Wednesday, April 24, 2013

ጥበብ እና ፍልስፍና



ስኬታማ ለሆነ ኑሮ ተግባራዊ የሆነ የህይወት ልምድ ያስፈልጋል በተለይም በርካታ ችግሮችን ያሳለፈ ሰው ችግሮች አስቀድመው ሊፈጠሩ ሲሉ አስቀድሞ ማየት ይችላል በአለም ላይ አይሁዳውያን በርካታ ችግሮችን አሳልፈዋል ከትምህርትና በማንበብ እውቀትን ከመሰብሰብ ውጪ አንድ ሰው በህይወት ውስጥ ተሳታፊና በመሆን የህይወት ልምድን ሊቀስም ይችላል ብዙ ጊዜ ሰዎች አንድን ነገር ከላይ የሚያዩትን ነገር እውነት አድርገው ነው እሚቀበሉት ሆኖም ግን ወደ ውስጥ ሲገባና ከላይ ሲታይ የተለያየ መሆኑን አይረዱም
አለማወቅ ራሱ ሰዎች ደስተኛ ሆነው እንዲኖሩ የሚያስችል ነገር ሲሆን ከተማሩ ሰዎች ይልቅ ያልተማሩ ሰዎች ደስተኛ ሆነው እሚገኙበት ጊዜ አለ እውቀት ብዙውን ጊዜ ትስስርን ስለሚፈጥር የሰዎችን ደስታ ይቀንሳል
በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ልሂቃን የሚባለው የህብረተሰብ ክፍል የሚሆኑት ሰዎች ለመምራት የሚያስፈልገውን እውቀትን የሰበሰቡና ተግባር ላይ የሚያውሉ ናቸው ብዙሀኑ ህብረተሰብ ክፍል ይህንን እውቀት ሊያሰባስብ ሳይችል ሲቀር ጥቂቶች ግን የሄን ማድረግ የቻሉ ግን በማህበረሱ ላይ ከፍ ያለ ቦታን ይይዛሉ
የሰው ልጅ ጥረት ለራሱ ያለውን የእኔነት ስሜት (Ego) ማርካት ነው ሰዎች ትልቅ ስልጣንን ብዙ ሀብትን በማግኘት ወይም ባለቤት በመሆን ራሳቸውን ትልቅ በሚሉት ቦታ በማዋል ለራሳቸው ያላቸውን አመለካከት ለማርካትና ስሜታቸውን ለማስደሰት ይመጥራሉ ነገር ግን እነኚህ ሁሉ ነገሮች በጊዜ ሲያልፉ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በነው ሲጠፉ ሊያዩም ይችላሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ በጣም ሲቆለማመጡ (Flatter) ሲደረጉ ይቀበላሉ ይህም ላላቸው ቦታ ሌሎች ሰዎች እንዲቀበሏቸው ከመፈለጋቸው የተሳ ብዙውን ግዜ በስልጣንና በሀብት ያሉ ሰዎች ይህንን ይፈልጉታል ለዚህም ምክንያቱ የሌሎች ሰዎችን ተቀባይነትን ለማግኘት ካላቸው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ነው
አንዳንዴ ሲታሰብ ማንኛውም ነገር በሚያልፍበትና በሚረሳበት አለም ለነገሮች ያን ያህል ክብደት መስጠት አስፈላጊ አይደለም ያስብላል ለምሳሌ ዛሬ በጣም ትልቅ ቦታን የምንሰጠው ነገር ነገ ከነገ ወዲያ የሚረሳና ብሎም የሚወገዝ ሁሉ ሊሆን ይችላል ዛሬ እውነት ነው ትክክል ነው የምንለው ነገ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ውሸት ነው ሊባል ይችላል ብዙ ሰዎች ግን ዛሬ እውነት ነው ትክክል ነው ለሚሉት ነገር ሊሞቱለትና ለገድሉለት ዝግጁዎች ናቸው ይሁን እንጂ ነገር ፍፁም ትክክል ስለመሆኑ በበቂ የሚያውቁት ነገር የለም፣ ወይም ዛሬ ትክክል ነው ቢባልም ነገ ከነገ ወዲያ ጥፋት ሆኖ ሊገኝ ይችላል በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚ የታየ ሀቅ ሲሆን ስፒኖዛ  የተባለው ታላቁ የሆላንድ ፈላስፋ በተደጋጋሚ የሚጠቀስለት አባባል እንዳለው «እውነት የራሷም የሀሰትም ማስረጃ  ነች» ብሏል
