Wednesday, April 24, 2013

ፍልስፍናዊ ጥያቄዎች



ምንድነው የሰው ልጅ መጨረሻው ? ሰው ተወለደ አደገ ጎለመሰ ኖረ አለፈ ይሄ ሁሉ መጨረሻው ምንድነው ?  የሰው ልጅ ኖረ ኖረ ሞተ ፣ ከዚያስ የመኖር አላማው ምንድነው ? ነፍስ አለ ወይስ የለም ? መንፈስስ ?


ማንኛውም ነገር የራሱ ጊዜና ቦታ አለው ለምሳሌ አንድ ነገር ምንም እንኳን ትክክል ባይሆንም ያለወቅቱ ብንቃወም ትክክል እንደማይሆነው ሁሉ ያንን ነገር ለመቃወምም ሆነ ለማውገዝ የራሱ የሆነ ጊዜና ቦታን ይጠይቃል ያለበለዚያ ግን ያለቦታውና ያለጊዜው መገኘት ይሆንብናል


ብዙሀኑ ሰዎች ከመኖር ይልቅ መሞትን ይፈራሉ  ነገር ግን ጥቂት ሰዎች ግን ከመሞት ይልቅ መኖርን ይፈራሉ እነኚህ ከአሁን ይልቅ ሁልግዜም ወደፊት የተሻለ ነገር ይመጣል ብለው የሚያስቡ ናቸው


በአገራችን አንድ ትክክል ያልሆነን ነገር ትክክል እንደሆነ፣ተገቢ ያልሆነን ነገር ተገቢ እንደሆነ አድርጎ ተቀብሎ የመኖር ልማድ አለ ይሄም ብዙ ችግራችን መፍትሄ ሳያገኝ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይና ባልተቋረጠ መከራና ችግር ለመኖራችን አንዱ ምክንያት ነው የረጅም ጊዜ መፍትሄን ማስፈንና የአጭር ጊዜ መፍትሄዎች ማስቀመጥ የተለያዩ ነገሮች መሆናቸውን መረዳት ይገባል


ሚዛናዊ የሆነ አስተሳሰብ እጅግ አስፈላጊ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ሰዎች ነባራዊውን እውነታ ቸል ብለው ወይንም አውቀው እንዳላወቁ ሆነው ነው የሚኖሩት በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ መታመም መሞት እና ሌሎችም ችግሮች ተዘንግተውና እንደሌሉ ተደርገው ነው


የምእራባውያን የፍልስፍና ሲጠቃለል ከጥንት ግሪካውያን ዘመን ጀምሮ በመንግስት ዙሪያ ሲሆን ሄግልም ቢሆን ዜጎች ለመንግስት መታዘዝ አለባቸው ይላል ነገር ግን መሪውን የሚመራው መንፈስ ነው ከተባለ በውስጠ ታዋቂ መሪው ከፍተኛ እውቀት ያለው ትክክለኛና እማይሳሳት መሆን አለበት ማለት ነው ከጥንት ጀምሮ ከግሪካውያኑ ጀምሮ ሁሉም የምእራባውያን ፍልስፍናዎች በመንግስት ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው ይሁን እንጂ የምእራባውያን ፍልስፍና አለምን በማተራመሱም ይታወቃል በተለይም ምእራባውያን በአለም ላይ በርካታ ጦርነቶችን አካሂደዋል  በርካታ የጦርነት ስትራቴጂዎችም ከምእራቡ አለም የፈለቁ ናቸው የቻይናውን ሱን ዙን ሳይጨምር ለዚህ አይነተተኛ ምሳሌ የሚሆነው የማርክሲዝም - ሌኒኒዝም ፍልስፍና ሲሆን ይህ ፍልስፍና በተዋወቀባቸው የአለም አካባቢዎች በርካታ ቀውሶችንና ጦርነቶችን አስነስቷል

ለምሳሌ ስፒኖዛ የተባለውን ፈላስፋ ብንወስድ ሂሳባዊና ጂኦሜትሪያዊ ቀመሮችን በመጠቀም ፍልስፍናውን ያሰፈረ ሲሆን እጅግ አስደናቂ ችሎታውን አሳይቷል

