንወስድ እንደዛው የባህር በር የሌላትና በጣም ትንሽ ሀገር ብትሆንም ሀብታምና ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ያላት ስትሆን ፣ከራሷ አልፋም ለአሜሪካ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ብድር ማበደር የቻለች ሀገር ነች

አጠቃላይ ምጣኔ - ሀብቱ እያደገ ሲሄድ በአንፃራዊነት ለወደብ ኪራይ የሚከፈለው ገንዘብ እየቀሰነ እንደሚሄድ ወይም የሚከፈለው ገንዘብ ከአጠቃላይ ምጣኔ - ሀብቱ አቅም አንፃር ድርሻው እያነሰ ይሄዳል ይህ ብቻ ሳይሆን ለአለም የንግድ መስመር ማለትም ለቀይ ባህርና ለመካከለኛው ምስራቅ ቅርብ በመሆኗ ወደብም በጣም የራቀች ስላልሆነች ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች የደረቅ ወደቦችን በማስፋፋት ሸቀጦች ወደብ ላይ የሚኖራቸውን ቆይታ በመቀሰን ለኪራይ የሚከፈለውን ገንዘብ ለመቀነስ ያስችላል

 
ስዊዘርላንድ በአለም ላይ አሉ ከሚባሉ የዲፕሎማቲክ ማእከል ከመሆኗም በተጨማሪ የበርካታ ኤግዚቢሽኖች የመኪኖች ትርኢትን ጨምሮ ስብሰባዎች የሚካሄድባት እንዲሁም በአውሮፓ ካሉ ዋና የቱሪስት መናሪያም ጭምር ነች


በአለም ላይ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው ከተሞች በርካቶቹ የወደብ ከተሞች መሆናቸው ይታወቃል ለምሳሌ ኒውዮርክ፣ ሆንግ ኮንግ ሻንግሀይ የመሳሰሉት ነገር ግን ሁሉም ደግሞ የወደብ ከተሞችም አይደሉም ለምሳሌ የጀርመን ብሎም የአውሮፓ የገንዘብ ዘርፍ ማእከል የሆነችውን ፍራንክፈርትን ብንወስድ የወደብ ከተማ አይደለችም ከዚህም በላይ በአለም ላይ ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ አላቸው በሚል በተደጋጋሚ የሚጠቀሱት የኦስትሪያዋ ቪየናና የስዊዘርላንዷ ዙሪክ ከፍተኛ ለኑሮ አመቺ ናቸው በሚል የሚጠቀሱ ሲሆን እነኚህም የወደብ ከተሞች አይደሉም


የወደብ ጉዳይ አንዱ የአንድን ሀገር ምጣኔ - ሀብት ለመረዳት ጠቃሚ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ ነው ወደብ አለመኖርም ብቻ ሳይሆን ሀገራቱ ቅርባቸው ከሆነው ወደብ ያላቸው ርቀት የባለወደብ የሆኑት ጎረቤቶቻቸው የሆኑት ሀገራት የመሰረተ ልማት አገልግሎት፣ መንገዶች መኖር ሲሆን ወደብ የሌላቸው በየብስ የተከበቡ (Land Locked) ሀገራት ለምጣኔ ሀብታቸው አወቃቀር ለራሳቸው ይበልጥ ተስማሚ ከመሆን ይልቅ ለጎረቤት ሀገራት በሚስማማ መልኩ የመቀረፅ እድሉም ሰፊ ነው ይህም ያቺ ሀገር ለራሷ የሚያዋጣትን ነገር ከማምረት ይልቅ ለጎረቤት ሀገሮች ይበልጥ አዋጪ በሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ እንድትገባም ያደርጋታል ለምሳሌ ከወደብ በጣም ሩቅ የሆነች ሀገር ካዛኪስታን ስትሆን 3000 . . ሜትሮች በላይ ትርቃለች


በተለይም ሀገራቱ ሰፋ ያለ መሬትና የራሳቸው የተፈጥሮ ሀብት የሌላቸው ከሆኑም ችግራቸው የባሰ ነው የሚሆነው የቆዳ ስፋታቸው በጣም ጠባብ የሆኑ ሀገራትም ቢሆኑ እንዲሁ ወደብ ከሌላቸው ነገር ግን ሰፋ ያለ መሬት ካላቸው ሀገራት የባሰ የሀብት ውሱንነት ሊያጋጥማቸው ይችላል በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የሚገኙ ትናንሽ ደሴቶችም ለኑሯቸው ግብር የሌለባቸው ወይም የማይከፈልባቸው የፋይናንስ ዘርፎችን በመስጠትና በቱሪዝም ላይ የተመሰረተ ነው ምጣኔ - ሀብታቸው   
ወደ አፍሪካም ስንመጣ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የባህር በር ስለሌላቸው ብቻ ደሀ ሆነው እንደማይቀሩ መገመት አያዳግትም በአጠቃላይ ግን የልማት መሰረቱ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ ሆኖ እናገኘዋለን