አንዳንድ ሰዎች በተቋም ደረጃ ሊሆኑ ይችላሉ በራሳቸው በችሎታቸው በስብእናቸው እና በአቅማቸው እንደ አንድ ተቋም ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች አሉ በአብዛኛው ሰዎች ቁሳዊ ነገርን በመፍጠር በኩል ነው የህይወታችንን አብዛኛውን ዘመን የምናሳልፈው ማለት ይቻላል የአብዛኛው ሰዎች ጥረትም በዚሁ ዘርፍ ሲሆን   ነገር ግን ቁሳዊ ነገርን ከመፍጠር አልፈው ለሰው ልጅ ብርሀንን የቀደዱ ለሌላው ብርሀን የሆኑ ሰዎች በመቶዎች ከሚቆጠሩ አመታት ውስጥ በጣት የሚቆጠሩ የዛ አይነት ሰዎች ናቸው የሚገኙት ቢባል ማጋነን አይሆንም
ማንኛውም በተፈጥሮ ሲሆን በሰዎች የተፈጠረ ነገር በሰዎች በቀላሉ ሊፈርስ ይችላል ለምሳሌ ሀገርን ብንወስድ በሰዎች የተፈጠረ ነገር ሲሆን ተፈጥሮ አህጉራትን ሲፈጥር ሰዎች ደግሞ አህጉሩን ተከፋፍለው ከዚህ እስከዚህ ድረስ ያንተ ከዚህ መልስ የኔ ብለው ነው ሀገር የምንለው ነገር የተፈጠረው ስለዚህ ይሁን እንጂ ሀገር ማለት ደግሞ የዛ ሀገር ዜጎች የመኖር ህልውና መሆኑ ደግሞ እማይዘነጋ እውነታ ነው በአለም ላይ ሀገር የሌላቸው ሰዎች ምን ያህል እንደሚሰቃዩ ሁላችንም የምናውቀው ሲሆን ያለሀገር የአንድ ሰው ህልውና አይታሰብም ይሁን እንጂ ሀገርን ላፍርስ ብሎ አንድ ሰው ቢነሳ ደግሞ ሊያደርግ የሚችለው ጉዳት ቀላል አይሆንም ሀሳቡ ባይሳካም እንኳን
ፍልስፍና በሁለት ዋና ዋና አቅጣጫዎች ሊታይ ይችላል በአንድ በኩል ተቋማትን መንግስትን ሀይማኖትን ከቤተሰብ ጀምሮ ያሉ ተቋማትን በመገንባትና በእነዛ ተቋማት አማካይነት የሰው ልጅ እዚህ ደረጃ ደርሷል ነገር በግን እነዚህ ተቋማት ባይኖሩ ኖሮ የሰው ልጅ ስልጣኔ፣ የቴልክኖሎጂ ግስጋሴና እመርታ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ አይችልም የነበረ ሲሆን በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ሰዎች በየትኛውም ትውልድና ሀገር ውስጥ ይገኛሉ ነገር ግን እውቀትን ለማሰባሰብ አዳዲስ ነገሮቸን ለመፍጠር ሰዎች በጋራ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የተሻለ ውጤትን ይሰጣል አንዱ አይነት አካሄድ አለምን እንደዚህ ነች ብሎ መግለፅና በሌላ በኩል ደግሞ አለም እንደዚህ መምሰል አለባት ወይንም እንደዚህ መሆን አለባት የሚል ነው ለምሳሌ ፕሌቶ «የኔ ማስወታወሻ በመጪዎቹ ትውልዶች ውስጥ የሚኖረኝ የባለውለታነት ሰሜት ነው» ብሏል
(ዮሴፍቢ፤የኢትዮጵያናየአፍሪካፈላስፋዎች፣2001..) በፃፈው መፅሀፍ ላይ እንዲህ ብሏል ፡-
መፈላሰፍ፡- ሁለንተናዊ ተሞክሮ ያምሆነይህእኔየምለውየአንድሕዝብፍልስፍናያንንፍልስፍናከሚያቀነቅኑትየከፍተኛትምህርትተቋምተመራማሪዎችጋርጥቂትወይምምንምዓይነትግንኙነትየለውምነው፡፡መፈላሰፍሁለንተናዊወይምዓለምአቀፋዊተሞክሮነው፡፡እያንዳንዱባህልየራሱየሆነአመለካከትአለው፡፡የፍልስፍናታሪክካጠናችሁየምትገነዘቡትነገርቢኖርየፍልስፍናንትርጉምበተመለከተምንምዓይነትስምምነትእንደሌለነው፡፡አንዳንዶቹፍልስፍናየእውቀትፍቅርነውይላሉ፡፡ሌሎችደግሞእውነትንመፈለግነውይላሉ፡፡የተቀሩትደግሞየመደነቅስሜትነውይላሉ፡፡በአጠቃላይፍልስፍናንበተመለከተየተደረሰበትስምምነትቢኖርበዙርያችንባለውዓለምውስጥበተለያዩክስተቶችአንፃርሥርዓትንለማስፈንመሞከሩነው፡፡እነዚህየተለያዩክስተቶችምንድናቸው? ነገሮች፣ድርጊቶች፣ክንዋኔዎች፣ልንረዳውየምንችለውዓለም፣ሥነምግባራዊዓለምእንዲሁምሜታፊዚካዊውዓለምናቸው፡፡

