ብዙውን ግዜ ጥንታዊ
ስልጣኔዎች
የተፈጥሮ
ሀብት
ባለበት
አካባቢ
ነው
የሚመሰረቱት
፣
ለዚህም
ምሳሌ
የሚሆነው
ለምሳሌ
የጥንታዊቷ
የኩሽ
ወይንም
የኢትዮጲያን
ስልጣኔ
ብንወስድ
የኢትዮጲያ
ምድር
ደጋማ
መሆኑና
የበርካታ
ወንዞችና
ለም
መሬት
የነበረው
እንደመሆኑ
ለምጣኔ
- ሀብት
እንቅስቃሴ
ምቹ
ሲያደርጋት
ከዚህም
ሌላ
ለአለም
አቀፍ
ንግድ
ያላት
መልከአ
ምድራዊ
አቀማመጥ
ለመካከለኛው
ምስራቅ
ያላት
ቅርበት
ጋር
ለሚደረግ
ንገድ
መተላለፊያነት
አመቺ
ያደርጋት
ስለነበረ
በዚህም
ለምጣኔ
- ሀብቷና
ለንግዷ
ማበብ
አስተዋፅኦን
አድርጎላታል
።
ኢቶጲያ ለጥንታዊ ነጋዴዎች ስጋ የምታበላበት ለጥ ያለ የተራራ ሜዳ እንደነበራትም ተጠቅሷል ።
አንዳንድ ጊዜ በቀደምት ስልጣኔዎች የተሰሩ ነገሮች በአሁኑ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ
እማይሰሩ
ናቸው
።
ለምሳሌ
ከአንድ
ወጥ
ድንጋይ
የተፈለፈለው
የአክሱም
ሀውልት
እንዴት
እንደቆመ
ብናይ
ቀጥ
ብሎ
ለመቆም
ለሺ
አመታት
ዘጠና
ዲግሪውን
ጠብቀው
ማቆማቸው
የጂኦሜትሪ
ህግጋትን
ያውቁ
እንደነበረ
ሲያመለክት
የጥንት
ግብፃውያንም
እንዲሁ
ፒራሚዶቹን
የሰሩበት
ሁኔታ90
ዲግሪውን
ጠብቀው
አራት
ማእዘኑን
መጠበቃቸው
የነበራቸውን
(Geometry) እውቀት
ያሳያል።
ከዚያ
በኋላ
ግን
ኢክሊድ
የተባለ
የጥንታዊ
ግሪክ
የሂሳብና
የጂኦሜትሪ
አዋቂ
በርካታ
የጂኦሜትሪ
ህግጋትን
በፅሁፍ
አድርጎ
ያወጣቸው።ግብፃውያኑም
ሆኑ
አክሱማውያን
ግን
ከኢክሊድ
በፊት
እነኚህን
የጂኦሜትሪ
ህግጋትን
ጠንቅቀው
ያውቋቸው
ነበረ
።
የጥንት አክሱማውያን ግን ከዚያ
በፊት
ያወቁት
እንደነበረ
ከሰሯቸው
ቋሚ
ሀውልቶች
መረዳት
ይቻላል
።
እነኚህን
ስልጣኔዎች
ለመስራት
የሚያስፈልገውን
ሀብትና
እውቀትም
ባለቤቶች
እንደነበሩ
መገመት
ይቻላል
።
ይህ
ብቻ
ሳይሆን
ጥንቃዊ
ግብፃውያንም
ስለ
ትርያንግል
(Triangle) ወይም
ሶስት
ማእዘን
በነበራቸው
እውቀት
ነው
እነኛን
ታላላቅ
ፒራሚዶችን
የገነቡት
።
ለምሳሌ
የሶስት
ማእዘንን
ህግ
አገኘ
የሚባለው
ፓይታጎራስ
ቢሆንም
እሱ
ከመወለዱ
በፊት
2 ሺ
አመት
በፊት
ግን
ጥንታዊ
ግብፆች
ታላላቆቹን
ስልጣኔዎች
በእነኛ
ህግጋት
ላይ
ተመስርተአው
የሰሯቸው
ነበሩ።
ሌላው ስለ አክሱም
ገናናነት
ስናነሳ
ለአክሱምስልጣኔ
መክሰም
እንደ
አንድ
ምክንያትነት
የሚጠቀሰው
ነገር
ለንግድ
ቁልፍ
የነበሩትን
የቀይ
ባህር
ዳርቻዎችን
አክሱማውያን
መቆጣጠር
እያቃታቸው
መምጣት
ሲሆን
በዚህም
ምክንያት
ዋናው
የንግድ
መስመር
የነበረውንና
የሸቀጦች
መተላለፊያ
የነበረው
ክልል
ከቁጥጥራቸው
ስር
እየወጣ
በአረቦችና
በፋርሶች
ቁጥጥር
ስር
እየዋለ
መምጣት
ነው
።
የቀይ
ባህር
ዳርቻዎችን
ብንመለከት
በአለም
ላይ
ካሉ
ቁልፍ
የንግድ
መስመሮች
አንዱና
ዋነኛው
ሲሆን
በዛን
ዘመን
ከነበሩ
ታላላቅ
ጥንታዊ
ስልጣኔዎች
በነበሩት
በግሪክ
፣
በሮም
፣
በፋርስ
፣
በህንድና
በቻይና
መሀከል
ለሚካሄድየባህርም
ሆነ
የየብስ
ንግድ
ዋነኛ
የመተላለፊያ
መስመር
የነበረ
ነው
።
ይህ ለአለም
አቀፍ
ንግድ
እጅግ
ጠቃሚ
የሆነውን
የባህር
ክልልና
ጠረፍ
አክሱማውያን
ለረጅም
ጊዜ
በቁጥጥራቸው
ስር
በማድረጋቸው
እንዲሁም
ቀይ
ባህርን
ተሻግረው
አረቢያንን
ይገዙ
በነበረት
