Thursday, May 2, 2019

ሲግመንድ ፍሮይድ

ስለ ሳይኮሎጂ ሳስብ ተሎ ወደ አእምሮየ የሚመጣልኝ ታላቁ የቬንያ ሰው ሲግመንድ ፍሮይድ ነው። ፍሮይድ በሃያኛው ክፍለ ዘመን በአእምሮ ጥናት (Mind) ላይ ተፅእኖ ፈጣሪና አነጋጋሪ ከነበሩ ምሁራን አንዱ ነው። ይህ የሳይኮአናሊሲስ ጠቢብ እሱ ከነበረበት ዘመን ቀድሞ የሄደ ወይም የተሻገረ (transcend) ነው ። ሳይኮአናሊቲክ ቴራፒ የሚባል በንግግር የሚደረግ የአእምሮ ህክምና ይዞ ብቅ ሲል ብዙዎችን አስገርሟል ። ከማስገረሙም በላይ ብዙ ተከታዮች አፍርተዋል ። አብዛኛዎቹ የሳይኮሎጂ ሙሁራን የፍሮይድን ሀሳብ ሳይጠቅሱ ወይም እንደ ማጣቀሻነት ሳይጠቀሙ ማለፍ የተለመደ አይደለም።

ከሁሉም በላይ ድንቅ የተባለለት የፍሮይድ ሀሳቦች የወቅቱን የስነ ልቦና ሳይንስ ሳይቀር ተፅእኖ በመፍጠር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ነው ። ሌሎች የስነ ልቦና ተማራማሪዎች የሆነ ጥናትና ምርምር በሚያካሂዱበት ግዜ እንኳን ሳይቀር መሰረት የሚጥሉት በፍሮይድ ፅንስ ሃሳብ ነው።

ፍሮይድ በመሠረቱ ስለ ሰው ልጅ ሲገልፅ በአጭሩ እንዲህ ይላል " የሰው ልጆች ባህሪ የሚወሰነው በ Irrational force, unconscious motive, biological and instinctual drive ነው ፤ ይህንን ደግሞ ባሉት የ Psychosexual ደረጃዎች ቀስ በቀስ ያድጋል። ዋናው የፍሮይድና ተከታዮቹ የስነልቦና ማጠንጠኛ ዘዴ "Instinct " ነው። እዚህ ላይ ፍሮይድ አክሎም የሰው ልጅ የመጨረሻ ግብ ደስታን ማግኘት ነው ይላል ። According to Freud, all humans "strive after happiness; they want to become happy and remain so"

ሲግመንድ ፍሮይድ ስለሰው ልጅ ሰብእና የተረዳበት ከታካሚዎቹ ባገኘው ተመክሮ ፣ ከራሱ የህልም ትንታኔ፣ ካነበባቸው ብዙ መፅሐፍትና ካደረገው ጥልቅ ጥናትና ምርምር ነው።

የፍሮይድ በንግግር የሚደረግ የአእምሮ ህክምና ዘዴ ግብ to uncover repressed memories through free association and dream analysis " የታመቀ ትዝታን ማከም ብለው የሚቀራረብ ትርጉም ይኖረዋል ።" the therapy works by transforming what is unconscious in to what is conscious. እዚህ ላይ ሌላው ግቡ ኢጎ እንዲጠነክር በማድረግ ከሱፐር ኢጎ ጥገኝነት ነፃ ማውጣት ነው።

ሳይኮኣናሊታክ ፔራፒ ከሌሎች በንግግር የሚደረጉ የአእምሮ ህክምናዎች በተለየ መልኩ ውስብስብ ነው። ረዘም ያለ ስልጠና ይፈልጋል በስልጠናው ወቅት ሰልጣኙ የአናሊሲሱ አንዱ አካል ነው። ሳይኮኣናሊታክ ፔራፒ የሚሰለጥን ሰው ለራሱም አናላይዝ ይደረጋል። ☺

No comments:

Post a Comment