ፍልስፍና ስለ ሰው የሚያወራ እንደመሆኑ የሰውን ልጅ ስነ - ልቦናን ማወቅ ለፍልስፍና መሰረት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም የፍልስፍና ዋና አላማው ምንድነው ቢባል ከላይ እንደተጠቀሰው ስርአትን ማስፈን ነው ይህንንም ስነ - ምግባርን በማስረፅ ይሆናል ሀሳዊ - ፍልስፍና (Pseudo-Philosophy) በመባል የሚታወቅ ፍልስፍናም አለ ነገር ግን ይሄ ፍልስፍና ሃሳዊ በመሆኑ ብዙም አያዛልቅም ።ዋናው የፍልስፍና አላማ ሰዎችን በሰለማዊና ፍትሀዊ በሆነ ህብረተሰብ ውስጥ እንዲኖሩ ማስቻል ነው ለምሳሌ ታላላቅ ሀይማኖቶችን ብንወስድ ዋናው አላማቸው የሰው ልጅ እርስ በእርሱ እንዳይበጣበጥ ፍትህ እንዳይዛባ በማድረግ ላይ የተመሰረተ ነው ይሄም ፍትህ ባይኖር ሰላም ባይሰፍን ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ውድመት ጦርነትን በመፍራትና ከመምጣቱ በፊት ለማስቀረት ነው
የፍልስፍና መሰረታዊ ጥያቄ የሚባሉት ውስጥ አንዳንዶቹን ብንጠቅስ ቁስ አካል ነው ወይስ መንፈስ (Idea) ነው እሚቀድመው? በዚህ ህዋው ውስጥ ከሰው ልጅ ሌላ ህይወት ያለው ህሊና (Conscious) ያለው ፍጡር አለን? የህይወት ትርጉም ምንድነው ? ነፍስ ወይም መንፈስ አለን ካለስ በምን መንገድ ነው ያለው ? የሰው ልጅ ለምን ይሰቃያል? የመሳሰሉት መሰረታዊ የፍልስፍና ጥያቄዎች ሲሆኑ እስካሁን ድረስም የሰው ልጅ ባለው ቴክኖሎጂና በደረሰበት ሳይንስ ቁልጭ ያለ መልስ የተሰጠባቸው አይደሉም ለምሳሌ የአሜሪካውን የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳን ብንወስድ ከአሜሪካ ግብር ከፋዮች በሚሰበሰብ ገንዘብ በርካታ ምርምሮችን በማድረግ የሰው ልጅ ስለጠፈር ያለውን እውቀት አሳድጎታል ቀድሞ ዝንባሌውና ችሎታው ያላቸው ሰዎች ቀደምት ሳይንቶስቶች በመነሳት እንደ እነ ጋሊሊዮ ኮፐርኒከስ የመሳሰሉት በግላቸው ምርምርን፣ ጥረትና ስራ በርካታ ፈር - ቀዳጅ ስራዎችን አበርክተዋል ነገር ግን አሁን የሰው ልጅ ከዛሬ 5እና 4 መቶ አመታት የተሻለ ደረጃ ላይ በመድረሱ ምክንያት እነኚህ ምርምሮች በተቋም ደረጃ እድገት ማሳየት ችሏል የሰው ልጅ ስለ እሚኖርበት ጠፈር ያለውን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ ኑሮውንም በአንድ እርምጃ ማራመድ ችሏል  
በፍልስፍና ውስጥ ሁለት አይነት አስተሳሰቦች ምንግዜም ቢሆን ትግልን ሲያደርጉ ይኖራሉ አንዱ ያለውን ወቅታዊውን ነባራዊ ሁኔታን (Status Quo) የሚደግፉ እና እርሱ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ሲሆኑ እነኚህም በአብዛኛው ከዛ ስርአት ውስጥ ተጠቃሚ የሆኑ ናቸው እነኚህም የፖለቲካ የሀይማኖት በተለያየ የኢኮኖሚያዊ አመራር ላይ ያሉ ናቸው በእርግጥ ስርአቱ ምን አይነት ስርአት ነው የሚለውም ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው ዲሞክራሲያዊ  በሆነ አመራር ውስጥቁንጮ ላይ ያሉ ሰዎች በምርጫ ሊቀያየሩና አዳዲስ ሰዎች የራሳቸውን አዳዲስ አስተሳሰብ ይዘው ሊመጡ ይችላሉ በአንፃሩ ዲሞክራሲ ከሌለ ግን የተወሰኑት ቁንጮነቱን ይዘው አንለቅም ሊሉና እንዲሁም የመሪነት ህጋዊ ተቀባይነታቸውና ብቃታቸው ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባ በውጥረት የተሞላ ስርአት ሊሆን ይችላል