ወቅት
ይቆጣጠሩት
የነበረ
እጅግ
ጠቃሚ
የንግድ
መስመር
ነው
፣
ለሀያልነታቸውንና
በንግድ
ለመበልፀጋቸው
አስፈላጊ
ነበረ
።
ይሁን
እንጂ
በስተመጨረሻ
ላይ
በገጠማቸው
ውስጣዊና
ውጫዊ
ግፊቶች
ምክንያት
አካባቢው
ከአክሱማዉያን
ቁጥጥር
ስር
መውጣቱ
ውሎ
አድሮ
ለአክሱም
ስልጣኔ
መዳከምና
መክሰም
አስተዋፅኦን
አድርጓል
።
ፐርሽያዎችና
አረቦች
አቅማቸውን
አጠንክረው
የአክሱማውያን
ግዛት
የነበረውን
የአረቢያን
ክልል
በመውረራቸው
ምክንያት
ከአክሱም
ቁጥጥር
ውጪ
ሊወጡ
ችለዋል
።
ከዚያም
ትኩረታቸውን
ለደህንነት
አስጊ
እየሆነ
ከመጣው
ከባህር
ጠረፉማው
አካባቢ
ይልቅ
ብዙ
ተቀናቃኝ
ወደ
ማይበዛበት
ወደ
ደጋውና
መሀል
አገር
አድርገዋል
።
የአክሱም ስልጣኔ ከተዳከመ በኋላ በርካታ የታሪክ ፀሀፊዎች በተደጋጋሚ እንደገለፁት ኢትዮጲያ ለሺዎች አመታት የዘለቀ አለምም ረስቷት ፣ እሷም አለምን ረስታ
፤
ከተቀረው
አለም
የመገለል
እጣ
ገጥሟታል
።
ነገር
ግን
ይህ
መገለል
በአብዛኛው
በምጣኔ
- ሀብትና
በሳይንስ
ካደገው
አውሮፓውያን
ጋር
በተለይ
የጎላ
ነበረ
።
በአካባቢው
ግን
በተለይም
አቅራቢያዋ
ካሉ
ሀገራት
እንደ
ግብፅና
የመን
ካሉት
ሀገራት ግን
የሞቀ
ግንኙነት
እንደነበራት
አንዳንድ
የታሪክ
ፀሀፊዎች
ይገልፃሉ
።
ለምሳሌ
ግብፅን
ብንወስድ
እስከ
1950ዎቹ
ድረስ
የኢትዮጲያ
ፓትርያርክ
ከግብፅ
ተሹሞ
ይመጣ
እንደነበረ
ይታወቃል
፣ከየመንም
ጋር
ካላት
መልከአ
ምድራዊ
አቀማመጥ
ቅርበት
የተነሳ
የንግድ
ግንኙነት
ነበራት
።
ይህም አልፎ አልፎ የተወሰኑ ማንሰራራቶች የነበሩ ቢሆንም የአክሱምን ያክል ገናናነት ፣ ሀብትና
ሀያልነትን
ግን
ዳግመኛ
አልተጎናፀፈችም
።
በተለይም
ከውጪ
ሀገራት
ጋር
የነበረው
ንግድ
ጨርሶ
ተቋርጧል
ባይባልም
ከቀድሞው
ጋር
ግን
ፈፅሞ
እሚወዳደር
አልነበረም
።
ይህ
መገለል
አገሪቱን
በኢኮኖሚም
ሆነ
በፖለቲካ
መጉዳቱ
በግልፅ
የሚታይ
ነው
።
በኢትዮጲያ
ሁኔታ
የውስጥ
ግጭቶች
ያደረሱት
ጉዳት
ከውጭ
ወረራ
እና
ጥቃት
የበለጠ
ሲሆን
፣
በአንፃሩ
የውጪ
ወረራ
ህዝቡ
በአንድነት
ሆ
ብሎ
የሚመክተው
ሲሆንበተደጋጋሚም
በአስተማማኝ
ሁኔታ
ተገትቷል
፣
የመገታት
እድሉም
ሰፊ
ነው
።
ለዚህም
ነው
አገሪቱ
በቅኝ
አገዛዝ
ስር
ወድቃ
የማታውቀው
፣
በአንፃሩ
ግን
ከውስጥ
የሚነሱ
ግጭቶችና
የእርስ
በእርስ
ጦርነቶች
ግን
ውጤታቸው
አስከፊ
ሆኖ
በተደጋጋሚ
በታሪክ
ተመዝግቧል
።
ራቅ
ያለውን
የአክሱምን
ዘመን
ብናይ
እንኳን
ለውድቀቱ
ዋና
አስተዋፅኦን
ያደገረው
የውስጥ
መበጣበጥና
የእርስ
በእርስ
ጦርነት
ሆኖ
እናገኘዋለን
።
ከዛ
ወዲህ
ቀረብ
ያሉትን
የግራኝ
አህመድ
ጋር
የተደረገው
ጦርነትና
፣
ዘመነ
- መሳፍንትን
መጥቀስ
ይቻላል
።
በአንፃራዊነት ሌሎችን ሀገራት ስናይ ግን የኢትዮጲያን
ያህል
ከተቀረው
አለም
የመራቅ
እጣ
አልገጠማቸውም
።
ለምሳሌ
ግብፆችን
ብንወስድ
የሀያላኖቹን
የፈርኦንን
ስልጣኔ
የኋለኞቹ
ግብፆች
ከዚያ
በኋላ
ባይደግሙትም
ያን
ያህል
ግን
እንደ
ኢትዮጲያ
ከተቀረው
አለም
ተገልለው
ርቀው
ለሺዎች
አመታት
አልተቀመጡም
።
መልከአ
- ምድራዊ
አቀማመጣቸውም
በአፍሪካ፣በአውሮፓና
በእስያ
መሀከል
ቁልፍ
ስለነበረ
ሃያላን
የውጪ
ሀይሎች
ያለማቋረጥ
በወረራም
ይሁን
በሰላም
ይጎበኟቸው
የነበረ