ቦትስዋናን ብንወስድ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ወዲህ በመልካም ሁኔታ እየተዳደረችና እያደገች የሄደች ሀገር ስትሆን፣እንደሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራትመፈንቅለ መንግስታትን የእርስ በእርስ ጦርነቶችን ያስተናገደች ሀገር አይደለችም ዋና ገቢዋ በአልማዝ በቱሪዝምና በስጋ ላይ የተመሰረተውይህቺው ሀገርትክክለኛ የእድገት መስመርን የተከተለች ነች ይህም ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያጋጠማቸው የእርስ በእርስ ጦርነትና መፈንቅለ መንግስታት ስላላጋጠማት እና በሰላማዊ የስልጣን ሽግግርና በዲሞክራሲ ጎዳና በመጓዟ በተሻለ የእድገት ደረጃ ላይ ትገኛለች ዙምባብዌንም ብንስድ እርሷም ወደብ የሌላት ሲሆን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ በወጣችበት ወቅት በግብርና በማምረት ጥሩ ደረጃ ላይ ከነበሩ ጥቂት የአፍሪካ ሀገራት የምትመደብ ሀገር ነበረች በእርግጥ በኋላ ላይ በሙጋቤ አመራር ኢኮኖሚዋ እያሽቆቆለና በአለም ከፍተኛውን የስራ አጥ ቁጥርና ከፍተኛ የተባለ የዋጋ ንረት የተመዘገበባት ሀገር ለመሆን ብትበቃም


ኡጋንዳን ብንወስድ ከወደብ ራቅ ያለች ሀገር ነች በዚህች ሀገር አንድ እቃ ከወደብ ተነስቶው እስከሚደርስ ድረስ 53 ቀናት ይፈጃል ሀገራችን ምንም እንኳን ወደብ ባይኖራትም እንደ እድል ሆኖ ግን ከወደብ ግን የራቀች ሀገር ግን አይደለችም ይህ ብቻ ሳይሆን ባለወደብ የሆኑትም ጎረቤቶቿ ምጣኔ ሀብታቸው ያነሱ ሀገራት ስለሆኑ ኢትዮጲያ በእነሱ ላይ ጥገኛ ከሚሆኑ ይልቅ እነሱ ይበልጥ በኢኮኖሚ ጥገኛ ይሆናሉ በተጨማሪም በአለም ከፍተኛው የንግድ ዝውውር ከሚካሄድበት ከቀይ ባህር የንግድ መስመርና ከዋናው ከነዳጅ ዘይት ምንጭ ማለትም ከመካከለኛው ምስራቅ የራቀች ባለመሆኗእንደ አንድ የተሻለ እድል ተደርጎ ሊቆጠርላት ይችላል


በእርግጥ የወደብ መኖር ለንግድ እንቅስቃሴ አስፈላጊ መሆኑ አሌ አይባልም ወደብ ያላቸው ሀገራት ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ዘርፍ በመሆኑ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ሲሆን ለወደብ ኪራይ ይከፍሉት የነበረውን ገንዘብ ከማሳዳናቸውም በላይ ለጎረቤቶቻቸውም የወደብ አገልግሎትን በመስጠት ከፍተኛ የገቢ ምንጫቸው ሊሆን ይችላል ያደጉትን ሀገራት ራሱ ብንወስድ በየእለቱ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙበት ዘርፍ ይኀው ከወደቦቻቸው የሚያገኙት ገቢ ዘርፍ ነው ቢያንስ አሁን ያለው ትውል እንኳን በትክክል ባይጠቀምበት እንኳን መጪው ትውልድ በአግባቡ ሊጠቀምበር ስለሚችል የወደብ ባለቤት የሆኑ ሀገራት ሰፊ የምጣኔ - ሀብትና የስታራቴጂ ጥቅም እንደሚኖራቸው መገመት አያዳግትም


የባህር ባህርን እና ክፍት የመርከቦች መተላለፊያን ለማግኘት በአለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን ለንግድ እንቅስቃሴ ቁልፍ ከሆኑ ስልታዊ መሰረተ - ልማት አውታሮች አንዱ ነው። ይህንን በመረዳት እንግሊዞችና ፈረንሳዮች የስዊዝ ካናልን በማስቆፈር ቀይ ባህርን ሜዲተራኒያን ባህርን ሲያገናኙ በአለም  ላይ በጣም ስራ የሚበዛበትንና ቁልፍ የሆነ የንግድ መስመርን መፍጠር ችለዋል እንዲሁም አሜሪካኖች  የፓናማ ቦይን በመቆፈር እንዱሁ ደቡባዊ አሜሪካንና ሰሜናዊ አሜሪካን አጭር በሆነ የመርከብ መስመር ለማገናኘት ችለዋል የሚጠይቀው መዋእለ ንዋይ ከፍተኛነት ካላገደ በስተቀር በአፍሪካ ቀንድም በዚህ አይነት መንገድ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮችን በቦይ በመቆፈር የወደብ ችግርን ማቃለል ይቻላል