በሌላ በኩል ደግሞ ስርአቱ እንዲቀየርና በመሰረታዊነት ልዩነታቸውን የገለፁ ናቸው ለዚህ አይነተኛ ዋቢ የሚሆኑት ማርክስ ስፒኖዛ ኔቼ የመሳሰሉት ሲሆኑ ከእነሱ ውስጥም አንዳንዶቹ የተሳካላቸው ናቸው ለምሳሌ እንደ ሉተር ቀዳማዊ አይነቶቹ ሉተር ጂኒየርም ምንም እንኳን በዘመኑ አስተሰሳቡ ስር ነቀል ቢሆንም ውሎ አድሮ የተሳካላቸውም አሉ ለምሳሌ ሁለቱ ሉተሮች ለዚህ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው
ሌሎች የመንግስታት የሀይማኖት ተቋማትን ብንወስድ ደግሞ ተመሳሳይ ነው በተቃራኒው ደግሞ ብንሄድ እነኚህ ነገሮች ባይኖሩ ኖሮ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ ባልተቻለም ነበረ።
በፍልስፍና አለም ውስጥ በአንድ በኩል ሓሳዊ - ፍልስፍና (Pseudo-Philosophy) ሲኖር ይህም የእውነት መሰረት የሌለው እና ሊሰራ የማይችል ፍልስፍና ተብሎም ሊጠራ የማይችል ነው በሌላ በኩል ደግሞ ሳብጀክቲቭ የሆነ የፍልስፍና አር ዘርፍም አለ ይህ ዘርፍ ፍልስፍና ሲሆን ሊሰራ የሚችልም ነገር ነው ነገር ግን የሚሰራው ለተወሰኑ ቡድኖች ልሂቃን ወይንም ከፍተኛ የማሰብ እና ግንዛቤ ላላቸው ሰዎች ብቻ ይሆናል ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት አን ራንድ የተባለችው አሜሪካዊነት አይሁድ ፈላስፋ የኒቼ ፍልስፍና እንዲሁም እንደ ሮበርት ኪዮሳኪ ያሉ በዘመናችን ያሉ ፀሀፊዎች የጠቆሙት   ከዚህ ዘርፍ የሚመደብ ነው ለምሳሌ አን ራንድ የሊበራሊዝም ፍልስፍና መሰረት የሆኑ በርካታ ሀሳቦችን የጠቆመች ቢሆንም በዋናው «Mainstream» በሚሰኘው የፍልስፍና አስተምህሮ ዘውግ ውስጥ ግን አልተካተተም  የኒቼንም Super-Man ብንወስድ ሊሰራ የሚችለው በዛ ደረጃ ላሉ ሰዎች ብቻ ሲሆን ለብዙሀኑ ማህበረሰብ ግን ሊሳራ ሰራ የማይችል ነው በነገራችን ካይ ላይ ይህንን ፍልስፍና ናዚዎች ልክ ለብዙሀኑ እንደተነገረ አድርገው ለፖለቲካ አላማቸው ተጠቅመውበታል፣ ነገር ግን በኒቼ ልእለ - ሰብ ማለት ማህበሰረብን ወይንምአንድ ዘርን የሚወክል ነገር አይደለም በነገራችን ካይ ላይ ይህንን ፍልስፍና ናዚዎች ልክ ለብዙሀኑ እንደተነገረ አድርገው ለፖለቲካ አላማቸው ተጠቅመውበታል ነገር ግን በኒቼ ልእለ - ሰብ ማለት ማህበሰረብን ወይንም አንድ ዘርን የሚወክል ነገር አይደለም ከዚያ ይልቅ ግን ጥቂት ላቅ ያለ ክህሎት ወይም ያላቸውን ጥቂት ልሂቃንን የሚወክል ነው
እኔ እኔን የሆንኩት ባንተ ምክንያት ነው የሚል ታዋቂ የደቡብ አፍሪካውያን አባባል አለ ይህም የሰው መድሀኒቱ ሰው መነው ከሚለው ሀገርኛ አባባል ጋር ተመሳሳይ ነው በብዙ ታላቅ ሀይማኖቶችም እምናገኘው ወርቃማው ህግ ማለትም በራስህ ላይ እንዲሆን እማትፈልገውን በሌሎችላይ አታድርግ የሚ ነው አን ራንድ የራስ ወዳድነት ፀጋዎች በሚል የሊበራሊዝም መሰረት የሆኑ ሀሳቦችን አንፀ ባርቃለች
ሁላችንም በመጀመሪያ የምንኖረው ለራሳችን ሲሆን ሌሎችን እንምንጠቅመው ከዚያ በኋላ ነው ።አንድ ሰው ማድረግ የሚፈልገውን በራሱ ጊዜና ሁኔታ ማድረግ ሲችል አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ሌሎች ሰዎችን መጠበቅ የለበትም ጊዜ እያለፈ ስለሚሄድ ማድረግ የምንፈልገውን ነገር በቅጡና በአግባቡና በጊዜውማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው በተለይም ለወደፊት ህይወታችን ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ትኩረትንና ጥረትን ማድረግ ይጠበቅብናል ሌላውንም እኮ ልንጠቅም የምንችለው መጀመሪያ ላይ የራሳችንን ህልውና (Survival) መጠበቅ ስንችል ነው

