Thursday, April 11, 2013

እስያናና ምእራባውያን





በእስያውያን ምጣኔ-ሀብታቸው በዚህ ፍጥነት ያንሰራራል ተብሎ ተጠብቆ አልነበረም ። ነገር ግን ካለፉት ከ1970 እና 80 ዎቹ ወዲህ ግን ምጣኔ-ሀብታቸውን በፍጥነት በማሳደግ ወዳ ልተጠበቀ የሀብት ፈጠራና የምጣኔ - ሀብት እድገት አምርተዋል ። ይህ በእንደ አንድ በኩል ምእራባውያን መንግስታትን ሲያስደነግጥ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እነኚህ ግዙፍ ህዝብ ያላቸው የእስያ ሀገራት ፣ ለምእራባውያን ግዙፍ ኮርፖሬሽኖች ተዝቆ የማያልቅ ገበያንና ርካሽ ምርቶችን የማምረት የሚያስችል እድልን ፈጥሮላቸዋል ።


ምእራባውያን በተለይም የቻይና የምጣኔ-ሀብት እድገት የተምታታ ስሜትን ፈጥሮባቸዋል ። በአንድ በኩል ቻይና የመገበያያ ገንዘቧን ሆነ ብላ ዝቅ በማድረግ ምርቶቿን በርካሽ ለአለም ገበያ በማቅረብ የሌሎች አገራት ምርቶች በገበያው ላይ ተወዳዳሪ አንዳይሆኑ አድርጋለች ብለው ሲተቿት ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ይሄው የቻይና የገንዘብ ስርአት የንግድ ሚዛናችንን አዛብቷል ብለው ምእራውያን ቅሬታ ገብቷቸዋል ። 

ምእራባውያን የቻይና ዲሞክራሲ አለመስፈኑ ያቺ አገር አንድ ውስጣዊ አለመረጋጋት ቢገጥማት ከባድ ችግር ሊገጥመን ይችላል ብለው ይሰጋሉ ።በአለም ላይ የግዙፍ ምጣኔ-ሀብት ባለቤት ለመሆን የበቃችው ቻይና ውስጣዊ ዲሞክራሲ የሌላትና ከአንድ ዲሞክራሲ ካላደገበት አፍሪካዊ አገር ያልተሻለ ሲሆን ዲሞክራሲዋ ፣ ይህም አንድ የፖለቲካ አለመረጋጋት ቢፈጠር በቻይና ሊከሰት የሚችለው የፖለቲካ ቀውስ በአለም ላይ የምጣኔ-ሀብት መናጋትን ሊያስከትል የሚችል ነው ።

ከዚህም በተጨማሪ ቻይና የፈረጠወመውን ክንዷንም ለማሳየትም ሆነ ለማንሳት የማትቦዝን ሐገር መሆኗ ሌላው የምእራባውያን ራስ ምታት ነው ። በደቡብ ምስራቅ ቻይና ባሉት የደሴቶች ይገባኛል ጥያቄ ጉዳይ ላይ ትናንሾቹ እኛም በበኩላችን ደሴቶቹ ይገባናል ባዮቹ ቬትናምና ፊሊፒንስ እና ሌሎቹም ቻይናን የሚቋቋም ወታደራዊ አቅም የሌላቸው አገራት የአሜሪካንን ጣልቃ ገብነት ለመጠየቅ ተገደዋል ።

የወንዶች አለም



ይህ አለም «የወንዶች አለም» መሆኑ በበርካታ «ፊሜኒስት» ፀሀፍት ተደጋግሞ የተገለፀ ነው ፡። በእርግጥ ይህ አለም «የወንዶች አለም» መሆኑ ባያከራክርም ለምን የወንዶች አለም ሆነ የሚለው ጉዳይ ምላሽን የሚሻ ነው ። ይህ አለም የወንዶች አለም ሆነበት የራሱ ምክንያት አለው ። ይህ አለም የሚመራው በጉልበት ወይም በስሜት ሳይሆን በምክንያት ፣ በቁጥርና በስሌት እንዲሁም በአመክንዮ «ሎጂክ» ነው ። ስልጣኔ እድሜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር የሳይንስ ስሌትና ምክንያታዊነት የበላይነቱን እየያዘ መጥቷል ። በጥንት ግሪክና ሮማ የነበሩ ህዝቦች አማልክቶቻቸው በሴት ፆታ ነበረ የሚመስሏቸው ። አፍሮዳይት፣ቬነስ፣ሜርኩሪ፣አቴና የመሳሰሉት በሙሉ በሴት ፆታ ይጠሩ የነበሩ እና በጥንታዊ ሰዎች እንደ አምላክ ይመለኩ የነበሩ ናቸው ።