ነገር ግን አፍሪካ ውስጥ እንደሌላው ዘርፍ ሁሉ የወደብ አገልግሎቱም በሚገባ ያላደገና ባለወደብ የሆኑ ሀገራትም ያላቸውን እምቅ አቅም በአግባቡ እየተጠቀሙበት አይደለም ማለት ይቻላል ለምሳሌ የኬንያው ሞምባሳ ወደብ ለማስተናገድ አንድ አመት የሚፈጅበትን የሲንጋፖር ወደብ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ማንቀሳቀስ ይችላል ይህም በአፍሪካ ዘርፉ ገና እንዳላደገና ገና ብዙ ማደግ እንዳለበት ያመለክታል  


እ.ኤአ.አ በ 2013 ዓ.ም. አፍሪካ በአለም ንግድ ላይ ያላት የንግድ ድርሻ 3 በመቶ የማይበልጥ ሲሆን ኢንትራ አፍሪካ የሚባለውም ንግድ ማለትም በአፍሪካ ሀገራት መሀከል ያለውን ንግድ 12 በመቶ አይበልጥም ይህ ብቻ ሳይሆ የንግድ ግብይት ዋጋው (Transaction Cost) በጣም ከፍተኛ ሲሆን ሌላው ደግሞ የአፍሪካ በአንድ ሸቀጥ (Mono commodity) ማለትም አንድ ወይንም ጥቂት ሸቀጦችን ብቻ ለአለም ገበያ የምታቀርብ ስለሆነ ነው 60 በመቶ የአፍሪካ ህዝብ በግብርና ነው የሚተዳደረው ለምሳሌ ቡና በኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ድርሻው 20 አመታት በፊት 68 ፐርሰንት ድርሻ የነበረው ሲሆን አሁን ግን በሌሎች እንደ አበባ ቆዳና ሌጦ ሰሊጥ በመሳሰሉ የወጪ ንግዶች ድርሻው በአንፃራዊነት እየቀነሰ መጥቷል ክልላዊ የምጣኔ - ሀብት ማህበረሰቦችን በማጠናከር ለዚህም መሰረተ ልማት አውታሮችን በመዘርጋት ጋር ማጠናከርና የሰው ሀይሉን ማሳደግ ትምህርትና ጤና የመሳሰሰሉ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ማጠናከር አስፈላጊ ሆነው ተገኝተዋል


ሌላው ደግሞ እንደ (UNDP) በ 2012 ዓ.ም. ባወጣው መረጃ መሰረት ፈጣኑ የአፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ረሀብን በማጥፋት በኩል የፈደው ነገር የለም ነገር ግን አፍሪካ ረሀብን ለማጥፋት አቅም አላት ነገር ግን የጠፋው የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው 2012 ግንቦት ወር ባወጣው ዘገባ ፈጣን የምጣኔ - ሀብት እድገት ረሀብን ማጥፋት አለበት ረሀብን ካላጠፋ የራሱን የእድገቱን ቀጣይነት እንዲሁም እየጨመረ ካለው የህዝብ ብዛት አንፃር ፖለቲካዊ መረጋጋቱን  ጥያቄ ውስጥ ሊከት ይችላል - እድገቱ ራሱ ድህነቱ በጥቂቱ ነው የቀነሰው 51 በመቶ ወደ 48 በመቶ ዝቅ ሲል ከአፍሪካ ህዝብ ውስጥ ስር ከሰደደው ድህነት አንፃር የድህነቱ ቅናሽ ብዙም የሚባል አይደለም ሲል ገልፀል የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም ድርጅት


