በአግባቡ ስሜቶቻችንን መግለፅ ለጤንነታችን አስፈላጊ ነው ። ለምሳሌ ከቁጥጥር ውጪ የወጣ ስሜት አደገኛ ሲሆን በአንፃሩ ግን በአግባቡ የተገለፀ ስሜት ግን ደስታንና ሰላምንና ሰላማዊ የሆነ ማህበራዊ
ግንኙነትን ይፈጥራል ። መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች ፍላጎቶች ማለትም ምግብ ፣ መጠለያ እና አየር ሲሆኑ ፣ ነገር ግን ሰላም እነኚህን መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ለማጣጣም አስፈላጊ ነው ። ነገር ግን ሰላም የሚሰፍነው ችግሮች ሲፈቱ ብቻ ነው ። ነገር ግን ስለ ጉዳዩ ወይም ስለችግሩ ባለማንሳት ፣ በማድበስበስ ችግሮች አይፈታም ። ነገሮች ወጥተው ግልፅ ውይይት ተደርጎባቸው ባለው ማንኛውም መንገድ ፣ ፍርድ ቤትም ጭምር ሄደው መፍትሄ ሲሰጣቸው ግድ ይላል ። ብዙውን ጊዜ ግን ስሜታችንን እንድንቆጣጠር እንመከራለን ፣ ነገር ግን ይሄ የሚሆነው አሉታዊ እና አፍራሽ የሆኑ ስሜቶችን ሲሆን ፣ በአንፃሩ ግን መጥፎ ነገር እየተደረገብን ወይንም የማንፈልገውን ነገር እያየን ያንን ነገር ዝም ብለን እንድንሸከም አይደለም ። ያለበለዚያ አፍኖ መቆየት በሽታን ብቻ ነው እሚያተርፍልን ።
ሆነም ቀረ ስሜቶቻችን ህልውናችንን የምናስቆይባቸው የስሜት መግለጫዎቻችን ናቸው ። ለምሳሌ የውሀ መጥማት ስሜት ሲሰማን ውሀ እንጠጣለን ፣ የረሀብ ስሜት ሲሰማን እንበላለን ወይም የምንበላው ነገር እንፈልጋለን ፣ ሌሎችም ደመነፍሳዊ የሆኑ ስሜቶቻችን እንደዛው ናቸው ።ነገር ግን ከልጅነታችን ጀምሮ በአብዛኛው ስሜቶቻችንን እንድንቆጣጠር ነው ሲነገረን የኖረው ፣ አሉታዊ ከሆኑ ስሜቶቻችንን መቆጣጠር አስፈላጊ ቢሆንም ግን በትክክል የተገለፀ ስሜት ጠቀሜታ አለው ። ለምሳሌ ወደ ውስጣችን ብዙ የማንፈልጋቸው ወይንም የማያስደስቱን ስሜትን ብንመጥና ያንን ባናወጣው ወይንም ወደ ውስጣችን የገባው ስሜት የምናስወጣበት መንገድ ከሌለ ፣ ያ በውስጣችን የሚንተከተከው ስሜት ውስጣችንን ይበላና ወደ ብስጭት ፣ ንዴትና ብሎም የጤና መዛባትን ያስከትላል ።
No comments:
Post a Comment