ሌላው የምእራቡ አለም ፍልስፍና መገለጫ ቁሳዊ ሀብትን መፍጠር ላይ ማተኮሩ ነው በእርግጥ ቁሳዊ ነገርን መፍጠር ቀላል ነገር አይደለም ለምሳሌ እንሰሳትን ብንወስድ ቁሳዊ የሆነ ነገርን መፍጠር በፍፁም የማይችሉ ሲሆን እፅዋት በተፈጥሮ የሚያድጉ ሲሆን እንሰሳትም ምግባቸውን ለመፈለግ አደን ቢያድኑ እንኳን ደመ-ነፍሳዊ ነው ስለዚህ የሰው ልጅ ብቻ ግን የሚያደርገውን ነገር አመዛዝኖና አስተውሎ ማድረግ የሚችለው ስለዚህ ቁሳዊ ነገርን ለመፍጠር መጀመሪያ ማሰብን ሲጠይቅ ቀጥሎም ያንን ሀሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥ እንቅስቃሴን ማድረግ ፣መውጣት መውድ እና መስራትን ይጠይቃል ስለዚህ በዚህ በኩል ቀላል አለመሆኑን መረዳት ይቻላል

በአንፃሩ የምስራቆቹ በመንፈሳዊነት ላይ የሚያተኩር ነው ለዚህም አይነተኛው የቲቤትን ቡድሂዝምን ብንወስድ እጅግ መንፈሳዊ ከመሆኑ የተነሳ ራሳቸው ቲቤታዊያን ራሳቸውን ለመከላከል ምንም አይነት የጦርነት ዝግጅት አልነበራቸውም በዚህም ምክንያት በቀላሉ በቻይና ወታደራዊ ቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል በአንፃሩ የጃፓናውያንን ዜን ቡድሂዝምን ብንወስድ ደግሞ በጃፓን ባህል ጦርነት መዋጋትና ማሸነፍ እንደ አንድ ባህል  አድርገው የሚወስዱት ሲሆን   ጃፓኖች በታሪክ እንደ ጦረኛ ህዝብ የሚቆጠሩ ናቸው ምስራቃውያን ያን ያህል እንደ ቲቤት ቡድሂስቶች የባሰ መንፈሳዊና አለምን የዘነጋ ግን የለም ማለት ይቻላል አይሁዳውያንንም ብንወስድ እጅግ መንፈሳዊ በመሆን ራሳቸውን ለመከላከል ትኩረትን ስለማያደርጉ በተደጋጋሚ በውጭ ወራሪዎች ይወረሩና በውጭ ሀይሎች ቤተ - መቅደሶቻቸው ይዘረፉና የፈራርሱባቸው ነበረ

 
አይሁዳውያን በምእራቡ አለም የረቀቁ መንፈሳውያን ህዝቦች ናቸው በመፅሀፍ ቅዱስን ብንወስድ ነቢያቶች ሀዋርያቶች እንዲሁም ባለራእዮች በርካቶቹ አይሀዳውያን ናቸው ማለት ይቻላል በመንፈሳዊነት ህንዳውያን የላቁ ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ከአይሀዳውያንም የላቁ ሆነው ይታያሉ በተለይም ቡድሀን ብንወስድ በጣም ታላቅ ሰው እንደነበረ የሚነገርለት ሰው ነው ምናልባትም በዚህች ምድር ተፈጥረው በዚህች ምድር ላይ ከተራመዱ ጥቂት ታላላቅ ሰዎች አንዱ ነው ማለት ይቻላል

እጅግ አክራሪ የኦርቶዶክስ አይሀድ በመባል የሚታወቁት ፣እኛ ጊዜያችንንም ሆነ  ጉልበታችንን ለመንፈሳዊ መፅሀፍትን በማንበብና መንፈሳዊ ተግባራትን በመፈፀም ማሳለፍ አለብን እንጂ በወታደራዊ ግዳጅ ውስጥ መመልመል የለብንም የሚል አቋምን አንፀባርቀል በዚህም አክራሪ የሆኑ የአይሁድ ፓርቲዎች ይህንን በመደገፍና በወታደርነት እንዲመለመሉ የሚያዘውን የቤንያሚን ኔታንያሁን የመንግስትን ትእዛዝ በመቃወም ከጥምር መንግስት ውስጥ ለመውጣት መዛታቸው አንዳንዶቹም  መውጣታቸው ይታወቃል ይህም መንፈሳዊነት ላይ ትኩረትን ሲያደርጉ አለማዊ ለሆኑ ነገሮች ትኩረትን መንፈግን የሚጣያሳይ ሲሆን አደገኛ በሆነችው አለማችን ውስጥ በተደጋጋሚ በታሪክ እንደታየው ትኩረታቸውን በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ካተኮሩ በተለያዩ ዘርፎች ፈተናና ተግዳሮት ገጥማቸው መቋቋም እንደማይችሉ ይታወቃል


የምእራባውያን ፍልስፍና አንዱ አንዱን በበላይነት ለማስፈን ማድረግ ሲሆን የምስራቃውያን ፍልስፍና ግን በመስተጋብር ወይም (Harmony) ላይ የተመሰረተ ነው ነገር ግን አንዱ አንዱን የሚጫንበት ፍልስፍና ግን ውሎ አድሮ ተቀባይነቱ እየቀነሰ የሚሄድ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ አንዱ በአንዱ ላይ የሚያደርገው ጫና ውሎ አድሮ እየታወቀ ስለሚሄድና ተቀባይነቱንም እየቀነሰ እንዲሄድ ስለሚያደርግ ነው


የምስራቃውያኑም ቢሆን እንደ ምእራቡ አለም ግልፅ በሆነ ወታደራዊ የበላይነት ላይ ብቻ ሳይሆን ረቀቅ ባለው በባህላዊ የበላይነትም የተመሰረተ ነው በተለይ ቻይናውያን እንደ ምእራባውያን በወታደራዊ የበላይነት ብቻ ሳይሆን ረቀቅ ባለ መልኩ የባህል የበላይነት ላይ ጭምር የተመሰረተ ነው ምስራቃውያን ምንም እንኳን ታዛዥና የሚስማሙ መስለው ቢታዩም በተግባር ግን የራሳቸውን አስተሳሰብንም ሆነ ባህልና አቋም አይለውጡም ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው እጅግ ስኬታማ በሆነ መንገድ ሩቅ ምስራቃውያን ከጃፓናውያን ጀምሮ የምእራቡን ሳይንስና ቴክኖሎጂን በመገልበጥ ከራሳቸው ከፈጣሪዎቹ ከምእራባውያን ልቀው መገኘት ችለዋል


ቅናት የታጠረው ሰው ሌላው ሰው ለሱ ብሎ የሚኖር ሲመስለው እሱም ለሌሎች ብሎ የሚኖር ይመስለዋል ከንሂሊዝም ጋር ይመሳሰላል ቅናት አደገኛም ሊሆን ይችላል በእርግጥ ቅናት አንዱ ጠላትን የመታገያ ስልትም እንደሆነ ይታወቃል አንድ ሰው እሚቀናበትን ወይም እንዲሳካለት የማይፈልገውን ሰው በቅናት አይን በመመልከት ስኬታማ እንዳይሆን ወይንም በሌሎች ሰዎች ዘንድ ቀሎ እንዲታይ እና ተደማጭነትን እንዳያገኝ ሆን ተብሎ የሚደረግ አንዱ ተቃናቃኝን የማቃለያ መንገድ ነው አንድ ሰው ከሌሎች የበለጠ አንድ ነገር ካለው ለምሳሌ ሀብት ወይም እውቀት ወይንም ማንኛወም ከሌሎች የላቀ ነገር ባለቤት የሆነ ሰው የቅናት ሰለባ የመሆን እድሉ ሰፊ ነው

