የመቶ አመት የቤት ሥራ ስጥቻለሁኝ" ፦
ኢሱ - የኤርትራው ፕ/ት ፦
እውነትም ኢትዮፒያውያን በብሄር ልዩነት እየተባሉ ባለበት በዚህ ሰአት በኢኮኖሚም ሆነ በዲፕሎምሲ ከኢትዮፒያ የምታንሰው ኤርትራ የተሻለ አንድነትና ጥንካሬ ላይ ስትገኝ ኢትዮፒያውያን ግን የመቶ አመቱን የቤት ስራ እንኩዋን ሊጨርሱት ገና የጀመሩት ይመስላል። እርስ በእርስ የመከፋፈሉን የቤት ስራ ተግተው እየሰሩ ይመስላል ።
ኤርትራና አማራ ክልል ስትራቴጂክ አጋር። ( strategic parthner ) ሆነዋል ይባላል ፥ ምክንያቱም ያማራ ክልልን ግዛቶችን በሃይል ቆርጦ ወደ ራሱ ግዛት የቀላቀለው ወያኔ መሃል ላይ ስላለ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ይመስላል። ህወህት ምናልባት ሊተማመንባት የሚችላት ወዳጄ ሊላት የሚችለው ጎረቤት ሱዳንን ቢሆንም ከእርሱዋ ጋር ድንበርን ቀጥተኛ ወሰንን አይጋራም። ሱዳንም ብትሆን ከተሸነፈ ወይም እየተሸነፈ ካለ ማጣፊያው እያጠረበት ካለ ሃይል ጋር እምታብርበት የስትራቴጂ ምክንያት አይኖራትም። በህዳሴው ግድብ ዙርያ ከማእከላዊ ፌደራልና ካማራና ቤንሻንጉል ክልል ጋር እየሰራች ሲሆን ፥ ጎንደር ላይ በተደረገው ስብሰባ ላይ ሱዳን አልተጋበዘችም ። ሶማሊያ በተጋበዘችበት በዚህ ስብሰባ ቅርብ ጎረቤት ሱዳን አለመጋበዙዋ ዶ/ር አብይ ህወህትን ለመክብበና ወደ ፌደራል መንግስቱ ፍላጎት እንዲመጣ አስበው ይሆናል። ሱዳን ከጎንደር መሬት የወያኔ መሪዎች ቆርጠው ስለሰጡዋት ይህን መሬት ትመልስ ብለው ያማራ ክልል ህብረተሰብና የክልሉ መንግስት ስለጠየቀ ሱዳንን አቶ ኢሳያስና የሱማሌው ፕ/ት በተገኙበት መጋበዝ አላስፈለገም። ያም ሆነ ይህ ግን ዶ/ር አብይ ከፌደራል መንግስቱ ፍላጎት ውጭ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ወያኔንን ከበባ ውስጥ በማስገባት ይህን ስብሰባ ተጠቅመውበታል። እሺ እማይል ከሆነም ከበባ ቀለበት ውስጥ አስገባሃለሁ በሚል ሊሆን ይችላል።
"ዘላለማዊ ወዳጅም ሆነ ዘላለማዊ ጠላት የለም " ፦
ኮ/ል መንግስቱ በገነት አየለ ሲጠየቁ "ዘላለማዊ ወዳጅነትና ፥ ዘላለማዊ ጠላትነት የለም " ሲባል እውነት አይመስለኝም ብለው ነበረ። በሁዋላ ላይ ግን ይህ አባባል እውነት እንደሆነ እውነት እንደሆነ አወቅሁ ሲሉ አመኑ። ህወህትም ይህን መሰረታዊ እውነታ ኮ/ሉ በስልጣን ዘመናቸው እንዳልተረዱት ሁሉ ህወህትም በስልጣን ላይ እያለ ይህን እውነታ ስቶታል። እሁን ሊረዳው ይችል ይሆናል ፥ ከበባ ውስጥ ሥለገባ ።
No comments:
Post a Comment