አለም በአንድ አፅናፈ - አለም አእምሮ ነው የምትመራው ይህ ዪኒቨርስ ነገር ግን ውድድርን ብንወስድ መወዳደር ማለት ከአንዱ ውድቀት የአንዱ ስኬት ነው የሚል ፅንሰ - ሀሳብ የሚነሳ ነው  


Tuesday, April 16, 2013

የኤርትራ የወደፊት እጣ ፈንታ




በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ሐገራት ያላት መልከአ-ምድራዊ አቀማመጥ ስልታዊ የሆነችው ኤርትራ ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ የሄደችበት አቅጣጫ ብዙዎችን አስገርሟል ። እንደ አንድ በቅርቡ ነፃ እንደወጣ ሐገር ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ በእርጋታና በጥንቃቄ ትጓዛለች ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ፤ በአንፃሩ የዚያች ሐገር አካሄድ ወዳልተጠበቀ አቅጣጫ ሆኖ ቆይቷል ። አደገኛ በሆነው በአካባቢው የፖለቲካ ጨዋታ ውስጥ ራሷን በሰፊው የከተተችው ኤርትራ ፣ ሀያላንንም ጭምር በሚጨምረው በዚህ አደገኛ ጨዋታዎች ውስጥ መግባቷ ውሎ አድሮ ለአለም አቀፍ ማእቀቦች ፣ ከአለም አቀፍና ከአካባቢያዊ ድርጅቶች መገለልን ፣ በዲፕሎማሲ አለም አቀፍ መገለልንና መነጠልን «Isolation» አስከትሎባታል ። 


ከጎረቤቶቿ ጋር በሙሉ መሳሪያን የተማዘዘችውና ከዚያም አልፋ ከሳኡዲ አረቢያ በስተቀረ ከየመንም ጭምር ጋር የተጣላችው ፣ እንዲሁም በሱማሊያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ራሱን የአልቃኢዳ ክንፍ ነኝ ብሎ ለሚጠራው ለአልሸባብም ጭምር ድጋፍን ስታደርግ የቆየችው ይህቺው አገር ፣ ከውጪ ለሚመለከቷት ተመልካቾች ወደ መንግስት አልባነት «Failed State»  ደረጃ ትወርዳለች ተብሎ አስግቷል ።

