Friday, February 6, 2015

ሰበርና በሌላ ጊዜ የተለየ አቋም የያዘባቸው



አንድ ሰውም የውርስ መብት አለኝ ብሎ የሚያን ከሆነ የውርስ ይጣራልኝ ክሱን አቤቱታውን በሶስት አመት ውስጥ ማቅረብ ሲኖርበት ከሶስት አመት በኋላ ግን ይህ መብት አይኖረውም ይህን የመሳሰሉት በስነ ስርአት ህጉም ሆነ በዋናው የፍትሀ ብሄር ህጉ በግልፅ ያልተቀመጡ ነገር ግን በሰበር ሰሚው የህግ ትርጓሜ የተሰጠባቸው ናቸው ፡፡
ለዚህም አይነተኛ ማሳያው የሰበር ሰሚ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚወስናቸው አስገዳጅ የህግ ትርጓሜን የሚሰጥባቸው ጉዳዮች አንዳንዶቹ በፍትሀ ብሄርም ሆነ በወንጀል ህጎቹና  በስነ ስርአት ህግጋቶች በግልፅ መደንገግ የነበረባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡ ነገር ግን ለአተረጓጎም ክፍትና አሻሚ ሆነው ሲያከራክሩ ሰበር ሰሚው በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ የተለያየ አተረጓጎነም ሊሰጥባቸው ይስተዋላል ፡፡ የዳኞችን ስልጣን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ላይ ሰበር ሰሚው በተመሳሳይ ጭብጥ ላይ ሌላ የተለየ ትርጓሜን መስጠት እንደሚችል የሚደነግግ ቢሆንም በስነ - ስርአት ህጉ ላይ በግልፅ ሊቀመጥ በሚገባው ጉዳይ ግን ሰበር ሰሚ ድረስ በተደጋጋሚ አከራካሪ መሆኑ ግን የህግ ክፍተት ነው ሊባል የሚችለው ፡፡ የክርክሩን ጭብጥ  በመለወጥም አንድ ሰው ምን ብሎ ነው ክስ ማቅረብ ያለበት የሚለውን እንዲሁ ሰበር ችሎት ከሰጠባቸው ውሳኔዎች ላይ ማየት ይቻላል፡፡
በፍትሀ ብሄር ህጉ በግልፅ ያልሸፈናቸው ለፍ/ቤት የቀረቡ ጉዳዮችን አካሄድ በተመለከተ ህጉ ከመውጣቱ በፊት ተፅፈው በስራ ላይ የነበሩ አግባብነት ያላቸውን ህጎች እንደ አግባብነቱ ስራ ላይ ሊውሉ የሚች ስለመሆኑ ነገር ግን አንድ ከሳሽ መጥሪያውን ለተከሳሽ ሳያደርስ ክሱን ቢተወው ወይም ከሳሽ ክስ አቅርቦ ለከሳሸ የሚላከውን መጥሪያ ከፍ/ቤት ውጪ አድርጎ ነገር ግን ለተከሳሽ መጥሪያውን ከማድረሱ በፊት ክሱ እንቋረጥ ያደረገ ከሳሽ ለዳኝነቱ የከፈለው ገንዘብ በሙሉ እንዲመለስለት የሚቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑና ፣ነገር ግን ክስ የመሰማቱ ሂደት ከመጀመሩ በፊት ክሱን በማንሳት መዝገቡ እንዲዘጋ ያደረገ ከሆነ ለዳኝነት ከከፈለው ገንዘብ ለፍ/ቤቱ በኪሳራ ስም የሚቀነሰው ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ ሊመለስት እንደሚገባ የፍብ/ስ/ስ ቁ 232 (1) 245 እና 278 እና የህግ ክፍል ማስታወቂያ 177/74 አንቀፅ 11 በመጥቀስ ብይን ሰጥቶበታል ፡፡
      አንድ ሰው መብቴ ነው ይመለከተኛል በሚለው ጉዳይ ላይ ሁለት ባለጉዳዮች በሚከራከሩበት ወቅት ክርክሩን የሚያውቅ ከሆነ ክርክሩ ከመጀመሩ በፊት ወይንም ክርክሩ ተጀምሮም ከሆነ ከመወሰኑ በፊት ችሎቱን አስፈቅዶ ወደ ክርክሩ መግባት እንዳለበት የፍትሀ ብሄር የስነ - ስርአት ሀጉ በግልፅ ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ እያወቀ ዝም ካለ ምን እንደሚሆን ግን የስነ  - ስርአት ህጉ በግልፅ ምንም የሚለው ነገር የለም ፡፡ እናም መብታችን ተነካብን የሚሉ ወገኖች