Tuesday, July 23, 2019

አረንጓዴ_አሻራ

ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በሚኒስቴሩ ስር የሚገኙ 15 ተጠሪ ተቋማት በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሐምሌ 15/2011 የችግኝ ተከላ አካሄዱ፡፡

ከ3,800 በላይ ሠራተኞች በተሳተፉበት በዚህ የችግኝ ተከላ ከ22,000 በላይ ችግኞችን በቦሌ ለሚና በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመትከል ተችሏል፡፡

በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበረው የቸችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተሳተፉት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየሱስ እንደገለፁት ይህ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በዋናነት የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ አቅም መፍጠሪያና በሐምሌ 22/2011 የሚካሄደው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን መንደርደሪያ ነው ብለዋል፡፡

ሐምሌ 22 ለሚካሄደው ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ሁሉንም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞችን ማሳተፍ እንዲቻል የቅድመዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን አውስተው በእለቱም በኦሮሚያ ክልል በፍቼ ከተማ አካባቢ 80,000 ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል፡፡

በችግኝ ተከላው የተሳተፉ ሠራተኞች እንደገለፁት በዚህ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ቀን ላይ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ በመቻላቸው የተሠማቸውን ደስታ ገልፀው በሀገራዊው የሠላም፣ የዴሞክራሲና የልማት እንቅስቃሴም ውስት ሁሉም በላፊነት የየግሉት አስተዋፅኦ በማድረግ የተጀመረውን ሀገራዊ መግባባት ማሳደግ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

Friday, July 12, 2019

ወደ ኋላ የመመለስ ስጋት

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር፤ የጸረ-ሽብር ሕጓን መልሳ ሥራ ላይ በማዋል እና የኢንተርኔት ግልጋሎትን በማቋረጥ ወደ ቀደመው የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት አፈና የመመለስ አደጋ እንደተጋረጠባት የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ፣ (CpJ ) አስጠነቀቀ።

በአሁኑ ወቅት በትንሹ ሦስት ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ (CPJ) አስታውቋል። ሌሎች ሦስት ጋዜጠኞች ታስረው ቢፈቱም አሁንም የፍርድ ቤት ሙግት እንደሚጠብቃቸው ከሰሐራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት የድርጅቱ ተወካይ ሞቶኪ ሙሞ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ሞቶኪ ሙሞ እንደሚሉት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ሥራቸውን በአግባቡ ለመከወን ፈተና በዝቶባቸዋል።
ሞቶኪ ሙሞ «ባለፈው ሰኔ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትን እጅግ ጎድቷል።

ጋዜጠኞች ሥራቸውን ለመሥራት፣ ከመረጃ ምንጮቻቸው ለመገናኘት፣ መረጃዎቻቸውን ለማጣራት ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት ለማተም ፈተና ሆኗል። በግንቦት እና በሰኔ ወራት የታሰሩ ጋዜጠኞች አሉ።

ቢያንስ አንድ ጋዜጠኛ እና ባልደረባው በሥራቸው ሳቢያ ክስ ተመስርቶባቸዋል። በቅርቡ ከዚህ ቀደም ለመገናኛ ብዙኃን ብዙ ችግር ሲፈጥር በቆየው የጸረ-ሽብር ሕግ ጋዜጠኞች መታሠራቸውንም ደርሰንበታል።» ብለዋል ።

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ባለፈው አንድ ዓመት የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት መሻሻል ቢያሳይም የመንግሥቱ የቀደሙ ልምዶች የማገርሸት ምልክት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በጀመራቸው ማሻሻያዎች ለውጥ ይደረግበታል የተባለው የጸረ-ሽብር ሕግ መልሶ ጋዜጠኞችን ለማሰር ግልጋሎት ላይ መዋሉ አሳሳቢ መሆኑን ጠቁመዋል። ሞቶኪ ሙሞ «አዎንታዊ መሻሻል ወደታየበት፣ መንግሥት ጋዜጠኞችን ወደማያስርበት እና ኢትዮጵያ የመገናኝ ብዙኃን ነፃነት የተከበረባት አገር ትሆን ዘንድ ሊያረጋግጥ ወደሚችለው የማሻሻያ እርምጃ እንመለስ ማለት እንፈልጋለን።

በእርግጥ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት መፃኢ እጣ-ፈንታ አሳስቦናል፤ የዛኑ ያህል የታዩ ለውጦችንም እንረዳለን። የምናነሳቸው አሳሳቢ ጉዳዮች ምላሽ አግኝተው ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ነፃነት የተከበረባት አገር ትሆናለች ብለን ተስፋ እናደርጋለን።» ሲሉ በአጽንዖት ተናግረዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ Amnesty International  ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ አገሪቱ ባለፈው አንድ ዓመት ገደማ ያሳየችውን መሻሻል ሊቀለብስ እንደሚችል በትናንትናው ዕለት አስጠንቅቆ ነበር። ወደ ኅንላ እንዳንመለስ ጎበዝ።

Wednesday, July 10, 2019

ምን ሊሆን ይችላል

መፈንቅለ መንግስታት ያደረሱት የኢኮኖሚ ጉዳት
በቅርብ ግዜያት የተደረጉት መፈንቅለ መንግስታት ለኢንቨስትመንት ፀር ነው - በተለይም የውጭ ኢንቨስትመንት ፤ የቱሪዝም ፍሰቱን ይቀንሳል ። መፈንቅለ መንግስት ተደረገ የሚል ዜና መሰማት እንኳን የሀገርን ገፅታ በእጅጉ ይጎዳል ። ለዚሕም ምሳሌዎቹ በቱርክ ፤ በታይላንድ ፤ በግብፅ እና በሱዳን የትድረጉት ኣይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው ።
ጃንሆይ እንኳን የተሞከረባቸውን የ53ቱን የነ መንግስቱ ንዋይን ሙከራ "የታህሣሡ ግልግር " ከማለት ውጭ  መፈንቅለ መንግስት ነው አላሉም።

