ኤክሀርት ቶሌ የተባለው የአሁንት
ሀይል ‹‹The Power of
Now›› የተሰኘና
ሌሎች በርካታ መሀፍትን ያበረከተው የዘመናችን እውቁ ረቂቅ መንፈሳዊ አዋቂ ‹‹ሚስቲክ››
መሆኑ የሚነገርለት ይህ መንፈሳዊ መምህር እንደሚለው ብዙ ሰዎች አሁንን ረስተው የሚያስቡት ገና ስላልደረሱበትና ወደፊት ስለሚመጣው
ወይም ሊመጣ ስለሚችለው ነገር ነው ፡፡ አሁን የሚያደርጉት ነገር በሙሉ ወደፊቱ ለሚሰጠው ውጤት ብለው ሲሆን ፣ የአሁንን ጊዜ ለወደፊቱ
መሸጋሪያ ብቻ አድርገው ይወስዱታል ፡፡ ነገር ግን ያ ወደፊት የሚሉት ነገር ወይም ሁኔታ ላይመጣም ፣ ላይኖርም፣ ላይከሰትም ይችላል
፡፡ በዚያን ወቅት እነርሱም ያንን ነገር ለማየትም ሆነ ለመመልከት በዚያ ቦታ ላይገኙም ፣ ላይኖሩም ይችላሉ ፣ ነገር ግን ልክ
በወደፊቱ ጊዜ እንደሚኖሩ እርግጠኛ በመሆን ላልደረሱበት ጊዜ አሁን የሚያደርጉትን የወደፊቱ እነርሱ ይመጣል ለሚሉት ነገር መሰረት
እየጣሉ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ ፡፡
በኤክሀርት አባባል ሰዎች ደስታ ወደፊት
ርቆ ያለ እና ገና ወደፊት እሚደረስበት ነገር መሆኑን አድርገው ያስባሉ ፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ከዚህም አልፈው የአሁን ወቅት የወደፊቱ
፣ የሚመጣው እንቅፋት እደሆነ አድርገው ያስባሉ ፣ ለአሁኑ ወቅት ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረትና ጥቃቄን ፣መደረግ ያለበትንም ነገር
በአግባቡ ሳያደርጉ ይቀራሉ ፡፡ የዚህ አይነት ሰዎች የአሁንን ወቅት በአግባቡ ሳይጠቀሙበት የሚቀሩት እነሱው ሲሆኑ ፣ ነገር ግን
ለራሳቸው የሚስቡት የአሁኑን ወቅት በትክክል እየተጠቀሙበት እንዳሉ ነው ፡፡ በዚህም በእጃቸው ያለውን የአሁኑን ወቅት በአግባቡ
ሳይጠቀሙበት ይቀራሉ ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ የሚያደርገው ነገርና የሰው ልጅ ቆይታም በጊዜ ሂደት ውስጥ ያለ ነገር እንደመሆኑ
የአሁኑ ወቅት አመለጠው ማለት በህይወት ጉዞው ውስጥ ‹‹ህይወቱ አመለጠው›› ማለት መሆኑን ኤክሀርት
አበክሮ ያስረዳል ፡፡
ኤክሀርት እንደሚያክለው ‹‹በሆነ
ወቅት ስኬታማ እሆናለሁ ብላችሁ አታስቡ እናም ወደፊት በአንድ ወቅት እንደዚህ እሆናለሁ ብላችሁ አትጠብቁ ፣ ከአሁኑ ወቅት ጋራ
ስኬታማ የሆነና የሚመቻሁን ግንኙነት ውህደትና መስተጋብርን ፍጠሩ እንዲሁም አሁን በምትሰሩት ማንኛውም ነገር ምሉእነትና እርካታ
ይሰማችሁ›› ይላል ፡፡ ብዙ ሰዎች እነሱ ለማይኖሩበት ዘመንና ለማይገኙበት ወቅት ሲዘጋጁ ማየትና
መስማት የተለመደ ነው ፡፡
በእርግጥ እዚህ ጋር የሰው ልጅ በእቅድ
የሚመራ እንደመሆኑ መጠን እቅድን አያውጣ ፣ ለወደፊቱ መሰረትን አይጣል ማለት እንዳልሆነ ግልፅ ነው ፡፡ ሰዎችን ትተን አገራትም
ጭምር የአምስት ፣ የአስር አመት እቅድን ያወጣሉ ግብ እና ራእይ ያስቀምጣሉ ፡፡ አሁን እምናደርገው ነገር ለወደፊቱ መሰረት መሆኑን
አሁን በትክክል ያላደረግነው ነገር አድሮ መልካም ውጤትን እንደማያስገኝልን የምናውቀው ሀቅ ነው ፡፡ አሁን መልካም ነገርን ካደረግን
ግን የዚያን ውጤነትን እንደምናጭድ ፣ አሁን ባልጣልነው መሰረት ላይ ወደፊት እንደማንገነባ የታወቀ ሲሆን ፣ ታላቁ መጽሀፍም ‹‹ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው››
ይለናል ፡፡
ኤክህርት ግን ይህንን ቀላል ሀቅ
በመዘንጋት ሳይሆን ሰዎች ግላዊ ህይወታቸውን በዚህ ምድር ላይ በሚኖሩበት ወቅት የዚህ ምድር ቆይታችን አጭር እንደመሆኑ መጠን በዚህ
በተወሰነ እድሜ ልናደርግ የምንፈልገውን ነገር ገና ለገና ወደፊት ላልመጣው ዘመን ማድረግ የምንፈልገውን ነገር ሳናደርግ በመዘጋጀት
ብቻ እንዳንጨርሰው ለመጠቆም መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
‘time isn’t precious
at all , because it is an illusion’ Eckhart Tolle
መፅሀፍ
ቅዲስ ትንቢተ ኢየሳያስ ‹‹ሃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ አመዳይ ብትሆን እንደ ሸማ ትነጣታለች››
ይላል ‹‹ኑና እንዋቀስ›› ያለፈውን እርሱንና ስለአሁኑ ብቻ አስቡ ፡፡ በአሁኑ ውስጣችሁ
ከተለወጠ ፡፡ ስለ አለፈው ሃጢአታችንም ሆነ ስለ መጪው ስኬታችን አብዝተን መተማመን የለብንም ፡፡ ይህ በቅዱሳን መፅፍት ውስጥም
የሰፈረ ነው ፡፡