ሌላዋ ደግሞ ሞሪሸስ ስትሆን በጨርቃ ጨርቅና በሌሎች ኢንዱስትሪዎቿ አማካይነት በእድገት ጎዳና ላይ የምትገኝ ሀገር ነች አንድ ሀገር የቆዳ ስፋት ካለው ለምሳሌ በአትላንቲክና ፓስፊክ ውቅያኖስ የሚገኙ ሀገራት ትናንሽ ደሴቶች የአውሮፓውያን ግዛት የሆኑት ከአውሮፓውያን በሚገኙት ገንዘብና የወታደራዊ መቀመጫ በመሆን ሲሆን ከዋና ዋና አህጉሮችም የራቁ በመሆናቸው አመቺ የሆነ  የምጣኔ - ሀብት እንቅስቃሴ ሊኖራቸው አልቻለም የመሬት ሰፋታቸውንም በያጣም ጠባብ በመሆኑና ከዋና ዋና አህጉራትም የራቁ ስለሆኑ ንግድን ለማካሄድ አይችሉም ስለዚህ ያላቸው አማራጭ ከዋናዎቹ የአውሮፓ ሀገራት በሚያገኙት ድጎማና እርዳታ መኖር ነው


ሌላው ደግሞ የሀገራት የራሳቸው የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የራሱ የሆነ ጥቅምም ሆነ ጉዳት አለው ለምሳሌ ሜክሲኮን ብንወስድ የሀብታሟ አሜሪካ ጎረቤት በመሆኗ ካናዳም እንዲሁ የቅርብ የሰሜን አሜሪካ አገር ስለሆነች ከእነኚህ ሀገራት ጋር በተዋዋለቻቸው የንግድ ውሎችና ስምምነቶች (NAFTA)ን ጨምሮ ነፃ የሆነ የኢንዱስትሪ ቀጠናን ለመገንባት ሲያስችላት የአሜሪካና የካናዳ ኩባንያዎች ያለውን የርካሽ ጉልበት የመሳሰለውን በመጠቀም ሜክሲኮ ውስጥ በርካታ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ አድርጓል በአንፃሩ ለሀብታሟ አሜሪካ ሜክሲኮ የወንጀል መፈልፈያ በሆነች ቁጥር የችግሩ ገፈት ቀማሽ ለመሆን ትገደዳለች ከእስያ አህጉርም እንዲሁ ደቡብ ኮርያ ታይዋንና ታይላንድ ብሎም ቻይና ከጃፓን የኢንቨስትመንትና የቴክኖሎጂ ድጋፍን ለማግኘት ሲያስችላቸው ውሎ አድሮም እነኚሁ ሀገራት ለጃፓን ምርቶች ትልቅ ገበያም ጭምር ሆነዋል አውሮፓንም ብንወስድ የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት የአውሮፓ ህብረት አባል በመሆን በብዙ መልኩ ከበለፀገው የአውሮፓውያን የጋራ ገበያ አባልነታቸው ተጠቃሚ አድርጓቸዋል



ሌላው ደግሞ ሀገራት ሰፊ የሆነ የቆዳ ስፋት ከሌላቸው አነስተኛ ደሴቶችም ከሆኑ ራሳቸውን ወደብ ካለመኖር የባሰ ሁኔታ ውስጥ ሊያገኙተር ይችላሉ ለምሳሌ ጃፓንን ብንወስድ የቆዳ ስፋቷ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ያለችበት የውቅያኖስ አካባቢም ለመሬት መንቀጥቀጥና ለሱናሚ ባለው ተደጋጋሚ ተጋላጭነት በአለም አደገኛ የሚባል ነው ይሁንና ጃፓና የፈጠራ ብቃቷን በመጠቀም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ባሉት ሰባና ሰማንያ አመታት ድረስ ደረጃዋ በቻይና ከመወሰዱ በፊት ከአሜሪካን ቀጥሎ በአለም በጣም ግዙፍ የሆነ ምጣኔ - ሀብትን መገንባት የቻለች ሀገር ነች እንግሊዝንም ብንወስድ ሰፊ የሆነ የቆዳ ስፋት የሌላት ሲሆን በባንክና በገንዘብ ዘርፍ በምታገኘው አብዛኛውን የግብር ገቢዋን እንደምታገኝ ይታወቃል እስከ 11 በመቶ የሚሆነውን ማእከላዊ መንግስት ከሚሰበስበው ውስጥ ከዚሁ ከፋይናንስና ከባንኩ ዘርፍ የሚመነጭ ሲሆን አንዱም የአውሮፓ ህብረት አባል አገር ያልሆነችበትምክንያት ይኀው በገንዘብ ፖሊሲዋ ላይ ያላትን ቁጥጥር ላለማጣት ነው


በበጎም ብቻ ሳይሆን በመጥፎም ቢሆን አንዳንድ ሀገራት መጥፎ እድል ያላቸው አሉ ለምሳሌ አሜሪካን በከባድ አውሎ ንፋስ «ሁሪኬን» እና በከባድ ወጀብ «ታይፎን» እንደምትጠቃ ይታወቃል አንዳንድ ሀገሮች ለተፈጥሮ አደጋ የተጋለጡ ናቸው ለምሳሌ ጃፓን በመሬት መንቀጥቀጥና በሱናሚ አደጋ በተደጋጋሚ የምትመታ ሲሆን እንደ ታይላንድ ያሉት ደግሞ ለአደገኛ ጎርፍ የተጋለጡ በናቸው ቻይናና፣ ቱርክና ኢራንም ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ ሲሆኑ የአፍሪካ ቀንድም ለድርቅና ለረሀብ አደጋ የተጋለጠ ነው  

