Thursday, April 4, 2013

የአለም የንግድ ስርአት


ለበርካታ ክፍለ ዘመናት የነበረው የአለም የንግድ ስርአት ከምእራባውያን ጥቅም ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ባልተጠበቀ ፍጥነት እየተቀየረ ይገኛል ። ላለፉት አምስት ክፍለ ዘመናት የቆየው የአለም የንግድ  ስርአት ለመጀመሪያ ጊዜ የአቅጣጫ እና የሽግሽግ ለውጥን ሲያደርግ የንግድ ሚዛኑም ወደ እስያ ፣ አፍሪካና ሌሎች ቀድሞ ታዳጊ ይባሉ ወደ ነበሩ አገራት እያዘነበለ ይገኛል ። ይህ ማለት ግን ምእራባውያን ሙሉ በሙሉ ያላቸውን የበላይነት ያጣሉ ማለት አይደለም ።

ምእራባውያን ያሏቸው «Strategic Advantages» በቀላሉ አያጧቸውም ። እንግሊዝ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት መሀከል ያላት መልከአ-ምድራዊ አቀማመጥ ወሳኝ በሆነ አቀማመጥ ላይ ነው ።  እንግሊዝ የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆነችው ካላት ወሳኝ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የተነሳ በራሷ ገንዘብ ብትገበያይ ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርገኛል በሚል ስሌት ነው ። አሜሪካንንም ብንወስድ በሁለት አቅጣጫ በአትላንቲክ ውስቅያኖስና በሰላማዊ ውቅያኖስ በኩል የባህር ተዋሳኝ ስትሆን በሁለቱም አቅጣጫ መነገድም ሆነ ጠላት ቢመጣ ያለምንም ችግር ራሷን መከላከል ያስችላታል ።

ሌላው የምእራባውያንን የበላይነት ጠብቆ ሊያቆይላቸው የሚችለው ነገር ፣ ያላቸው በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ኩባንያዎች እንደ ኮካኮላ፣ ማይክሮሶፍት ፣ ጎግል ፣ አፕል ፣ ያሆና የመሳሰሉ ቁሳቁስን ሳይሆን እውቀትን የሚሸጡ ኩባንያዎቻችቸው የአለም ገበያ እየሰፋ በሄደ ቁጥር ትርፋቸው እየናረና ተጠቃሚ እየሆኑ ይሄዳሉ እንጂ እየቀነሱ አይሄዱም ። 

ሌላው ምእሬውያን በእድገትና በምርምር ላይ ያላቸው ከፍተኛ የሚያፈሱት መዋእለ - ንዋይና አሁንም ድረስ ከታዳጊው አለም ወደነሱ የሚጎርፈው የሰው ሀይል ሌላው የበላይነታቸው ሚስጥር ነው ።

ከዚህም በተጨማሪ ምእራባውያን ለበርካታ ክፍለ ዘመናት እያዳበሩ የመጡት በዲሞክራሲ የበላይነት የሚመራው የመንግስት ስርአታቸው ሌላው የውስጣዊ ሰላማቸውና መረጋጋታቸው ሚስጥር ነው ። ጠንካራው የዲሞክራሲ ስርአታቸው የትኛውም ሀገር በምጣኔ-ሀብት ቢያድግ በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል አይደለም ። ህንድን ብንወስድ በሙስና የተዘፈቀ የዲሞክራሲ ስርአት ያላት ሲሆን ፤ በቻይና ግን የአሜሪካ ዲሞክራሲ አይነት አይታሰብም ። በእነኚህ ምክንያቶች በምእራባውያኑ የበላይነት የተያዘው የአለም የንግድ ስርአት፤በቀላሉ ይለወጣል ተብሎ አይታሰብም ። በተለይም ደሀዎቹ ሀገራት ከዚህ የአለም የንግድ ስርአት ተጎጂነታቸው ላልተወሰነ ጊዜ መቀጠሉ አይቀርም ።

ለምሳሌ ሐገራችንን ብንወስድ ለምታካሂዳቸው ግዙፍ ሜጋ ተብለው ለሚጠሩት ፕሮጀክቶቿ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በቀላሉ ማግኝ ባለመቻሏ ፣ በሀገር ውስጥ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሊፈጠር ችሏል ። በግብርና ምርቶች ከሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ላይ የተመሰረተው የሀገራችን ምጣኔ-ሀብት በአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት የአበባና የቡና ዋጋና ፍላጎት ሲወርድ በውጭ ምንዛሬ ገቢአችን ላይ ቀላል የማይባል አሉታዊ ተፅእኖን ሊፈጥር በቅቷል ።

No comments:

Post a Comment