የዳኝነት አካሉ የዜጎች በህግ ፊት እኩል የመሆንን ፣እንዲሁም ፍትህ
የማግኘት መብት በህገ መንግስቱ የተረጋገጡትን ለማስፈፀም የተቋቋመ አካል መሆኑ በህገ መንግስቱ እውቅና የተሰጠው መሆኑ ግልፅ ነው
፡፡ የሰበር ስርአት አላማው ወጥ የሆነ የህግ አተረጓጎም እና አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል ነው ፡፡ የሰበር ስርአት የህግ የበላይነትን
ለማረጋጥ የተቋቋመ እና ማረጋገጫ ዘዴ ነው ፡፡ የውሳኔዎች ወጥነትና ትክክለኝነት የሚረጋገጠው በዳኝነት አካሉ የመጨረሻ አካል በሆነው
በሰበር ሰሚ ችሎት ነው ፡፡ የህግ ስህተት ያለበትን ውሳኔ ፀንቶ እንዲቆይ ማድረግ የዳኝነት አካሉ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ተአማኒነትና
ከበሬታን ይጎዳል ፡፡ይህንንም ለማስተካከል ይህ የዳኝነት አካል ስልጣን ተሰጥቶታል ፡፡ ከዚህ በኋላ የዳኝት ስርአቱን እርከኖችን
ከጨረሰ በኋላ አንድ ሰው ሊሄድ የሚችለው ወደ ህገ - መንግስታዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ወደሚገኘው ተቋም ይሆናል
፡፡ አንዳንድ ግዜ ህግ ሲተረጎም የግለሰቦችን ወይንም የተቋማትን የማይገሰሱ ህገ - መንግስታዊ መብቶችን ሊጥስ ይችላል ይህን ለማስተካከል
ደግሞ የህገ መንግስዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሊያያቸው እንደሚችል ተደንግጓል ፡፡
ይህ ስርአት ከቀድው የግርማዊ ንጉሰ ነገስት የዙፋን ችሎት የነበረና
በኤፌደሪ ህገ መንግስት በ1987 ዓም በወጣው በአንቀትፅ 83 ስር የሚገኝ ሲሆን ዝርዝር በአዋጅ ቁጥር 25 / 1988 እና አዋጅ
ቁጥር 454 /97 የተደነገገ ስርአት ነው፡፡ ይህ ከአምስት ያላነሱ ዳኞች የሚሰየሙበት ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም ራሱ በሌላ
ጊዜ እስካለወጠው ድረስ በየትኛውም ደረጃ ለሚገኝ የዳኝነት አካል አስገዳጅ ሃይል (ፕሪሲደንስ) ያለው ስለመሆኑ በአንቀፅ 2
(4) ተቀምጧል፡፡ በዚህም መሰረት ሰበር ችሎቱ የቀድሞውን ውሳኔ
በአዋጅ ቁጥር 454 / 1997 አንቀፅ 2(4) መሰረት መለወጥ እንደሚችል ተደንግጓል ፡፡
No comments:
Post a Comment