በአንፃሩ አፍሪካን ብንወስድ ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት በስተቀር የዚህ አይነት ጂኢግራፊያዊ ትስስር ብዙም ተጠቃሚ አይደለችም ከሰሜን አፍሪካ ሀገራት እንደ ግብፅ ሊቢያ ቱኒዝያ ያሉት ለአውሮፓ ቅርብ በመሆናቸው ለቱሪዝም ሰፊ እድል አላቸው የአውሮፓ ህብረትም ከቱርክ በመቀጠል በረጅም ጊዜ ወደ አውሮፓ ህብረት አባልነት ሊገቡ ይችላሉ ብሎ ተስፋ የሚያደርጋቸው ሲሆኑ ለምሳሌም ከአረብ አመፅ በኋላ ለግብፅና ቱኒዚያ የአውሮፓ ህብረት በአስርት ቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ለማበደር ቃል ገብቷል

አውሮፓውያን ቱሪስቶች የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ሰፊ የሆኑ የባህር ዳርቻዎችን ስለሚመርጡ ግብፅን ብንወስድ ካላት ጥንታዊ ከሆኑ ብዙ ቅርሶች በተጨማሪ አቀማመጧ ለአውሮፓ ቅርብ ነው ሊቢያንም ብንወስድ ካላት ግዙፍ ከሆነ የነዳጅ ሀብት በተጨማሪ ያላት አቀማመጥ ሰፊ የቱሪዝም አቅም ያላት ስትሆን ካላት ረጅም ከሆነ የሜዲተራኒያን ባህር ዳርቻ ጠረፍ ለአውሮፓ በተለይም ጣሊያን ቅርብ በመሆኗ ለቱሪዝም ራሱ ያላት አቅም ከፍተኛ ነው  

ምስራቅ አፍሪካ ለምሳሌ ለመካከለኛው ምስራቅ ቅርብ ቢሆንም ክልሉ በራሱ ውስጣዊ መረጋጋት ስለሌለው ከእነኚህ የአረብ ሀገራትን ገበያ በደንብ ለመጠቀም እስካሁን አልታደለም ነገር ግን ካለው ጂኢግራፊያዊ ቅርበት አንፃር ግን ወደፊት ትልቅ እድል እንደሚኖረው መገመት ይቻላል ይሁን እንጂአንዳንድ ሰዎች ምስራቅ አግተ ፍሮካሪካ የተፈጥሮ ሀብት የለውም ቢሉም ክልሉ ከፍተኛ የተፈጥሮ ሀብት ያለው ነው ለምሳሌ የኢትዮጲያን ደጋማ ቦታዎችን ብንወስድ በበርካታ ወንዞች የተንጣለለ ሲሆን መሬቱም ለግብርናና ለከብረት እርባታ አመቺ ነው ይህ ብቻ ሳይሆን ክልሉ በውስጡ አምቆ ያዘው ሀብት ለመፈለግ ለመቆፍሮ ለማውጣት ሀገራቱ ለብዙ አመታት በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ  ተጠምደው ማሳለፋቸው ዋነኛው ምክንያት ነው ክልሉ ቢያንስ ቢያንስ ከሌላው የአለም ሀገራት ያላነሰ የማእድናት ሀብት ሊኖረው እንደሚችል መገመት ይቻላል ይህ ብቻ ሳይሆን ሶማሊያን ብነወንሰወስ በጣም ረጅም የሆነ የባህር ክልል ሲኖራት ከኬንያ እጥፍ የሚሆን የቆዳ ስፋትም ባለቤት ነች ክልሉ በአጠቃላይ በአለም ላይ ካሉ ሀብታም ከሚባሉ ገበያዎች ማለትም ለመካከለኛው ምስራቅ በባህርም በአየርም ቅርበት አለው