Sunday, July 7, 2019

ራስ -ተፈርያውንና ጃንሆይ

‌«ወደ አህጉረ አፍሪካ ተመልከቱ አንድ ጥቁር ይነግሣል፤ ነፃነትም ይሆናል» ጃማይካዊው የመብት ታጋይ ማርከስ ጋርቬይ ነበር ይህን የተነበየው።  ኢትዮጵያን ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ የገዙት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በ1923 ዓ. ም. የንግሥና ዙፋናቸውን ጫኑ።

የእሳቸው ንግሥና ዜና አህጉረ አፍሪካን አልፎ ጃማይካ ደረሰ። ወሬውን የሰሙ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ፈጣሪ በሥጋ ተገልጿ፤ ጠባቂያችን ነግሧል በማለት ወደ ኢትዮጵያ ጎረፉ። ራስ ተፈሪያን ጃህ እያሉ የሚጠሯቸው ጃንሆይ፣ በፈረንጆቹ 1966 ዓ. ም. ወደ ጃማይካ አቀኑ። ሥፍር ቁጥር የሌለው ሰው ተቀበላቸው። ባዩትም ነገር እጅግ ተደነቁ። እሳቸው ወደ ኪንግስተን ባቀኑ ጊዜ የሰማይ ውሃ ዓይንሽን ለአፈር ብሏት የነበረችው ጃማይካ በዝናብ እንደራሰችም ይነገራል።

የሬጌ ሙዚቃ ንጉሡ ቦብ ማርሌም በሙዚቃው አፍሪካን እና ኢትዮጵያን እንዲሁም ንጉሡን የመፃኢ ዘመን ተስፋ እና መጠጊያ አድርጎ ይስላቸው ነበር። ለአፍሪካ አንድነት በሠሩት ውለታ ሊታወሱ ይገባል ተብሎ በቅርቡ ሃውልት የቆመላቸው ጃንሆይም ወደ አፍሪካ መመለስ ለሚሻ ጥቁር ይሁን በማለት ሻሸመኔ አካባቢ 200 ሄክታር ገደማ መሬት ለገሱ።

የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ከደቡባዊ የአፍሪቃ ክፍል እስከ ምዕራቡ ጥግ፤ ከሰሜን እስከ ምስራቅ ይገኛሉ። እንደ ሻሸመኔ ግን ያለ አይመስልም።
መጀመሪያ ላይ 12 ጃማይካዊያን ብቻ ወደ ሻሸመኔ እንዳቀኑ ይነገራል። ኋላ ላይ ግን የትየለሌ ራስ ተፊሪያኖች ጉዟቸውን ወደ ሻሸመኔ አደረጉ።

አሁን ላይ ሻሸመኔ ውስጥ በርካታ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታይ ጃማይካዊያን ይኖራሉ። አሁን ግን ትኩረቱ ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ ከቆዩባት ሻሸመኔ ወደ ሐረር የዞረ ይመስላል። ለምን?

ከሻሼ ወደ ሐረር  ራስ እዝቄል ኩማ ለበርካታ ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የኖረ የራስ ተፈሪያን እምነት ተከታይ ነው። ኢትዯጵያ ውስጥ ወልዶ ከብዷል። ሕይወቱን መሥርቷል። ከሻሸመኔ ወደ ሐረር የሚደረገውን መንፈሳዊ ጉዞ የሚመራው ራስ እዝቄል ኩማ ለራስ ተፈሪያን ማሕበረሰብ ከሻሸመኔ ይልቅ ሐረር የተሻለ ቅርበት እንዳላት ይናገራል።

«ልንሆን የሚገባው ሐረር ነው። ጃህ፤ ንጉሳችን የተወለዱበት ሥፍራ ነው። እዚያ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስትያን አለች። እዚያ ነው እትብታቸው የተቀበረው» ይላል። እርግጥ ነው ይህን ጉዞ ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ራስ ተፈሪያኖች ጥቂት እንደሆኑ ራስ እዝቄል አይሸሽግም። መኖሪያቸውን ሐረር ያደረጉ ጃማይካውያን እንዳሉም ይናገራል።

«ጉዞው ለኛ ትልቅ ትርጉም አለው። ወደ ሐረር እንድንጓዝ የሚያደርግ መንፈሳዊ ጥሪ ደርሷል። ይህን ጉዞ እኛ ለመጀመር እናስበው እንጂ ጥሪው ለሁሉም የራስ ተፈሪያን እምነት ተከታዮች ነው።»

ራስ ኩማ ሐረር ለራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ያላትን ሥፍራ ሲያስረዳ፤ «እኔ ሁሉም የራስ ተፈሪ እምነት ተከታይ በሕይወት ዘመኑ አንዴ ኤጀርሳ ጎሮን ቢያይ ደስ ይለኛል። የእስልምና እምነት ተከታዮች ወደ መካ እንደሚያቀኑት ሁሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ቤተልሔምን ለማየት እንደሚጓጉት ሁሉ እኛም ሐረርን ማየት እንናፍቃለን» ይላል። ግን ግን የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ሐረር ውስጥ እንዴት ያለ ማሕበረሰብ ይሆን ለመመሥረት የሚሹት? ራስ እዝቄል ጉዞው ገና ጅማሮ ላይ ያለ ቢሆንም ልናቋቁም ያሰብነው ማሕበረሰብ ሻሸመኔ ከሚገኘው ለየት ያለ ነው ይላል።