ሮማውያኑ
እነ
ጁልየስ
ቄሳር
፣
ታላቁ
አሌክሳንደር
አንዲሁም
ከቅርቡም
የፈረንሳዩ
ሀያሉ
ንጉሰ
ነገስት
ናፖሌዎን
ቦናፖርቴ
ምሳሌዎች
ናቸው
።
ስለዚህ
በአንፃራዊነት
ሲታይ
ካላቸው
የጂኦግራፊያዊ
አቀማመጥና
፣ተገልለው
ባለመቀመጣቸው
ከኢትዮጲያ
የተሻለ
የኢኮኖሚ
አቅምን
ለመገንባት
እንዲሁም
በአውሮፓ
ከተፈጠረው
ዘመናዊነት
ጋር
ለመተዋወቅ
እድልን
ለማግኘት
ችለዋል
።
ይህም ብቻ ሳይሆን
በሀገራችን
ውስጥ
የነበረው
ፋታ
እማይሰጥ
የእርስ
በእርስ
ጦርነት
የኢትዮጲያን
እድገት
ለክፍለ
ዘመናት
ከጎተቱት
ሌላው
አቢይ
ምክንያት
ሆኖ
ቆይቷል
።
ለዚህ
ምክንያቱ
በርካታ
ሲሆን
በየዘመኑ
የነበሩ
የፊውዳል
መሳፍንትና
መኳንንት
መሀከል
የነበረው
የስልጣን
ሽኩቻ
፣
የውጪ
ሀይሎች
ጣልቃ
ገብነት
በተለይም
የአባይን
ወንዝ
ምንመጭ
መቆጣጠር
፣
ለመቆጣጠር
ካልተቻለም
ሀገሪቱ
ሰላም
እንዳይኖራት
በወንዙ
ላይ
ምንም
ነገርን
እንዳትሰራ
፣
ለማድረግ
ይደረጉ
የነበሩ
በርካታ
የጀርባ
ሴራዎች
የውስጥ
ችግሩን
ሲያቀጣጥሉ
ቆይተዋል
።
ለዚህም ነው በአንድ
ወቅት
ከነ
ሮም
፣
ፋርስ
፣
ግሪክ
፣
እና
ከቻይና
እኩል
አቅም
የነበራት
ሀገር
ብሎም
በአንድ
ወቅት
በአለም
ላይ
ካሉ
ሀያላን
ስልጣኔዎች
ሀገሮች
ሶስተኛ
ደረጃ
ይዛ
የነበረች
ሀገር
፣የራሷን
የፊደል
ገበታ
የፈጠረች
፣
የአለምን
ታላላቅ
ሀይማኖቶችን
አስቀድማ
የተቀበለች
ሀገር
በድህነት
፣
በረሀብ
፣
በውስጣዊ
ችግሮችንና
በእርስ
እርስ
ጦርነት
ውስጥ
ተጠምዳ
በድህነትና
በችግር
ለበርካታ
ክፍለ
ዘመናት
መቆየቷ
ለብዙ
የውጪ
ሀገር
ሰዎችአስገራሚ
የሚሆንባቸው
ለዚህ
ነው
።
ነገር ግን አንድ
አለም
አቀፋዊ
የሆነ
ሀቅ
ምንድነው
ብንል
፣
መፅሀፉም
ፊተኞች
ኋለኞች
፣
ኋላኞችም
ፊተኞች
ሆናሉ
እንደሚለው
ቀደም
ሲል
በአለም
መድረክ
ላይ
ስልጡን
የነበሩ
ውሎ
አድሮ
መልሰው
ማቆልቆላቸውና
በሌሎች
ከነሱ
በሚጠነክሩ
መተካታቸው
አይቀሬ
ነው
።ይሄ
እውነታ
እንኳን
ብዙ
ሺ
አመታት
ባለፈበት
ዘመን
በጥንቱ
አለም
ቀርቶ
በአሁኑ
በዘመናዊው
አለም
እንኳን
በየቀኑ
የሚታይ
ሀቅ
ነው
።
ከዚያም በኋላ በዘመነ - መሳፍንት ነገሮች የተወሳሰቡበት ጊዜ የነበረ
ሲሆን
አፄ
ምንሊክን
ብንወስድ
ከአድዋ
ድል
በኋላ
የኢትዮጲያን
የድንበር
ግዛቶችን
ከወቅቱ
ኢትዮጲያን
ዙሪያዋን
ያሉ
ሀገራትን
በቅኝ
ገዢነት
ይገዙ
ከነበሩት
ሀያላን
ጋር
ያካለሉ
ሲሆንየመጀመሪያውን
የባቡር
፣የፖስታ
አገልግሎት
ድርጅት
፣
ቴሌኮሚኒኬሽን
ያቋቋሙ
ሲሆን
የልማት
ጎዳና
እድገቱ
እንዲፋጠን
ብርቱ
ፍላጎት
ነበራቸው
ሲሆን
በወቅቱ
በቤተክህነትም
ሆነ
በመሳፍንቱና
በመኳንንቱም
ጭምር
በዘመኑ
ተቀባይነት
ያልነበራቸውን
እንደ
መኪናን
እንደ
ልዩ
ነገር
ይታይ
የነበረ
ሲሆን
፣
ሲኒማ
እንደ
ሰይጣን
ስራ
ይቆጠር
በነበረበት
ዘመን
አዳዲስ
ነገሮችን
ለማስተዋወቅና
ስራ
ለማዋል
ጥረት
አድርገዋል
።
ከአድዋ
ጦርነት
በኋላ
እነኚህም
የልማት
ስራዎች
ወጥነዋል
ሆኖም
ብዙም
ቀጣይነት
ያልነበራቸው
ሲሆን
የእድሜ
እና
የስልጣን
ዘመናቸውም
ብዙም
ሳይቆይ
አብቅቷል
።
በወቅቱ የነበረው አስተዳደር የአንድ ክልል አስተዳዳሪ በዛ ክልል
ለነበረው
የአስተዳደር
ስራ
ዋና
ሀላፊ
የነበረ
ሲሆን
በሚያስተዳድረው
ክልል
ፈላጭ
ቆራጭ
ነበረ
ማለት
ይቻላል
።