 
ሌላው ደግሞ ለአገራት ድህነት የሚጠቀሰው ነገር የካፒታል ያቺን ሀገር ጥሎ መውጣት (Capital Flight) አንዱ ሲሆን በአፍረካ ሀገራትም በተለይም ነዳጅ ላኪ የሆኑእንደ ናይጄሪያ ያሉት ሀገራት ገንዘባቸው በከፍተኛ ደረጃ ወደ ውጪ ሀገር እንደሚወጣ ይገመታል ከኢትዮጲያ በየአመቱ ወደ ውጪ የሚወጣው ካፒታል ፍላይት በአመት 2 ቢሊየን ዶላር ነው ተብሎ ይገመታል ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር በእርግጥ ይሄን ያህል መጠን ብዙ ነው ላይባል ይችላል ይሁን እንጂ በቅርቡ የወጣ ግሎባል ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲ የተሰኘ ተቋም ባወጣው አንድ ሪፖርት እንደጠቆመው 2009 . . 3.5 ቢሊየን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ከኢትዮጲያ እንደወጣ ሲገመት ከፍተኛ የገንዘብ አገሩንጥሎ መውጣት እያጋጠማቸው ካሉ አስር አገራት አንዷ ኢትዮጲያ መሆኗ ተረጋግጧል ይህም ገንዘብ አገሪቱ 2011 . በወጪ ንግድ ካገኘችው ገንዘብ እኩል ሲሆን በእርዳታና በብድር ካገኘችውም ይበልጣል ስለዚህ ብዙ ካፒታልና ገቢ የሌላት አገር ሆና ይህን ያህል ገንዘብ መውጣቱ በአገሪቱ ምጣኔ - ሀብት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መገመት አያዳግትም ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 70 እስከ 75 በመቶ የሚሆነው ገንዘብ ወደ ውጪ የሚወጣው በወጪና በገቢ ንግድ ደረሰኞችን ወጪ ዝቅና ከፍ በማድረግ (Under & Over invoicing) ነው ምንም እንኳን ይህ ተግባር ወንጀል ቢሆንም ይህንን አሰራር የሚታገል የገንዘብ ዝውውርና ከሌሎች ሀገራት በጋራ የተቀናጀ የታክስ መረጃ ልውውጥ መዘርጋት አለበት

የተፈጥሮ ሀብት አለመኖርም ብንወስድ ለምሳሌ ጃፓንን ብንወስድ ምንም አይነት የተፈጥሮ ሀብት የሌላት ሀገር ስትሆን ነገር ግን ከጃፓን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በቻይና ከመቀደሟ በፊት ከአለም ሀገራት አሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ግዙፍ ምጣኔ - ሀብትን መገንባት የቻለች ሀገር ነች ።ከእስያ በርማ (ማይናማር) እና ካምቦዲያ በተፈጥሮ ደሀ አገራት አይደሉም በተለይም ማይናማር በአለም በተፈጥሮ ሀብትም ሆነ አቀማመጥ እጅግ ከታደሉ ሀገራት አንዷ ነች

ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን  «ዲ አር ሲን» ብንወስድ በአፍሪካ በጣም ሰፊ የቆዳ ስፋት አላቸው ከሚባሉ ሀገራት አንዷ ስትሆን በከርሰ - ምድሯ ብቻ 24 ትሪሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ የተገመተ  ሀብትን የያዘች ሀገር ነች ነገር ግን ከአለም ካሉ ሀገራት እጅግ ደሀ ከሚባሉት የምትመደብ ነች ህዝብ ብዛቱ ስለበዛም አንድ ሀገር ደሀ ይሆናል ማለት አይደለም ለምሳሌ ህንድን ብንወሰድ ግዙፍ ህዝብ ቢኖራትም ቀድሞ የነበራትን ድህነት በማሸነፍ ግዙፍ ምጣኔ - ሀብትን እየገነባች ያለች ሀገር ነች ቻይናም እንዲሁ

ስዊዘርላንድና ጃፓን የበለፀጉ ሀገራት ስለሆኑ አር (DRC) ደግሞ ታዳጊ ሀገር ስለሆነች ሊባል ይችላል ይህም ማለት የበለፀጉት ሀገራት እንዴት አደጉ ታዳጊ ሀገሮች ደግሞ እንዴት ደሀ ሆነው ቀሩ ወደሚል መሰረታዊና ሰፊ ወደ ሆነ ጥያቄ ያመራናል ታዳጊ አገራት የተፈጥሮ ሀብት እያላት እንዴት ደሀ ሆነው ቀሩ ያደጉት ደግሞ ብዙ የተፈጥሮ ሀብት ሳይኖራቸው እንዴት ሊበለፅጉና ሊያድጉ ቻሉ ወደሚል ሰፋ ወዳለው ጥያቄ ያመራል