     አንዳንድ ፊሜኒስቶች «የሴቶች ጠላቶች፣ ራሳቸው ሴቶች ናቸው» የሚል አቋም አላቸው ። ይህም በአንድ በኩል ራሳቸው ሴቶችን በመጨቆን ፣ ራሳቸው ሴቶች ዋነኛ ጨቋኞች ሲሆኑ ነው ። ሴት «ማህፀን ነች» የሚለው አባባል የሴትን ልጅ ደረጃ ዝቅ እሚያደረግ ነው ። ይህም የተዋልዶ አካል ናት ፤ የሰውን ዘር ለማስቀጠል ብቻ ነው የተፈጠረችው እንደ  ማለት ነው ። በዚህ አስተሳሰብ ከሄድን ወንድም ዘሩን ለማባዛት ብቻ ነው የተፈጠረው ወደሚል አስተሳሰብ ያመራናል ።

በነገራችን ላይ የሴቶች ስኬት ከአገር አገር ይለያያል ። እንደ ስዊድን ባሉ የሰሜን አውሮፓ ሀገራት ላይ የሴቶች ስኬትና የኑሮ ደረጃ እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ፣ በአንፃሩም በእስያ ሀገራትም እንዲሁ ሴቶች ለከፍተኛ የመሪነት ቦታዎች የሚታጬ ናቸው ። እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት ግን ሴቶች እምብዛም ለከፍተኛ የፖለቲካ ወንበር ላይ አይታዩም ፣ ለዚህም ምክንያቱ እንደ አሜሪካ ባሉ ሀገራት ፡ ለመመረጥ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስፈልግ ሲሆን እንደ አሜሪካ ባሉ የምእራብ ሀገራት ለመመረጥ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማግኘት ስለማይችሉ በፖለቲካውም መስክ ስኬታማ ሊሆኑ አልቻሉም ። 

     የአንድ ማህበረሰብ በቅርፅና በይዘት በጊዜ ውስጥ እየተለወጠ ይሄዳል ። በዚህም በፆታዎች መሐከል ያለው ግንኙነትም በዚህ መንገድ እየተቃኘና እየተለወጠ ፣ እየተሻሻለ ይሄዳል ። በዚህም መስክ ሴቶች መብታቸውን ለማስከበር እጅግ የመረረ ትግልን አካሂደዋል ። አሁን በወንድና በሴት መሐከል ያለው የሀይል ሚዛን ፣ የግንኙነት መስፈርትና ሚዛን እዚህ ደረጃ የደረሰው እና አሁን የያዘውን ቅርፅ የያዘው በቀላሉ አይደለም ።  
     ማህበረሰቡ ወንዱ በፈጠረው አለም የሴትን ማፈንገጥና ማመፅ «ሪቤል» አጥብቆ እንደሚፈራው የታወቀ ነው ። ለምሳሌ ግርዛትን ብንወስድ የግርዛት አላማው የሴት ልጅን ወሲባዊ ስሜትን ማዳከም ወይም ታፍኖ እንዲቆይ እና በሙሉ ሀይሉ እንዳይወጣ ለማገድ ፣ ብሎም ሴቷን በቀላሉ ለመቆጣጠርና ተገዢ ለማድረግ ነው ። ሴት በወንዱ አለም ውስጥ በተለያየ መንገድ ፍንገጣዋንና አመፃዋን ትገልፃለች ። የወንድ የበላይነት ስልጣኔ በአለም ላይ ከሰፈነ ወዲህ ፣ ሙሴ ሴት አጥፍታ ብትገኝ «አይንህ እንዳይራራላት» ሲል ለተከታዮቹ ይገልፃል ።