አመታዊ
ግብሮችን
ከገበረ
፣
ወራሪ
ሲመጣ
ከንጉሰ
- ነገስቱ
መንግስት
ጋር
ክተት
ሰራዊት
ብሎ
አብሮ
ከዘመተ
ወይም
ሰራዊት
ካዋጣ
፣
ከውጪ
ሀገራት
ጋር
በራሱ
ግንኙነትን
እስካልፈጠረ
እና
ውል
እስካልተዋዋለ
ድረስ
የንጉሰ
- ነገስቱን
ስልጣን
እንደተቀበለ
ተቆጥሮ
የያዘውን
ክልል
ያስተዳድር
ነበረ
- በተለይ
እስከ
ጣሊያን
ኢትዮጲያን
እስከወረረበት
ጊዜ
ድረስ
።
ይህም
አሁን
በዘመናዊ
አለም
የፌደራል
ስርአት
ከምንለው
ጋር
በጣም
ተመሳሳይ
ነው
።
በኢትዮጲያ ሁኔታ ስናየው የፌደራል ስርአት በታሪክ ቀድሞም የነበረ በመሆኑ፣ በዛ ላይ
ብዙም
ክርክር
ባይኖርም
ምንምአይነት
የፌደራል
ስርአት
ነው
ለኢትዮጲያ
እሚያስፈልገው
የሚለው
ግን
ሊያወዛግብና
ሊያከራክር
ይችላል
።
ነገር
ግን
ፌደራል
ስርአት
ለማስተዳደር
በጣም
ውስብስብና
፣
ብዙ
ክትትልን
የሚፈልግ
እንዲሁም
የተጠናከረ
የህፍግና
ገፈ
የህገ
- መንግስት
መሰረትን
የሚፈልግ
ነገር
ነው
።
ለምሳሌ
በአሜሪካን
አገር
ክፍላተ
-ሀገራቱ
በአንድ
ጉዳይ
ላይ
ውሳኔን
ሲሰጡ
፣
ህገ
- መንግስቱን
ተላልፈዋል
፣
ከስልጣን
ወሰናቸው
አልፈዋል
በሚለው
ክስ
ወደ
ወደ
ዋናው
ጠቅላይ
ፍርድ
ቤት
ክርክር
የሚሄድበትና
በጠቅላይ
ፍርድ
ቤቱ
ውሳኔ
ጉዳዩ
እልባት
የሚያገኝበት
ጊዜ
በርካታነው
።
እንደውም ከአፄ ምንሊክ ዘመንና ከዛ በፊት
የየክልሉ
አስተዳዳሪዎች
በጣም
ጠንካሮች
የነበሩ
ከመሆናቸው
የተነሳ
አንዳንዶቹ
ንጉስ
ተብለው
የሚጠሩም
ነበሩ
።
ዋናው
ንጉሰ
ነገስት
አፄ
ዮሀንስ
በነበሩ
ጊዜ
ንጉስ
ተክለሀይማኖትም
የነበሩ
ሲሆን
፣
አፄ
ምንሊክም
እንዲሁ
ንጉሰ
- ነገስት
ከመባላቸው
በፊት
ንጉስ
ምንሊክ
ተብለው
ነበረ
እሚጠሩት
።
የተለያየ
ማእረግም
እንደ
ራስ
ቢትወደድ
፣
ራስ፣
ቀኛዝማች
፣
ግራአዝማች
የመሳሰሉት
የማእረግ
ስሞች
የሚጠሩ
ሲሆን
ይህም
በፊውዳላዊው
ስርአት
የነበሩ
የአካባቢ
ገዢዎች
ጠንካራ
እንደነበሩ
፣ዋናዎቹ
ነገስታትም
የነሱን
ስልጣን
እስካልተፈታተኗቸው
ድረስ
ውስጣዊ
የአስተዳደር
ጉዳዮችን
ይተውላቸው
ነበረ።
በተለይም
ይህ
በዘመነ
መሳፍንት
ዘመን
በግልፅ
ይታይ
የነበረ
ሲሆን
፣
አንዳንዶቹም
ለይስሙላ
የነበረ
የላላ
ተገዢነትን
የመቀበል
ስሜት
ነበራቸው
።
ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጲያን ሲወር በከፍተኛ ደረጃ ጣሊያኖችን የተፋለሙት እነኚህ አካባበቢያዊ ገዢዎች የነበሩ ሲሆን ቁጥራቸው ቀላል እማይባሉትን ፋሺስት ኢጣሊያ ፈጅቷቸዋል ወይም በጦርነቱ ውስጥ ህይወታቸውን አተዋል ።
በወቅቱ
የነበረው
አለም
አቀፍ
ተቋም
የሊግ
ኦፍ
በኔሽንስ
ድርጅት
እ.ኤ.ኤ
በ1935
ዓ.ም.በወራሪዋ
ኢጣሊያ
ላይና
በተወራሪዋ
ኢትዮጲያ
ላይም
በሁለቱም
ላይ
የጦር
መሳሪያ
ማእቀብን
የጣለ
ሲሆን
የኋላ
ኋላ
ለድርጅቱ
ተአማኒነት
መቀነስና
መፍረስ
አስተዋፅኦን
ያደረገው
በዚሁ
በኢትዮጲያ
የኢጣሊያ
መወረር
ላይ
የወሰደው
የተዛነፈ
አድሏዊ አቋም
ነው
።
በተለይም ንጉሰ ነገስቱ በታሪክ አወዛጋቢ በሆነው ስደት ወይስ ሽሽት በሚያስብል ሁኔታ በባቡር ተሳፍረው በጅቡቲ በኩል አድርገው ሀገሪቱን ጥለው ሲወጡ ከፋሺስት ኢጣሊያ ጋር ከፍተኛ
የአርበኝነት
ትግልን
አካሂደዋል።
በዚህም
ብዙዎች
ለሞት
፣
ለእስራት
ተዳርገው
ንጉሰ
ነገስቱ
ወደ
አዲሳባ
ሲመለሱ
ዋና
ዋና
እሚባሉት
ወይ
ህይወታቸውን
አጥተው
የነበረበት
ሁኔታ
ነው
የነበረው
።
አንዳንድ የታሪክ ፀሀፊዎች እንደሚሉት ዋና ዋና
እሚባሉት
የየአካባቢው
ገዢዎች
በፋሺስት
ኢጣሊያ
ተወግደው
መቆየት
ንጉሰ
ነገስቱ
ጠንካራ
የተማከለ
አስተዳደር
ለመፍጠር
ቀላል
አድርጎላቸዋል
፣አብዛኞቹ
ከምንሊክ
ዘመን
ጀምሮ
የነበሩ
እንደመሆናቸውም
ጠንካራ
የሆነበውስጣዊ
ጉዳዮች
ላይላቅ
ያለ
ስልጣንና
ተሰሚነት
የነበራቸው
ነበሩ
።በአንፃሩ
አፄ
ሀይለስላሴ
ስልጣን
ከያዙ
ጊዜ
ጀምሮግን
ሀገሪቱን
የተማከለ
አሀዳዊ
አስተዳደር
እያጠናከሩት
ነው
የሄዱት
።
ቀደምት
በሆኑት
ነገስታት
በተለይም
ከአፄ
ቴዎድሮስ
ጊዜ
ጀምሮ
የተጀመረውን
ስራ
ኢትዮጲያን
አንድ
የማድረግ
ስራ
በዘመናቸው
ከፍፃሜ
አድርሰውታል
።
ከ19ኛው
ክፍለ
ዘመን
ከነበሩ
ነገስታት
፣
አፄ
ዮሀንስ
በግዛት
ዘመናቸው
ቀላል
የማይባል
የውጪ
ወረራ
ያጋጠማቸው
ንጉሰ
ነገስት
ነበሩ
።
በአንድ
በኩል
መጀመሪያ
ላይ
ግብፆች
፣
ከዚያም
መሀዲስቶች
ከዚያም
እንደገና
ግብፆችን
ለማስለቀቅ
የእንግሊዝ
ቅኝ
ገዢዎችከሆኑት
ከእንግሊዝ
ጋር
ቢዋዋሉም
የሂወት
ስምምነት
(Hiwot Treaty) ተብሎ
በታሪክ
በሚታወቀው
ስምምነት
፣
እንግሊዞች
ግን
በፈንታቸው
ውላቸውን
ሳያከብሩ
ቀርተው
ጣሊያኖችን
በምፅዋ
እንዲሰፍሩ
አድርገው
ወጥተዋል
።
ይሁን
እንጂ
ራሳቸው
አፄ
ዮሀንስ
በወቅቱ
ከመሀዲስቶች
ይልቅ
ምሽግ
እየቆፈረ
መሬቱን
በሚችለው
አቅም
እያሰፋ
የመጣው
ጣሊያን
የፈጠረው
ስጋት
የበለጠ
መሆኑን
ተረድተውታል
።
ነገር
ግን
ከመድሂስቶች
ጋር
የነበረው
ፀብ
የተካረረ
ደረጃ
በመድረሱ
ምክንያት
ትኩረታቸውን
ወዳዛው
አድርገዋል
፤
በዚህ
አጋጣሚም
ጣሊያን
በሰሜናዊ
ኢትዮጲያ
እየተጠናከረ
እንዲሄድ
እድልና
ጊዜ
ተመቻችቶለታል
።
ከምንሊክ በኋላ የመጡት ተፈሪ መኮንን መጀመሪያ ላይ በርካታ
ማሻሻያዎችን
ያደረጉ
የነበረ
ሲሆን
በወቅቱ
በነበሩት
የተማሩ
ሰዎችም
ጭምር
ድጋፍ
ነበራቸው
።
ተቀናቃኛቸው
ከነበሩት
ከልጅ
ኢያሱም
የተሻለ
ግንዛቤና
ለአገር
አመራርም
ልምድ
የነበራቸውና
በብዙሀኑ
ህዝብም
ተቀባይነትም
የነበራቸው
ነበሩ
- በዘመኑ
ምሁራንም
ጭምር
ከልጅ
ኢያሱ
ይልቅ
የተሻለ
ተቀባይነት
ነበራቸው
።
ይሁን
እንጂ
በፊውዳላዊት
ኢትዮጲያ
መንግስት
የህዝቡን
የኑሮ
ደረጃ
ለመለወጥ
መሰራት
እዳለበት
ተደርጎ
አይወሰድም
የነበረ
ሲሆን
ህዝቡ
ሰርቶ
፣
ግብር
ገብሮ
መኳንንቱንና
መሳፍንቱን
ተደላደለ
ኑሮ
እንዲኖሩ
ማስቻል
ነው
እንጂ
እድገትንና
ልማትን
ማግኘት
የህዝቡ
መብት
እንደሆነ
ተደርጎ
አይቆጠርም
ነበረ
።
ይሰሩ የነበሩ ስራዎችም በገዢዎቹ መልካም ፈቃድ እንደተሰሩ እንጂ እንደ ገዢዎቹ ግዴታና እንደ ህዝቡ መብት ተደርገው ባለመወሰዳቸው ምክንያት በልማቱ በኩል በጣም ጠንካራ የሚባል ተነሳሽነት አልነበረም ።ያ ብቻ
ሳይሆን
በአንድ
ሀገር
ውስጥ
የልማት
መኖር
የፖለቲካውን
ጫና
እንደሚቀንስ፣
የህዝቡን
ቅሬታ
ሊያለዝብ
እንደሚችል
፣
እና
የውስጥ
ሁኔታዎችን
እንደሚያረጋጋ
ግንዛቤው
አልነበረም
።
በዚህ ምክንያት በአፄ
ሀይለ
ስላሴ
ስርአት
በስተመጨረሻው
አካባቢ
በእቅድ
የልማት
ጅምሮች
የነበሩ
ሲሆን
በውጭ
ለጋሾችም
እንደ
(CADU) ካዱ
፣
