የመግባባት ችሎታ ለመሪነት ብቻም ሳይሆን ለአንድ ሰው የህይወት ስኬት እጅግ ቁልፍ ከሆኑ ክህሎቶች አንዱና ዋነኛው ነው ። እንኳን መሪ ይቅርና አንድ ሰው በህይወት ውስጥ የሚፈልገውን
ማንኛውንም ነገር በቀላሉ ሊያገኝና በሚፈልገው መንገድ ለመኖር የመግባባት ክህሎት አስፈላጊ ነው ።
የስነ - ልቦና ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት
የመግባባት ችሎታ ለመሪው እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ችሎታዎች አንዱ ሲሆን ተግባቦት (Communication)
የሚባለው ነገር 64 በመቶው በአካላዊ እንቅስቃሴ መግባባት የሚካሄድበት
ሲሆን የተቀረው 36 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በንግግር ፣ በፅሁፍና በስእል መግባባት የሚደረግበት
ነው ። መሪም እነኚህን የመግባባት መንገዶችን ጠንቅቆ ማወቅ ሲኖርበት ፣ ይህንን የመግባባት ችሎታን ያልተረዳ መሪ ግን ሊያስተላልፍ
የሚፈልገውን
መልእክት ሳያስተላልፍ
ይቀራል ። መልእክቱን በአግባቡ ካላስተላለፈ
ደግሞ ለመምራት ያለውን እድል ይቀንሰዋል ።
አንድ መሪ በአራትና በአምስት አቅጣጫ መግባባት መቻል አለበት ። ከበታቾቹ ጋር ፣ ከእርሱ ትይዩ ካሉ እኩዮቹ ጋ ፣ እንዲሁም ከበላዮቹ ጋርና እንዲሁም ከደንበኞቹ እንዱሁም በአጠቃላይ ከሚያገለግለው
ህዝብ ጋር ፣ ሌላው ቀርቶ አንድ መሪ ከጋዜጠኞች ጋር ያለው ግንኙነት ሁሉ ለስኬቱ ወሳኝነት አለው ። በተለይም በእንዲህ አይነቱ ግንኙነት ወቅት ከአለባበሱና
ከአነጋገሩ ጀምሮ ስነ - ስርአትን በጠበቀ መልኩ ግንኙነትን መፍጠር አለበት ። ከስርአት ውስጪ የሆኑ ባህሪያቶችን
ማስወገድ አለበት ይህም በሌሎች ሰዎች ዘንድ ቅሬታን ሊፈጥር ስለሚችል ሌሎችን እንደናቃቸውና
ዝቅ እንዳደረጋቸው
አሰድርገው እንዳይወስዱት
ያደርገዋል ።
ከዚህም በተጨማሪ ስኬታማ ለሆነ የቡድን ስራ ተግባቦት እጅግ አስፈላጊ ነው ። በቂ ተግባቦት የሌለባቸው የስራ ከባቢዎችመግባባት
ከማጣት የታወኩና ውስጥ ውስጡን የማያቋርጥ የእርስ በእርስ ሽኩቻ የሚደረግባቸው
ናቸው ።
ለጥሩ ተግባቦች መሪው ራሱን በቅጡ ማወቁ እጅግ አስፈላጊ ነው ። ለምሳሌ መሪው የራሱን እሴቶችን ፣ አስተሳሰቦችን
እውነት ብሎ የያዛቸውን ሀቆችን ፣ እንዲሁም የራሱን የተዛቡ አስተሳሰቦችንም ጭምር
የሚያውቅ መሪ ከሌሎችን ጋር በቀላሉ መግባባት ይችላል ። ራሱን በሌሎች ሰዎች ቦታ አድርጎ የመመልከት ልማድ መሪው የሌሎችን ፍላጎትና አላማና ችግር በቀላሉ ለመረዳት ያስቸግረዋል
።ሌሎችንም እንዲሁ ማወቅ አስፈላጊ ነው ። የሌሎችን ስሜት ፣ ፍላጎት ፣ ሀሳብ መረዳትም እንዲሁ ለተሳካ ተግባቦት አስተዋፅኦን
ያደርጋል ።
መሪዎች አወዛጋቢ ከሆኑ የስልጣን እድሜአቸውን
ያሳጥራል ። አወዛጋቢ መሪዎች በስልጣን የመቆየት እድሜቸው አጭር ነው ። መሪዎች አወዛጋቢ ከሆኑ ብዙ ተቃዋሚዎችን
ስለሚያፈሩ ሌሎች ሰዎች በዚያ ስልጣን ሊያቸው አይፈልጉም ፣ ብዙውንም ጊዜ ለሀላፊነታቸው
እንዲለቁ ግፊት ይደረግባቸዋል
። መቼ ነው ከስልጣን የሚለቁት የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄም ይቀርብላቸዋል
። በእርግጥ ሁሉም
ጠላታቸው ይሆናል ማለት
ባይሆንም ፣ ነገር
ግን ለስራቸው መቃናት
ግን እንቅፋትን ይፈጥርባቸዋል
።