ለባቢሎን ንጉስ የቀረብ ምልጃ ፦
ያለም ጭቁን ህዝቦች ፥
ያለም ዳኛና ፖሊስ እኔ ነኝ ፥
ወደሚለው የባቢሎን ንጉስ ዘንድ ፥
አቤቱታቸውን ይዘው ቀረቡ ፥
የአለም ፖሊስና ዳኛ እኔ ነኝ
ብልሃል አሉ።
"የአለም ፖሊስና ዳኛ ፥
አንተ ነህ ተብሎል ፥
ለዚህ ነው አቤቱታችንን
ወዳንት ይዘን የቀረብነው ፥ " አሉት።
እርሱም ጥያቄያቸውን በአንክሮ ፥
ካዳመጠ በሁዋላ ምላሹን ፥
እንደሚከተለው ሰጠ ፦
የባቢሎን ንጉስ የሰጠው ምላሽ ፦
እባቢሎን ንጉስ ዘንድ ሄደው ከሰሱት ፥
አንተ በላያችን ላይ የሾምክብን ገዢያችን ፥
ሰዋዊ መብታችንን አይጠብቅልንም ፥
ሲፈልግ ያስረናል ፥ ሲፈልግ ይገድለናል ፥
ሃብታችንና መሬታችንን ዘርፎ አዘረፈነ ፥
ያሻውን እያደረገብን ነው።
የአለም ፖሊስና ዳኛ እኔ ነኝ ፥
ብልሃል አሉ ለዚህም ነው ወዳንተ ፥
የመጣነው ሲሉ ክሳቸውን አሰሙ ፥
የባቢሎኑ ንጉስም ባለጉልላታም ከሆነውና ፥
ሃጫ በረዶ ከሚመስለው ቤተመንግስቱ ፥
ምላሽ ሊሰጥ ብቅ አለ።
እርሱም ዘውድ አለመድፋቱና ፥
በእጁ በትረ ሙሴን ካለመያዙ በስተቀረ ፥
ከፈርኦንና ከቄሳር የተለየ አልነበረም።
እርሱም ሲመልስ እንዲህ አለ ፦
እርግጥ ነው ያደረሰባችሁን በደል፥
ሰምቻለሁ ፥ አውቃለሁም ፤
ነገር ግን የኔን ጥቅም ለማስከበር፥
የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ፥
ለዚህ ነው ያደረገባችሁን አይቼ ፥
እንዳላየ የሆንኩት ሲል ፥
ጀነን ኮራ ብሎ ምላሽ ሰጠ።
እነርሳቸው የድሆች አገር ሰዎችም ፥
እያለቃቀሱ እንባቸውን ወደ ፥
ሰማይ እየፈነጠቁ ወደ የመጡበት ፥
ተበታተኑ።
No comments:
Post a Comment