የካፒታሊዝም
ስርአት ከቀደምቶች ከብሉይ የምጣኔ - ህሀብት ፈላስፋዎችሁሉ በስርአቱ ውስጥ ያሉትን ተቃርኖዎች አስቀምጠዋል ። ዴቪድ ሪካርዶ ይህንን
ተቃርኖ የተረዳ ሲሆን ፣ ካርል ማርክስ በአንፃሩ ይህን ተቃርኖውንና በስርአቱ ውስጥ ያሉትን ተግዳሮቶቸን በዝርዘሮ ያስቀመጠ የብሉይ
የምጣኔ - ሀብት ፈላስፋ ነው ። የካፒታሊዝም ስርአት ሁለት ዋና ዋና ችግሮች ያሉበት ሲሆን በአንድ በኩል ራሱ ስርአቱ ያለበት
ውስጣዊ ተቃርኖዎች (Inherent Contradictions) ያሉት
ሲሆን ሌላው ደግሞ ከአስተዳደርና ከቁጥጥር እና ከአመራር ግድፈቶች የሚመነጩ ችግሮች የተጋለጠ መሆኑ ነው ። ለምሳሌ በ1930ዎቹ
የተከሰተው የምጣኔ - ሀብት ቀውስና በ2008 የተከሰቱት ቀውሶች ከስርአቱ ውስጣዊ ተቃርኖ የመነጩ ብቻ ሳይሆኑ በዋናነት የመንግስት
ተቋማት በአግባቡ ባለመቆጣጠራቸው የተፈጠረ ነው ፣ የላላ ቁጥጥር ፣ እና የፋይናንስ ተቋማት ከልክ ያለፈ ለትርፍ መስገብገብ የፈጠረው
ነው ።
ሌላው
ግን ከካፒታሊዝም ስርአት ውስጣዊ ተቃርኖ የሚመነጨው ዋናው ነገር የሀብት ክፍፍል መዛባት ነው ። እ.ኤ.አ. በ 2011 ጥቅምት
ላይ በአሜሪካን አገር የተደረገው ህዝባዊ ሰልፍም (Occupy Wall Street) በመባል የተጀመረውን ቀጥሎም ወደ ተቀረው አሜሪካ
የአለም ሀገራት ከተሞች የተስፋፋው የሚታወቀው ይህንን የኑሮ አለመመጣጠንና ብሎም የግብር ከፋዩ ገንዘብ እነኚህን የገንዘብ ቀውስ
እንዲከተል መነሾ የሆኑትን ኮርፖሬሽኖችና ባንኮችን ከኪሳራ ለማዳን በመዋሉ ነገር ግን የተጠበቀው ውጤት ሳይመጣ መቅረቱን ፣ ይባስ
ብሎም የስራ አጥነትና የዋጋ ንረትና የመሳሰሉ ሌሎች የኢኮኖሚ ችግሮች እየተባባሱ በመሄዳቸው ነው ። በዚያኛው ፅንፍ ደግሞ «Tea
Party» እንቅስቃሴ በመባል የሚታወቀው ደግሞ በቀኝ አክራሪዎች የሚመራ እና ከሰራተኞች እንቅስቃሴ ከሚባለው ከዎል ስትሪትን መቆጣጠር
(Occupy Wall Street) የሚባለው ጋር ተቃራኒ ነው ።
በርካታዎቹ
የአሜሪካን ኩባንያዎች በተለይም የፋብሪካ ስራዎችን ወደ ርካሽ ጉልበት ወዳለባቸው ሀገራት በማዛወራቸው ምክንያት ፣ በምእራብ ሀገራት
ያለውን የስራ እድል እያጠበበው ሄዷል ፣በተለይም የፋብሪካና የማምረት ስራዎች ። ለኩባንያዎቹ ግን ርካሽ ጉልበትና አነስተኛ ግብር
ወደሚከፈልበት ሀገር ስለሚሄዱ አትራፊ ቢሆንላቸውም ለአገራቱ ዜጎች ግን የስራና ለመንግስታቱም የገቢ ማጣትን አስከትሏል ።ይሁን
እንጂ አሜሪካ ይህንን የነፃ ገበያ መርህ በሁለትዮሽ ስምምነት ወደ ተጨማሪ ሌሎች የእስያ ሀገራት እንደ ደቡብ ኮርያና ጃፓን ወዳሉት
እያስፋፋች ሲሆን በተለይም ካላት ሰፊ መሬትና ብዙ የግብርና ምርቷ አንፃር በግብርና ምርት ሰፊ ገበያን እንደሚከፍትላት ይጠበቃል
።
ሌላው
ምክንያት የካፒታል መከማቸት በጥቂቶች እጅ እየገባ መሄድ ሲሆን ይህም የካፒታሊዝም እድገት እየቀጠለ በሄደ ቁጥር በጥቂት ኩባንያዎች
እጅ እየተከማቸ ይሄዳል ። ይሄም አብዛኛው ነባር የነበረውም ሀብት ጭምር በካፒታሊስቶች እጅ ተጠቅልሎ እየገባ ሲሄድ አዲስ የተፈጠረውም
ሀብትም ቢሆን በአብዛኛው ወደ ትላልቆቹ ኩባንያዎቹና ኮርፖሬሽኖች እጅ እየገባ ነው የሚሄደው ። ይሄ እንዳይሆን መንግስታት በተለያየ
መንገድ መታገል ሲኖርባቸው ፣ ከታክስ ስርአቱ ጀምሮየተለያዩ ፖሊሲዎችን በሚገባ መጠቀም አለባቸው ። ነገርግን ፖለቲከኞች በንግዱ
ሰዎች በቀላሉ እሚደለሉና ለኩባንያዎቹ ብቻ ተስማሚ የሆነ ፖሊሲን ካወጡ ውሎ አድሮ ኩባንያዎቹ በብዙሀኑ ህዝብ ኪሳራ የሚያተርፉ
እየሆኑ ይሄዳሉ ።
ነገር
ግን ካርል ማርክስ በአንድ በኩል ፣ አብዮት እንዲሳካ በትክክለኛው ጊዜና ሰአት መካሄድ ያለበት ሲሆን ይህ ትክክለኛ ጊዜ እንዴት
ይታወቃል ? በ1871 የተካሄደው የፓሪስ ኮሚዩን ምንም እንኳን ማርክስ ራሱ በህይወት እያለ የተካሄደና ተስፋ ጥሎበት የነበረ ቢሆንም
መክሸፉ ይታወቃል ። ሌላው ደግሞ አብዮቱ ከተደረገ በኋላ በአልተፈለጉ ሰዎች እጅ ድሉ ቢገባስ ይህ በተደጋጋሚ የሶሻሊስት አብዮት
አካሂደናል ባሉ ሀገራት የታየና አንዱ የኮሚኒዝም ስርአት በተሳሳተ መንገድ ስራ ላይ እንዲውል ምክንያት የሆነ እና ስርአቱ በብዙ
ሀገራት ውድቀት የተዳረገበት ምክንያት ይህው ትክክለኛ መሪዎችም ማግኘት አለመቻሉ ነው ። በሊበራል ዲሞክራሲ የሚመራው የካፒታሊዝም
ስርአት ራሱን ከሁኔታዎችና ከወቅቱ ጋር የማስማማትና የማዛመድ አቅሙን ማርክስ አሳንሶ ገምቷል ።
No comments:
Post a Comment