Thursday, August 15, 2013

የወንዶች ዓለም ክፍል -2


በብዙ እንሰሳት ውስጥ የወንዱ ቦታ ጎላ ሊል ይችላል ። በአንበሳ ብንመለከት ዋናውን አደን  የምታከናውነው ሴቷ አንበሳ ስትሆን ፣ በአንፃሩ ወንዱ አንበሳ ብዙውን ጊዜ አያድንም ። ሴቷ አንባሳ  የሚያስቸግር ነገር ሲመጣ ካልሆነ በስተቀር ወንዱ ብዙም በአደን አይሳተፍም ። ይሁን እንጂ አንድ አነስተኛ የአንበሳ መንጋ የሚመራውም ሆነ ጥበቃ የሚደረግለት በወንዱ አንበሳ አማካይነት ነው ። ይሁን እንጂ ይህ በአንበሶች ዘንድ «የፖለቲካ» ችግር የለም ።
ሜሪቶክራሲ ከሴቷ ይልቅ የወንዱን የበላይነትን የሚያጠናክር ነው ። በአብዛኛው ሜሪቶክራሲ ውስጥ መወዳደር የሚችለው የተሻለ የመወዳደር አቅምን የሚሰጠው ለወንዱ ነው ። ይህም አንዱ በወንዱና በሴቷ መሀከል የበዛ የሰፋ  ልዩነት እንዲፈጠር ካደረጉት ነገሮች አንዱ ይሄው ነው ።
አንዳንድ ዘርፎች በአብዛኛው በወንዶች ብቻ የተያዙ አሉ ። ለምሳሌ የሲልከን ቫሊ ፣ ዎል ስትሪትና ብንመለከት በአብዛኛው ወንዶች ናቸው ። እንዲሁም ፊፋን ብንወስድ ፊፋ «የወንዶች ክበብ» ነው ይባላል ።
እንደ ስካንዴበኒቪያና አንዳንድ የእስያ ሀገራት ሴቶች በአንፃራዊነት ከወንዱ ጋር የሚመጣጠን ስፍራን ይዘው ይገኛሉ ። በአብዛኛው ለሴቶች ከወንዱ ይልቅ አለማደግ ምክንያቱ በስራቸውና በቤተሰባቸው መሀከል አመጣጥኖ መጓዝ መቻል ለብዙ ሴቶች  ፈተና እንደሆነ ብዙ ተመራማሪዎች የደረሱበት ጊዳይ ነው ።

No comments:

Post a Comment