ምንም እንኳን ኤርትራ የቆዳ ስፋቷ ከኢትዮጲያ እጅግ ያነሰ ቢሆንም ፣ ያላት ከአንድ ሺ ማይል በላይ የሆነ በአለም ዋነኛ የንግድ መስመር በሆነው በቀይ ባህር ጠረፍና ለመካከለኛው ምስራቅ ያላት ቅርበት ተፈላጊ ያደርጋታል ። በአንድ ወቅት እንደውም አሜሪካኖች ከኢትዮጲያ ይልቅ ለኤርትራ ነው የሚያደሉት ይባሉ ነበር ። ካላት እጅግ ስልታዊ ከሆነ መልከአ ምድራዊ አቀማመጧ የተነሳ ፣ የውጭ ሀይሎች በዚህችው አገር የውስጥ ጉዳይ መግባታቸው የማይቀር ነው ። ከጎረቤቷ ሱዳን ፣ መካከለኛው ምስራቅ አረብ ሀገራትና ግብፅ ጭምር እንዲሁም እንደ አሜሪካን ያሉ ሀያላን በዚያች ሐገር የውስጥ ጉዳይ እጃቸውን አይሰዱም ማለት አይቻልም ።

ኤርትራ በነፃነት ትግል ወቅት ኤርትራን ነፃ ለማውጣት እንደ ጀብሀን የመሳሰሉ የነፃ አውጭ ድርጅትች የነበሩ ቢሆንም በትግል ወቅት ጀብሀ ተሸንፎ ከትግል ሜዳ በሀይል ነው የተወገደው ። ይህችው አገር ውስጣዊ አንድነት ራሱ ጥያቄ ውስጥ ሊገባ የሚችል ነው ። ከአስር በላይ ብሄር ብሄረበሰቦች ያሏት ይህችው አገር የአሰብ ወደብ ባለቤት ጭምር የሆነው የአፋር ፣እንዲሁም የብሌን ፣ የሳሆ ፣ የቤጃን የመሳሰሉ ብሄር ብሄረሰቦች አገር ነች ።


በአንፃሩ በስልጣን ክፍፍል እኚህ አናሳ ብሄረሰቦች ተገቢውን የስልጣን ውክልና አላገኙም ። ኤርትራን ነፃ በማውጣት በኩል አሸናፊ ሀይል ሆኖ የወጣው በአብዛኛው በክርስትያኖች የበላይነት የሚንቀሳቀሰው ሻእቢያ ነው ከዚህም በተጨማሪ በእስልምና እና በክርስትና እምነት ተከታይ ኤርትራውያንም የቆየ የስልጣን ትግልም እንዳለ በነፃነት ትግል ወቅት ጀምሮ የታወቀ ነው ። ስለዚህ በዚያች ሐገር ያለው መንግስት ሀገሪቱን ማስተዳደር ቢያቅተው ሊከተል በሚችለው የስልጣን ክፍተት አደገኛ የሆነና ለብዙ አሰርት አመታት የቆየው የተዳፈነው የስልጣን ሽኩቻ ሊቀሰቀስ ይችላል ። ካላት እጅግ ስልታዊ ከሆነ መልከአ-ምድራዊ አቀማመጥም የተነሳ የውጭ ሀይሎችም በሰፊው እጃቸውን ሊሰዱ ይችላሉ ።

የዚህ ውጤትም ለአፍሪካ ቀንድ የባሳ አለመረጋጋትን ሊፈጥር ሲችል ፣ ገና በእግሯ መቆም ከጀመረችው ሶማሊያ ሌላ መንግሰት አልባ የሆነ አገር ሊፈጠር ይችላል በሚል ምእራባውያንን ክፉኛ አሳስቧል ። ከዚህም በተጨማሪ ከኢትዮጲያ ጋር ያለው የድንበር ውዝግብ ገና መቋጫ ያላገኘ ከመሆኑ አንፃር ከኢትዮጲያ ጋር ያለው ሁኔታ ወዴት ሊያመራ  እንደሚችልም አንዱ ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው ።