Wednesday, December 5, 2012

የምጣኔ ሀብት አስተዳደር




አሁን የምንኖርባት አለማችን በየቀኑ እየተለወጠችና እየጠበበች በመምጣት ላይ ትገኛለች ።በብዙ ዘርፎች ከፖለቲካና ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጀምሮ ቴክኖሎጂ እያደገና የንግድ ልውውጦች እየተስፋፉ በሄዱ ቁጥር የእርስ በእርስ ግንኙነቶችም እንደዚያው እያደጉ እና እየተለወጡ ይሄዳሉ ። ይሄ ብቻ ሳይሆን አለማችን ይበልጥ እማትጨበጥ ፍሉድ አንዳንድ ጊዜም ይበልጥ ውስብስብና አደገኛ እየሆነች በመሄድ ላይ ትገኛለች ። ለዚህ ዋናው ምክንያቱ አለማችን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እርስ በእርስ የተሳሰረች በመሆኗና አንዱ ባንዱ ላይ ያለው ጥገኝነት እየጨመረ በመሄዱ ነው ። ለዚህ የህዝቦችና የሀገሮች ትስስር ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ያደረገው ደግሞ ምጣኔ - ሀብታዊ ትስስሮሽ ሲሆን ፣ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ የምጣኔ ሀብት እውቀትና መረጃ አስፈላጊነት ጎልቶ ይታያል ።

ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው በአንዱ ሀገር ኢኮኖሚ ችግር ቢከሰት ወዲያውኑ ወደ ተቀረው የአለማችን ክፍል ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ይስፋፋል። በአሁኑ ሰአት አንድ ሀገር ምጣኔ - ሀብት ከብዙ ነገሮች ጋር የተሳሰረ ነው ። ለምሳሌ የሀገራችንን ወንዞችን ብንወስድ አሁን በፊት ያለስራ ሲውሉ የቆዩ ቢሆንም አሁን ግን ከሀገሪቱ የምጣኔ ሀብትም ሆነ የፖለቲካ ጉዞ ጋር ቀጥታ ትስስር ያላቸው ጭምር ናቸው ። ወጣቶችን ብንወስድ በአሁኑ ወቅት በአንድ ሀገር ያለ የወጣቶች ሁኔታ - ያደገም ይሁን ያላደገ ሀገር - የዛን ሀገር የምጣኔ - ሀብትና የፖለቲካ እጣ - ፋንታ እሚወስበንበት ደረጃ ላይ ደርሷል ። የብዙ ነገሮች ትስስር ከዚህ በፊት ይታሰብ ከነበረው የበለጠ ነው ።


በአሁኑ ሰአት በአለማችን ላይ ምጣኔ - ሀብት አስፈላጊነት ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣበት ዘመን ላይ ደርሰናል ። በአለም ላይ ከዚህ በፊት በታሪክ ታይተው የማይታወቁ የምጣኔ - ሀብት ችግሮች በመታየት ላይ ሲሆኑ ፣ ለመፍትሄዎቻቸውም በመንግስታት ብቻ የሚፈቱ እንዳልሆኑ ከችግሮቹ ጥልቅነት የተነሳ መገነት ይቻላል ።   


በአሁኑ ሰአት አለማችን የመላው የሰው ዘር እየሆነች በመሄድ ላይ ስትሆን ፣አንደ ሰው የፈለገ ሀገር ፣ በሚፈልገው የአለም አካባቢ ሄዶ መኖር የሚችል ሲሆን ፣ ታዋቂው ሊባኖሳዊ ገጣሚ ካህሊል ጂብራን ሁሉም ማንም ሰው የትም ቢሆን አገሩ ነው የሚል ሀሳብን ያቀርባል ። በአንድ ሀገር ውስጥም ከተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የተውጣጡ ሰዎች በተለያዩ የአለማችን ሀገራት ከአሁን ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንደሚኖሩ ይጠበቃል ።   


ከዚህ በኋላ በአለም ላይ በየትኛውም ሀገር የውስጥ ጉዳይ የሚወሰነው በዋናነት በኢኮኖሚ ጉዳይ ይሆናል ። የብዙ ሀገራት መሪዎችም ስለ ኢኮኖሚው እንቅስቃሴ የተወሰነ ሙያዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሲጠበቅ ፤ ሀገራት ከኢኮኖሚ ውጪ ሌላ እንደ ቀድሞው የድንበር ውዝግብ ወይም ጦርነት ጉዳይ በብዙው የአለማችን ክፍል የለም - ጥቂት ከሆኑ የአለማችን ክፍሎች በስተቀር በእነሱም አካባቢ ጉዳዮች በእንጥልጥልና ባሉበት ቆመው ነው ያሉት እንጂ የፖለቲካና የአስተሳሰብ ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው ፤ በሀገራት መሀከል እንደ ቀድሞው ጊዜ የተጧጧፈ ጦርነት እሚካሄድበት ሁኔታ የለም ።


የሀገር መሪዎችም ዋናው ከሚጣልባቸው ግዳጆች አንዱና ዋናው ሀገራዊ ማእዱን ማስፋት ሲሆን ሀገራዊ ማእዱ ከሰፋ ለብዙ ዜጎች የተሻለ የስራ እድል ፣ የገቢ እድል ፣ ለመኖሪያ አስፈላጊና ምቹ የሆኑ ነገሮችን ማመቻቸት ይቻላል ። ነገር ግን ሀገራዊ ማእዱ አነስተኛ ከሆነ ግን ለብዙሀኑ ዜጎች የሚዳረስ ነገር ስለማይኖር እርስ በእርስ መበጣበጥና ሙስና የመሳሰሉት የፍትህ መጓደሎች ይከሰታሉ ።   


ቀደም ባለው በአውሮፓ አስከ ህዳሴው (Renaissance) ዘመን ብንወሰድ አንድ መሪ ማወቅ አለበት ተብሎ የሚታሰበው የጦርነትን ጥበብን (The Art of War) ማወቅ የነበረበት ሲሆን በዛን ግዜ በነበረው የአለማችን ሁኔታ የብዙ ሀገሮች እንዲሁም መሪዎች እና የነገስታት ህልውና እሚወሰነው በጦርነት በሚያመጡት ድልና ሽንፈታቸው የነበረ በመሆኑ ነው ። ነጋሲዎችና ልጆቻቸውም በቤተመንግስት ውስጥ በአብዛኛው እሚሰጣቸው ስልጠናም ይኀው የጦርነት ጥበብ እና ስልት ነው ። በርካታ የዘመኑ ምሁራንም በዚሁ በጦርነት ጥበብ ጉዳይ ላይ በርካታ ድርሳኖችን አበርክተዋል ። ለዚህም አይነተኛ ምሳሌዎች ቻይናዊው ሱን ዙ ፣ ቮን ክላሽዊትዝ እና በጦርነት ጥበብ ላይ አሁንም ድረስ እሚሰራባቸውን በርካታ ሀሳቦችን አመንጭተዋል ። 