ነገር ግን አንድ ሀገር ብዙ የተፈጥሮ ሀብት፣ የባህር በር ከሌላት ዜጎቿ ብዙ ማሰብና ፣እእምሯቸውን ማስጨነቅና ጠንክረው መስራት አለባቸው ።ለምሳሌ በነዳጅ ዘይት የከበሩ ሀገራት ዜጎች እቃዎችን በመሸመት በመዝናናት ጊዜያቸውን ሊያሳልፉ ይችላሉ በአለም ዙሪያ ትናንሽ የሆኑ ምንም የተፈጥሮ ሀብት የሌላቸው በየብስ የተከበቡነገር ግን የተሳካ የኢኮኖሚ እድገት ደረጃ ላይ የደረሱ ሀገራት አሉ ለምሳሌ እንግሊዝን ስዊዘርላንድንና ጃፓንን ብንወስድ ይህ ነው እሚባል ሰፊ መሬት የሌላቸው ሲሆን እንግሊዝን ብንወስድ በባንክ፣ እንዲሁም በሌሎች አገልግሎት ዘርፎች ላይ የተመሰረተ ነው ሌላው ቀርቶ ስፖርትን እንኳን ወደ ትልቅ ገቢ ማስገኛነት መቀየር የቻለች ሀገር ነች ፤በእግር ኳስን  በቴኒስ፣ በክሪኬት በሌሎችም የስፖርት ውድድሮች አይነቶች ሁሉ ገቢን የሚያስገኙላቸው ናቸው። በቂ መሬት ስለሌላት የምግብ ሰብሏን እስከ 60 በመቶ ከውጪ ነው እምታስገባው

አንድ ሀገር በራሱ ሀብት ነው እንጂ በሌላ ሀገር ሀብት ዘላቂ የሆነ እድገት ሊኖረው አይችልም ያን ሀብቱን ሳይጠቀምበት በሚቀርበት ወቅት ግን ደሀና ችግረኛ ሊሆን ይችላል በቅኝ ግዛት ዘመን አውሮፓውያን በአለም ዙሪያ ሰፊ ቅኝ ግዛት ስለነበራቸው አሁን እንደምንሰማው አይነት የምጣኔ - ሀብት ችግር አልነበረባቸውም ይሁን እንጂ ቀስ በቀስ የነበራቸውን ቅኝ ግዛቶች እያጡ ሲመጡ ግን ከተወሰኑ አስርት አመታት በኋላ ግን ቀድሞ እነሱ ቅኝ ይገዟቸው የነበሩት ሀገራት ከእነሱ የበለጠ አመታዊ አጠቃላይ ምርት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ለምሳሌ የህንድ አጠቃላይ አመታዊ ምርት (GDP) ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ከእንግሊዝ የሚገዝፍ ሲሆን ይህን ተከትሎም እንግሊዝ ለህንድ ትሰጥ የነበረውን  እርዳታ ማቆሟን አስታውቃለች የቻይናም ምጣኔ - ሀብት አመታዊ ምርት ከጃፓንም ሆነ ከሌሎች ምእራባውያን  የበለጠ ሆኗል የብራዚልም አጠቃላይ አመታዊ አገራዊ ምርት ከቀድሞ ቅኝ ገዢዋ ፖርቱጋልም ሆነ ከጎረቤቷ ስፔን በእጅጉ የላቀ ከሆነ በርካታ አመታት አልፈዋል
 
አንዳንድ ፖለቲከኞች የችግሩን ምንጭ ውጫዊ ምክንያት አድርገው ሊያቀርቡት ይችላሉ ወደ ለምሳሌ ቻይናን ብንወስድ ያቺ ሀገር ያደገችው በሌላ በማንኛውም ሀገር ኪሳራ አይደለም በአሁኑ ወቅትም አንዳንድ የአሜሪካ ፖለቲከኞች በአሜሪካን አገር ለተፈጠረው ስራ አጥነት ቻይናን ተጠያቂ ለማድረግ የሞከሩ ሲኖሩ ፣የገንዘብ ምንዛሬዋን ዝቅ በማድረግ ነው በርካሽ ምርቶቿን እምታራግፈው (Damp) እሚያደርጉት በማሰለት ይከሳሉ ይሁን እንጂ የአንድን ሀገር የገንዘብ ምንዛሪ መጠን የሚወስነው ራሱ ሉአላዊው ሀገር ነው እንጂ በውጪ የጣልቃ ገብነት ምንዛሪውን እንዲህ ወይም እንዲያ አድርግ መባል እንደሌለበትም የሚታወቅ ነው ይሁን እንጂ የአንድን ሀገር የገንዘብ ምንዛሪ መጠን የሚወስነው ያው ሉአላዊ ሀገር ነው እንጂ በውጪ የጣልቃ ገብነት ምንዛሪውን እንዲህ ወይም እንዲያ አድርግ መባል የለበትም ሚል ክርክርም አለ