የዚህ አይነት ሰው ከሌሎች የማያስደስተውን ነገር በተደጋጋሚ ሲመለከት ነገር ለምን በእርሱ ላይ እንደሚሆን ይገርመው ይሆናል ብዙውን ብዙ ጊዜ ሰዎች ባያምኑትም ቅናት ምቀኝነትና ንዴት የብዙ ሰዎች በሰዎች ውስጥ ተቀብሮ ያሉ ስሜቶች ናቸው ስሜትን መቆጣጠር ማለት ንዴትን ብቻ ሳይሆን የቅናት ስሜትን ጭምር መቆጣጠርን ይጨምራል ቅናትን ከአረም ጋር የሚያመሳስሉት አሉ አንድ ሰው ለደህናዎቹ ተክሎች ውሀን እንደሚያጠጣቸው ሁሉ አረሞችም አብረው ውሀውን እየጠጡ ያድጋሉ ስለዚህ አረሞቹ ውሀውን እንዳይጠጡ ማድረግ ቅናትን ማለትም አረሙን ማጥፋት የራሱ የሰውየው ሀላፊነት ይሆናል

አመፃ በሁለት መንገድ የሚገለፅ ሲሆን አንዱ ለሌሎች በማይመች ሁኔታ አንድን ነገር እንዲቀጥል ስርአቱን እንዲቀጥል ማስደረግ ሲሆን ሌላው ደግሞ ስርአቱ እንዳይሰራ ማድረግ መስራት እንዳይችልማድረግ ነው እነኚህ ስርአቱ ወደሚፈለገው አይነት እስከሚስተካከል ድረስ እንደ የስራ ማቆም አድማዎች ሲቪል ዲስ ኦቢፊየንስ የመሳሰሉት ስርአቶችን የማሰናከል ሲሆን የበለጠ ውጤታማ  የበለጠ ውጤታማ የሆነው ይኀው ነው ለምሳሌ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው የጋንዲ በእንግሊዞች ላይ ያደረገው ትግል የእንግሊዝ የቅኝ አገዛዝ በህንድ እንዳይሰራ ማድረግ ነው


ብዙ ጊዜ በሰዎች መሀከል አንድነትን መፍጠር የሚችሉት በጣም ታላላቅ የሆኑ ወይንም በጣም መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች እንደ ነፃነትና የእኩልነት ጥያቄዎች የመሳሰሉት ሲሆኑ እነሱም የሚፈጥሩት አንድነት ከድል በኋላ ዘላቂ አይሆኑም። እውነተኛው ነፃነት ውስጣዊ ነፃነት ነው ይሉ ምስራቃዉያን  በምእራቡም ቢሆን እውነተኛው በነፃነት ያለው በግለሰባዊነት ውስጥ እንደሆነ እና የአንድ ሰው (ዩኒክ) እሚያደርገው ነገር ከሌሎች ሰዎች የሚለው ነገር እንዲሁም የራሱ የሰው የሆነ አቅምን ፤ያ ማለት ግን ማህበረሰቡ በሰላም እንዲኖር የሚያስችሉ ህጋግጋትና ደንቦች ለጋራ ማህበረሰባዊ ደህንነት መሰረት መሆናቸው እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ውጫዊ የሆኑ ነፃነቶች ማለትም በህግ መብት መከበር በህግ በፊት እኩል መሆን የመሳሰሉት ውጫዊ ከሆኑ ህግ ለማንኛውም ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ የሚያጎናፅፋቸው ነገሮች ናቸው

 
አመፃን አለመጠቀም የሚሰራው ያኛው ወገን ያንን ለመረዳት የሚያስችለው ህሊና ተጨባጭ ሁኔታዎች ካሉ ብቻ ሲሆን እነኚህ ሁኔታዎች በሌሉበት ሁኔታ ግን አመፃ ያለመኖር ምን ያህል እንደሚሰራ አጠራጣሪ ሊሆን ይችላል በተለይም ግዴለሽ በሆነ ሁኔታ አመፅን የሚጠቀም ከሆነ አንደኛው ወገን ነገር ግን ሌላኛው ወገን ይህንን የማያደርግ ከሆነ ጊዜያዊ ድልም እንኳን ቢሆን አመፅን የሚጠቀመው ሊያገኝ የሚችልበት እድል ይኖረዋል