የ1965/66 እና የ1977
ረሀቦች መነሻቸው ድርቅ የነበሩ ሲሆን በሀገሪቱ ህዝብ ስነ - ልቦና ላይ እንዲሁም በሀገሪቱ ብሄራዊ አለም አቀፋዊ ገፅታ (National
Image) ላይ አሉታዊ ተፅእኗቸውን አሳርፈው አልፈዋል ። በተለይም በሀገሪቱ አለም አቀፋዊ ገፅታ ላይ ያስከተለው
አሉታዊ ተፅእኖ በቀላሉ እሚገመት ካለመሆኑም በላይ ይህንን ሙሉ በሙሉ ለመፋቅም ቀላል እንደማይሆን መገመት ይቻላል ። ረሀብ በኢትዮጲያ
ታሪክ ውስጥ ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም ካለፉት አርባ አመታት ወዲህ ግን ዋና አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል ። የመሬት ይዞታ ጉዳይ
ላይ በርካታ ክርክሮች ያሉ ሲሆን የመሬት ጉዳይ ተዘግቶለታል ለማለት ግን አያስደፍርም ። በ2003
/ 4 ዓ.
ም.
ከ60
አመታት ወዲህ ታይቶ የማይታወቅ ድርቅ ቢከሰትም ከ30 አመት በፊት የተከሰተው ሁኔታ ግን አልተደገመም ።
ድርቅ
መከሰቱ ተፈጥሯዊ ጉዳይ በመሆኑ ማስቀረት ባይቻልም በአሁኑ ወቅት ግን ይበልጥ በድርቅ ተጋላጭ የሆኑት አርብቶ አደሩ በብዛት እሚኖርባቸው አካባቢዎች ናቸው ። መንግስት ሰብአዊ ቀውስ እንዳይደርስ
ማድረግ ሲሆን ፣ በተለይም በአርብቶ አደር አካባቢ ያለው ህዝብ እንደ ቀድሞው በአርብቶ አደርነት ብቻ ኑሮውን መግፋት ሊያስቸግረው
ይችላል ። የህዝብ ብዛቱ እየጨመረ በመሆኑ ፣ በአለም ላይ እየተከሰተ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እንደ ቀድሞው ሳይሆን
በአሁኑ ወቅት የውሀና የዝናብ ምንጮች ፣የተፈጥሮ እፅዋት እየተመናመኑ በመምጣታቸው ተደጋጋሚ ድርቆች ሊገጥሙት እንደሚችሉ መገመት
ይቻላል ።
ይህንን
ችግር ለመቅረፍ አማራጭ የሆኑ ሌሎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች በአካባቢው መዘርጋት ሲኖርባቸው ፣ ከእነዚህም ውስጥአንድ ቦታ ሰፍሮ
ግብርና እንዲጀምር ማድረግ ፣ ለከብቶቹ በዘመናዊ መንገድ ህክምናና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እንዲጠቀም ማድረግ ፣ የተቀረውን ወደ ከተሞች
በመምጣት የስራ እድል መፍጠር እና የስራ እድሎችን እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል ። የውሀ ምንጮችን ማጎልበት ፣ የመስኖ እርሻን
ማስፋፋት አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው ። በተለይም የህዝብ ብዛቱ እየጨመረ ስለሚሄድ ይበልጥ ችግሩ እየተባባሰ ሊሄድ ይችላል ።ድርቅ
በቻይናም በአሜሪካም በአውስትራሊያም ሊከሰት የሚችል ሲሆን ።
ከ19ኛው
ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ አፄ ምንሊክ በነገሱበት ወቅትም ረሀብ ተከስቶ የነበረ ሲሆን ምክንያቱ ግን በወቅቱ ተከስቶ በነበረው የአባ
ሰንጋ አንትራክስ በሽታ ምክንያት የእርሻ በሬዎችና ከብቶች በማለቃቸው ምክንያት ነው ። ከዚያ በኋላም በእጅ እየተቆፈረ እየተዘራ
ችግሩ እየተቃለለ ሄዷል ።
ቀደም
ባሉት የኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ህትመቶች ረሀብ በሚለው ቃል ፍቺ ሲሰጥ የኢትዮጲያን ስም ያነሳ የነበረ ሲሆን ። ከዛ ቀደም ባሉ
የኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ህትመቶች ብንመለከት ረሀብ በሚለው ቃል ስር ትርጓሜውን ሲሰጥ ህንድን ምሳሌ ያደርግ ነበረ ። በእርግጥ
መዝገበ- ቃላቱ በእንደዛ አይነት ሁኔታ የአንድን ሀገር ስም ማንሳቱ የሀገራቱን ገፅታን ማበላሸቱ የታወቀ ሲሆን ህጋዊ ውዝግብም
ሊያስነሳበትም ይችላል ። ይሁን እንጂ መዝገበ - ቃላቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚያወጣቸው ህትመቶች የየትኛውንም የሀገር ስም አያነሳም።
No comments:
Post a Comment