አሁንም ቢሆን ባለችው አለማችን ከምጣኔ-ሀብት በፊት የሚቀድመው ደህንነት መሆኑ ግልፅ ነው ። አንደ አገር ራሱን መከላከል ከቻለ ብቻ ነው በኢኮኖሚ ሊያድግ የሚችለው ፤ የራሱን ደህንነት ማስጠበቅ ያልቻለ ሐገር ስለኢኮኖሚ እድገት ሊያወራ አይችልም ። እነ አሪስቶትልን የመሳሰሉ የጥንት ግሪካውያን ፍለፍልስፍናን፣ ህግን ከምጣኔ-ሀብት ያስቀድሙ ነበረ ። ምጣኔ-ሀብትን በኤቲክስ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ከተውት የነበረ ሲሆን ይህም በነጋዴ በስነ-ምግባር የታነፀ መሆን አለበት ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው ። አብዛኛውን የዘመናዊውን አለም የንግድን ስርአትን መሰረት የጣሉት የጥንት አይሂደሁዳውያን ናቸው ፡። ንግድ እንደ ዝቅተኛ ስራ በሚታይበት ዘመን ሐገር አልባ የነበሩት አይሁዳውያን የአክስዮን ገበያን ፣ የአክስዮን ደረሰኝ ፣ ዘመናዊ ባንክን የመሳለሰሉትን የንግድ አሰራሮችን የፈጠሩት እነሱው ናቸው ።


በሀገራችንም ብንወስድ አመራርን የሚያስረዳው መፅሀፍ ፍተሐ - ነገስት ሲሆን ዝርዝር የአመራር መንገዶችን አለማዊም መንፈሳዊም መንገዶችን የሚጠቁም ሲሆን ፤ የጥንት አባቶቻችን ስለ አስተዳደር ምን ያህል ትኩረትን ይሰጡት እንደነበረ የሚያሳይ ነው ። ነገር ግን ፍትሐ - ነገስት ለብዙሀኑ ህብረተሰብ እንደ አሁኑ ዘመናዊ ትምህርት የሚሰጥ ሳይሆን የነገስታት ልጆች ብቻ ራቅ ብለው የሚማሩት ነበር ይባላል 1።  


ቀደም ያሉት የአውሮፓ ፀሀፍትም መሪዎች እንደ ሰውም እንደ አውሬም መሆን አለበት ሲሉ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ። ይህም በዘመኑ የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነትና መተላለቅን  ፣ ከኛው ዘመነ መሳፍንት ጋር የሚመሳስሰል የእርስ በእርስ የማያቋርጥ ግጭቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው እና ለዛም ነገስታትና መሪዎች ራሳቻቸውን ከጥቃት መከላከል አለባቸው ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው  ።


በአሁኑ በአለም በየትኛውም ሀገራት ያሉ የአለም ህዝቦች ዋነኛው ጥያቄያቸው ምጣኔ - ሀብት ሲሆን ፤ እንደ ቀድሞው ሌላ ሀገር ላይ ጦር ለማዝመት ፣ ወይም የሌላን ሀገር ግዛት ለመያዝ የሚታሰብበት ዘመን አብቅቷል ማለት ይቻላል ። አለም እርስ በእርስ የተሳሰረች መሆኗንም በመረዳት በአንዱ ሀገር የተፈጠረ ችግር ለሌላውም የሚተርፍ መሆኑ በአለም ህዝብ ዘንድ ግንዛቤ ተይዟል ። ስለዚህ በአንደኛው መጎዳት ሌላው የሚያተርፍበት ሁኔታ በአሁኗ አለማችን ተቀባይነቱ እየቀነሰ መቷል ። የሀገራት መሪዎችም እንዲሁ በአንዱ ሀገር የሚፈጠር የምጣኔ - ሀብት ችግር ወደ እነሱም ሊመጣ እንደሚችልና ለዛም ዝግጅት ማድረግንና ሊተላለፉ የሚችሉ ችግሮችን መረዳትና ለመቋቋም የሚያስችል እርምጃን መውሰድ የሚያስችል አቅምን መፍጠር ይኖርባቸዋል ።


አሁን ባለችው ግን አለማችን ሀገሮች ከውጭ እስካልተወረሩ ድረስ ፣ ጥቅማቸውን በጦርነት የሚያስከብሩበት ጊዜ አይደለም ። ግዙፍ ወታደራዊ አቅም ያላቸው ሀያላን ሀገራትም ጭምር ይሄን ቢያደርጉ የሚያስከትለውን አንድምታ በአግባቡ ይረዳሉ ። ይህ ብቻ ሳይሆን እርስ በእርሷ በብዙ ነገር ይበልጥ እየተሳሰረች በሄደችው አለማችን ወታደራዊ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፤ እውቀት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት በሀገራት መሀከል ጦርነቶች ቢካሄዱ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳትና እና ውድመት መገመት አያስቸግርም ።


ያ ብቻ ሳይሆን የምእራብ አገራት በተለይም በእዳ ውስጥ የተዘፈቁት ሀገራት እንደ ቀድሞው በጀት መድበው መደበኛ ጦርነትን ለማድረግ የሚያስችል ፣ እንዲሁም ግዙፍ ወታደራዊ አቅምን የሚያንቀሳቅስ አቅም የሌላቸው ሲሆን በአብዛኛው በአለም ዙሪያም ለዚህ አይነት ጦርነቶች የህዝብ ድጋፍ የለም ማለት ይቻላል ። 

ከዚያ ወዲህ ባለው ጊዜያቶች ግን የጦርነት አመራር፣ የወታደራዊ ስልትና ስትራቴጂ እውቀት ወዳላቸው ጄኔራሎችና የጦር መሪዎች ሲተላለፍ የፖለቲካ አመራሩ ግን ወደ ፖለቲከኞች ተዛውሯል ። አንድ ሀገር ወረራ ወይም ጥቃት ቢያጋጥመው ከፖለቲከኞች የሚጠበቀው አመራር የመስጠት ሲሆን ወደ ተግባር እሚያሸጋግሩት ግን የጦር አዛዦች ናቸው ። የአሁኑ የፖለቲካ መሪው እንደ ቀድሞ በሜዳ ላይ እሚደረጉ የጦርነት ስልቶችን ማወቅ አይጠበቅበትም ።


ነገር ግን ዶላር ከአለም ምጣኔ - ሀብት መድረክ ላይ ቀስ በቀስ እየወረደ ሊሄድ ይችላል ። ለምሳሌ ቻይናና ጃፓን በአመት ወደ 350 ቢሊየን ዶላር የሚገመተውን ንግዳቸውን ቀድሞ በዶላር አማካይነት ያካሂዱ የነበረ ቢሆንም በ2011 ግን ንግዳቸውን በቀጥታ በየራሳቸው ገንዘብ ለማካሄድ ወስነዋል ። ዶላርን ገዝተው ያካሂዱ በነበረው ንግድ የውጭ ምንዛሬውን ለመግዛት ገንዘብ ያስወጣቸው የነበረ ሲሆን ፣ አሜሪካ ገንዘቧ የአለም ኢኮኖሚ መገበያያ መሆኑ ለራሷ ለአሜሪካ ትልቅ ጥቅም እንዳለው ይታወቃል ። ነገር ግን ሀገሮች በእንዲህ አይነት መንገድ በየራሳቸው ገንዘብ ንግዳቸውን የሚያካሂዱ ከሆነ የዶላርን ተፈላጊነት እና ዋጋውን እያወረደው እንደሚሄድ ግልፅ ነው ።