     የካፒታሊዝም ስርአት ለራሱ ህልውና ሲል ለፈጠረው የሸማችነት ስርአትን ብንወስድ ግን ፤ ለሸማችነት  ሴት ተጠያቂ አይደለችም ፣ እንደውም የሸማችነት ሰለባ ነች ። ሸማችነት አንዱ የካፒታሊዝም ስርአት መገለጫ ነው ። በአብዛኛው ሴቶችን እሚያማልሉ ሸቀጧችን ወደ ገበያ በማውጣት ካፒታሊስቶች እጅግ የበዛ ገንዘብን እንደሚያፍሱ ይታወቃል ። የጌጣጌጥ፣ የቅባት ፣ የሽቶ ንግዶች በአለም ላይ ከፍተኛ የበርካታ ቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ የሚንቀሳቀስባቸው ናቸው ። ሸማችነት ከፆታ ጋር የሚያያዝ ነገር አይደለም ለምሳሌ ከፍተኛ የገቢ ደረጃ ባላቸው የአረብ ሀገራት ብንወስደ ፣ የእነኚህ አገራት ህዝቦች ከፍተኛ ገቢ ያላቸው መሆናቸው ይታወቃል ። በእነኚህ ሐገራት በአብዛኛው ዜጎቻቸው ምንም ስራ ስለሌላቸው በየሱቁ እየዞሩ እቃ ሲሸምቱ ነው እሚውሉት ።

የወሲብ ስሜትን «በማፈን» የተገኘው ስልጣኔ



ሲግመን ፍሮይድ ይህ የሠው ልጅ ስልጣኔ የሰው ልጅ «የወሲብ ስሜቱን በማፈን ያገኘው ነው» ሲል እንዲሁም ፍሬደሪክ ኒችም ይህ ስልጣኔ «ራስን በማሰቃየት የተገኘ ነው» ሲል ገልጿል ። ለዚህ የኒች አባባል ማስረጃ የሚሆነው ማርክስ «ዳዝ ካፒታል» በተሰኘው መፅሀፉ በዝርዝር እንደገለፀው ካፒታሊዝም ስርአት በመጀመሪያው የእድገት ዘመኑ እጅግ አነስተኛ ደሞዝ እና በጣም አስቸጋሪ በሆነ የስራ ሁኔታ የሰራተኞችን ብሎም የህፃናትን ጉልበት ጭምር ያለ ምህረት ይበዘብዝ  ፣ እንደነበረ ይገልፃል ።

የወሲብ ስሜት ልክ እንደ ማንኛውም እንሰሳ ለሰው ልጅም ራሱን እንዲራባና ዘሩን ተክቶ እንዲያልፍ የሚያስችል ነው ። ብዙውን ግዜ ታላላቅ ሀይማኖቶች ሰው ራሱን እንዲገዛ ከሚያስተምሩባቸው ምክንያቶች በአንድ በኩል የሰው ልጅ የወሲብ ስሜቱን ካልተቆጣጠረ ወደ ሌላ አላማ ሊውል የሚችል እምቅ ሀይሉን ያዳክማል ፣ በሌላ በኩል ግብረ-ገባዊ የሆነና ስርአትና ወግን የተከተለ ማህበረሰብን ለመፍጠር አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል ። በምእራቡ አለም አንድ የፖለቲካ ሰው ከሚስቱ ውጪ ከማገጠ እና በማስረጃ ከተረጋገጠ የፖለቲካ ህይወቱ ያበቃለታል ። የወሲብ ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው ለከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ አይታጭም ማለት ይሆን ?


የወሲብ ስሜት በሁለት እርስ በራሳቸው ተቃራኒ በሆኑ አቅጣጫዎች የሚመራ ነው፣ አንደኛው የወሲብ ስሜት ሀይል ሲሆን ፣ በአለም ላይ ከፍተኛ ስኬትን የሚቀዳጁ ሰዎች ከፍተኛ የወሲብ ስሜት ያላቸው ሰዎች ናቸው ። አንዳንዶቹ እንደ አይዛክ ኒውተን ያሉት ታላላቅ ሰዎች ደግሞ በድንግልና ኖረው የሞቱ ናቸው ። በተቃራኒው የወሲብ ሰሜት ካልተገራና ወደ ሌላ ጠቃሚ ወደ ሆነ ነገር ካልተለወጠ በስተቀር ፣ የሕይወት ብክነትን ይፈጥራል ።
የወሲብ ስሜት እንደ ማንኛውም እንሰሳ ለሰው ልጅ የተሰጠው ራሱን እንዲያራባበት  ነው ። ይህም ማለት የወሲብ ስሜት አንድ እምቅ ሀይል ነው ። ይህ ሀይል አለልክ ሲባክን የዛን ሰው የህይወት ግብ ያመክናል ። ሲታፈን ደግሞ እንዲሁ የተቆጣና የተናደደ ሰውን ይፈጥራል ። ናፖሌዎቸን ሂል የተባለው ፀሀፊ እንዳስቀመጠው «አንድ ሰው ከአርባ አመቱ በፊት ስኬታማ አይሆንም» ፣ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ አንድ ሰው ከአርባ አመት እድሜው በፊት የወሲብ ስሜቱን መቆጣጠር ስለማይችል ነው ።