(WADU) ዋዱ
ያሉ
ትላልቅ
የግብርና
ልማት
ፕሮጀክቶች
ተጀምረው
ነበር
እንዲሁም
አንዳንድ
ባለሀብቶች
የሰፋፊ
ግብርና
ስራዎችን
እየጀመሩ
የነበረ
ቢሆንም
በአንድ
በኩል
ያገሪቱ
ችግር
ስር
የሰደደና
ሰፊ
በመሆኑ
በጥቂቱ
እየተጀመረ
የነበረው
ልማት
የህዝቡን
ፍላጎት
ሊያረካ
አልቻለም
፣
እንደውም
አንዳንዶቹ
ትላልቅ
የእርሻ
ስራዎች
ጭሰኛ
የነበረውን
አርሶ
አደር
ፍትሀዊ
ባልሆነ
ሁኔታ
ከመሬቱ
እንዲፈናቀል
በማድረጉ
ነባርብሶቶችን
አባብሷል
።
ከዚህም ሌላ ደግሞ
ዋናው
ስርአቱ
ማሻሻያዎቸን
በተለይም
የመሬት
ስርአቱን
በተመለከተ
፣ እና
በሌሎችም
የፖለቲካ
ጉዳዮች
ላይ
ይህ
ነው
እሚባል
ማሻሻያዎችን
ካለመደረጉም
በላይበርካታ
ወጣትና
የተማረ
ሀይል
እየተፈጠረ
ሲሄድ
ያነሳቸውን
ጥያቄዎችንና
ያገሪቱንም
ሆነ
የአለም
- አቀፍ
ሁኔታውን
ራሱ
በትክክል
ተረድቶት
ነበረ
ለማለት
ያስቸግራል
።ወጣቱ
በዚያ
ቀደም
ነፃ
ከወጡ
የአፍሪካ
ሀገሮች
በቅኝ
ግዛት
ተገዝታ
እማታውቀው
ኢትዮጲያ
ማነሷ
ወጣቱንትውልድ
ውስጥ
የብስጭት
ስሜትን
መፍጠሩ
አንዳንድ
ፀሀፊዎች
ዘግበውታል
።
ሀዲስ
አለማየሁ
።ነገሮች
እስከመጨረሻው
ደረጃ
እስኪደርሱ
መጠበቅ
ነው
እንጂ
፣
ማሻሻያዎችን
አድርጎ
የመቀጠል
የዚህ
አይነት
ልማድ
በሀገራችን
እምብዛም
የተለመደ
አይደለም
።
በወቅቱ ያስፈልግ የነበረውን ጥገናዊ ለውጥ ከፓርላማው ፣ በሚኒስትሮች
ምክር
ቤት
ተነሳሽነት
ቀርቦ
ማሻሻያ
ሊደረግ
ይችል
የነበረ
ቢሆንም
የፓርላማው
አባላት
አብዛኞቹ
የገዢው
መደብ
አባላት
የነበሩ
በመሆናቸው
እና
ራሳቸውም
ከስርአቱ
ተጠቃሚዎች
የነበሩ
በመሆናቸው
ስርአቱ
እንዲሻሻል
ከልብ
ፍላጎት
ነበራቸው
ለማለት
ያስቸግራል
ከጥቂት
አባላት
በስተቀር
እነሱም
ብዙ
አቅም
እንደማይኖራቸው
ግልፅ
ነው
።
የሚኒስትሮች
ምክር
ቤትም
እንደውም
ፓርላማው
አድርግ
የሚለውን
እራሱ
እንደማያደርግ
በወቅቱ
የነበሩ
ሰዎች
ከፃፏቸው
መፅሀፍት
ላይ
ጠቁመዋል
።
ራሳቸው
ንጉሰ
ነገስቱ
በስልጣን
ዘመናቸው
መጨረሻ
ላይ
በእጃቸው
በፃፏች
የኑዛዜ
ደብዳቤዎች
ላይ
ልጆቻቸውና
የልጅ
ልጆቻቸው
ዘውዳቸውን
እንደሚወርሱና
ስርአቱ
እንደሚቀጥል
ያስቡ
እንደነበረ
መረዳት
ይቻላል
።
በወቅቱ አንዳንድ ሰዎች ንጉሰ - ነገስቱ የገባር ስርአቱን ማሻሻል ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን የመሬት
ባላባቶችና
ፊውዳሎች
እምቢ
ብለዋቸው
ነው
የሚሉ
አሉ
።
ነገር
ግን
መጀመሪያ
ወደ
ስልጣን
ሲመጡ
ካደረጓቸው
ማሻሻያዎች
ውጪ በተግባር
የጭሰኛው
ስርአትን
ካገሪቱ
ለማጥፋት
በራሳቸው
ተነሳሽነት
ያደረጓቸው
ተጨባጭ
የሆኑ
ተግባራት
ግን
አልነበሩም
ማለት
ይቻላል
።ራሳቸው
ንጉሰ
ነገስቱም
ቢሆኑ
ስዩመ
- እግዝአብሄር
ነን
፣ስልጣን
ከመለኮት
ነው
የተሰጠን
ብለው
የሚያምኑ
እንደመሆናቸው
ስልጣናቸውን
ሊያስቀንስ
የሚችልን
ጥገናዊ
ለውጥን
ወይም
ማሻሻያን
ከልብ
ይደግፋሉ
ለማለት
ያስቸግራል
።
ፋሺስት
ኢጣሊያ
ከኢትዮጲያ
ከወጣ
በኋላ
በተለያዩ
በሚቀርቧቸው
ሰዎች
ስርአቱን
ወደ
ህገ
- መንግስታዊ
ዘውዳዊ
ስርአት
እንዲቀየር
ይቀርቧቸው
በነበሩና
በዙሪያቸው
በነበሩ
አንዳንድ
ሰዎች
ይቀርብላቸውን
የነበሩ
ተደጋጋሚ
ጥያቄዎችን
ንጉሰ
ነገስቱ
በእሺታ
አልተቀበሉም
(1ፋና ዊጊ )።ወደ
ስልጣን
ሲመጡ
እንደ
ለውጥ
ፈር
ቀዳጅ
ይታዩ
የነበሩት
ንጉሰ
ነገስት
ወደ
መጨረሻው
የስልጣን
ዘመናቸው
ላይ
የለውጥ
እንቅፋት
ተደርገው
በተለይም
በተማረው
ወጣቱ
ትውልድ
ዘንድ
መታየታቸው
አልቀረም
።
ከዚያ ይልቅ ግን ራስ
እምሩ
ሚካኤል
የነበራቸውን
መሬት
ለገበሬዎች
በማከፋፈላቸው
ሞገሱ
እንደነበረ
ይታወቃል
ንጉሰ
ነገስቱም
ራስ
እምሩ
ሚካኤልን
ያርቋቸው
እንደነበረና
በያሀገሩ
አምባሳደር
አስርገው
ይልኳቸው
እንደነበረ
አንዳንዶች
ይናገራሉ
።
ይህን ሁሉ በወቅቱ
የነበሩት
መሪዎች
ሁኔታውን
በአግባቡ
ተረድተውት
ቢሆን
ኖሮ
መጣሁ
፣መጣሁ
እያለ
የነበረውን
አብዮት
አቅጣጫ
ማስቀየር
፣
እንዲለዝብ
ወይም
ጊዜው
እንዲራዘም
ማደረግ
በተቻለ
ነበረ
።
ይሁን
አንጂ
ከ1953ቱ መፈንቅለ
መንግስት
ማሻሻያዎችን
በኋላ
ብዙ
ጊዜና
እድሎች
የነበሩ
ቢሆንም
እነኛን
ሁሉ
መጠቀም
ባለመቻሉ
ጉዳዩ
ወደ
ዋጋ
ወደሚያስከፍል
አብዮትነትና
ወደ
ስር
ነቀል
ለውጥ
ደረጃ
ተሸጋግሯል።
በዚህ ሁሉ ሁኔታም
በሀይለስላሴ
ስርአት
የተከሰተው
የ1965/66ቱ ረሀብ
የሁኔታውን
አስከፊነት
በመግለጡ
እንዲሁም
ረሀቡ
መደበቁ
በራሱ
በፈጠረው
የህዝብ
ቁጣ
ምክንያት
ስርአቱ
ከዛ
አልፎ
ሊቀጥል
አልቻለም
።
አንዳንድ
የታሪክ
ፀሀፊዎች
እንደሚስማሙበት
ንጉሰ
- ነገስቱ
ከእሳቸው
በኋላ
ኢትዮጲያ
በምን
አይነት
ሁኔታ
ልትቀጥል
እንደምትችል
፣
ወይም
ከሳቸው
በኋላ
በሀገሪቱ
ላይ
ምን
ሊመጣ
እንደሚችል
አላሰቡበትም
ይላሉ
።
ይሁን
እንጂ
ይሄ
ጥያቄ
ንጉሰ
- ነገስቱን
ብቻ
ሳይሆን
በዙሪያቸው
የነበሩትን
ከፍተኛ
ባለስልጣናት
ይመለከታል
።
በወቅቱ
የነበረው
የገዢ
መደብ
ስለሀገሪቱ
መፃኢ
እድል
ያሰበው
ወይም
ያስቀመጠው
እቅድ
እንዳልነበረም
መገመት
ይቻላል
።
ንጉሰ - ነገስቱ በአንድ ወቅት ከእሳቸው በኋላ ስለሚሆነው የሀገሪቱ ሁኔታ በጋዜጠኞች ሲጠየቁ ቆጣ
ብለው
ምላሽ
የሰጡ
ሲሆን
እንደዛ
ብሎ
ማንሳትም
ሆነ
ማሰብ
ተገቢ
አይደለም
ተብሎ
በወቅቱ
ይታመን
እንደነበረ
ያመለክታል
፤
ይህም
ከእውነታው
ወይም
ከተጨባጩ
ሁኔታ
ውጪ
መሆኑን
መረዳት
አያዳግትም
።
የ66ቱ
አብዬት
ከተከሰተ
በኋላ
በወቅቱ
የነበሩት
ምሁራንና
ተማሪዎች
ዋናው
አላማቸው
የነበረው
ዘውዳዊውን
ስርአት
ማስወገድ
ነው
እንጂ
ከዚያ
በኋላ
ሀገሪቱ
ስለምትቀጥልበት
መንገድ
ወጥ
የሆነ
ስምምነት
አልነበረም
።
የንጉሰ
ነገስቱ
ስርአትም
እንደወደቀ
በወቅቱ
በነበሩት
የፖለቲካ
ሀይሎች
መሀከል
የነበረው
የአስተሳሰብ
፣
የፍልስፍናና
የአላማ
ልዩነት
ገንፍሎ
ወጣ
።
ከአብዮቱ
በኋላ
የሀገሪቱ
የወደፊት
መስመር
በአግባቡ
አለመበጀቱ
ሀገሪቱንና
ህዝቧን
ከባድ
ዋጋ
ያስከፈለ
ሆኖ
አልፏል
። በዚህ
ሁሉ
ግርግር
ነው
እንግዲህ
ወታደራዊው
መንግስት
ስልጣን
ላይ
እራሱን
እያደላደለ
እና
እያጠናከረ
በመሄድ በመጨረሻም
በአብዮቱ
የተገኙትን
ድሎች
በመቀልበስ
ከእርሱ
ቀደሞ
ከነበረው
የባሰአምባገነናዊ
ስርአትን
የገነባው
።
አብዮቱም ከመስመሩ አልፎ በመሄድ ሀገሪቷ ያፈቻቸውን ምሁራንና ወጣቶችን ህይወት የበላ ሲሆን ፣ የተቀሩትም
ከሀገር
ጥለው
ለመሰደድ
በቅተዋል
።
አብዮት
ስር
ነቀል
ለውጥ
እንደመሆኑ
ብቻም
ሳይሆን
ከዚያ
በኋላ
ሀገሪቷ
በየትኛው
አቅጣጫ
መሄድ
አለባት
በሚለው
ላይ
ውሎ