ምሳሌ ብንወስድ ፣ ስታር ባክስ በአንድ ፓውንድ 3 ዶላር ገዝቶ በ13 ዶላር ነው የሚሸጠው በጥሬው የገዛውን ቡና በዚህን ያክል ዋጋ ነው ለገበያ የሚያቀርበው ። ምንም እሴረት ያልተጨመረበትን ቡና በጥሬው ከሀገራችን ገዝቶ የዚህን ያክል ያተርፍበታል ።



እ.ኤ.አ ከ2008 የአለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ አውሮፓውያንን ብንወስድ ለምሳሌ እ.ኤአ. በ2011 ግሪክና ጣሊያን በእዳ ውስጥ በተዘፈቁበት ወቅት  በህዝብ ያልተመረጡ ነገር ግን ምጣኔ - ሀብት  ባለሙያ ሆኑ ባለሙያዎች (Technocrats) ወደ ስልጣን የመጡበት ሁኔታ ነበረ ። ቀውሱ በጣም አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ በፓርቲዎች ስምምነት ፣በጣሊያን ሲልቪዮ ቤርሎስኮኒን ፣ እንዲሁም በግሪክ ጆርጅ ፓፓንድርዩን የተኩት የምጣኔ  - ሀብት ባለሙያ የሆኑ ነገር ግን በቀጥታ በህዝብ ያልተመረጡ ፣ ነገር ግን በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የሰሩና በምጣኔ - ሀብት ጉዳዮች ላይ እውቀትና ልምድ ባላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተተክተዋል ። ጉዳዩ በጣም አሳሳቢና መፍትሄን የሚሻ ከመሆኑ የተነሳ የፖለቲካ ስርአቱም ጭምር ለባለሙያዎቹ ስልጣኑን የለቀቀበት ሁኔታ እስከመፈጠር ደርሷል ።
 


ሌላው ደግሞ የአሁኗን አለማችንን የሚገልፀው ጉዳይ የበርካታ ሀገራት ህዝቦች ውስጣዊ ነፃነታቸውን ለመቀዳጀት ፣ ሙሉ የሆነ የዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ከመጎናፀፍ እያደረጉ ያሉት ትግል ሲሆን ፣ የውጪ ጠላትን ከመቋቋም ባልተናነሰ ከውስጥ የሚነሱ አምባገነኖችን መታገልም አንዱና ዋነኛው የዘመናችን ዋነኛው የትግል መስክ ነው ። እ.ኤ.አ በ2012 ዓ.ም. በተለይ በአረብ አገራት ከታየው ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች መረዳት እንደሚቻለው ጦርነት የሚካሄደው ከውጪ ወራሪዎች ጋር ብቻ አይደለም ። ለዘመናት በህዝቡ ላይ ተቀምጠው የቆዩ አምባገነኖችንም ለመጣል ጦርነቶችን ሊካሄዱ እንደሚችሉ ፣ በሰሜን አፍሪካ በሊቢያ በጋዳፊ ፣ በየመን ፣ በሶርያ የታዩት ስኬታማ እንቅስቃሴዎች አመላካች ናቸው ።    



ሌላው በአለም አቀፍ ደረጃ በአለማችን ሀገራት ላይ ያለው ፣ የሀገራት እርስ በእርስ ትስስር መጨመር ሲሆን ፤ ይህም በሉላዊነት ዘመን በግልፅ የሚታይ ጉዳይ ሲሆን ፣ «ሁላችንም በአንድ ጀልባ ላይ ነው የተሳፈርነው» የሚል አባባል አለ ። ይህም በአለማችን ላይ በአንዱ አካባቢ የሚፈጠር ችግር ወደ ሌላውም የአለም ክፍል በቀላሉ ሊስፋፉ እንደሚችል ለመረዳት የሚያስችል ሲሆን ፣ በአለም ላይ የምናያቸው ችግሮችም ሆኑ መልካም አጋጣሚዎች ወደ ተቀረው የአለም ክፍል በቀላሉ ይስፋፋሉ ፤ ለምሳሌም የሚሆነው የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ለመላው አለም ችግር ሲሆን ፤ ሌሎችም ችግሮች  እንደዛው በፍጥነት ይሰራጫሉ ።    



እዚህም እዚያም በርካታ የአለም አቀፍ ምሳሌዎች የገቡበት ምክንያት ስለ ሀገራችን ለመረዳት አለምንም መረዳት ጠቃሚ መሰረት መሆኑን በማመን ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅት አገራዊ የሆኑ ችግሮች አንዳንዶቹ አለም አቀፋዊ ዳራ ያላቸው ናቸው ። ለምሳሌ የዋጋ ግሽበትን ብንወስድ መነሻው ከአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአለም አቀፋዊ ካለው የዋጋ ጭማሬም ጭምር ነው ።



አለም አቀፋዊ ቴክኖሎጂዎችም ስላሉ አሁን የአለም ህዝብ ያለው ግንዛቤ ጨምሯል። በአለም ሀገራት መሀከል ያሉ ትስስሮች እየጨመሩ ስለሆነ አለም አቀፋዊ የሆነውን ተጨባጭ ሁኔታ መረዳት ለብዙ ምጣኔ - ሀብታዊም ሆነ ፖለቲካዊ እውነታዎችን ለመረዳት ያስችለናል ።



ለምሳሌ የአለም ምጣኔ - ሀብት ባደጉት ሀገራት መሀከል ብቻ ሳይሆን ፣ ብቅ ብቅና እየጎለመሱ ያሉ (Emerging) በመባል የሚታወቁት ሀገራትም ጭምር ያላቸው ትስርስር መጨመሩንና ፣ ከቀን ወደ ቀን በአለም ምጣኔ - ሀብት ላይ ያላቸው በጎም ይሁን አሉታዊ ተፅእኖ በመጨመር ላይ ይገኛል ። ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ2008 ዓ.ም. ተከስቶ በነበረው የአለም ምጣኔ - ሀብት ቀውስ ፣ የምእራብ ሀገራትን ካሉበት ቀውስ እንዲወጡ ያስቻላቸው የቻይናና እንዲሁም የሌሎች ብሪክስ በመባል የሚታወቁት ሀገራት ምጣኔ - ሀብት በእድገት ላይ ስለነበረ የተፈራው የምጣኔ - ሀብት ዝቅጠት (Depression) ቀርቶ ከአጭር ጊዜ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ (Recession) በኋላ እንደ ቀድሞው ባይሆንም ምጣኔ - ሀብታቸው ሊያገግም ችሏል ።



በተመሳሳይም በ2011 ተከስቶ በነበረው የአውሮፓውያን የእዳ ቀውስ ምክንያት አውሮፓውያን መጀመሪያ ላይ ቻይና ባላት ግዙፍ የውጭ ምንዛሪ ተቀማጭ ምክንያት ድጋፍ ልታደርግልናንና ገንዘብ ልታበድረን ትችላለች ብለው ቢጠብቁም ቻይና በማንገራገሯ ፣ እና አሜሪካም አቅሟ የደከመበት ጊዜ ስለነበረ ፣ የላቲን አሜሪካ ሀገራትም እንዲሁ ያን ያህል አቅም የሌላቸው በመሆኑ ፣ ወደ አፍሪካ አይናቸውን በማማተር አፍሪካ የአለምን ምጣኔ - ሀብት ከገባበት ቀውስ ላልታወጣ ትችላለች እስከማለት ደርሰዋል ፣ ቀድሞ በችግርና የምትታወቀው የአፍሪካ አህጉር ለዚህ መታሰቧ ራሱ የደረጃዋ መሻሻል ነው ሊባል ይችላል ፣ ይህም የአለም ምጣኔ - ሀብት ትስስር ደሀ ይባሉ የነበሩትን ሀገራትንም ጭምር እያካተተና ሀገራት ተፅእኖንና ተደማጭነት እያገኙ እንደሚሄዱ መገመት ይቻላል ።      



አሁን ባለው የአለማችን ሁኔታ ግን የየትኛውም ሀገር መሪ የሆነ ሰው ቢያንስ የምጣኔ - ሀብት መሰረታዊ ሀሳቦችን በሚገባ እሚረዳ መሆን አለበት ። የብዙ በተለይም ያደጉ ሀገራት ችግሮች በሀገር ውስጥ የምጣኔ ሀብትን እድገት ማስቀጠል፣ ስራ አጥነትን ፣ የዋጋ ግሽበትን መግታት ፣ የመሳሰሉት ፈተናዎች ናቸው ። ቀድሞ በነበረው አለም ግን የቅኝ ግዛትን መያዝ ፣ ግዛትን ማስፋፋት የመሳሰሉት ከጦርነት ጋር የተያያዙ ፈተናዎች የነበሩ ሲሆን ፤ የአሁኑን አለማችንን ለመረዳት መሰረታዊ የሆኑትን  የምጣኔ - ሀብት መርሆዎች መረዳት ጠቃሚ  ሲሆን የምጣኔ - ሀብት ምንነትን መረዳት ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ አስፈላጊነቱ እየጨመረ የመጣበት ጊዜ ነው ።

ነገር ግን ይህ ብቻ ሳይሆን ዋናውም ማህበረሰብ የምጣኔ - ሀብትን ህግጋቱንና አካሄዱን መረዳት ዝንባሌ ቢኖረው ጥሩ ሲሆን ባደጉት ሀገራት ሳይቀር ያለው ማህበረሰብ ትኩረቱ በጎላ ብለው በሚታዩ ዋና ዋና የፖለቲካና የምጣኔ - ሀብት ጉዳዮች ላይ ነው እንጂ በምጣኔ - ሀብታዊ ጉዳዮች ላይ አይደለም ። ጥቂቶች የተማሩ ሰዎችና መሪዎች ብቻ የሚያውቁት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ሌላውም ማህበረሰብ ሊረዳው የሚችል ጉዳይ ነው ። እንደሚታሰበውም በጣም ረቂቅ ሙያዊ (Technical) አይደለም ።

ብዙሀኑ ህብረተሰብ የምጣኔ-ሐብት አሰራሮችን መረድዳት ቢችል የሰፋ የህሀቦ  ብት ልዩነት እንዳይኖር ፣ ንብረት በጥቂቶች እጅ ገብቶ ብዙሀኑ የጥቂቶች አገልጋይ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር እና ፍትሐዊ የሆነ ህብረተሰብ እንዲፈጠር ያግዛል ።

ሰው ለሰው



የህይወት ጥያቄዎች

አንድ ሰው ለምንድነው የሚኖረው ?

የህይወት ፈተናዎች ምንድናቸው ? 


ሰው መሆን ጥበብ

ይብዛም ይነስም ማንኛውም ሰው የሚመራበት የራሱ የሆነ የህይወት ፍልስፍና ፣ አስተሳሰብ ፣ አመለካከት አለው ። ህይወታችን ራሱ የአስተሳሰባችን ነፀብራቅ ነው ። ትክክኛውን ፍልስፍናና አመለካከት የያዘ ሰው በህይወት ውሰጥም መርሁ እየሰራለት በስኬት ላይ ስኬትን እየደራረበ ሲሄድ ፣ በአንፃሩ ግን በህይወት ውስጥ ትክክለኛውን ጎዳና ያልያዘ ሰው ግን ወደ አዘቅቱ እየገባ ሲሄድ መመልከት የተለመደ ነው ። ፍልስፍና በህይወታችን ውስጥ ከምናስበው በላይ የተራሱ በጎም ይሁን አሉታዊ ተፅእኖና አሻራ አለው ። ለምሳሌ የምናምንበትን ሀይማኖት ብንወስድ ከታላላቅ ፈላስፎች አለማዊም ሆነ መንፈሳዊ ከሆኑ የሚነሱ በርካታ ፍልስፍናዎች የተደገፈ ሲሆን ፣ ያም እምነት በህይወታችን ፣ በአኗኗራችን ላይ በየቀኑ ሲንፀባረቅ ማየት የተለመደ ነው ።    
      በዚህ ጉዳይ ላይ የተፃፉ ፅሁፎች በአብዛኛው አለም እንዲህ መምሰል አለባት ፣ እንደዚህ መሆን አለባት ፣ ስለዚህ እንደዚህ መሆን አለበት የሚሉ ሲኖሩ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አለም እንደዚህ ነች ፣ አለም ይህቺ ነች በቃ የሚሉም አሉ ። የሁለቱን ልዩነት መረዳት ያሻል ። ለምሳሌ ስነ - ምግባርን ብንወስድ በውስጡ በርካታ የግብረ - ገብ ህግጋት አሉት ፣ ራሱ ስነ - ምግባር ከጋርዮሽ ጀምሮ የነበረ አስተምህሮ ሲሆን ፣ ነገር ግን ገሀዳዊው አለም ግን ከእነኚህ ህግጋት አፈንግጦ ማየት የየእለት ትእይንታችን ነው ። ምንም እንኳን የስነ - ምግባርና የግብረ - ግብ ፈላስፋዎች የተለያዬ ነገርን ቢሉም በተግባር ግን እነሱ የሚሉት ሲጣስ የየእለት ትእይንታችን ነው ።   
     ሳይንስ እንደየ አመለካከታችን ሊተረጎም የማይችል «Objective» የሆነ ነገር ስለሆነ ለሁሉም ጥያቄዎች ምላሽን አይሰጥም ። ሳይንስ በአመክንዮና በህልዮት ላይ የተመሰረተ ነው ። በማህራዊ ሳይንስ እነኚህ ነገሮች ሊሰሩም ላይሰሩም ይችላሉ ። በመሆኑም ማህበራዊ ሳይንስ ከላይ ሲታይ ቀላል ቢመስልም ይበልጥ ውስብስብና አስቸጋሪ ነው ። ሳይንስ ተጨባጭ በሆኑ እውነታዎች ላይ የተመሰረተ ነው ። ሆኖም ሳይንሳዊ እውነታዎች አይለወጡም የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊትም የነበሩ ናቸው፣የሚሰሩትም በመሬት ላይ ብቻ ሳይሆን ለመሬት ውጪ  በህዋው እና በአፅናፈ - አለም (Universe) ውስጥ ጭምር ይሰራሉ ። በዚህ አያያዝ ከሄደ የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታ ያለው ስለሆነ እና ንቃተ - ህሊና ያለው ፍጡር ስለሆነ በጊዜ ሂደት በርካታ ሳይንሳዊ ሚስጥር የነበሩ ነገሮች እየተገለፁና እየተብራሩ መሄዳቸው አይቀሬ ነው ። 
          ሳይንስ ዋናው ስራው ጥያቄዎችን መመለስ ሳይሆን ጥያቄዎችን መጠየቅ ነው ። ስለዚህ ሳይንስ የማይቆም ሲሆን ፣ የሳይንስ አላማውም ተፈጥሮን የመቆጣጠር ሂደት ነው ። ምንግዜም ቢሆን አዳዲስ ምርምሮች ፣ አዳዲስ ይሄ ለምን እንደዚህ ሆነ የሚሉ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ - የአይቆሙም ። በአንፃሩ ሀይማኖት መጠየቅ ሳይሆን መመለስ ነው ። በርካታ ታላላቅ አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶች በአለም ላይ ተገኝተዋል ፣ እየተገኙም ነው ። ነገር ግን ለምሳሌ አሁን በቅርቡ ሂክስ ቦዞን ወይንም የእግዜር ቅንጣት በመባል የሚታወቀውን ሂክስ በተባለው እንግሊዛዊ ሳይንቲስት በ 1965 ዓ.ም. ሊኖር የችላል ብሎ የገመተውን በ2012 ዓ.ም. በስዊዘርላንድና በፈረንሳይ ድንበር መሀከል በሚገኝ ላብራቶሪ ውስጥ በምርምር ደርሰውበታል ። ነገር ግን አዳዲስ ግንኝቶች ሲገኙ የሀይማኖት ሰዎችና ፣ በሀይማኖት የማያምኑ ወይንም በእግዝአብሄር መኖር በማያምኑ ሰዎች መሀከል የተለያዩ አመለካከቶች ይንፀባረቃሉ ። አንዳንዶቹ ይህ የእግዝአብሄር መኖር ማረጋገጫ ነው ሲሉ ፣ ሌሎቹ ደግሞ የለም ይህ የእግዝአብሄር አለመኖር የበለጠ ማረጋገጫ ነው በማለት ይከራከራሉ ።