«ለሁሉም የራስ ተፊሪያን እምነት ተከታይ የሚሆን ምቹ ሥፍራ እንዲሆን ነው ፍላጎታችን። እዚያ ከሚኖረው ማሕረበሰብ ተነጥለን የመኖር ዕቅድ የለንም። አንድነትን መሠረቱ ያደረገ፤ እርስ በራስ የሚከባበር እና የሚግባባ ማሕበረሰብ የመፍጠር ፍላጎት አለን።»
ከአርባ ዓመታት በላይ ጃማይካውያንን ያስጠለለችው ሻሸመኔስ ምን ይሰማት ይሆን? ራስ እዝቄል ጉዞው ከሻሸመኔ ጠቅልሎ ወጥቶ ወደ ሐረር የሚደረግ 'ፍልሰት' ተደርጎ እንዳይታሰብ ይሰጋል።

«ጉዳዩ አዲስ ምዕራፍ የመክፈት ጉዳይ ነው። በርካቶቻችን በምዕራብ ሃገራት ተጠልለን የምንኖር ነበርን። አሁን ግን አንድ የሚያደርገንን ነገር እንፈልጋለን። ይህን ስናስብ ደግሞ 'ጃህ' ከተወለዱበት ሥፍራ የተሻለ ቦታ የሚገኝ አይመስለኝም።»

ኤጀርሳ ጎሮ ጉዞው ጅማሬ ላይ ነው ያለው። ኤጀርሳ ጎሮ ላይ አንድ ቤተ - ክርስትያን የማነፅ ሥራ ከዕቅዱ መካከል ይገኛል። በሁለት ዓታት ጊዜ ውስጥ ብዙ ነገሮች ተሳክተው ጉዞ ሻሸመኔ - ሐረር የተሳካ እንደሚሆን ራስ እዝቄል እምነት አለው።

ከሐረሪ ክልል ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በትብብር እየሠሩ እንደሆነም ይናገራል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የምስራቅ ሐረርጌ ፅህፈት ቤት ጉዞው የተሳካ አንዲሆን ከራስ ተፈሪያኖች ጋር በጥምረት እንዲሰራ እንደሚፈልጉ ራስ እዝቄል ይጠቁማል። በመላው ዓለም የሚገኙ ራስ ተፈሪያኖች ለጉዳዩ ጆሮ መስጠት እንደጀመሩ የሚናገረው ራስ እዝቄል ቤተክርስትያን የማነፁን ሥራ እንዲሁም ሌሎች ተግባራት የሚጠናቀቁ ከሆነ እርዳታው ከዚያም ከዚህም መምጣቱ አይቀርም ባይ ነው።

ኤጀርሳ ጎሮ አዲሲቷ የራስ ተፈሪ እምነት ተከታዮች ትሆን ይሆን? በስተመጨረሻ የእምነቱ ተከታዮች የጃንሆይን የትውልድ ስፍራ መጠጊያቸው አድረርገው ኃይማኖታዊ ጉዟቸውን ወደ ተስፋይቱ ምድር ያደርጉ ይሆን? ።

Saturday, July 6, 2019

Sidama ክልል

የሲዳማን ክልልነት ጥያቄ የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ መንግሥት በድርድር እንዲፈታው ዐለም ዐቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን አሳስቧል፡፡ ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ #ICG ከናይሮቢ ቢሮው ባወጣው ወቅታዊ ሪፖርታዥ መፍትሄው የሕዝበ ውሳኔውን ቀን በቶሎ ቆርጦ ማሳወቅ ነው ብሏል፡፡ ዞኑ በተናጥል ክልልነቱን ካወጀ ደሞ እንደ ሀዋሳ ያሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች እስኪፈቱ የመንግሥት ምስረታውን እንዲያዘገየው መክሯል፡፡ ጉዳዩ በጥንቃቄ ካልተያዘ ደቡብ ክልል በሞላ ብጥብጥ ውስጥ ሊገባ ይችላል፤ ሕገ መንግሥታዊ ዝግጅት ሳይደረግ መንግሥት የሲዳማን ክልልነት ከተቀበለም ያው ግጭት ሊከሰት ይችላል ሲል አስጠንቅቋል፡፡ ሕዝበ ውሳኔው በጊዜ ገደቡ ካልተካሄደ በመጭው የፈረንጆች ሐምሌ 18 የሲዳማ ክልልን በተናጥል ለማወጅ ሲዳማ ዞን በያዘው አቋም እንደጸና ነው፡፡ በተያያዘ ዜና የሲዳማ እጀቶዎች ዛሬ ሃዋሳ ላይ ባደረጉት ስብሰባ የትኛውንም ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ውሳኔ ላለመቀበል መወሰናቸውን የሲዳማ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡

Tuesday, July 2, 2019

የ ኢራን -አሜሪካን ውዝግብ ዚቅ

የኢራን አብዮት 40ኛ አመት ፥

ሻሁ የዘመናት አንፀባሪቂ ጀንበራቸዉ በ38ኛዉ ዓመት ከምዕራብ አድማስ ጥግ መድረሷን የተረዱት መሠለ።ጥር 1979 «ለዕረፍት» በሚል ሰበብ ጓዛቸዉን ጠቅልለዉ ከቴሕራን ዉልቅ አሉ።በወሩ የአመፁ በተለይ እስልምናን እንደ ርዕዮተ ዓለም አንግበዉ የሚታገሉ ወገኖችን--- ይመሩ የነበሩት ታላቁ አያቱላሕ ሩሆላሕ ኾሚኒ ከ16 ዘመን ስደት በኋላ ቴሕራን ገቡ ።

