Monday, March 11, 2013

የአለም የፖለቲካና የምጣኔ- ሀብት አሰላለፍ መለዋወጥ



         በአጭሩ ሲገለፅ መንግስት ማለት ህግ ነው ዋናው ትልቁ የመንግስት ስራ በየትኛውም የዜጎች እንቅስቃሴ ውስጥ ህግና ስርአትን ማስፈን በመሆኑ ነው ነገር ግን መንግስት በምን አይነት መንገድ ስልጣኑን እንደሚጠቀምበት የዛን መንግስት ባህሪና አፈጣጠር ያሳያል ።ምጣኔ - ሀብቱንም በተመለከተም የመንግስት ሚና መቆጣርና ማበረታቻዎችን በማድረግ ላይ የተመሰረተ ነው ለምሳሌ አንደ ባለሀብት አንድ ፖሊስ የሚሰራውን ስራ አይሰራም ነገር ግን ልክ አንድ መንግስት ሲቀየር በውስጠ ታዋቂ የህጎች መለወጥ እንዳለም እንረዳለን ።አውሮፓውያን 11ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲጣጣሩበት የቆዩት የስልጣኔ ጉዳይ ከሶስትና አራት መቶ አመታት በኋላ ውጤት ማሳየትን በመጀመሩ 15ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ግን የአውሮፓ ህዳሴ ተጀምሮ ውጤትን መስጠት የጀመረው በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በማህበራዊ ሳይንስ በፖለቲካ ሳይንስ በህክምና በሳይንስ በስነ - ክዋክብት በኢንጂነሪንግ በመሳሰለው ሀይማኖታዊ ከሆኑ ጉዳዮች ውጪ ባሉ ዘርፎች አዳዲስ ውጤቶች ማስመዝገብ የጀመሩት


በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ አዲስመልክና ቅርፅን በመያዝ ላይ የሚገኝ የአለም የገናናነት አሰላለፍ አለ ይህም ከአስርና አስራ አምስት አመታት በኋላ በግልፅ ወቶ የሚታይ ሲሆን አሁን ግን ገና ቅርፅ በመያዝ ላይ ነው የሚገኘው ይኀውም በግርድፉ ሲገለፅ 500 አመታት የዘለቀው የምእራባውያን የበላይነት እየቀነሰ እስያውያን የምጣኔ - ሀብት ገናናነቱን ስፍራ በመረከብ ላይ መገኘት ነው።የምጣኔ - ሀብቱ ሚዛን ወደ እስያውያን እየተሸጋሸገ (Shift) ሲሆን እንዲሁም ቀድሞ ጨለማው አህጉር በመባል ይታወቅ የነበረው አፍሪካ ሳይቀር የእድገትና የስልጣኔ ጮራን በማየት በአለም መድረኮችም ላይ ሁነኛ ተፅእኖን ማሳረፍ እየጀመረ ነው

ለምሳሌ በአውሮፓ 2011 . ግሪክ፣ ጣሊያንና ስፔን ያሉት ሀገራት በእዳ ውስጥ ስትያዝ የአውሮፓ ሀገራት ብቻቸውን መወጣት ባቃታቸው ወቅት ፊታቸውን ወደ አሜሪካ ሳይሆን ወደ ቻይና ነበረ ያዞሩት ሳይውሉ ሳያድሩም ወደ ቻይና የልኡካን ቡድናቸውን ልከዋል ይህንንም አንዳንድ ተመልካቾች የአሜሪካ ስልጣኔ የበላይነት ማቆልቆሉንና በቻይና መተካቱን አመላካች ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል ነገር ግን በምጣኔ - ሀብት ማደግ ወይም ከፍተኛ የአገራዊ ምርት ባለቤት መሆን ብቻውን ከፍተኛ የስልጣኔ ደረጃ ላይ መድረስ ነው ወይ የሚለው አከራካሪ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም ምንም እንኳን ቻይና በጥቂት አመታት ውስጥ አከለም ግዙፉ ምጣኔ- ሀብት ባለቤት እንደምትሆን በርካታ የምጣኔ- ሀብት ባለሙያዎች እየተነበዩ ቢሆንም ቻይና በዲሞክራሲ ረገድ እንኳን ከአሜሪካ ከአፍሪካ አገራት ጋር እንኳን የማይወዳደር በአንድ ብቸኛ የኮሚኒስት ፓርቲ የምትገዛ ሀገር መሆኗ ይታወቃል በአንድ በኩል ምእራባውያንን ስጋት ውስጥ እየጨመራቸው  ያለውም ይሄው ሲሆን  በአለም የግዙፍ ምጣኔ ሀብት ባለቤት የሆነች ሀገር ዲሞክራሲ ከሌላት ከባድ የውስጥ ችግር ቢያጋጥማት ወይም ብትወድቅ የሷ ችግር ለአለም የሚተርፍ የከፋ መዘዝን ያስከትላል የሚል ስጋት አላቸው  


ቀደምት የሆኑ ስልጣኔዎች ብዙውን በወንዝ ዙሪያ አካባቢ ነው የሚመሰረቱት። ለምሳሌ የግብፆችን ስልጣኔ ብንወስድ በአባይ ወንዝ ዳርና ዳር ላይ ለም የሆነውን ግብርናና ለመኖሪያ አመቺ በሆነው አካባቢ ነው ተቋቋመው ግብፅ የአስዋንን ግድብ በሚሰሩበት ወቅት ዳርና ዳር የነበሩትን ቅርሶች ለማንሳት ተገደው የነበረ ሲሆን ቅርሶቹ እየተቆረጡ እንዲነሱ ተደርገዋል ።በአሁኑ ወቅት ግን በመሰራቱ አግባብ አልነበረም የሚል እምነት አላቸው። በመካከለኛውም ምስራቅ ብንወስድ የሜሶፖታሚያና የባቢሎን ስልጣኔዎች ተመሰረቱት በኤፍራጥስና በጤግሮስ ወንዝ ዙሪያ ነው

No comments:

Post a Comment