     የሰውን ልጅ የታሪክ አካሄድ ልብ ብለው የታዘቡ የታሪክና የፍልስፍና ባለሙያዎች፣ የሰው ልጅ አደገኛ ወደ ሆነው የታሪክ ምእራፍ እየገባ ነው ይላል ። እንደ ሀውኪንግስ አባባል ከሆነ በመሆኑም ሌሎች ፕላኔቶችን መፈለግና በእነሱ ላይ መስፈር (ኮሎናይዝ) ማድረግ አለበት ባይ ነው ። ምድርን አደገኛ የሚያደርጓት እንደ አካባቢ አየር መበከል ፣ የኒውክሊየር ጦርነት ስጋቶች ፣ የመሳሰሉት ናቸው ።

       በዚህች ምድር ላይ በርካታ ባለቤቶች ነበሯት ። ከ60ና ከ70 ሚሊየን አመታት በፊት ዱይኖሰሮችና መሰል ግዙፍ እንሰሳት የዚህች ምድር ባለቤት የነበሩ ሲሆን አሁን ደግሞ ተራው የሰው ልጅ ሲሆን ራሱ በፈጠረው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ራሱን ካላጠፋ ።

ይሁን እንጂ በአጠቃላይ ሳይንሳዊ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት የሰው ልጅ ከእርሱ እጅግ የገዘፈና ሀያል የሆነ አለም አካል ነው ። ነገር ግን እስካሁን ድረስ በዚህ ስርአተ - ፀሀይም ሆነ በአፅናፈ - አለሙ ውስጥ ከተፈጠሩት ፍጥረታት ሁሉ ማሰብ የሚችለውና ህሊናዊ ንቃት ያለው ፍጡር የሰው ልጅ ብቻ ነው ። ስለሆነም ራሱን ከተቀረው አለም ጋር አስማምቶ ማኖር ይችላል ። የሰው ልጅ እንደ ዘርም ጭምር እነኚህን የአፅናፈ - አለሙ ህግጋት ሊረዳቸውና ለህልውናው ሲል ሊጠብቃቸው የሚገቡ ናቸው ፣ እንጂ ሊቀይራቸው የሚችላቸው አይደሉም ። ሳይንቲስቶች እንደሚነግሩን እነኚህ ህግጋት የተፈጠሩት ጊዜ ከተፈጠረ ጀምሮ ነው ተብሎ ይታመናል ። ይህ ማለት የሰው ልጅ ራሱ ከመፈጠሩና ፕላኔቶችና ፀሀይም ጭምር ከመፈጠራቸው ጀምሮ እነኚህ ህግጋት ነበሩ ወደ ፊት ከሰው ልጅ ህልውና በኋላም ይኖራሉ ።


    አብዛኛው ሀይላችን የሚገኘው በምናደርገው ነገር ውስጥ ሳይሆን ፣ በማናደርገው ነገር ውስጥ ነው ። ኒቼ ይህንን ሀሳብ አንፀባርቋል ። ሀይል ወይንም የምንፈልገው ማንኛውም ነገር በአለም ላይ በብዛት ያለ ሲሆን አንድ ቦታ ብቻ ያለ ነገርም አይደለም ። በአገርኛው አባባል እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል እንዲሉ ፣ በሌላ ቦታ ያን ነገር በበለጠ ልናገኘው እንችላለን ፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሰዎች ያን ነገር ለማግኘት አስቸጋሪ በሆነ ቦታ ላይ በአንድ ቦታ ላይ ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ያጠፋሉ ። ያም ሆኖ ግን እኛ ሰዎች መጨረሻ ላይ ተሸናፊዎች ነን ። ብዙ ብንታገልም መጨረሻ ላይ ግን ሽንፈትን መከናነባችን አይቀርም ።

     ማታለል አንድ ሰው በራሱ የሚፈልገውን ነገር ለማግኘት ብቃት እንደሌለው ያለመክታል ። ብዙ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች መድረስ የሚፈልጉበት ደረጃ መድረስ ላይ የማይችሉ ሰዎች የሚፈልጉበት ደረጃ ለመድረስ ማታለል አቋራጭ መንገድ አድርገው ይቆጥሩታል ። ሆኖም ግን ብዙም ርቀት መሄድ ሳይችሉ ይቀራሉ ። በሌላ በኩል አታላይ የሆነ ሰው የእውነትን ዋጋ ያልተረዳ ነዉ ። ቻይናዊው ፈላስፋ ሜንሲየስ  እንዳለው ።

