Saturday, March 14, 2015

Property Rights In Ethiopian Law የኢትዮጲያ ህግና የንብረት ባለቤትነት (Property Right) መብት አፈፃፀም

 

            አንድ የፍርድ ቤት ሙግት በርካታ ወራትን ብሎም አመታትን የሚፈጅ ሲሆን ይህም ማለት ይህ ጉዳይ ፍርድ   ቤት ይዞታል በሚል ብቻ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ አመታትን መፍጀቱ የንብረት ባለቤትነት መብትን ህጉ በአግባቡ ማስከር ችሏል ወይ ? የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልካም ነው ፡፡ በሃገራችን እንደሚታወቀው የፍርድ ቤት ሙግት በቀላሉ የማያልቅ ሲሆን በቀላሉ ወረዳዎች ወይንም ባስ ካለም ክፍለ ከተማዎች መፍትሄ ሊሰጡት የሚገችሉት ጉዳይ አመታትን ሰዎችን ሲያመላልስ ይስተዋላል ፡፡

          አንዱ መዋእለ ንዋይን ለማበረታታት ከሚመከሩት የተመቻቹ ሁኔታዎች አንዱ የንብረት ባለቤትነት (Property Right) መብትን ማስከበር ሲሆን በምእራባውያን የምጣኔ - ሐብት ባለሙያዎወች እንደተጠናው ከሆነ ለአፍሪካ ኢንቨስትመንትን አግባቡና  በበቂ ላለመሳቧ ዋነኛው ምክንያት የንብረት ባለቤትነት መብት በበቂ አለመከበሩ ነው ይላል ፡፡

          አንድ መዋእለ ንዋይ አፍሳሽ አንድ የውጭ ሃገር ሄዶ ገንዘቡን ሲያፈስ የሚያፈሰውን ገንዘብ ሲፈልገው መልሶ ማውጣት ሚፈልግበት በማንኛውም ሰዓት ላይ ማውጣትን የሚፈልግ ሲሆን የንብረት መብት (Property Right) በአግባቡ የማይከበርባቸው ሃገራት የውጭ መዋእለ ንዋይን የማግኘት እድላቸው በጣም ጠባብ ነው የሚሆነው ፡፡  ይህም አወዛጋቢ በሚሆንበት ወቅት የሚከበር ፍርድ ቤቶች አማካይነት በተፋጠነና በተከራካሪ ወገኖች ላይ የማያስፈልግ ወጭንና ኪሳራን በማያስከትል ሁኔታ በአንዱ ኪሳራ ሌላኛው አለአግባብ በማይጠቀምበት ሁኔታ መሆን አለበት ፣ የነገሩ መንዛዛት አንደኛው ወገን በአንደኛው ኪሳራ አለአግባብ እንዲጠቀም የሚያደርግ ሲሆን ፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ በሁለቱም ወገኖች ላይ ከባድ ኪሳራንና መጓተትን ያስከትላል ፡፡ ለምሳሌ በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው ሶማልያን እናስብ ፤ አንድ የውጭ ሃገር ኢንቬስተር ሶማልያ ሄዶ መዋእለ ንዋዩን እንደማፍሰስ ብለን ብናስብ አንድ ባለሃብት እርዳታ አድርጎ ቢሰጠው ይሻለኛል ፣ ዝም ብዬ ሄጄ ገንዘቤን ከማፈስና ከምነጠቅ ብሎ ነው እሚያስበው ፣ ስለዚህ ሶማልያ መዋእለ ንዋይ የማግኘት እድሏ አነናሳ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡

          በአፍሪካ የንብረት ባቤትት መብት በአግባቡ የማይከበር ሲሆን ለኢንቨስትመንት አስፈላጊ የሆነ መሬት ያለ በቂ ሰነድ የሚያዝ ሲሆን መዋእለ ንዋይን ለማፍሰስና ለማሳደግም ሆነ ለማሻሻል አስቸጋሪ ሲሆን አድርጎታል ብለው የውጭ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ ከዚህ ተጨማሪ ግን ፍርድ ቤቶች ጠንካራ ሆነው የንብረት ባለቤት ህጉን ለማስከበር ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መፍታት ካልቻሉ ረጅም ግዜን መውሰዱ መዋእለ ንዋይን ከማረታታት አንፃር አሉታዊ ጎን ይኖረዋል ፡፡ ለምሳሌ አከራይና ተከራይ መሐከል ያለ ክርክር አመታትን ሊወስድ ይችላል በዚህም ምክንያት አከራዩ ፣ ክርክሩ ቤቱ ተይዞት ከሆነ የሚካሄደው ቤቱን እስከሚያስለቅቅ ድረስ የሚደርስበትን ኪሳራን ከውል ውጭ ጉዳት ደርሶብኛል በሚል ሌላ መዝግብ በመክፈት ድጋሚ ከሶ ብቻ ነው ማስከፈል የሚችለው ፡፡ ይህ ራሱ ደግሞ ከውል ውጭ ምን ያህል ነው የደረስብህ ኪሳራ የሚለው ለዳኝነት ቁልጭ ያለ ባለመሆኑ ምክንያት አሻሚ  ስለሚሆን ከውል ውጭ ጉዳት ለደረሰበት ወገን አርኪ ላይሆን ይችላል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪም ጉዳቱ ለደረሰት ወገን የደረሰበት ጉዳት ሌላ ተጨማሪ ወጮጪን ፣ የጠበቃ አበልን የሚያስወጣው ሲሆን ጉዳቱ የበዛ ነው የሚሆነው ፡፡

          የኢንቨስትመንት አዋጁ እንደሚደነግገው ከዚህ ቀደም አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ ኢትዮጲያ ውስጥ ቤት መግዛትም ሆነ መስራት የማይችል ሲሆን ነገር ግን የዚህ አዋጅ መሰረት ግን ኢንቨስተሩ ቤት ለመስራት ይፈቀድለታል ፡፡ ለምሳሌ በ2004 ዓ.ም. የወጣው የሊዝ አዋጁን ብንወስድ አዋጁ የወጣትበት ዋነኛው ምክንያት የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ማሳካት የሚል ሲሆን ፣ የግል የንብረት ባለቤትነት መብትን ይጋፋል በሚል በህግ ባለሙያዎች የተተቸ ሲሆን ነገር ግን አዋጁ የወጣበት አላማ ግን መንፈሱን መረዳት ይቻላል ፡፡