አድሮ
ሰፊ
ልዩነቶች
መታየት
የሚጀምሩበት
እንደመሆኑ
መጠን
ከፍተኛ
ጥንቃቄንና
ምን
ድረስ
መሄድ
እንዳለበት
አጥብቆ
ማሰብን
ይጠይቃል።
በኢትዮጲያ ሁኔታ ስናየው የዚህ አይነት ስር ነቀል
ለውጥ
ለማስተናገድ
ጨርሶ
ልምድ
የለም
ማለት
ይቻላል
።
ነገሮች
በፍጥነት
አቅጣጫቸውን
የመሳትና
ወዳልተፈለገ
አቅጣጫ
የመሄድ
እድላቸው
በጣም
ሰፊ
ሲሆንበተደጋጋሚ
የሀገሪቱን
የወደፊት
አቅጣጫ
ወደ
ተሻለ
ጎዳና
አቅጣጫና
እድል
ሊያመሩ
ይችሉ
የነበሩ
ታላላቅ የታሪክ
አጋጣሚዎች
ባልተጠበቀ
ሁኔታ
ተጨናግፈዋል
።መሰረታዊ
የስርአት
ለውጦችን
በተፈለገው
አቅጣጫ
ለመምራትና
ወደ
ሚፈለገው
ትክክለኛ
ግብ
ለማድረስ
ከፍተኛ
ዲሲፒሊንና
፣
ከግላዊና
ቡድናዊ
ጥቅም
ይልቅ
የሀገርን
ጥቅምን
ማስጠበቅንና
፣
በህብረተሰብ
ደረጃም
ከፍተኛ
ግንዛቤ
ድጋፍንና
ትብብርን
ይጠይቃል
።
በዚሁ ሁሉ ሂደት
ነው
እንግዲህ
የ66ቱ አብዮት
ለኢትዮጲያ
ትልቅ
እድልን
ይዞ
የመጣ
ቢሆንም
ለአብዮቱ
መጀመርም
ሆነ
መሳካት
ምንም
አስተዋፅኦን
ያላደረገው
ደርግ
ስልጣኑን
ጠቅልሎ
፣
የነበሩትን
ፓርቲዎች
አጥፍቶ
የወታደራዊ
የአምባገነን
ስርአትን
የመሰረተው
።
በአጠቃላይ ስናየው ከአክሱም ዘመነ መንግስት መውደቅ በኋላ እስከ 20ኛው ክፍለ
ዘመን
መጨረሻ
ድረስ
የነበረው
የኢትዮጲያ
ታሪክሲ ጠቃለል
፤
በአንድ
በኩል
ከውጪ
ወራሪዎችና
ቅኝ
ገዢዎች
ጋር
የተደረጉ
ትግሎችና
፣
በሌላ
በኩል
ደግሞ
በውስጥ
የነበሩት
አስተዳደሮች
የተዳከመውን
የማእከላዊ
መንግስት
መልሶ
የማቆም
ትግል
፣
ከዛ
በተፃራሪ
ደግሞ
ስልጣንን
በብቸኝነት
ጠቅልሎ
ለመያዝ
የሚደረግ
ጥረትና
ያንን
በመቃወም
ይደረጉ
በነበሩ
የእርስ
በእርስ
ጦርነቶች
የታጀበ
ነበር
ማለት
ይቻላል
።
ቀደም ባለው
ዘመን
የነበሩ
የኢትዮጲያ
ምሁራን
ኢትዮጲያ
የጃፓንን
ምሳሌ
በመከተል
ልታድግ
ትችላለች
የሚል
ሀሳብ
አቅርበው
የነበረ
ሲሆን
በሁለቱ
ሀገራት
መሀከል
ያለውን
መመሳሰል
በተለይም
ሁለቱም
የራሳቸውን
ባህል
መጠበቃቸውን፣
በቅኝ
ግዛት
አለመገዛታቸውንና
፣
ሁለቱም
የዘውዳዊ
ስርአትን
የሚከተሉ
መሆናቸውን
መሰረት
በማድረግ
ነበረ
።
ይሁን
እንጂ
ሁለቱ
ሀገራት
ከላይ
ሲታይ
ተመሳሳይ
ቢመስሉም
መሰረታዊ
የሆነ
ግን
ልዩነቶች
ነበሯቸው
።
ለምሳሌ
በጃፓን
ከሁለተኛው
የአለም
ጦርነት
በኋላ
የጃፓን
ንጉስ
በፖለቲካው
ውስጥ
ያለው
ቦታ
እጅግ
አናሳ
ከመሆኑ
የተነሳ
ምንም
አይነት
የፖለቲካ
ተፅእኖ
ያልነበረው
ሲሆን
፣ፖለቲካውንም
ይመራ
የነበረው
በህዝብ
በተመረጡ
ፖለቲከኞች
ነበረ
።
ይህ
በኢትዮጲያ
ከነበረው
ፊውዳላዊና
ፍፁማዊ
የዘውድ
አገዛዝ
በአያሌው
የተለየ
ነው
።ከዚህም
ሌላ
የጃፓን
መንግስት
ኢንዱስትሪዎችን
ይደጉምና
ያበረታታ
የነበረ
ሲሆን
ከምርምር
ጀምሮ
ኢንዱስትሪዎች
እንዲበረታቱ
ያልተቋረጠ
ጥረትን
በማድረጉ
መጨረሻ
ላይ
ጃፓን
በኢንዱትሪ
ራሷን
የቻለች
ሀገር
ልትሆን
በቅታለች
፣
ይህም
በኢትዮጲያ
ከነበረው
የጭሰኛ
ስርአት
በእጅጉ
የተለየ
ነው
በታሪክ
እንደሚታወቀው
ሁሉ
የጃፓን
ባለመሬቶች
ቀደም
ብለው
መሬታቸውን
ለህዝቡ
እንዳከፋፈሉም
ይታወቃል።
ይህ
ብቻም
ሳይሆን
መመሳሰሎች
እንዳሉ
ሆነው
የጎሉ
ልዩነቶች
ግን
ነበሩ
፣
ስለዚህ
የጃፓን
ተምሳሌትነት
(Role Model) ብዙም
ሊሰራ
አልቻለም
።