    ሰዎች ችግር ውስጥ ሲገቡ አይታወቃቸውም ። ሆኖም ግን ቀስ እያሉ እየሰመጡ ይሄዳሉ ። አንዴ ከሰመጡና ከዘገየ በኋላ ሙሉ በሙሉ ይነቃሉ ። ከባድ የሆነ ችግር በተለይ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ። እዚህ ጋር እድልም የራሱ ሚና አለው ። በእድል አንዳንድ ጊዜ ከባድ የሚመስለን ችግር በቀላሉ ይወገዳል አንዳንዴ ደግሞ ቀላሏ ነገር ወደ ከባድ ችግር ትለወጣለች ።  

ስኬታማ ለሆነ ኑሮ ተግባራዊ የሆነ የህይወት ልምድ ያስፈልጋል ። በተለይም በርካታ ችግሮችን ያሳለፈ ሰው ችግሮች አስቀድመው ሊፈጠሩ ሲሉ አስቀድሞ ማየት ይችላል ። በአለም ላይ አይሁዳውያን በርካታ ችግሮችን አሳልፈዋል ። ከትምህርትና በማንበብ እውቀትን ከመሰብሰብ ውጪ አንድ ሰው በህይወት ውስጥ ተሳታፊና በመሆን የህይወት ልምድን ሊቀስም ይችላል ። ብዙ ጊዜ ሰዎች አንድን ነገር ከላይ የሚያዩረትን ነገር እውነት አድርገው ነው እሚቀበሉት ። ሆኖም ግን ወደ ውስጥ ሲገባና ከላይ ሲታይ የተለያየ መሆኑን አይረዱም ።

         አለማወቅ ራሱ ሰዎች ደስተኛ ሆነው እንዲኖሩ የሚያስችል ነገር ሲሆን ፣ ከተማሩ ሰዎች ይልቅ ያልተማሩ ሰዎች ደስተኛ ሆነው እሚገኙበት ጊዜ አለ ። እውቀት ብዙውን ጊዜ ከነገሮች ጋር ያለንን ትስስርን ስለሚፈጥር ፣- ማወቅ ትስስርን ይፈጥራል ስለዚህ- የሰዎችን ደስታ ይቀንሳል ።

       በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ልሂቃን የሚባለው የህብረተሰብ ክፍል የሚሆኑት ሰዎች ለመምራት የሚያስፈልገውን እውቀትን የሰበሰቡና ተግባር ላይ የሚያውሉ ናቸው ። ብዙሀኑ ህብረተሰብ ክፍል ይህንን እውቀት ሊያሰባስብ ሳይችል ሲቀር ጥቂቶች ግን የሄን ማድረግ የቻሉ ግን በማህበረሱ ላይ ከፍ ያለ ቦታን ይይዛሉ ።

             የሰው ልጅ ጥረት ለራሱ ያለውን ስሜት (Ego) ማርካት ነው ። ሰዎች ትልቅ ስልጣንን ፣ ብዙ ሀብትን በማግኘት ወይም ባለቤት በመሆን ራሳቸውን ትልቅ በሚሉት ቦታ በማዋል ለራሳቸው ያላቸውን አመለካከት ለማርካትና ስሜታቸውን ለማስደሰት ይመጥራሉ ። ነገር ግን እነኚህ ሁሉ ነገሮች በጊዜ ሲያልፉ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በነው ሲጠፉ ሊያዩም ይችላሉ ። ሰዎች ብዙውን ግዜ በጣም ሲቆለማመጡ (Flatter) ሲደረጉ ይቀበላሉ ። ይህም ላላቸው ቦታ ሌሎች ሰዎች እንዲቀበሏቸው ከመፈለጋቸው የተሳ ብዙውን ግዜ በስልጣንና በሀብት ያሉ ሰዎች ይህንነን ይፈልጉታል ለዚህም ምክንያቱ የሌሎች ሰዎችን ተቀባይነትን ለማግኘት ካላቸው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ነው ።  

            አንዳንዴ ሲታሰብ ማንኛውም ነገር በሚያልፍበትና በሚረሳበት አለም ለነገሮች ያን ያህል ክብደት መስጠት አስፈላጊ አይደለም ያስብላል ። ለምሳሌ ዛሬ በጣም ትልቅ ቦታን የምንሰጠው ነገር ነገ ከነገ ወዲያ የሚረሳና ብሎም የሚወገዝ ሁሉ ሊሆን ይችላል። ዛሬ እውነት ነው ፣ ትክክል ነው የምንለው ነገ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ውሸት ነው ሊባል ይችላል ። ብዙ ሰዎች ግን ዛሬ እውነት ነው ፣ ትክክል ነው ለሚሉት ነገር ሊሞቱለትና ለገድሉለት ዝግጁዎች ናቸው ይሁን እንጂ ያ ነገር ፍፁም ትክክል ስለመሆኑ በበቂ የሚያውቁት ነገር የለም ፣ ወይም ዛሬ ትክክል ነው ቢባልም ነገ ከነገ ወዲያ ጥፋት ሆኖ ሊገኝ ይችላል ። በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚ የታየ ሀቅ ሲሆን ። ስፒኖዛ የተባለው ታላቁ የሆላንድ ፈላስፋ በተደጋጋሚ የሚጠቀስለት አባባል እንዳለው «እውነት የራሷም ፣ የሀሰትም ማስረጃ  ነች» ብሏል ።

             አንዳንድ ሰዎች በተቋም ደረጃ ሊሆኑ ይችላሉ ። በራሳቸው በችሎታቸው ፣ በስብእናቸው እና በአቅማቸው እንደ አንድ ተቋም ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች አሉ ። በአብዛኛው ሰዎች ቁሳዊ ነገርን በመፍጠር በኩል ነው የህይወታችንን አብዛኛውን ዘመን የምናሳልፈው ማለት ይቻላል ፣ የአብዛኛው ሰዎች ጥረትም በዚሁ ዘርፍ ሲሆን  ። ነገር ግን ቁሳዊ ነገርን ከመፍጠር አልፈው ለሰው ልጅ ብርሀንን የቀደዱ ፣ ለሌላው ብርሀን የሆኑ ሰዎች በመቶዎች ከሚቆጠሩ አመታት ውስጥ በጣት የሚቆጠሩ የዛ አይነት ሰዎች ናቸው የሚገኙት ቢባል ማጋነን አይሆንም ።

             ማንኛውም በተፈጥሮ ሲሆን በሰዎች የተፈጠረ ነገር በሰዎች በቀላሉ ሊፈርስ ይችላል ። ለምሳሌ ሀገርን ብንወስድ በሰዎች የተፈጠረ ነገር ሲሆን ተፈጥሮ አህጉራትን ሲፈጥር ሰዎች ደግሞ አህጉሩን ተከፋፍለው ከዚህ እስከዚህ ድረስ ያንተ ከዚህ መልስ የኔ ብለው ነው ሀገር የምንለው ነገር የተፈጠረው ። ስለዚህ ይሁን እንጂ ሀገር ማለት ደግሞ የዛ ሀገር ዜጎች የመኖር ህልውና መሆኑ ደግሞ እማይዘነጋ እውነታ ነው ። በአለም ላይ ሀገር የሌላቸው ሰዎች ምን ያህል እንደሚሰቃዩ ሁላችንም የምናውቀው ሲሆን ያለሀገር የአንድ ሰው ህልውና አይታሰብም ። ይሁን እንጂ ሀገርን ላፍርስ ብሎ አንድ ሰው ቢነሳ ደግሞ ሊያደርግ የሚችለው ጉዳት ቀላል አይሆንም ሀሳቡ ባይሳካም እንኳን ።

               ፍልስፍና በሁለት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ሊታይ ይችላል ። በአንድ በኩል ተቋማትን ፣ መንግስትን ፣ ሀይማኖትን ፣ ከቤተሰብ ጀምሮ ያሉ ተቋማትን በመገንባትና በእነዛ ተቋማት አማካይነት የሰው ልጅ እዚህ ደረጃ ደርሷል ። ነገር በግን እነዚህ ተቋማት ባይኖሩ ኖሮ የሰው ልጅ ስልጣኔ፣ የቴልክኖሎጂ ግስጋሴና እመርታ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ አይችልም የነበረ ሲሆን ። በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ሰዎች በየትኛውም ትውልድና ሀገር ውስጥ ይገኛሉ ። ነገር ግን እውቀትን ለማሰባሰብ ፣ አዳዲስ ነገሮቸን ለመፍጠር ሰዎች በጋራ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤትን ይሰጣል ። አንዱ አይነት አካሄድ አለምን እንደዚህ ነች ብሎ መግለፅና ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አለም እንደዚህ መምሰል አለባት ወይንም እንደዚህ መሆን አለባት የሚል ነው ። ፕሌቶ የኔ ማስወታወሻ በመጪዎቹ ትውልዶች ውስጥ የሚኖረኝ የባለውለታነት ሰሜት ነው ብሏል ።

                    መፈላሰፍ፡- ሁለንተናዊ ተሞክሮ
        
ያም ሆነ ይህ እኔ የምለው የአንድ ሕዝብ ፍልስፍና ያንን ፍልስፍና ከሚያቀነቅኑት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመራማሪዎች ጋር ጥቂት ወይም ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም ነው፡፡ መፈላሰፍ ሁለንተናዊ ወይም ዓለምአቀፋዊ ተሞክሮ ነው፡፡ እያንዳንዱ ባህል የራሱ የሆነ አመለካከት አለው፡፡ የፍልስፍና ታሪክ ካጠናችሁ የምትገነዘቡት ነገር ቢኖር የፍልስፍናን ትርጉም በተመለከተ ምንም ዓይነት ስምምነት እንደሌለ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ፍልስፍና የእውቀት ፍቅር ነው ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እውነትን መፈለግ ነው ይላሉ፡፡ የተቀሩት ደግሞ የመደነቅ ስሜት ነው ይላሉ፡፡ በአጠቃላይ ፍልስፍናን በተመለከተ የተደረሰበት ስምምነት ቢኖር በዙርያችን ባለው ዓለም ውስጥ በተለያዩ ክስተቶች አንፃር ሥርዓትን ለማስፈን መሞከሩ ነው፡፡ እነዚህ የተለያዩ ክስተቶች ምንድናቸው? ነገሮች፣ ድርጊቶች፣ ክንዋኔዎች፣ ልንረዳው የምንችለው ዓለም፣ ሥነ ምግባራዊ ዓለም እንዲሁም ሜታፊዚካዊው ዓለም ናቸው፡፡  (ዮሴፍ ቢ፤ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ፈላስፋዎች፣ 2001 ..)

             ፍልስፍና ስለ ሰው የሚያወራ እንደመሆኑ የሰውን ልጅ ስነ - ልቦናን ማወቅ ለፍልስፍና መሰረት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ።የፍልስፍና ዋና አላማው ምንድነው ቢባል ከላይ እንደተጠቀሰው ስርአትን ማስፈን ነው ። ይህንንም ስነ - ምግባርን በማስረፅ ይሆናል ። ሀሳዊ - ፍልስፍና (ሲዶ ፍልስፍና) በመባል የሚታወቅ ፍልስፍናም አለ ። ነገር ግን ይሄ ፍልስፍና ሃሳዊ በመሆኑ ብዙም አያዛልቅም ። ዋናው የፍልስፍና አላማ ሰዎችን በሰለማዊና ፣ ፍትሀዊ በሆነ ህብረተሰብ ውስጥ እንዲኖሩ ማስቻል ነው ። ለምሳሌ ታላላቅ ሀይማኖቶችን ብንወስድ ዋናው አላማቸው የሰው ልጅ እርስ በእርሱ እንዳይበጣበጥ ፣ ፍትህ እንዳይዛባ በማድረግ ላይ የተመሰረተ ነው ።  ይሄም ፍትህ ባይኖር ፣ ሰላም ባይሰፍን ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ፣ ውድመት ፣ ጦርነትን በመፍራትና ከመምጣቱ በፊት ለማስቀረት ነው ።    

                   የፍልስፍና መሰረታዊ ጥያቄ የሚባሉት ውስጥ አንዳንዶቹን ብንጠቅስ ቁስ አካል ነው ወይስ መንፈስ (Idea) ነው እሚቀድመው? በዚህ ህዋው ውስጥ ከሰው ልጅ ሌላ ህይወት ያለው ህሊና (Conscious) ያለው ፍጡር አለን? የህይወት ትርጉም ምንድነው ? ነፍስ ወይም መንፈስ አለን ካለስ በምን መንገድ ነው ያለው ? የሰው ልጅ ለምን ይሰቃያል? የመሳሰሉት መሰረታዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ሲሆኑ እስካሁን ድረስም የሰው ልጅ ባለው ቴክኖሎጂና በደረሰበት ሳይንስ ቁልጭ ያለ መልስ የተሰጠባቸው አይደሉም ። ለምሳሌ የአሜሪካውን የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳን ብንወስድ ፣ ከአሜሪካ ግብር ከፋዮች በሚሰበሰብ ገንዘብ በርካታ ምርምሮችን በማድረግ ፣ የሰው ልጅ ስለጠፈር ያለውን እውቀት አሳድጎታል ። ቀድሞ ዝንባሌውና ችሎታው ያላቸው ሰዎች ቀደምት ሳይንቶስቶች በመነሳት እንደ እነ ጋሊሊዮ ፣ ኮፐርኒከስ ፣ የመሳሰሉት በግላቸው ምርምርን፣ ጥረትና ስራ በርካታ ፈር - ቀዳጅ ስራዎችን አበርክተዋል ። ነገር ግን አሁን የሰው ልጅ ከዛሬ 5 እና 4 መቶ አመታት የተሻለ ደረጃ ላይ በመድረሱ ምክንያት እነኚህ ምርምሮች በተቋም ደረጃ እድገት ማሳየት ችሏል የሰው ልጅ ስለ እሚኖርበት ጠፈር ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ፣ ኑሮውንም በአንድ እርምጃ ማራመድ ችሏል  

              በፍልስፍና ውስጥ ሁለት አይነት አስተሳሰቦች ምንግዜም ቢሆን ትግልን ሲያደርጉ ይኖራሉ ። አንዱ ያለውን ወቅታዊውን ነባራዊ ሁኔታን ስታተስ ኩን የሚደግፉ እና እርሱ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ሲሆኑ እነኚህም በአብዛኛው ከዛ ስርአት ውስጥ ተጠቃሚ የሆኑ ናቸው ። እነኚህም የፖለቲካ የሀይማኖት ፣ በተለያየ የኢኮኖሚያዊ አመራር ላይ ያሉ ናቸው ። በእርግጥ ስርአቱ ምን አይነት ስርአት ነው የሚለውም ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው ፣ ዲሞክራሲያዊ  በሆነ አመራር ውስጥ ቁንጮ ላይ ያሉ ሰዎች በምርጫ ሊቀያየሩና ፣ አዳዲስ ሰዎች የራሳቸውን አዳዲስ አስተሳሰብ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ ፣ በአንፃሩ ዲሞክራሲ ከሌለ ግን የተወሰኑት ቁንጮነቱን ይዘው አንለቅም ሊሉና ፣ እንዲሁም የመሪነት ህጋዊ ተቀባይነታቸውና ብቃታቸው ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባ በውጥረት የተሞላ ስርአት ሊሆን ይችላል ። 

                በሌላ በኩል ደግሞ ስርአቱ እንዲቀየርና በመሰረታዊነት ልዩነታቸውን የገለፁ ናቸው ለዚህ አይነተኛ ዋቢ የሚሆኑት ማርክስ ፣ ስፒኖዛ ፣ ኔቼ የመሳሰሉት ሲሆኑ ከእነሱ ውስጥም አንዳንዶቹ የተሳካላቸው ናቸው ለምሳሌ እንደ ሉተር ቀዳማዊ አይነቶቹ ሉተር ጂኒየርም ምንም እንኳን በዘመኑ አስተሰሳቡ ስር ነቀል ቢሆንም ውሎ አድሮ የተሳካላቸውም አሉ ለምሳሌ ሁለቱ ሉተሮች ለዚህ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው ።

             ሌሎች የመንግስታት ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ብንወስድ ደግሞ ተመሳሳይ ነው ። በተቃራኒው ደግሞ ብንሄድ እነኚህ ነገሮች ባይኖሩ ኖሮ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ባልተቻለም ነበረ ።

             በፍልስፍና አለም ውስጥ በአንድ በኩል ሓሳዊ - ፍልስፍና (Pseudo-Philosophy) ሲኖር ይህም የእውነት መሰረት የሌለው እና ሊሰራ የማይችል ፍልስፍና ተብሎም ሊጠራ የማይችል ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ሳብጀክቲቭ የሆነ የፍልስፍና አር ዘርፍም አለ ። ይህ ዘርፍ ፍልስፍና ሲሆን ሊሰራ የሚችልም ነገር ነው ። ነገር ግን የሚሰራው ለተወሰኑ ቡድኖች ፣ ልሂቃን ወይንም ከፍተኛ የማሰብ ፣ እና ግንዛቤ ላላቸው ሰዎች ብቻ ይሆናል ። ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት አን ራንድ የተባለችው አሜሪካዊነት አይሁድ ፈላስፋ ፣ የኒቼ ፍልስፍና እንዲሁም እንደ ሮበርት ኪዮሳኪ ያሉ በዘመናችን ያሉ ፀሀፊዎች የጠቆሙት ፣  ከዚህ ዘርፍ የሚመደብ ነው ። ለምሳሌ አን ራንድ የሊበራሊዝም ፍልስፍና መሰረት የሆኑ በርካታ ሀሳቦችን የጠቆመች ቢሆምንም በዋናው የፍልስፈና አስተምህሮ ውስጥ ግን አልተካተተም ።  የኒቼንም ልእለ-ሰብ «Superman» ብንወስድ ሊሰራ የሚችለው በዛ ደረጃ ላሉ ሰዎች ብቻ ሲሆን ፣ ለብዙሀኑ ማህበረሰብ ግን ሊሳራ ሰራ የማይችል ነው ። በነገራችን ካይ ላይ ይህንን ፍልስፍና ናዚዎች ልክ ለብዙሀኑ እንደተነገረ አድርገው ለፖለቲካ አላማቸው ተጠቅመውበታል፣ ነገር ግን በኒቼ ልእለ - ሰብ ማለት ማህበሰረብን ወይንም አንድ ዘርን የሚወክል ነገር አይደለም ፣ በነገራችን ካይ ላይ ይህንን ፍልስፍና ናዚዎች ልክ ለብዙሀኑ እንደተነገረ አድርገው ለፖለቲካ አላማቸው ተጠቅመውበታል ነገር ግን በኒቼ ልእለ - ሰብ ማለት ማህበሰረብን ወይንም አንድ ዘርን የሚወክል ነገር አይደለም ፣ ከዚያ ይልቅ ግን ጥቂት ላቅ ያለ ክህሎት ወይም ያላቸውን ጥቂት ልሂቃንን የሚወክል ነው ።      

            እኔ እኔን የሆንኩት ባንተ ምክንያት ነው የሚል ታዋቂ የደቡብ አፍሪካውያን አባባል አለ ። ይህም የሰው መድሀኒቱ ሰው መነው ከሚለው ሀገርኛ አባባል ጋር ተመሳሳይ ነው ። በብዙ ታላቅ ሀይማኖቶችም እምናገኘው ወርቃማው ህግ ማለትም በራስህ ላይ እንዲሆን እማትፈልገውን በሌሎች ላይ አታድርግ የሚ ል ነው ። አን ራንድ የራስ ወዳድነት ፀጋዎች በሚል የሊበራሊዝም መሰረት የሆኑ ሀሳቦችን አንፀ ባርቃለች ።

ሁላችንም በመጀመሪያ የምንኖረው ለራሳችን ሲሆን ሌሎችን እንምንጠቅመው ከዚያ በኋላ ነው ። አንድ ሰው ማድረግ የሚፈልገውን በራሱ ጊዜና ሁኔታ ማድረግ ሲችል አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ሌሎች ሰዎችን መጠበቅ የለበትም ። ጊዜ እያለፈ ስለሚሄድ ማድረግ የምንፈልገውን ነገር በቅጡና ፣ በአግባቡና በጊዜው ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው ። በተለይም ለወደፊት ህይወታችን ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ትኩረትንና ጥረትን ማድረግ ይጠበቅብናል ። ሌላውንም እኮ ልንጠቅም የምንችለው መጀመሪያ ላይ የራሳችንን ህልውና (Survival) መጠበቅ ስንችል ነው ።

               አለም በአንድ አፅናፈ - አለም አእምሮ ነው የምትመራው ። ይህ ዪኒቨርስ ነገር ግን ውድድርን ብንወስድ መወዳደር ማለት ከአንዱ ውድቀት የአንዱ ስኬት ነው የሚል ፅንሰ - ሀሳብ የሚነሳ ነው ።