በዝግመተ-ለውጥ አስተሳሰብ መሰረት አንድ ሰው ወጣትና ለተቃራኒ ፆታ መስህብ የሚኖረው በወጣትነቱ ዘመን ብቻ ነው - ይህም ለመራባትና ራሱን መተካት አንዲያስችለው ነው ። የወጣትነቱ ዘመን ሲያልፍ ተፈጥሮ እንሰሳው ወይም ተክሉ ራሱን አንደተካ በማመን ለእርሱ እምትሰጠውን እንክብካቤ ማለትም ወጣትነቱንና ሀይሉን ውበ አማላይ አካላዊ ገፅታውንና ጥንካሬውን በአጠቃላይ የአንድ ሰው ትልቁ ፀጋ እሚባለውን ወጣትነቱን ቀስ በቀስ ትወስድበታለች ። ከዚያም እያረጀ ፣ እያረጀ ይሄድና ወደ ተፍፃሜ - ህይወቱ ማለትም ወደ ሞት ያዘግማል ።

Thursday, April 4, 2013

የአለም የንግድ ስርአት


ለበርካታ ክፍለ ዘመናት የነበረው የአለም የንግድ ስርአት ከምእራባውያን ጥቅም ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ ባልተጠበቀ ፍጥነት እየተቀየረ ይገኛል ። ላለፉት አምስት ክፍለ ዘመናት የቆየው የአለም የንግድ  ስርአት ለመጀመሪያ ጊዜ የአቅጣጫ እና የሽግሽግ ለውጥን ሲያደርግ የንግድ ሚዛኑም ወደ እስያ ፣ አፍሪካና ሌሎች ቀድሞ ታዳጊ ይባሉ ወደ ነበሩ አገራት እያዘነበለ ይገኛል ። ይህ ማለት ግን ምእራባውያን ሙሉ በሙሉ ያላቸውን የበላይነት ያጣሉ ማለት አይደለም ።

ምእራባውያን ያሏቸው «Strategic Advantages» በቀላሉ አያጧቸውም ። እንግሊዝ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት መሀከል ያላት መልከአ-ምድራዊ አቀማመጥ ወሳኝ በሆነ አቀማመጥ ላይ ነው ።  እንግሊዝ የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆነችው ካላት ወሳኝ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የተነሳ በራሷ ገንዘብ ብትገበያይ ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርገኛል በሚል ስሌት ነው ። አሜሪካንንም ብንወስድ በሁለት አቅጣጫ በአትላንቲክ ውስቅያኖስና በሰላማዊ ውቅያኖስ በኩል የባህር ተዋሳኝ ስትሆን በሁለቱም አቅጣጫ መነገድም ሆነ ጠላት ቢመጣ ያለምንም ችግር ራሷን መከላከል ያስችላታል ።

ሌላው የምእራባውያንን የበላይነት ጠብቆ ሊያቆይላቸው የሚችለው ነገር ፣ ያላቸው በእውቀት ላይ የተመሰረቱ ኩባንያዎች እንደ ኮካኮላ፣ ማይክሮሶፍት ፣ ጎግል ፣ አፕል ፣ ያሆና የመሳሰሉ ቁሳቁስን ሳይሆን እውቀትን የሚሸጡ ኩባንያዎቻችቸው የአለም ገበያ እየሰፋ በሄደ ቁጥር ትርፋቸው እየናረና ተጠቃሚ እየሆኑ ይሄዳሉ እንጂ እየቀነሱ አይሄዱም ። 

ሌላው ምእሬውያን በእድገትና በምርምር ላይ ያላቸው ከፍተኛ የሚያፈሱት መዋእለ - ንዋይና አሁንም ድረስ ከታዳጊው አለም ወደነሱ የሚጎርፈው የሰው ሀይል ሌላው የበላይነታቸው ሚስጥር ነው ።