እስራኤል እንደ ሐገር ከተመሰረተች ከ1948 ጀምሮ የፀናዉ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ፖለቲካዊ ሥርዓት ባዲስ ጎዳና ይሾር ገባ።ከ1917 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ) ጀምሮ ዓለምን በኮሚንስት-ካፒታሊስት እሁለት ገምሶ የሚያናክሰዉ ርዕዮተ-ዓለም፣ እስላምን-ከአብዮት የቀየጠ ሰወስተኛ አስተሳሰብ ታከለበት።የካፒታሊስቱ ቁንጮ የዓለም ልዕለ-ኃይል ዩናይትድ ስቴትስ ሐብታም ታማኝ፣ታዛዥ ጥብቅ ወዳጅዋን አጣች።የፋርሶች የ2500 ዘመን ንጉሳዊ አገዛዝ ተገረሠሠ።

የዩናይትድ ስቴትስና የብሪታንያ ሰላዮች ከአንድ ዓመት በላይ ያሴሩ፣ያቀነባበሩ፣በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የረጩበት የመፈንቅለ መንግስት ሴራ በድል ተጠናቀቀ።ዘመቻ አጃክስ ብለዉት ነበር። በ1951 በኢራን ሕዝብ የተመረጡት ጠቅላይ ሚንስትር መሐመድ ሞሳደጊ ከስልጣን ተወገዱ።የለንደን ዋሽግተን ታማኝ አገልጋይ ንጉስ መሐመድ ሬዛ ፓሕላቪ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩ።

ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ሲታገሉ የነበሩት ኢራኖች በጅምር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታቸዉ ቅጭት አንገታቸዉን ሲደፉ፣ ለለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ፅናት እንደሚታገሉ ጧት ማታ የሚደሰኩረት የለንደን-ዋሽግተን መሪዎች በሴራቸዉ ድል ይቦርቁ ገቡ።ደስታ-ፌስታዉ ወዳጅነቱን አጠንክሮ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ቴሕራንን እንዲጎበኙ ምክንያት ሆኖ ነበር።

«ፕሬዝደንቱ ቴሕራን ሲገቡ ከሩብ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ አቀባበል አድርጎላቸዋል።ለዚሕ ታሪካዊ ጉብኝት ሻሕ ፓሕላቪ ንጉሳዊዉ ቤተ-መንግስት ዉስጥ ልዩ አቀባበልና ለፕሬዝደንቱ ስጦታ አቅርበዉላቸዋል።»

ታሕሳስ 1959።

በርግጥም 1977፣ 1952 ወይም 53 ወይም 59 አልነበረም።ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተርም አይዘናወርን አይደሉም።ካርተር በ1977 ማብቂያ ወደ ቴሕራን የተጓዙት ግን አይዘናወር በ1953 ከዙፋናቸዉ ከተከሏቸዉ፣ በ1959 ቴሕራን ድረስ ተጉዘዉ ከጎበኟቸዉ ከንጉሰ-ነገስት መሐመድ ሬዛ ፓሕላቪ ጋር የ1978ን አዲስ ዓመት ዋዜማን ለማክበር ነዉ።

ካርተር እንደ ልዕለ ኃያል ሐገር መሪ ቴሕራን ቤተ-መንግሥት ዉስጥ ሲንበሻበሹ በድፍን ኢራን፣  ዉስጥ ዉስጡን የሚንተከተከዉን ሕዝባዊ ብሶትና ቁጣ ያወቁት አይመስሉም።የዓለምን እንቅስቃሴ እያጮለገ ሰዓት-በሰዓት

ለመሪዎች ያቀርባል የሚባለዉ CIAም ሆነ ተባባሪዎቹ የብሪታንያዉ MI6 ወይም የእስራኤሉ ሞሳድ ለአሜሪካ መሪ የሰጡት መረጃ አልነበረም።ከነበረም ሰዉዬዉ ይፋ ማድረግ አልፈለጉም።

የፈለጉት ንጉሰ ነገስት መሐመድ ሬዛ ፓሕላቪ ለ37 ዘመን ረግጠዉ የገዟት ኢራን «የሰላም ደሴት» እንደሆነች ማወደስ ነበር።«ኢራን በሻህ ታላቅ አመራር ምክንያት፣ በዓለም እጅግ ከሚታወከዉ አካባቢ አንዱ በሆነዉ አካባቢ የመረጋጋት ደሴት ናት።ይሕ ሊሆን የቻለዉ፣ ግርማዊ ሆይ፣ በእርስዎ አመራርና ሕዝብዎ በሚሰጥዎ ክብር፣ አድናቆትና ፍቅር ምክንያት ነዉ።»

ካርተር ያንቆለጰሷቸዉ መሐመድ ሬዛ ፓሕላቪ የኢራን ንጉሰነገስ ናቸዉ።ሻሐንሻሕ፣ የአርያን ነገድ ብርሐን ናቸዉ።የኢራን ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸዉ።የኢራን ዘመናይ ሥርዓት መሥራች ናቸዉ።በ1979 በኢራን የአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ማይክል ሜኪንኮ እንዳሉት ደግሞ ለአሜሪካኖችም ታማኝ አጋልጋይ ናቸዉ።«እሳቸዉ በኢራን የኛ ሰዉ ናቸዉ።የሳቸዉ ኢራን የኛ ሐገር ናት።ኢራን የነዳጅ ምንጫችን ናት።ኢራን የጦር መሳሪያ ደንበኛችን ናት።ኢራን በራስዋ መንገድ ከሶቭየት ሕብረት ጥቃት የምትከላከለን ናት።»

ሰዬዉ ለታማኞቻቸዉና ለሚታመኑላቸዉ በርግጥም ሁሉም ናቸዉ።ለአብዛኛዉ ኢራናዊ ግን ረጋጭ፣ጨቋኝ፣ ጨካኝ ናቸዉ።የ37 ዘመኑ ጭቆና ያንገሸገሸዉ ሕዝብ የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ቴሕራንን ከጎበኙ ከጥቂት ወራት በኋላ የተደበቀ ቁጣ ተቃዉሞዉን ባደባባይ ይዘርገፈዉ ገባ።

