አንዳንደ አገራት እንደ ጃፓን ያሉ
አገራት የፓተንት ህግ ያላቸው ሲሆን አንድ ሰራተኛ በሚሰራበት ኩባንያ ውስጥ አዲስ ነገርን ፈልስፎ ቢገኝ ቀድሞ ኩባንያዎች በጣም
ትንሽ ገንዘብን ይከፍሉና ምርቱን ግን በመቸብቸብ እጅግ ትርፋማ ይሆኑ የነበረ ሲሆን በአንፃሩ ግን ፈጠራውን ላመነጨው ሰው ግን
ምንም ሳይከፍሉ እነሱ የፈጠራው ባለቤት ይሆኑ ነበረ ፡፡ ነገር ግን ጃፓናውያን ይህን በመመልከት ሰራተኛው ለሚፈጥረው ፈጠራ ግን
ከድርጅቱ ትርፍ መካፈል እንደሚችልና ወቅታዊ የሆነ ለክፍያን እንደሚያገኝ ደንግገዋል ፡፡
ይህን ህግ በማሻሻል ይበልጥ ሰራተኛው
ቋሚ ተከፋይና ባለቤት እንደሆነ ደንግገዋል በዚህም የሰራተኞችን የፈጠራ በማበራታታት ላይ ይገኛሉ ፡፡ ነገር ግን የዚህ ችግሩ አንድምታ ለምሳሌ 500 ፓተንቶችን ሊጠመቀም
ይችላል ስለዚህ እነኚህን ሁሉ ፓተንቶች ባለቤቶችን መክፈልና ምን ያህል ሊደርሳቸው ይባል ገባል የሚለከውን ኮሚቴዎችን በማቋቋም
ይወስናሉ ፡፡ በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የኤክትሮኒክስ ምርቶች እስከ አስር ሺህ ፓተንቶችን ሲጠቀሙ ለእነኛ ሁሉ ማከፋፈሉና ክፍያውን
መወሰኑ ይበልጥ ፈታኝ ስሆነባቸው ማበረታቻ ወይንም እንደ ቦነስ ያለ ክፍያን ለመክፈል በማሰብ ላይ ናቸው ፡፡
የፓተንትና የቅጂና ተዛማጅ መብቶች
(Patent & Copyright) በአለም ላይ ውስብስብ ለአሰራር አስቸጋሪ ከሆኑ ህጎች አንዱና ዋነኛው ነው ፡፡
No comments:
Post a Comment