በክርክሩ ወቅት ዝም ብለው ክርክሩ እንደሚደረግ እያወቁ ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ ግን ውሳኔው አይመለከተንም ወይንም ውሳኔው ውድቅ ይደረግልን ቢሉ ምን ይሆናል የሚለው በሰበር በተደረገ ክርክር ላይ ሰበር የወሰነው ውሳኔ እንደሚያመለክተው ክርክሩን እሚያውቅ ወገን ከመወሰኑ በፊት ወደ ክርክሩ በመግባት መብቱን ማስከበር አለበት ፡፡ በፍትሀ ብሄር የስነ - ስርአት በአንቀፅ 41 መሰረት ጥቅም አለን የሚል ወገን ከሳሽን ወይንም የተከሳሽን እግር በመተካት ካልተቻለም ጣልቃ ገብ ሶስተኛ ወገን ሆኖ ችሎቱን አስፈቅዶ በክርክሩ ውስጥ መግባት እንደሚችል የፍትሀ ብሄር የስነ - ስርአት ህጉ ደነግጋል ፡፡ እነኚህን አንቀፆችን ሳይጠቀም ቢቀርና እያወቀ ዝም ቢል ግን ከፍርዱ እንደማያመልጥ ሰበር በሰጠው አስገዳጅ በሆነ (Precedent) የህግ ትንታኔ ተደንግጓል ፡፡ ይህም ፍርድ ቤቶችን ተገማች ለማድረግ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
ሌላውም እንዲሁ አንድ ፍርድ በሃሰት በተመሰረተ መረጃ ከተበየነ በመጀመሪያ የሰበር ውሳኔ ከይግብባኝ በኋላ ይህንን ድጋሚ አንስቶ መጠየቅ አይቻልም ብሎ ሲወስን በሌላ ወቅት ደግሞ ይግባኝ ተብሎበት ከጸናም በኋላ ቢሆን በሀሰት መረጃ የተፈረደ ከሆነ ፍርዱ ሊሻር እንደሚችል ውሳኔ ሰጥቷል ፡፡ ይህም ሰበር በአንድ ጉዳይ ላይ የተለየ ጭብጥን በመያዝ ውሳኔን መስጠት እንደሚችል በተደነገገው መሰረት ነው ፡፡ በተመሳሳይም ተከራካሪዎች በሽምግልኛ ዳኝነት ለመጨረስ ‹‹አርቢትሬሽን›› (Arbitration) ተስማምተው ሲያበቁ የግልግል ዳኝነት ጉባኤው የሚሰጠው የመጨረሻ ይሆናል ብለው በውላቸው ውስጥ ከተዋዋሉ የግልግል ዳኝነት ጉባኤ ውሳኔ ለሰበር ቀርቦ ሊታይ አይገባም በማለት ከዚህ ቀደም የሰጠውን ውሳኔ የፌደራል ፍርድ ቤቶችን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ 454/ 1997  አንቀጽ 2 (4) መሰረት በቅፅ 10 በሰ/መ.ቁጥር 42239 በሰበር ሊታይ ይችላል ሲል በይኗል ፡፡ ሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች በውላቸው የዳኝነት ጉባኤው የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ነው ብለው ቢዋዋሉም የግልግል ዳኝነት ጉባኤው ውሳኔ በፍርድ ቤት ሊታይ የሚችል ነው ብሎ አቋሙን ለውጦ ፈርዶበታል ፡፡ 
የአከራይ ተከራይን ህግን ብንወስድ በአንድ ወቅት አከራዩ በተከራዩ ላይ ምክንያትን በመጥቀስ እንዲለቅ ሲጠይቅ ምክንያቱ በቂ አይደለም በማለት ይልቀቅ መባሉ ተገቢ አይደለም ሲል ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ አከራዩ ምክንያት ጠቅሶ ተከራዩ ይልቀቅልኝ ሲል የጠየቀውን ደግሞ አከራዩ ይልቀቅ ማለት ይችላል ፣ ያለበለዚያ የአከራዩን መብት የሚያጣብብ ነው በማለት ቤቱ በአከራዩ ጥያቄ መሰረት ተከራዩ መልቀቅ አለበት ሲል የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቷል ፡፡ ምክንያት የጠቀሰው አከራይ ምክንያቱ በቂ አይደለም በሚል ማስለቀቅ አይችልም ሲባል በአንፃሩ ምክንያት ያልጠቀሰው አከራይ ግን በጥያቄው መሰረት ቤቱ እንዲለቀቅለት ተወስኖለታል ፡፡

No comments:

Post a Comment