ካርተር የመካከለኛዉ ምሥራቅ «የሠላም ደሴት» ያሏት ጥንታዊት ሐገር በአመፅ፣ ሁከት፣ ግድያ ተተረማሰች።ኮሚንስቶች፣ዴሞክራቶች፣ብሔረተኞች፣ እስላማዉያን ባንድ አብረዉ የመሩት ሕዝብ የአሜሪካኖች ጥይት፣የአሜሪካ-እስራኤል-ብሪታንያ የስለላ መረብ፣ የአረቦች ገንዘብ አልበገረዉም።«ሞት ለሻሕ»ን ይፈክር ያዘ።

ሻሁ የዘመናት አንፀባሪቂ ጀንበራቸዉ በ38ኛዉ ዓመት ከምዕራብ አድማስ ጥግ መድረሷን የተረዱት መሠለ።ጥር 1979 «ለዕረፍት» በሚል ሰበብ ጓዛቸዉን ጠቅልለዉ ከቴሕራን ዉልቅ አሉ።በወሩ የአመፁ በተለይ እስልምናን እንደ ርዕዮተ ዓለም አንግበዉ የሚታገሉ ወገኖችን መጀመሪያ ኢራቅ ኋላ ፈረንሳይ ሆነዉ ይመሩና ያስተባብሩ የነበሩት ታላቁ አያቱላሕ ሩሆላሕ ኾሚኒ ከ16 ዘመን ስደት በኋላ ቴሕራን ገቡ።የካቲት 1 1979።

«ኢማሙ ገና ወደ ፈረንሳይ ከመሰደዳቸዉ ወይም አብዮቱ መልክና ቅርፅ ከመያዙ በፊት የሐገሪቱ መሪ መሆናቸዉ ሐቅ ነዉ።ምን ማለት ነዉ ሕዝብ እሳቸዉን ከተከተለ፣የሚሉትን ከሰማና ገቢር ካደረገ ወደድንም ጠላንም እሳቸዉ መሪ ናቸዉ።»

ከኮሚኒ ተከታዮች አንዱ።

በርግጥም የኢራን ሕዝብ እንደ

ታላቅ መሪ በደማቅ ስርዓት ተቀበላቸዉ።የሚሉትንም ገቢር ያደርግ ገባ።የሻሁን አገዛዝ ጥላቻ ብቻ ባንድ አብረዉ የነበሩት ኮሚንስቶች፣ዴሞክራቶችና ብሔረተኞች በእስላማዉኑ ተራ በተራ እየተደፈለቁ ተበታተኑ።ኾሚኑ ቴሕራን በገቡ በአስረኛዉ ቀን የኢራን አብዮት ድል በይፋ ታወጀ።የካቲት 1979።ዛሬ 40 ዓመቱ።

ከወር በኋላ በተደረገዉ ሕዝበ ዉሳኔ የአምስት ሺሕ ዘመን ባለታሪኳ፣የፋርሶች ስልጣኔ መሠረትዋ፣ የነዳጅ ዘይት ሐብታሚቱ ሐገር ከ2500 ዘመን በላይ የፀናባትን ንጉሳዊ አገዛዝ በይፋ አስወግዳ እስላማዊት ሪፐብሊክ ሆነች።የመካከለኛዉ ምሥራቅ የፖለቲካ አጥኚ ፕሮፌሰር ዓሊ አንሳሪ እንደሚሉት የኢራን አብዮት በጣሙን የመካከለኛዉ ምሥራቅን በመጠኑም የዓለም ፖለቲካዊ ሥርዓትን ለዉጦታል።

«እስላማዊዉ አብዮት በዓለም ላይ ያስከተለዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነዉ።መካከለኛዉ ምሥራቅን ቀይሮታል።የዩናይትድ ስቴትስና የምዕራባዉያንን ቁልፍ ተባባሪ አስወግዷል።ከዚያ ጊዜ በኋላ የመካከለኛዉ ምሥራቅን እንቅስቃሴ በሙሉ እየነካ ነዉ።»

በርግጥም የአረብ-እስራኤል ጦርነት-ከአረብ እስራኤል ይልቅ የኢራን እስራኤል ጦርነት ዓይነት መልክ ይዟል።የሊባኖስ፣የሶሪያ፤የኢራቅ፣ የሳዑዲ አረቢያ የባሕሬን፣ አሁን ደግሞ የየመን ጦርነት፣ፖለቲካዊ ዉዝግብ፣የስልጣን ሽኩቻ ይሁን ሕዝባዊ አመፅ ባንድ ወይም በሌላ መልኩ የእራን እጅ አለበት።

ዩናይትድ ስቴትስ ለረጅም ጊዜ ጥቅሟ «አደገኛ» የምትለዉን አብዮት ለመቀልበስ ገና ከጅምሩ መሞክሯ አልቀረም።የቀድሞ ታማኟን መደገፍ ቀዳሚዉ ነበር።ይሁንና ሐገር አልባዉን ንጉስ አንዴ በሕክምና ሌላ ጊዜ በሰብአዊነት ሰበብ ከሆስፒታል-ሆቴል ስታመላልስ ከ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ አሜሪካ ላይ ያቄመዉ የኢራን ሕዝብ በተለይም ታሪኩን የሰማዉን ወጣት ለበቀል ከማነሳሳት በስተቀር ለዋሽንግተንም ለስደተኛዉ ንጉስም የተከረዉ የለም። 

ሕዳር 4 1979።አሜሪካ ላይ ያቄሙት የኢራን ወጣቶች በቴሕራን የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲን ወረሩ።«በመስኮቴ በኩል ወደ ዉጪ ስመለከት የኾሚንን ፎቶ ግራፍ ያነገቡ ወጣቶች ኤምባሲዉ አጥር ላይ ሲንጠላጠሉ አየሁ።ያ ዕለት ለኔ በጣም አስፈሪ ቀን ነዉ።»

የያኔዉ የኤምባሲዉ ባልደረባ ባሪይ ሮዘን።ወጣቶቹ 52 አሜሪካዉያንን አገቱ።የአጋች-ታጋች አስለቃቂዎች ድራማ ከ444 ቀናት በኋላ አብቅቷል።ሁሉም ታጋቾች ተለቀዋል።መዘዙ ግን ዛሬም በአርባ-ዓመቱ ቴሕራንና ዋሽግተኖችን እንዳወዛገበ ነዉ።

የኢራን አብዮት ከፈነዳ ወዲሕ ዩናይትድ ስቴትስ 6 ፕሬዝደንት ቀያይራለች።የኢራንን እስላማዊ አብዮተኞች ለማጥፋት ያልዛተ ፕሬዝደንት የለም።የኢራን እስላማዊ አብዮተኞችም «ትልቋ ሰይጣን» የሚሏትን አሜሪካንን ያለወገዙ «ሞት ለአሜካን»ን ያልፈከሩ-ያላስፈከሩበት ጊዜ የለም።

ኢራን ድብቅ የኑክሌር መርሐ-ግብር እንዳለት ከታወቀ ወዲሕ ደግሞ የሁለቱ መንግስታት ዉዝግብ

መልኩን ቀይሮ ኑክሌር ቦምብ-የመስራት አለማስራት ባሕሪ ይዟል።ዉዝግቡን በድርድር ለመፍታት የሞከሩት፣ከአዉሮጳና ከቻይና ኃያላን መንግስታት ጋር ተባብረዉ ከኢራን ጋር የተስማሙት ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ነበሩ።ኦባማ በትራምፕ ሲተኩ ግን የነበረዉ ሁሉ እንዳልነበር ሆነ።

«ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር የተደረገዉን ስምምነት ማፍረሷን ዛሬ አዉጃለሁ።ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢራን ላይ ተጥሎ የነበረዉን ማዕቀብ ዳግም የሚያፀና ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ እፈርማለሁ።በጣም ከፍተኛ ደረጃ ያለዉን ምጣኔ ሐብታዊ ማዕቀብ ገቢር እናደርጋለን።»

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ግንቦት 2018።ማዕቀቡም ዳግም ተጣለ።ዉግዘት፣ፉከራ፤ሽኩቻ፣ የእጅ አዙር ዉጊያዉም ከየመን-እስከ ፍልስጤም፣ ከሶሪያ እስከ ሊባኖስ ቀጠለ።

የቴሕራን መሪዎች እንደሚሉት በአሜሪካ-እስራኤሎች የሥለላ መረጃ፣ ከሶሪያ በስተቀር በአረቦች ገንዘብ የተደገፈዉን የኢራቅን ጦር ስምንት ዓመት ተዋግተዉ ድል አድርገዋል።ዩናይትድ ስቴትስ ኢራቅን ወርራ የባግዳድ ቤተ-መንግሥትን ለቴሕራን ወዳጆች ለማስረከብ ተገድዳለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ወዳጅ ሳዑዲ አረቢያ የምትመራቸዉ የዓረብ መንግስታት በኢራን የሚደገፉ የየመን አማፂያን ለማጥፋት ያዘመቱት ጦር የመን ዉስጥ ይዳክራል።አራተኛ ዓመቱ።በኢራንና ሩሲያ የሚደገፉትን የሶሪያዉን ፕሬዝደንት በሽር አል-አሰድን ለማስወገድ ዩናይትድ ስቴትስ የምትመራቸዉ 29 መንግሥታት በቀጥታም፣በተዘዋዋሪም፣በዲፕላሚስም፣በገንዘብም፣ በጦርም መዋጋት ከጀመሩ-ስምንት አመታቸዉ። እስካሁን አሸናፊ ካለ በሽር አል-አሰድ ናቸዉ። አሜሪካ በትራምፕ ዘመን #Cripling የሚያሽመደምድ ያለችውን ማእቀብ ኢራን ላይ ጥላለች።

ህሩይ ወልደ ስላሴ

የዛሬው የታላላቅ ሰዎች ዝግጅታችን እውቁን የአማርኛ ስነጽሁፍ አባት ህሩይ ወልደ ስላሴን ይዘክራል፡፡

ባሕር ዳር፡ ህዳር 30 / 2009 ዓ.ም (አብመድ) ህሩይ ወ/ስላሴ ከአባታቸው አቶ ወልደ ስላሴ እና ከእናታቸው አመተ ማርያም ዜና ግንቦት 1 1871 ዓ ም የተወለዱ ሲሆን በአባታቸው በኩል መርሃ ቤቴ በእናታቸው ወገን ደግሞ መንዝ ናቸው ፡፡
የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት አባታቸው ልጃቸውን ለማስተማር ቆርጠው በመነሳታቸው ህሩይን በሰባት አመታቸው እንዲማሩ አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ቤተክርስቲያን ላኳቸው ፡፡
በቀለም አያያዛቸው በመምህራቸው ደብተራ ስነ ጊዮርጊስ አድናቆትን ያተረፉት ህሩይ በሁለት አመት ውስጥ የግእዝ ትምህርትን አቀላጥፈው መናገር ሲችሉ የፊደል አጣጣልን ግን ዘግይተው ነው የተለማመዱት ፡፡