ይህ ብቻ ሳይሆን በወጪ ንግድ አንድ ሀገር አደገ ማለት በሌሎች ምርቱን በሚገዙት ሀገራት ምጣኔ - ሀብት እንቅስቃሴ ላይ ይመሰረታል ለምሳሌም 1 በመቶ የአውሮፓውያን ኢኮኖሚ ቢቀንስ የሆንግ ኮንግ ምጣኔ ሀብት 1.5 በመቶ ይቀንሳል ይላል አይ ኤም ኤፍ የራሳቸውን የውስጥ ምጣኔ - ሀብት እንቅስቃሴን ፈጥረው የሀገር ውስጥ ገበያን መፍጠር ካልቻሉ በውጪ ገበያ ብቻ ተመስርቶ መቀጠልም አዳጋች እየሆነ ይሄዳል በተለይም እንደ ቻይና ያሉ ግዙፍ የማምረት አቅም ያላቸው ሀገራት ይህንን እውነታም ቻይናውያንም እየተረዱት መጥተዋል ለበርካታ አስርት አመታት በወጪ ንግድ ላይ ተመስርቶ የቆየው የቻይና ምጣኔ - ሀብት አውሮፓና አሜሪካ ችግር ውስጥ በገቡ ቁጥር የወጪ ንግዷ እየተጎዳና የምጣኔ - ሀብት እድገቷ እየቀዘቀዘ መምጣቱን በማየት የውስጥ ፍላጎቷን ማሳደግ አማራጭ እንደሌለው ተረድታለች


ምንም እንኳን የእስያ ሀገራት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ቢኖራቸውም በቴክኖሎጂ በእውቀትና በፈጠራና በእድገት በኩል ግን አሁንም ቢሆን በምእራባውያን ላይ ጥገኛ ሆነው መቀጠላቸው አይቀሬ ነው በዚህ በኩል ምእራባውያን ሰፊ ተሞክሮና አቅም ያላቸው ስለሆነ ነው

 
ኢትዮጲያንም ብንወስድ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ወንዞቿን ማእድናቶቿን መሬቷን በስፋት እየተጠቀመች ስትሄድ ምጣኔ - ሀብቷም እንደዛው እያደገ ይሄዳል እነኚህ ሀብቶች ግን ለብዙ ሺዎች ዘመናት አብረውን ኖረዋል በእነኛ ሁሉ አመታት ግን ስራ ላይ ስላልዋሉ ሀገሪቱ ከነሱ እምታገኘው ይህ ነው የሚባል ጥቅም አልነበረም ማለት ይቻላል የሀገራችን የቆዳ ስፋት የፈረንሳይን እጥፍ የሚሆን ሲሆን የህዝብ ብዛቱም የበለጠ ነው ያም ብቻ ሳይሆን በርካታ ወንዞች እና ገና ያልታረሰ በቂ ዝናብ እሚያገኝ ሰፊ መሬት ባለቤትም ነች ወደብ አለመኖሩ ብቻ ፈረንሳይ የበለጠ እንዲኖራት ቢያደርግም

 
አሁን የአውሮፓ ምጣኔ ሀብት በአንፃራዊነት እድገቱ እየቀነሰ ያለው ምክንያት የህዝብ ብዛት እየቀነሰና እያረጀ ሲሄድና የወጣቱ ቁጥር መመናመን በራሱ ያለውን ውስጣዊ አቅም እንዲዳከም ስለሚያደርገው ነው


በቀድሞው ጊዜ 16ኛው፣ 17ኛው፣18ኛው ክፍለ ዘመናት በእንግሊዝ ሀገር የተጀመረ ሜርካንታሊዝም የሚባል የኢኮኖሚ ስርአት የነበረ ሲሆን ይህ ስርአት አንዲት ሀገር ከውጪ ሀገራት ወርቅንና ብርን በመሰብሰብ አንድ ሀገር ሀብታም ትሆናለች የሚል ነው ይህም ወደ ውጪ ምርትን ብቻ በመላክና ለውጪ ብዙ ባለማስገባት ወይም ባለመግዛት የወርቅና የብር ማእድናትን መጨመር የሚል ነው ነገር ግን አንዳንድ አሜሪካውያንም የቻይናን የገንዘብ ምንዛሪዋን ዝቅ በማድረግ የወጪ ንግዷን መጨመርና የገቢም ንግድ መቀነስና እንደ ቀድሞ በአውሮፓ ከነበረው የሜሪካንታሊዝም ስርአት ጋር ያመሳስሉታል። ይሁን እንጂ ይሄ ስርአት በሀገር ውስጥ የዋጋ ግሽበትን በመፍጠር ተመልሶ እድገትን የመጎተት ውጤት ይኖረዋል በእርግጥ ለተወሰነ ጊዜ አንድ ሀገር በእጅጉ አስፈላጊ የሆነ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲኖራት ያስችላል፤ ነገር ግን ዘላቂ የምጣኔ - ሀብት እድገት ፖሊሲ ግን ሊሆን እንደማይችል የታወቀ ነው