ምጣኔ - ሀብቱ በገንዘብ አማካይነት የሚንቀሳቀስ «ሞኒቱይዝድ»
ባልሆነባቸው ፣ በገንዘብ አማካይነት የሚካሄድ ንግድ ባልዘመነባቸው ሀገራት ገንዘብ ማተም በዋጋዎች ላይ ያን ያህል ውጤት አያመጣም
የሚል አስተሳሰብ አለ ። ነገር ግን የጊዜ መርዘም ነው እንጂ ፣ እንደ ካፒታሊዝም እንዳደገባቸው ፣ የአክስዮንና የካፒታል ፣ የቦንድ ገበያ እንዳለባቸው ሀገራት ውጤቱ በአንድ ጊዜ የሚታይ አይደለም ። ነገር ግን አንድ አመትም ፣ ሁለት አመትም ይፍጅ ዞሮ ዞሮ ግን የገንዘቡ መጠን እስከጨመረ ቁጥር የዋጋ ግሽበትን ማስከተሉ አይቀሬ ነው ።
ነገር ግን የዋጋ ግሽበት የመንግስትን በጀትንም ጭምር የሚያቃውስ ነገር ነው ። መንግስት ራሱ ከገበያው ላይ ሸማች እንደመሆኑና የተለያዩ አገልግሎቶችንና ኮንትራቶችን የሚሰጥ እንደመሆኑ ፣ የራሱን በጀት እየተቃወሰበትና ከሚጨምረው የዋጋ ግሽበት ጋር ባጀቱን ማመጣጠን እያቃተው እንዲሄድ ያደርገዋል ።
ይህም ብቻ ሳይሆን ግሽበት የመንግስት ፖለሲ ውጤትም ሊሆን ይችላል ወይም ከመንግስት ፖሊሲ ሊመነጭ ይችላል ። ለምሳሌ የገንዘብ ምንዛሬን ዝቅ ማድረግን ብንወስድ በሀገር ውስጥ ያለ ዋጋ ግሽበትን ሊያባብስ ይችላል ። የወጪ ንግድ (Export)ምርታቸው የግብርናና
የፋብሪካ ያልሆኑ ሀገራት የዋጋ የገንዘባቸውንም ምንዛሬ ዝቅ ቢያደርጉት ተጠቃሚላይሆኑ ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ፣ በምርት ፣ በንግድና በወጪ ንግድ
ላይ የተመሰረተ ምጣኔ
- ሀብት የአገሩ ገንዘብ
በሚወደድበት ወቅት
የሚያመርተው እቃ
በአለም አቀፍ ደረጃ
ውድ ስለሚሆንበት ተወዳዳሪነቱን ይቀንስበታል ይህም
በርካታ የጃፓን ኩባንያዎችን እየገጠመ ያከለ
ችግር ሲሆን ፤ የመኪና አምራቹን ቶዮታን ጨምሮ
እየገጠመ ያለ ችግረር
ነው ። Pro , trade
and exports
እድገት መጣ የሚባለው በአገልግሎት ዘርፍ ሲሆን ይህም ዘርፍ በአብዛኛው በመንግስት ወጪ የሚገፋ ሲሆን ከእነኚህ ዘርፎች ውጪ ያሉ ዘርፎች ግን የሚደርሳቸው ብዙም ሀብት አይኖርም ። እድገቱ በተወሰኑ ዘርፎች ላይ ብቻ መመስረቱ የሀብት ክፍፍሉን ሲያዛባ ፣ በሌሎችም ዘርፎች ማደግ አለበት በተለይም በግብርናና በኢንዱስትሪ ዘርፎችም እድገቱ ተመጣጣኝ አይደለም ።የገንዘብ ምንዛሬን ዝቅ ማድረግ (Devaluation) እንደዚሁ
መንግስት ለሚሰራቸው ፕሮጀክቶች ብዙ የውጪ ምንዛሪን ስለሚፈልግ የገንዘብ ምንዛሬውን ዝቅ በማድረግ ፣ ብዙ ገንዘብ ለመሰብሰብ ነው ።(Devaluation) እንደ
እንደ ኢትዮጲያ ላሉ የግብርና ምንርትንና የማእድን ሀብታቸውንበዋናነት ወደ ውጪ ለሚልኩ ሀገራት ፣ የገንዘብ ምንዛሬያቸውን ዝቅ ማድረግ ያን ያህል ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን ገቢ ላያሳድገው ይችላል። በዚህ ዘርፍ የተጠኑ በርካታ ጥናቶች ቢኖሩም ቁልጭ ያለ ድምዳሜ ግን የላቸውም ። አንዳንዶቹ ጥናቶች የገንዘብ ምንዛሬን ዝቅ ማድረግ የውጪ ምንዛሪ ግኝታቸውን ከፍ ያደርጋል ይላሉ ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ የገንዘብ ምንዛሬን ዝቅ ማድረግ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱ ላይ ለውጥን አያመጣም እንደውም በአገር ውስጥ የዋጋ ንረትንና ሸቀጦቻቸውን በርካሽ ወደ ውጪ መላክን ነው እሚያስከትለው የሚሉ አሉ ። ለምሳሌ በጋና ላይ የተጠናው ጥናት ….
የአንድ አገር ውስጥ ያለ የሸቀጦችም ሆነ የአገልግሎት ዋጋ በዛች ሀገር የገቢ ደረጃ ላይ ነው የሚመሰረተው ። ለምሳሌ በእንድ የአውሮፓ አገር ያለን ዋጋ አንድ ደሀ አገር ካለ ዋጋ ጋር ማወዳዳር አይቻልም። ምክንያቱም በዛች ሀገር ገቢ ደረጃ ላይ የተመሰረተ ስለሚሆን ነው ።በአውሮፓ እጅግ ሀብታም በሆነችው በጀርመን ሀገር የአንድ ስኒ ቡና ዋጋና በአዲስ አበባ የአንድ ስኒ ቡና ዋጋ እኩል ሊሆን አይችልም። የነፍስ ወከፍ ገቢ ከዋጋ ግሽበቱ ጋራ ተመጣጣኝ ሆኖ ማደግ አለበት ። ትክክለኛ የሆነ የጥቅል ምጣኔ - ሀብት አስተዳደር (Macroeconomic Management) ለአንድ መንግስት ህልውና እጅግ ቁልፍ ጉዳይ ነው ። ምጣኔ - ሀብቱን በትክክል መምራት ካልቻለ ፣ የፖለቲካ ህልውናው እየደበዘዘና በተቃዋሚዎቹ በቀላሉ ለከፍተኛ ትችትና ብሎም ለህዝብ አለመረጋጋትንና ድጋፍን ማጣትን ያስከትላል ።
የዋጋ ጭማሪውን ማስቆም ወይም ድጎማ ማድረግ አለበት ። የዋጋ መናር በሚፈጠርበት ጊዜ መንግስት ሁለት አማራጭ አለበት ። መንግስት ራሱ ነጋዴ ሲሆን ፣ መንግስት የፖሊሲ መሳሪያዎችን ብቻ ነው መጠቀም ያለበት እንጂ ። በምጣኔ - ሀብቱ ውስጥ በቀጥታ ራሱ ነጋዴና አከፋፋይ ከሆነ አስቸጋሪ ነው ። በመንግስት የተደገፈ ልማት በተካሄደባቸው እንደ ጃፓንና ደቡብ ኮርያ መንግስት አጋዥ ነው መሆን ያለበት ፣ እንጂ ራሱ በኢኮኖሚው ውስጥ ተሳታፊ ሆኖ አልነበረም ።