የህሩይን ምጡቅ ችሎታ የተረዱት አባታቸው የተሻለ ትምህርት እንዲማሩ እድሜያቸው አስር ዓመት ሲሆን መድሃኒ አለም ወደተባለ የአብነት ትምህርት ቤት በመላክ ለልጃቸው መማር ትልቁን ሚና ተጫውተዋል፡፡
በጊዜ ሂደትም ህሩይ ውዳሴ ማርያምን እና ሌሎችንም የቅዳሴ መጻህፍት በማጥናት የዲቁና እና የቅስና ማእረግን አግኝተዋል፡፡
ህሩይ በዕውቀት እንዲታነጹ ጉልህ እገዛ ያደረጉላቸው አባታቸው በ53 አመታቸው በሞት ሲለይዋቸው ህሩይ ገና የ13 አመት ታዳጊ ነበሩ ፡፡

ህሩይ በአባታቸው ሞት ቢደናገጡም ትምህርታቸውን በጀመሩበት ትምህርት ቤት አጠናክረው በመቀጠል ከቀለሙ ጎን ለጎን ወደእርሻው ፊታቸውን በማዞር የተዋጣላቸው አርሶአደር ሆኑ፡፡
በግብርናውም ዘርፍ ተጠቃሚ በመሆን ብዙ የቀንድ ከብት እና ፈረሶች ማርባት ችለዋል ፤ምንም እንኳ ጥሩ የፈረስ ጋላቢ ባይወጣቸውም ፡፡
የህሩይ የስነ ጽሁፍ ዕውቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመምጣቱ የሰላሌ አገረ ገዥ የደጃዝማች በሻህ የግል ጸሃፊ እስከ መሆን ደርሰዋል ፡፡
በጸሃፊነት ብዙም ሳይቆዩ የንጉስ ሃይለስላሴ አባት የራስ መኮንን ጸሃፊ ሆነው አገልግለዋል ፡፡
በኋላም ወደ ሸዋ - አድአ በርጋ በመጓዝ ለቀኝ አዝማች መቁረጭ በግብር መዝጋቢነት ተቀጥረው ሰርተዋል ፡፡
በዚህም ስፍራ ተወዳጅነት በማትረፋቸው ከአሰሪያቸው ‹ የሆነው ፍሬ ›የሚል ስያሜን አግኝተዋል ፡፡

ህሩይ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ይህ ስማቸው በመግነኑ የተነሳ በርካታ መኳንንቶች ለማሰኮብለል ጥረት ቢያደርጉም ህሩይ ግን በቀላሉ የሚደለሉ አልሆኑም ፡፡
የቀኝ አዝማች መቁረጭ እና የህሩይ መለያየት ቁርጥ የሆነው የጣሊያንን ወረራ ለመመከት ዳግማዊ ዓጼ ምኒልክ በ1887 ዓ.ም የክተት አዋጅ ባሳወጁበት ወቅት ነው ፡፡
አዋጁን ተከትለው ቀኝ አዝማቹ ጠላትን ለመፋለም ወደጦር ግንባር በመዝመታቸው የስራ ግንኙነታቸው ተቋረጠ ፡፡
ህሩይ በጣሊያን ወረራ ወቅት ከጽህፈት ስራቸው በመነጠል ለተወሰነ ጊዜ በትውልድ ቀያቸው ቆይተዋል ፡፡

ከጦርነቱ በኋላ ህሩይ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት በእንጦጦ ኪዳነምህርት አከናውነዋል ፡፡
የህሩይ የስነ ጽሁፍ ስራ እየናኘ በመምጣቱ የዳግማዊ ምኒልክ የግል ታሪክ ጸሃፊ የሆኑት ጸሃፌ ትዕዛዝ ገብረ ስላሴ አስጠርተዋቸው ከተወያዩ በኋላ አንድ ቁና እህል ወይም 5 ኪሎ ግራም እህል በወር እየተሰጣቸው ለመስራት ወሰኑ ፡፡

በሁለት አመት ቆይታቸው ህሩይ 27 ያህል መጽሃፍትን በማጥናት መተርጎም ችለዋል፡፡
ይህን እንዳጠናቀቀቁ ከዳግማዊ ምኒልክ አራት ያህል ሽልማቶችን ከአንድ የእጅ ሰአት ጋር ተሸልመዋል ፡፡
ህሩይ የተለያዩ የስነጽሁፍ መጻህፍትን እና ፍትሃ ነገስት የተባለውን ታሪካዊ መጽሃፍ አጥንተዋል ፡፡
ቤተሰብ ለመመስረት የተነሱት ህሩይ የጸሃፈ ትዕዛዝ ገብረስላሴን ልጅ እንዲያገቡ ቢታጭላቸውም በድህነታቸው ምክንያት ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡
ይሁን እንጂ ሃሳባቸውን ለማሳካት ወደ ቀዬአቸው ደን አቦ በመመለስ ሚስት ሲያፈላልጉ ከቆዩ በኋላ ግንቦት 17 1895 ዓ.ም. ጎጆ ወጡ፡፡

ህሩይ ሚስታቸው ባተሌ የቤት እመቤት ከሚባሉት ተርታ በመሆናቸው ለስኬታቸው ቁልፍ ሆነዋል ፡፡
በ1882 ዓ ም. በኢትዮጵያ ድርቅ ተከስቶ በርካታ እንሰሳት በማለቃቸው ንጉስ ምኒልክ ከፈረንሳይ ሃገር የእንሰሳት ዶክተሮችን ለማስመጣት ወሰኑ ፡፡
ሆኖም ወደፈረንሳይ ተጉዞ ለመደራደር ብቃት ያላቸው ህሩይ መሆናቸውን ወልደ ጻድቅ የተባሉ የቤተመንግስት ሰው በመጠቆማቸው እንዲሰሩ ግዳጅ ተሰጥቷቸው ወደ ፈረንሳይ አቅንተዋል ፡፡
እዚያም የተሰጣቸውን አደራ በብቃት ለመወጣት ቡድኑን አስተባብረው ተልዕኳቸውን አሳክተዋል ፡፡
በ1890 ዓ.ም. ህሩይ ወርሃዊ ደመወዛቸው ወደ 10 ብር ከፍ ብሎላቸው የተጣለባቸውን የስራ ሃላፊነት በተሻለ መንገድ ወደ መስራት ተሸጋገሩ ፡፡

