በዓለም ታሪክ ውስጥ ግለሰብ ሰዎች ለዓለም ያደረጉት አበርክቶ
ለክፍለ ዘመናት ህልውና ከነበራቸው ታላላቅ ኢምፓየሮችና ነገስታት ካደረጉት በብዙ እጥፍ ይበልጣል ፡፡ ለምሳሌ ከግሪክ ስልጣኔ እና
ኢምፓየር ይልቅ ታላላቆቹ የግሪክ ፈላስፎች በዘመናቸው ለሰው ልጅ ያበረከቱት ይልቃል ፡፡ ግሪክን ከሚያክል ስልጣኔ ይልቅ በተደጋጋሚ
ስማቸው የሚነሳው ፕሌቶ፣አሪስቶትል እና ሶቅራጥስ እና መሰል የግሪክ ፈላፋዎች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡
በዚህም በአንድ ዘመን ወይም በጥቂት ክፍለ ዘመናት ውስጥ ተነስተው
ገነው ከዚያም ከሚደበዝዙት ኢምፓየሮችና ማንም የሚያስታውሳቸው ከማይኖረው ነገስታት እና ስልጣኔዎች ይልቅ ዘመንና ጊዜን ፣ ትውልድን ቋንቋን መሻገር የሚችለው እውቀትና ሃሳብ እንዲሁም የዚሁ እውቀት ጥበብና ሃሳብ ባለቤቶች ፈላፎችና ገጣሚዎች፣ደራሲዎች፣ሰአሊዎች ይበልጣሉ
፡፡ ለምሳሌ የጥንት ሮማውያንን ብንወስድ ኦቪድን የመሰለ ገጣሚን አፍርተዋል፡፡ ሜታሞርፎሲስንና
(Metamorphosis) የፍቅር ጥበብ (The Art of
Love)ን የመሳሰሉ ፅሁፎችን በቅኔ የፃፈው ይህ ባለቅኔ ፣ ገጣሚና ፈላስፋ የጥንት ሮማውያን ለመቶዎች አመታት በዓለም ላይ በሀያልነት ሲቆዩ ካፈሯቸው በጣት ከሚቆጠሩ ጥቂት ታላላቅ ሰዎች ሆኖ በታሪክ ሲሰፍር ፅሁፎቹ አሁንም ድረስ እንደ አዲስ ይነበባሉ ፡፡ ይህ ገጣሚ፣ በአብዛኛው ስማቸው በደግ ከማይነሳው እንደ ኔሮና ካሊጉላን ከመሳሰሉት ሮማውያን ነገስታት ይልቅ ታሪክ ሲያስታውሰው ይኖራል ፡፡
ሰአሊዎችንም ብንወስድ ለምሳሌ ፓብሎ ፒካሶ ስራዎች ሰአሊው ካለፈ በኋላ፤ አሁንም ድረስ በዋጋም ሆነ በተወዳጅት
የላቁ ሲሆን የእርሱ ስራዎች ዋጋም የአክስዮን ገበያዎችን የሚበልጥ የዋጋ እድገትና ዋስትና ያላቸው ሆነው ተገኝተዋል ፡፡ ሊኦናርዶ
ዳቬንቺም እንዲሁ ከጣልያን የህዳሴው ዘመን ሰአሊና ፈላስፋዎች አንዱ ሆኖ ሁለገብ እና ተወዳጅ አርቲስት ሆኖ በታሪክ ሲሰፍር እርሱ
የኖረበት ዘመን የጣልያን መሳፍንትና መኳንንት እነማን እንደነበሩም ማንም ትዝ አይለውም ፡፡
የዓለም ቱጃሮችን ታሪክን ብንመለከት ከነገስታቱ ብዙም የተለየ አይደለም ፡፡ የአለም ህተ ሀብታሞችም እንደ
ነገስታቱ በቀላሉ የሚረሱ ሲሆን በጣም ደግና ለጋስ ካልሆኑ በስተቀርማ ስማቸውን ማንም አያነሳውም ፡፡ ለምሳሌ አሜሪካዊው ቱጃር
ሮክፌለርን ብንወስድ ተወዳዳሪዎቹን ከገበያ በማስወጣት የሚታወቀው ይሄው የንግድ ሰው ተፎካካሪዎቹን አግባብ ባልሆነ መንገድ ከገበያ
በማሰወጣት ሲታወቅ እርሱ በመሀል ኒውዮርክ ያሰራው የኢምፓየር ስቴት ህንፃ አሁንም ድረስ በኒውዮርክ ከተማ ሲገኝ ለስሙ መታሰቢያ
ቢሆነውም እና የአሁኖቹን የአሜሪካንን የነዳጅ ኩባንያዎች መሰረት ጥሏል ቢባልም ሌላ እምብዛም የሚታወስበት ነገር የለም፡፡
ከዚህ እምንረዳው በታሪክ ለሰው ልጅ አንድ እርምጃ አስተዋፅኦን ያበረከቱ ሰዎች የበለጠ ዋጋ እንደሚሰጣቸው
ሲሆን ፣ ምንም እንኳን ብዙዎቹ በዘመናቸው የማይወደዱና ተሰሚነት ያልነበራቸው ፣ ወይም የተረሱና የተገለሉ የነበሩ ሊሆኑ ቢችሉም
ካለፉ በኋላ ግን የስራቸውን ጥቅም በማየት በመጪዎቹ ትውልዶች የሚከበሩና ዋጋ የሚሰጣቸው ይሆናሉ ፡፡ ከምእራቡ ዓለም አዳዲስ ቴክኖሎጂን
በመፍጠር እንደ ቶማስ ኤዲሰን ፣ስቲቭ ጆብስ ፣ ቢል ጌትስን የመሳሰሉት ሰዎች በታሪክ ስፍራ የሚሰጣው ናቸው ፡፡
ይህ በአፍሪካ የባሰ ሲሆን አፍሪካ ውስጥ ከእውቀት ሰው ይልቅ አሁን በስልጣን ወይም በሀብት ማማ ላይ ያሉ
ሰዎች የበለጠ ዋጋና አክብሮት የሚሰጣቸው ሲሆን ለጥበበኞችና ፣ ለደራሲዎች ፣ ለሰአሊዎችና ለመሳሰሉ አሁን በህይወት እያሉ የሚሰጠው
ክብር እጅግ ዝቅ ያለ ነው ምናልባት ካለፉ ከጊዜ በኋላ ሊሆን ይችላል የተሻለ ክብርንና መታወስን ሊያገኙ የሚችሉት ፡፡
No comments:
Post a Comment