Wednesday, November 14, 2018

የክሩስቸቭ ቀልዶች

ይህ እንግዲህ በየቴሌቭዥኑ ይሄ ሁሉ ጄኔራልና ኮሎኔል ሜቴክ እንደዚህ አድርጎ ፤ ጄኔራል ክንፈ እንዲህ ብሎ ሲሉ ፥ የት ነበሩ እኝህ ሁሉ ሰዎች አትሉም ጎበዝ። 

ይሄ ሁሉ ወፈ ሰማይ ጄኔራልና ኮሎኔልና የመንግስት ሹማምንት ሁላ በቲቪ እየቀረበ "ሜቴክ እንዲህ አድርጎ ፥ ክንፈ ዳኜ እንዲህ ብሎ " ፤ ጄኔራሉ በድፍረት ጨረታ አናደርግም ሲል እንኩዋን ለምን ያለ ጋዜጠኛ ኣልነበረም
ዋልታ ቴሌቭዥን ሜቴክ ላይ ሲወርድበት ሳይ አንድ የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ቀልድ ትዝ አለኝ ፦

የቅድሞዋ ሶቭየቱ አምባገነን ጆሴፍ ስታሊን እ.ኤ.አ በ53 ኣ.ም  ከሞተ በሁዋላ ፥ በእግሩ የተተካው ክሩስቼቭ በስብሰባ ላይ በስታሊን ዘመን የተፈጸሙትን ግፎችንና ወንጀሎችን ይዘረዝራል።

ከመሃከላቸው አንዱ " ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈጸም አንተ የት ነበርክ !! " አለው ድምጽን ከፍ አድርጎ።
ክሩስቼቭም የሰውየውን ማንነት መለየት ስላልቻለ እርሱም መልሶ "ማነው ይህን ያለው? " ሲል ጉባኤተኞቹን በተራው መልሶ ያፋጥጣል። በዚህ ግዜ ለክሩስችቭ መልስ እሚሰጥ ጠፋ ሁሉም ጸጥ ጭጭ አሉ ፥ ደፍሮ መልስ እሚሰጥ ጠፋ ፤ ከእነርሱ መሃል አንዳቸውም መልስ ለመስጠት አልደፈሩም ።

ከአፍታ ቆይታ በሁዋላ ........
ክሩስቼቭም እሚመልስ እንደሌለ ካየ በሁዋላ መልሶ " አያችሁ ያኔም እንደዚህ ነበር የሆነው " አላቸው።

No comments:

Post a Comment