Friday, November 23, 2018

ብሄራዊ መግባባት ለመድረስ የታሪክ ሂሳብን ማወራረድ ኣያስፈልግም" ፦

ሲሉ ፕ/ር መረራ ተናግረዋል ጎበዝ።

የታሪክን ሂሳብ ይወራረድ ቢባል እኮ መቼም ቢሆን ሂሳቡ ተወራርዶ ኣያልቅም ። የታሪክ ትርክትን ለወቅታዊ የፖለቲካ ክርክር ማድረግ በራሱ ምን ያኽል ተገቢ ነው ? ለምሳሌ ጥቁር ኣሜሪካውያን በነጮች የደረሰባቸውን በደል በየ4 ኣመቱ በሚደረግ ክርክር ደጋግመው ማንሳት እንደ ማለት ነው። በጭቅጭቅና ውዝግብ የተሞላ የታሪክ ትርክት ፥
(contested historical  narration ) ወይም
( distorted historical version ) የተዛባ የታሪክ ትርጉዋሜና ታሪካዊ ክስተቶች ስያሜ ባለበት ሁኔታ እንኩዋን የዛሬ መቶ ኣመቱን ትተን የዛሬ ኣስርና ሃያ ኣመት እንኩዋን ስንት በደልና ወንጀል ተፈጽሞአል ጎበዝ ።
ብሄራዊ መግባባትን ለማስፈን ከአዋቂዎች ይልቅ ታዳጊዎች ላይ መሰራት ኣለበት። ታዳጊዎችን ስራዎች ማስተማርና የማስረጽ (indoctrination ) መሰራት አለባቸው።

No comments:

Post a Comment