ቀጣዩን ክፍል ሳምንት እናቀርብላችኋለን

ለህብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

የህግና አዋጅ ቁጥጥር ከደህንነት አንጻር

# የደሕንነት አዋጅ ቁ 804/2005 ★★★★★★
የፌድራል ዓቃቢ ሕግ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይፋ ሲያደርግ ፥የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያፀደቀውና ሐምሌ 16/2005 ዓ.ም በነጋሪት ጋዜጣ “የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የተደነገገው” አዋጅ ቁጥር 804/2005 ስለሕግ ከለላና ስላለመገደድ (Immunity and Non–compellability) በሚያትተው አንቀፅ 20(1) ሥር፡– “ማንኛውም የአገልግሎት #ኃላፊ ወይም ሰራተኛ #ከስራ_ሲሰናበት ወይም ወደ ሌላ ቦታ ስራ ሲዘዋወር በአገልግሎት ተመድቦ በሚሰራበት ወቅት ከተልዕኮው ጋር ተያይዞ ስላወቃቸው መረጃዎች ወይም በእጁ ስለገቡ ሰነዶች ለፍርድ ቤት ወይም አጣሪ ኮሚቴ ወይም ለሌላ አካል እንዲገልጽ ወይም እንዲያቀርብ አይገደድም’ ሲል ያትታል። በዚህ መሰረት የፌድራል ዓቃቢ ሕግ ለፍርድ ቢያቀርባቸውና የአዋጁን አንቀፅ ጠቅሰው #መረጃ_አልሰጥም ቢሉ #ዓቃቢ_ ሕግ በምን መስፈርት ጥፋተኛ ናቸው ወይም ጥፋተኛ አይደሉም የሚል ውሳኔ ሊያሳልፍ ይቻለዋል? የሰራተኛው ተጠሪነት ለ#ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሆኑ የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር  ስራቸውን በአግባቡ ባለመምራታቸው ተጠያቂ ሊሆኑ አይገባምን? …ወዘተረፈ ** አንድ አዋጅ ሲወጣ ከህገ መንግስቱ ጋር መጣረስ የለበትም ነገርር ግብ ግን ከፍተኛው ተስልጣን አካል የህዝብ ተወካዮች ም /ቤት ስለሆነ ይህ ያወጣው ህግ ማለትም በህገ መንግስቱ መሰረት ሰብአዊ መብትን የጣሰ ይቅርታ ወይም ምህረት አይርረግለትም ሥለሚል ይህ የደህንነት መስርያ ቤትን እሚምመለከት አዋጅ ከህገ መንግስቱ ጋር ይጣረስ አይጣረስ ያየው የለም። ለሰብአዊ መብት ጥሰት መንስኤ የሆነው የጸረ_ሽብር አዋጁም ከህገ_መንግስቱ አንጻር የፈተሸው የለም። “ማንኛውም የአገልግሎት #ኃላፊ ወይም ሰራተኛ #ከስራ_ሲሰናበት ወይም ወደ ሌላ ቦታ ስራ ሲዘዋወር በአገልግሎት ተመድቦ በሚሰራበት ወቅት ከተልዕኮው ጋር ተያይዞ ስላወቃቸው መረጃዎች ወይም በእጁ ስለገቡ ሰነዶች ለፍርድ ቤት ወይም አጣሪ ኮሚቴ ወይም ለሌላ አካል እንዲገልጽ ወይም እንዲያቀርብ አይገደድም’ ሲል ያትታል።" ይህ ማለት ለህዝብ ተወካዮች ም /ቤት በተቁዋቁዋመ ኮሚቴ ፊትም ጭምር ያወቀውን መረጃ እንዲሰጥ አይገደድም። የደህንነት ተቁዋሙ የአስፈጻሚው አካል እንደመሆኑ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው። ከም /ቤቱ እሚደበቅ ሚስጥርም ሊኖር አይገባውም። ለተወካዮች ም / ቤት ሪፖርት ሢያቀርብም አልተሰማም። ይህ የደህንነት መ/ቤትን በአግባቡ መቆጣጠር አለመቻል አሜሪካኖችን ጭምር የደህንነት ተቁዋማቶቻቸውን መጀመርያ ሲያቁዋቁሙ አጋጥሞአቸው በሁዋላ ጠንካራ ለምርቆጣጠር የሚያስችላቸውን አውጥተው ፈትተውታል። ይህም ባለስልጣናት አዋጁ ይፈቅድልናል የፈለግነውን መስራት እንችላለን በሚል ሊያደፋፍር ይችላል። የፌዴሬሽን ም / ቤትም በበኩሉ ህግን ተርጉዋሚ እንጂ አንድ ህግ ወይም ደንብም ሆነ እዋጅን ህገ መንግስታዊ ነው ወይንስ አይደለም ብሎ የመፈተሽ ስልጣን የለውም። ይህም የህግ ክፍተት በቅርቡ ስለ ፍትህ ስርአቱ በተደረገ ውይይት የህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሊኖር እንደሚገባና ተነስቶአል። ህገ መንግስቱን እሚጻረር ህግም ሆነ አዋጅ እንዳይወጣ ሊያደርግ ይችላል።