ከዚህም በተጨማሪ ምእራባውያን ለበርካታ ክፍለ ዘመናት እያዳበሩ የመጡት በዲሞክራሲ የበላይነት የሚመራው የመንግስት ስርአታቸው ሌላው የውስጣዊ ሰላማቸውና መረጋጋታቸው ሚስጥር ነው ። ጠንካራው የዲሞክራሲ ስርአታቸው የትኛውም ሀገር በምጣኔ-ሀብት ቢያድግ በቀላሉ ሊደርስበት የሚችል አይደለም ። ህንድን ብንወስድ በሙስና የተዘፈቀ የዲሞክራሲ ስርአት ያላት ሲሆን ፤ በቻይና ግን የአሜሪካ ዲሞክራሲ አይነት አይታሰብም ። በእነኚህ ምክንያቶች በምእራባውያኑ የበላይነት የተያዘው የአለም የንግድ ስርአት፤በቀላሉ ይለወጣል ተብሎ አይታሰብም ። በተለይም ደሀዎቹ ሀገራት ከዚህ የአለም የንግድ ስርአት ተጎጂነታቸው ላልተወሰነ ጊዜ መቀጠሉ አይቀርም ።

ለምሳሌ ሐገራችንን ብንወስድ ለምታካሂዳቸው ግዙፍ ሜጋ ተብለው ለሚጠሩት ፕሮጀክቶቿ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በቀላሉ ማግኝ ባለመቻሏ ፣ በሀገር ውስጥ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሊፈጠር ችሏል ። በግብርና ምርቶች ከሚገኝ የውጭ ምንዛሬ ላይ የተመሰረተው የሀገራችን ምጣኔ-ሀብት በአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀውስ በሚፈጠርበት ወቅት የአበባና የቡና ዋጋና ፍላጎት ሲወርድ በውጭ ምንዛሬ ገቢአችን ላይ ቀላል የማይባል አሉታዊ ተፅእኖን ሊፈጥር በቅቷል ።

Tuesday, April 2, 2013

በተቃርኖዎች ላይ የተመሰረተው ስልጣኔ

የውስጣዊ የስልጣኔ ተቃርኖ ፦

በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ያለው ስልጣኔ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በተቃርኖዎች ላይ የተመሰረተ ነው ። በአለማችን ታሪክ በተደጋጋሚ እንደታየው ፣ ስልጣኔዎች የሚመሰረቱት በተቃርኖዎች ላይ ነው ። ይህም ለመጥፋታቸው ዋነኛው ሰበብ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ። ሁሉም በአለም ላይ ተከስተው የነበሩ ስልጣኔዎች የራሳቸውን መቃብር ራሳቸው ቆፍረዋል ተብሎ ይታመናል ። 

ካርል ማርክስ የካፒታሊዝም ስርአት «የራሱን መቃብር ራሱ ይቆፍራል» ሲል በውስጡ ያለውን ተቃርኖ #Inherent Contradiction በመንተራስ ነው ።በሠራተኛው ጉልበት የሚፈጠረው ሀብት በካፒታሊስቱ እጅ መከማቸት ውሎ አድሮ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስን በካፒታሊስቱ ማህበረሰብ ይፈጥራል ነው እሚለው ማርክስ።

በእርግጥ በከበርቴው ስርአት ውስጥ ያለው ተቃርኖ ከምንግዜውም በላይ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ነው ። በአሁኑ ወቅት በስነ-ህዝብ በኩል ፣ በምጣኔ-ሀብት ፣ በአለም አቀፍ ንግድ ፣ በአለም የገንዘብ የመገበያያ ገንዘብ ጉዳይ፣ በአለም አቀፍ ግንኙነት በመሳሰሉት ላይ በርካታ ተቃርኖዎች ሲኖሩ ፤ እኘኚህም ማህበረ-ኢኮኖሚ መሰረት ሊንዱ ፣ እንዲሁም የአለማችንን ስልጣኔ ሊያፈራርሱ የሚችል አቅም ያላቸው ናቸው ።

ስነ-ህዝብ ጉዳይን ብንወስድ የአለምን የስነ-ህዝብ የአለምን የህዝብ ቁጥር መቆጣጠር ተገቢ ቢሆንም ፣ በአንፃሩ በአውሮፓ የሚታየው የወጣት ቁጥር መመናመን ፣ በእድሜ የገፉ ዜጎች መበራከት በዚህም ምጣኔ-ሀብቱ ላይ የሚፈጥረው ጫና ፣ እንዲሁም በእስያ ሀገራት የሚታየው የፆታዎች ስብጥር መዛባት ፣የአየር ንብረት ለውጥና በአገራት መሀከል በጉዳዩ ላይ ስምምነት አለመኖር የመሳሰሉት ተፈጥሯዊ ከሆነው ጋር ተቃርኖን የሚፈጥሩና የማህበረሰቡን መሰረት ሊያናጉ የሚችሉ ናቸው ። 

በአለም የንግድ ስርአት ላይም እንዲሁ የሚታየው የገንዘቦች የተዛባ የምንዛሬ ሸርፍ እንዲሁ ውሎ አድሮ የአለምን ምጣኔ-ሀብት እንዲዛናባና በአለም ላይ የተፈጠረውም ሆነ ወፊተት ወደፊት የሚፈጠረው ሀብት በጥቂት አገራትና ሀይሎች እጅ ቁጥጥር ስር እንዲገባ ስለሚያደርግ ውሎ አድሮ በአለም ላይ የተዛባ የንግድ ስርአትንና የፖለቲካ የስራ አጥነትና የኢኮኖሚ ቀውስን ብሎም ወታደራዊ ግጭት ድረስ ሊያስከትል የሚችል ነው ፥ ቻይናና አሜሪካ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው።  ይህንን የገንዘብ ምንዛሬ ቀውስን አንዳንድ መነጋናኛ ብዙሀን «Currency War» በማለት ጠርተውታል ። የሁለተኛው የአለም ጦርነት መነሾ የኢኮኖሚው  ቀውስ እንደሆነ ይታወቃል ።

ታይሜሲየስንና ክሬቲያስ የተሰኙትን ታላላቅ የግሪካዊው ፈላስፋ ስራ ሰጠፋችው አትላንቲስ ስለምትባለው አህጉር ያትታል ።

የስልጣኔዎች አወዳደቅ



ብዙዎቹ ማለት ይቻላል መሰረታዊ የጂኦሜትሪ ህግጋትን ደርሰውባቸው ነበረ ማለት ይቻላል ፣ ማያዎች እንኳን ከሌላው አህጉር ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ከግብፃውያን ፒራሚድ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ፒራሚዶችን ማነፅ ችለዋል ። ዳር ዳሩ ማእዘኑ ላይ ደረጃ የወጣለት ከመሆኑ በስተቀር የማያዎች ፒራሚድ ከግብፃውያኑ ጋር በቅርፅም ሆነ በመልክ ተመሳሳይ ነው ፣ በእኛም ሀገር አክሱማውያን በተመሳሳይ መንገድ ቀጥ ያሉ ሀውልቶችን ሲገነቡ በእነኚሁ መሰረታዊ የጂኦሜትሪና የሂሳብ ህግጋት እየተመሩ እንደሆነ ግልፅ ነው ።

አንድ ሰው የጥንቶቹን ስልጣኔ ባለቤቶችን በኮኮብ ቆጠራ ማመናቸውን አለማወቅና የዋህነት ነው ሊል ይችላል ፣ ነገር ግን የጥንቶቹ ሰዎች አላዋቂዎች እልነበሩም ፣ ነገር ግን ታላላቅ ፒራሚዶችን ከሰሜን አፊረካ ፣ ምስራቅ አፍሪካ አሜሪካ ድረስ የገነቡ ነበሩ ። የሂሳብን ፣ የፊዚክስን እንዲሁም የጂኦሜትሪን ህግጋትን በራሳቸው ጊዜና መንገድ ድረሰውባቸዋል ።

ለምሳሌ ከጥንት ስልጣኔ ባለቤቶች ዋነኞቹ የነበሩትን የጥንት ግባብፃውያንን ብንወስድ  ስልጣኔአቸው ለሶስት ሺ ዘመናት ዘልቋል ። በሺ ለሚቆጠሩ ዘመናት የዘለቀው የጥንታዊ ግብፃውያን ስልጣኔ በመንፈስ በኩል እንዲሁም በሀይማኖትና በሂሳብ በሳይንስ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሰው የነበሩ ሀያላን ነበሩ ።

በአለም ላይ በርካታ ስልጣኔዎች ውድቀታቸው ከምን የመነጨ ነው ? ብዙዎቹ ስልጣኔ ዎች መሰረታቸው በተቃርኖ ላይ ነው ። ይህም ለኋላ ኋላ ውድቀታቸው በርን የሚከፍት  ሲሆን ፣ በተፈጥሮ አደጋ ከጠፉት የሰው ልጅ ስልጣኔዎች በስተቀር ፣ማለትም በመሬት መንቀጥቀጥ ፣ በእሳተ-ገሞራ ፣ በሱናሚ ከመሳሰለው ባልተጠበቀ የተፈጥሮ አደጋ ከጠፉት ውጪ ብዙዎቹ ስልጣኔዎች የራሳቸውን መቃብር ራሳቸው ቆፍረው ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል ።