በእስያውያን ምጣኔ-ሀብታቸው በዚህ ፍጥነት ያንሰራራል ተብሎ ተጠብቆ
አልነበረም ። ነገር ግን ካለፉት ከ1970 እና 80 ዎቹ ወዲህ ግን ምጣኔ-ሀብታቸውን በፍጥነት በማሳደግ ወዳ ልተጠበቀ የሀብት ፈጠራና
የምጣኔ - ሀብት እድገት አምርተዋል ። ይህ በእንደ አንድ በኩል ምእራባውያን መንግስታትን ሲያስደነግጥ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እነኚህ
ግዙፍ ህዝብ ያላቸው የእስያ ሀገራት ፣ ለምእራባውያን ግዙፍ ኮርፖሬሽኖች ተዝቆ የማያልቅ ገበያንና ርካሽ ምርቶችን የማምረት የሚያስችል
እድልን ፈጥሮላቸዋል ።
ምእራባውያን በተለይም የቻይና የምጣኔ-ሀብት እድገት የተምታታ ስሜትን ፈጥሮባቸዋል ። በአንድ በኩል ቻይና የመገበያያ ገንዘቧን ሆነ ብላ ዝቅ በማድረግ ምርቶቿን በርካሽ ለአለም ገበያ በማቅረብ የሌሎች አገራት ምርቶች በገበያው ላይ ተወዳዳሪ አንዳይሆኑ አድርጋለች ብለው ሲተቿት ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ይሄው የቻይና የገንዘብ ስርአት የንግድ ሚዛናችንን አዛብቷል ብለው ምእራውያን ቅሬታ ገብቷቸዋል ።
ምእራባውያን የቻይና ዲሞክራሲ አለመስፈኑ ያቺ አገር አንድ ውስጣዊ አለመረጋጋት ቢገጥማት ከባድ ችግር ሊገጥመን ይችላል ብለው ይሰጋሉ ።በአለም ላይ የግዙፍ ምጣኔ-ሀብት ባለቤት ለመሆን የበቃችው ቻይና ውስጣዊ ዲሞክራሲ የሌላትና ከአንድ ዲሞክራሲ ካላደገበት አፍሪካዊ አገር ያልተሻለ ሲሆን ዲሞክራሲዋ ፣ ይህም አንድ የፖለቲካ አለመረጋጋት ቢፈጠር በቻይና ሊከሰት የሚችለው የፖለቲካ ቀውስ በአለም ላይ የምጣኔ-ሀብት መናጋትን ሊያስከትል የሚችል ነው ።
ከዚህም በተጨማሪ ቻይና የፈረጠወመውን ክንዷንም ለማሳየትም ሆነ ለማንሳት የማትቦዝን ሐገር መሆኗ ሌላው የምእራባውያን ራስ ምታት ነው ። በደቡብ ምስራቅ ቻይና ባሉት የደሴቶች ይገባኛል ጥያቄ ጉዳይ ላይ ትናንሾቹ እኛም በበኩላችን ደሴቶቹ ይገባናል ባዮቹ ቬትናምና ፊሊፒንስ እና ሌሎቹም ቻይናን የሚቋቋም ወታደራዊ አቅም የሌላቸው አገራት የአሜሪካንን ጣልቃ ገብነት ለመጠየቅ ተገደዋል ።

No comments:
Post a Comment