የአፍሪካ ቀንድ በአለም ላይ ካሉ አደገኛ ከሚባሉ
አካባቢዎች አንዱ ነው ። ለዚህም በአንደ መካከለኛው ምስራቅ በአለም ላይ ካሉ አደገኛ ከሚባሉ ቀጠናዎች አንዱ ነው ። ይህ ክልል በተደጋጋሚ በድርቅና እርሱንም ተከትሎ በረሀብ የሚጠቃ ሲሆን በአለም ላይ እጅግ ደሀ ከሚባሉ አካባቢዎችም ዋነኛ ነው ።
የአፍሪካ ቀንድ አገራት ላለባቸው ችግሮች ምንጭ በርካታ ምክንያቶች አሉ ። አንዳንዱ ችግር ከቅኝ አገዛዝ
ዘመን የወረሱት ሲሆን ፣ በአንፃሩ ደግሞ ሌሎች ደግሞ ክልሉ ራሱ ካለው ስልታዊ መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሳ የተከሰቱ ናቸው
። ለዚህም ስልታዊነቱ ለመካከለኛው ምስራቅ ያለው ቅርበት ፣ እንዲሁም የአለም የንግድ ዋነኛ መስመር የሆነው የቀይ ባህር ተዋሳኝ
መሆኑ ፣ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከሰሜን አፍሪካ ለጥቆ የአፍሪካ ቀንድን እጅግ አስፈላጊና ስልታዊ «ስትራቴጂክ» ያደርገዋል ።
ይህ
ብቻም ሳይሆን ለምእራባውያንም ሆነ በአረቡ አለም ሁነኛ ስልታዊ የሆነችው ግብፅ ህልውና የሆነው የናይል ወንዝም እሚነሳው ከዚሁ
ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ሲሆን ፣ ግብፅም በበኩሏ የራሷ የሆነ መሰረታዊ ህልውናዋ ከዚሁ ክልል ጋር የተያያዘ ነው ።
አንዳንዶቹ
የአፍሪካ ቀንዱ አገራት በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ሲኖሯቸው እንደ ኢትዮጲያና ኬንያና ዩጋንዳ ያሉት ፣ በአንፃሩ ደግሞ እንደ ደቡብ
ሱዳንና ሶማሊያ ያሉት ደግሞ በጎሳ ላይ የተመሰረተ ማህበረሰባዊ አወቃቀርን ይከተላሉ ።
በአፍሪካ ቀንድ ከተከሰቱ ዋና ዋና ሁነቶች መሀከል በኢትዮጲያ ውስጥ ለበርካታ አስርት አመታት ሲካሄድ የቆየው
ጦርነትና ማብቃትና ይህን ተከትሎም የኤርትራ ራሷን የቻለች አገር መሆን ፣ በሱዳንም እንዲሁ በሰሜንና በደቡብ ሱዳን መሀከል ሲደረግ የቆየው ጦርነት ማብቃትና እንዲሁም
ደቡብ ሱዳንም ራሷን የቻለች ሀገር ሆና መወለድ ፣ የክልሉን ጆኦ - ፖለቲካዊ አሰላለፍ ከለወጡ ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው ። ከዚህም
በተጨማሪ ቀድሞ የተረጋጋች ሀገር ሆና ከቅኝ አገአዛዝ ነፃ ከወጣች ወዲህ በአንፃራዊ ሰላም የኖረችው ኬንያ ባልተጠበቀ ሁኔታ ምርጫዎችን
ተከትሎ በእርስ በርስ ውዝግብ ውስጥ መግባት መጀመሯ ለአካባቢው አንደ ስጋትን የጨመረ ጉዳይ ነው ።
በአንፃሩ በእርስ በርስ ጦርነትና በአምባገነናዊ አገዛዝ ስር የነበሩት
ኢትዮጲያና ፣ ኡጋንዳ በተረጋጋ ሁኔታ ምጣኔ - ሀብቷን ማሳደግ መጀመራቸው ፣ ተጠቃሽ ከሆኑ የአፍሪካ ቀንድ ሁነቶች ዋነኞቹ ናቸው
። ይህ ክልል ለምጣኔ- ሀብት እድገት ትልቅ እምቅ አቅም ያለው ክልልም መሆኑ የታወቀ ነው ። በርካታ ወንዞችን አቅፎ የያዘና ለግብርና
አመቺ የሆነ አካባቢ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ደቡብ ሱዳን ያሉት የነዳጅ ሀብት ባለቤትም ጭምር ናቸው ።
የወደፊት እድገቱን በተመለከተ የማደግ እምቅ አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን ፣ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ካላቸውና ህዝባቸው እያደጉ ካሉ አገራትም ይገኙበታል ።
ይህም በመሆኑ የምእራባውያን ትኩረት በዚህ ክልል እያደገ የመጣ ሲሆን ፣ በተለይም በሶማሊያ የባህር ጠረፎች የተከሰተው የባህር ላይ ውንብድና ፣ አልቃኢዳን መሰል አክራሪዎች በአካባቢው ማቆጥቆጥ ሌላው የሀያላኑን ትኩረት እንዲስብ ሰበብ ሆኗል ።
የሀያላኑን ትኩረትን መሳቡ በአንድ በኩል አካባቢው አለም አቀፋዊ ትኩረትን እንዲያገኝ ሲያደርገው ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በሩቅ ያሉ ሀያልላን ጥቅማቸውን ለማስከበር በሚያደርጉት ድርጊት ለአካባቢው አለመረጋጋት የራሱን አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል ። የአሜሪካ በፓኪስታን ፣ በአፍጋኒስታንና በየመን መግባቷ አካባቢዎቹን ማተራመሱ እና መረጋጋት ማጣታቸው የታወቀ ሲሆን ፣ በድሮኖች (drons) አማካይነት አሜሪካ በአካባቢው የምትፈፅማቸው የአየር ጥቃቶች ለበርካታ ሲቪሎች መገደልና ለሀገራቱ የውስጥ ፖለቲካ አለመረጋጋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑም ይታወቃል ። ምስራቅ አፍሪካም ምእራባውያኑ በዚህ መንገድ የሚገቡ ከሆነ መረጋጋቱን የማጣት አደጋ ውስጥ ሊገባ ይችላል ።

No comments:
Post a Comment