Friday, February 6, 2015

Ethiopian Economy Challenges and Opportunities



የኢትዮጲያ ምጣኔ ሀብት ግመታዊኔተነት ምርታማ ከሆነ ስራ ይልቅ የበለጠ ገቢን የሚያስገኝ ፣ የማያደለም ቀላልና በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንዘብ የሚታፈስበት ነው (in Ethiopia speculative behavior is more rewarding than productive work) ፡፡ ለዚህ ግምታዊነት ዋነኛ ምክንያቶቹ  ምንድን ናቸው ቢባል በርካታ ምክንያቶች ሊቀርቡ ይችላሉ ፤-
አንዱ የመንግስት ፖሊሲ ሲሆን ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ኢትየጲያ እንደ ነዳጅና የመሳሰለው የተፈጥሮ ሀብት የሌላት አገር በመሆኗ ነገር ግን ለምና ለኑሮ ፣  ለግብርናና ለከብት እርባታ አመቺ ሰፊ መሬት ያላት አገር ነች ፡፡
በዚህ ምክንያት መሬት ምንም እንኳን በገጠርም ሆነ በከተማ መሬት ዋነኛው የሀብት ምንጭ ቢሆንም ነገር ግን የሚጠራው የመሬቱ ዋጋ እጅግ የናረ ሲሆን ፤ ለምሳሌ መርካቶ በርበሬ ተራ የሚገኝ መሬት በካሬ ሜትር 305 ሺህ ብር ጨረታ ቀረበለት ሲባል ይህም የመሬት ዋጋ ምናልባት ለንደንና ከኒውዮርክ ወይም ከቤጂንግ ጋር ቢወዳደር ነው እንጂ በአንዲት ታዳጊ አፍሪካዊት አገር ነው ቢባል አስገራሚ ሊሆን ይችላል ፡፡ ገዢውስ ቢሆን ይህን ያህል ለመሬቱ ግዢ አውጥቶ መቼና እንዴት ሊመልሰው ነው ? ምን ሊያገኝበት ነው ? ሊያስብል ይችላል፡፡ 
ሌላው ደግሞ የባህሉ እንዲሁም በአጭር ጊዜ ውስጥ የመክበር ፍላጎት እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ያሉት ሀብትን የማግኛ እድሎች እጅግ ጠባብ መሆን ለዘመናት በአስከፊ በድህነት ውስጥ በኖረና ሰፊ እድል በተነፈገው ህብረተሰብ ውስጥ የዚህ አይነት ባህሪ ቢኖር አስገራሚ አይሆንም ፡፡
የተለመደው የዋጋ ትመና መርሆ በሀገራችን አንዳንድ ጊዜ አልሰራ የሚልበት ወቅት አለ ፡፡ ለምሳሌ የነዳጅ ዋጋ በአለም በቀነሰ ወቅት በ2014 ዓ.ም ከ60 ዶላር በታች ወርዶ በነበረበት ወቅት ሲሆን በሃገራችን ግን የነዳጅ እጥረት ተፈጥሮ ነበረ ፡፡ አንድ በአንፃሩ ደግሞ አንድ ጊዜ ዋጋ ከጨመረ ተመልሶ የማይቀንስ ሲሆን ፣ የአንድ ሸቀጥ ዋጋ በአለም ወይም በአገራችን ሲቀንስ ደግሞ ሸቀጡ ከገበያ ይጠፋል ፡፡

የአሜሪካ የኢራቅ ወረራ



ፖል ብለሬመን አሜሪካ ሆነ ብላ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲን ትከተል እንደነበረ በፃፉት መፅሀፍ አጋልጠዋል ፡፡ አሜሪካና እንግሊዝ የኢራቅን የመከላከያና የፖሊስና የደህንናት ተቋማትን በማፈራረስ ፣ ሃገሪቱን በእጃቸው ካገቡ በኋላ በአገሪቱ ላይ ያደረጉት ጉዳት ከባድ ነው ፡፡  በ 1991 የህዝብ አመፅ በኢራቅ የነበረ ሲሆን አሜሪካውያን ይህንን የህዝብ አመፅ ባልደገፉትም አሜሪካ እንግሊዝ የፈለጉት አልላገኙም ፡፡
አሜሪካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርት ወዲህ በዓለም ዙሪያ 54 መንግስታትን በቀጥታ በራሷ ጣልቃ ገብነት ገልብጣለች ወይንም በተዘዋዋሪ መንገድ በደህንነት ተቋማቶቸዋ እና ከሌሎች ታባባሪዎቿ ጋር ሆና አስገልብጣለች ፡፡
አሜሪካ ለአልማሊኪ መንግስት ኢራቅን ለቃ እንድትወጣና በአለም ግዙፉን ኤምባሲ በማቋቋም ለማካከስ ብትሞክርም አሜሪካ ስትራቴጂያዊ  በሆነችውና የገዘፈ የነዳጅ ክምችት ባላት ኢራቅ ወታደራዊ የጦር ሰፈር መኖሩ እጅግ ይጠቅማት የነበረ በመሆኑ መቆጨቷ ግልፅ ነው ፣ ነገር ግን ኢራቃውያን የአሜሪካንን ወታደራዊ የጦር ሰፈር አንፈልግም በማለታቸው ግን ፕሬዝዳንት ኦባማ ሌላ አማራጭ ስላልነበራቸው ለቀው ለመውጣት ተገደዋል ፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ በኢራቅ ምክር ቤት እንዲሁም በሺአ የበላይነት የምትመራው ኢራቅ ወደ ኢራን ማዝመሟ ስላላስደሰታት ኢራቅን ለኢራቅ እጅግ አስፈላጊ የነበረውንና ልትሰጥ የሚገባውን ወታደራዊ የጦር መሳሪያ አቅቦትን አላደረገችም ፡፡ በዚህ ምክንያት ደካማውና አስፈላጊውን ትጥቅ በሚገባ ያላገኘው የኢራቅ ሰራዊት አይ ኤስ ኤስን መቋቋም አልቻለም ፡፡
የእንግሊዝ መሪዎች በተደጋጋሚ ለአሜሪካ ጥቅም ተጋሪ ሆነው አሜሪካ ወረራን ሲፈፅም አብረው የሚሄዱትና ወደ ጦርነት የሚገቡበት ምክንያት አንግዳ ሊሆን ይችላል ፡፡ ነገር ግን እንግሊዝ የአለም ሀያል ቅኝ ገዢ ከነበረችበት ጊዜ ጀምሮ ምንም እንክዋን ወታደራዊ የበላይቷንና በርካታ ግዛቶቿን ብታጣም ከዚያው ከቅኝ ግዛት ዘመኗ የወረሰቻቸው እጅግ ግዙፍ የኢኮኖሚና የንግድ አውታሮች ባለቤት ነች ፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ ሀይሏን ለመከላከልም የአሜሪካንን ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ሃያልነት እንደ ጃንጥላ በመጠቀም ነው የራሷን ጥቅም የምታስከብረው ፡፡
ለምሳሌ በስኮትላምደነንድ ሎከርቢ አየር ላይ የፈነዳው የፓን አም አወረውሮፕላንን በወቅቱ በጋዳፊ የምትመራው የሊቢ የደህንነት ሰዎች አፈነዱት ቢባልም አልጀዚራ የራሱን የወንጀል መርማሪዎችንና ሳይንቲስቶችን በመቅጠር በሰራቸው ጥናታዊ የዘገባ ፊልሞች ግን ትክክለኛው የፍንዳታው አቀናባሪ የኢራን የደህንነት ሃላፊዎች እንጂ የጋዳፊ ሊቢያ አለመሆኗን አረጋግጧል ፡፡ ይህም የሚያሳየው የእንግሊዝ ሆነ የአሜሪካ ባለስልያተጣናት የጉዳዩን ትክክለኛ ገፈፃሚ ቢያውቁም አልሚግራሂ የተባለው የሊቢያ የደህንነት አባል እንዳደረገው ተቆጥሮ ለእስር ተዳርገዋዋል ፡፡፡  
እንግሊዝ በተደጋጋሚ የአውሮፓ ህብረት ጋር ለመተሳርም ሆነ ዩሮን ለመጠቀም ፈቃደኛ የማትሆንበት ምክንያትም አብዛኛው የኢኮኖሚ ጥቅሟ ቀድሞ የቅኝ ተገዢዋ ከነበረችው ከአሜሪካ ጋር ይበልጥ የተሳሳሰረ በመሆኑ ሲሆን ይህንን ጥቅሟንም የምትከላከልላት ግዙፍ የመከላከያ ሃይል ያላት አሜሪካ ስለሆነች አሜሪካ በገባችበት ገብታ ጦርት ውስጥ የምትገባው ፡፡ 

ኢራንና ምእራባውያን

የኢራን ኢኮኖሚ ከሌሎች በመገለል ሊድግ እንደማይችል የኢራኑ መሪ ሃሰን ሮሀኒ አስታውቀዋል ፡፡ ኢራብንና ሩስጠያ ሶርያን በመደገፋቸው ዋጋን ከፍለዋል ይህም የነዳጅ ዋጋ እንዲወርድ መደረጉ እንዲሁም ሩስያ በዩክሬይን ሰበብ ሩስያ የከባድ ማእቀብ ሰለባ ሆናለች ፣ አውሮፓውያን ሳይቀር ተጎጂ በመሆናው ሩስያ ላይ የተጣለው ማእቀብ ሩስያን ይጎዳል ቢሉም አሜሪካ ግን ሩስያ ላይ አምራ ቆይታለች ፡፡
ፍልስጥኤማውያን የአለም አቀፍ የወንጀል ኮሚሽን አባል ለመሆን ያመለከቱ ሲሆን ይህም በፍልስጥኤማውያን ላይ የጦር ወንጀልን ዩፈፀሙ እስራኤላውየን የአይ ሲ ሲ አባል በሆኑ አገራት ጉዞን በሚያደርጉበት ወቅት የመታሰር እጣ የሚገጥማቸው ሲሆን የእስራኤል ባለስልጣናት በጦር ወንጀለኝነት እንዲጠየቁ ያደርጋል፡፡
ሳሂብ ኤራካት የተባሉ የፍልስጥኤማውያን ተደራዳሪ እስራኤል ምንም አማራጭ አልሰጠችኝንም በማለት እስራኤል ፍልስጥኤማውያን ላይ በፈጸመቻቸው ወረራዎችና የጦር ወንጀሎች በሰብአዊ መብት ላይ በተፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተጠያቂ እንድትሆን ለማድረግ ነው፡፡ 
ይን እንጂ እስራኤልም በበኩላቸው ይህ የፍልስኤማውያን ድርግጊት መልሶ ራሳቸውን ፍልስጥኤማውያንን ይጎዳል ያለች ሲሆን እርሷም በበኩሏ በየወሩ ለፍስጥኤማውያን ማስገባት የነበረባትን 128 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የያዘች ሲሆን አሜሪካ ለፍልስጥኤማውያን የምትሰጠውን ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሆነ ገንዘብንም አሜሪካ እንድትይዝ እየገፋፋች ትገኛለች ፡፡ እስራኤል ወታደሮቿና ባለስልጣናቷ በዓለም የጦር ወንጀለኛ በሚያደርግ የዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኝነትን በሚያየው ፍርድ ቤት መቅረባቸው አደጋውን በመረዳት ያሰጋት ሲሆን ለዚህም ይመስላል ሁኔታውን ፍልስጥኤማውያንን መልሶ ይዳል በማት ለማስፈራራት እየሞከረች ያለችው ፡፡
ሁሉንም ሙአባውያን ግደል በሚል መፅሀፍ ቅደስ ላይ የሰፈረውን ለመተግባር ይመስላል የአሁኑ ቤንያሚን ኔታንያሁ እያደረጉ ያሉት ብለው ይተቿቸዋል ፡፡እ.አ.አ. በህዳር 2012 ፍልስጥኤም በተባሩት መንግስተት ውስጥ የታዛቢነት ወንብርን ያገኘች ሲሆን ምንም እንኳን እስራኤል ብትቃወምም የታዛቢነት ወንበሩን አግኝታለች ፡፡

የመካለኛው ምስራቅና ነውጡ

መካከለኛው ምስራቅ ሰላምን ካጣ እጅግ በርካታ አስርት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን እስራኤል እንደ ሀገር ከተቋቋመችበት ጊዜ ጀምሮ የዓረብና የእስራኤል ውዝብ ግብ የብዙዎቹን ህይወት ሲበላ ቆይቷል ፡፡ ‹‹የእስራኤልን ምርት ፣ እቃና አገልግሎት አትግዙ ፣ እስራኤል ላይ ማእቀብ ጣሉ›› በሚል እስራኤልን ከቀድሞው የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ስርአት ጋር በማመሳሰል እስራኤሎች በበኩላቸው  በበኩላቸው ሲመልሱ እስራኤል በአለም ላይ የብዝሀ ዘረ የሰው ዘሮችን በአገር መሆኗንና ፣ በመካከለኛው ምስራቅ በነፃነት የሚኖሩት አረብ የሆኑት የእስራኤል ዜጎች መሆናቸውንና ሲከራከሩ እንዲሁም እስራኤል ምርትና አገልግሎትን ማእቀብ መጣልና ማግለል ማለት ናዚ ጀርመን በእስራኤል እቃዎች ላይ ያደረገውን እ.ኤ.አ በ1930ዎቹ በእስራኤል ነጋዴዎችና ምሁራን ላይ ካደረገው ማግለልና ማእቀብ ጋራ ያመሳስሉታል ፡፡
እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረገችውን ድብደባና ጦርነትን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ፍርድ ቤት ሃማስን ከአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ ሲወስን የእስራኤል መሪዎችን አብግኗል ፡፡
ራሳቸው አንዳንድ አይሁዳውያን ሳይቀሩ ፣ ሜድ ኢን እስራል የሚሉ ሸቀጦችን አንገዛም ማለት የጀመሩም አሉ ፡፡ በአንዳንድ አገራት እንደ ባንግላዲሽ ባሉ አገራት የእስራኤልን ብቻም ሳይሆን የአሜሪካንን እንደ ፔፕሲና ኮካ ኮላ ያሉትን ምርቶችን ላለመግዛት ማእቀብ እስመጣል ደርሰዋል፡፡ ስቴፈን ሀውኪንጊስና ስቲቪ ወንደር እስራኤል የነበረው ኮንሰርት ሲሰርዝ ሀውኪንግስ ከእስራኤላውያን ዘፋኞች ጋ የነበረውን መገናኘትን ሰርዘዋል፡፡ የዚህ አይነት ጉዳዮች የምእራቡ ዓለም ሚዲያ ብዙም የማይዘግባቸው ናቸው  ፡፡
ሳላህዲን እየሩሳሌምን ሲይዝ ምንም ደም ያልፈሰሰ ሲሆን በአንፃሩ ግን የመስቀል ተዋጊዎች እየሩሳሌምን ሲይዙ ግን የመስቀል ተዋጊዎች በርካታ ደም አፍስሰዋል የሚል ክርክርን የዓረብ ታሪክ ጸሀፍት ታሪክን በመጥቀስ  ያወሳሉ፡፡
የዛሬውን አያድርገውና በስፔን እስላሞች ገዢ በነበሩበት ወቅት አይሁዳውያን በነፃነት እንያምኑ ይፈቅዱ ስለነበረ
ስሊሞች የጸሎት አቅጣጫቸውን ወደ አልአቅሳ መስጊድ አድርገው ነው የሚሰግዱት ፡፡ ለሶስቱም እምነቶችም ማለትም ለክርስትናም ፣ለአይሁድና ለእስልምና እምነቶች አልአቅሳ መስጊድ ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡ ነቢዩ ፣መሀመድ ሲያርፉ ከመካ ወደ አልአቅሳ መስጊድ ከዚያም ወደ አላህ ያረጉበት ነው ብለው ሙስሊሞን የሚያምኑበት ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡ እስራኤል በእየሩሳሌም ለመጣ ምንም አይነት ምህረት እንደሌላት በተደጋጋሚ በወሰደቻቸው የጭካኔ እርምጃዎች አሳይታለች ፡፡
የእስላሙ ዓለም ችግር አንድነት አለመኖር ፣ አንዱ ሲሆን ሌላው ምንም እንኳን ሂሳብን ፣ ሳይንስንና አስትሮኖሚንና ህክምናን የመሳሰሉ ጥንታዊ ጥበቦች ያፈለቁትና አውሮፓውያን በጭለማው ዘመን በነበሩበት ወቅት ከግሪኮችና ከሮማውያን የተገኙ ታላላቅ አስተሳሰቦችን የፕሌቶን ጨምሮ ለተቀረው የሰው ልጅ ጠብቀው እንዲተላለፍ ያደረጉት አረቦች ቢሆኑም በዘመናዊ ጊዜ ግን የአረቡ ዓለም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ወደ ኋላ መቅረቱ በትምህርት እና በእውቀት ከአይሁዳውያን ጋራ የሚወዳር አለመሆናቸው ሌላው የአረቦች ድክመት ነው ፣‹‹በአላህ ገመድ ላይ በአንድነት ተንጠላጠሉ ፣ አትለያዩ ›› ቅዱስ ቁርአን ላይ የሰፈረ ቢሆንም እስላሞች እርስ በእርስ አንድነት ያላቸው አይደሉም ፡፡
በእስልምና ሃይማኖት የሚደረጉ ቅጣቶች ለምሳሌ በጅራፍ መግረፍ ፣ የመሳሰሉት እስላማዊ ምሁራን በሚከራከሩበት ወቅት እንደሚሉት በምእራቡ ዓለም እንደሚታየው አንድን ሰው በትንሽ ጥፋት አስርት አመታትን በእስር የሚያሳልፍበት ፣ በርካታ ገንዘብ የሚቀጣበት ስርአት ይልቅ ለጥቱ ከተፀፀተ ይቅርታን የሚያደርገው የእስልምና ሃይማኖት የተሻለ ነው የሚል ክርክርን ያቀርባሉ ፡፡
አይሁዳውያን 10 እና 13 በመቶ ድረስ በፒኤች ዲ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን በአረቦች ግን አንድ ከሚሊንም አይገኝም ይላሉ ራሳቸው አረቦች ፡፡ ከዘከ
ከዚህ አንፃር ለክፍለ ዘመናት አይሁዳውያን አንድነታቸው እጅግ ጠንካራ ሲሆን በየትኛውም አገር የሚገኙ አይሁዳውያን ዓለም ዓቀፍ በሆነ ሁኔታ የሚኖሩበት አገር መለያየት የተነሳ ዜግነታቸው እንኳን ቢለያይ በአይሁድነታቸው ግን አንድነታቸውን እንደጠበቁና እርስ በእርስ በመገናኘት የአውሮፓንና የሃያሊቱን አሜሪካን መሪዎችንና ግዙፍ ዓለም ዓቀፍ የንግድና የሚዲያ ተቋማትን በመዳፋቸው በማስገባታቸው ምክንያት አይሁዳውያኑ ያላቸው ዓለም አቀፋዊ ሀይልና አቅም እጅግ ጠንካራና የማይደፈር ነው ፡፡
በምእራቡ ዓለም ያሉ አይሁዳውያያን በእስራኤል ካሉ አይሁዳውያን ጋር ያላቸውን ትስስር እየቀነሰ መጥተዋል የሚሉ ጥናች አሉ ፣ በምእራቡ አለም ያሉ አይሁዳውያን ለፅዮናዊቷ እስራኤል ያላቸው ድጋፍ እየሳሳ መጥቷል ፡፡
አል አቅሳ መስጊድ በሰለሞን የተነገነባ በነቢዩ ሱሌይማን ነው ፡፡ ሙሴ እስላም ነው ፡፡
ቦኮ ሀራምና አይ ኤስ አይኤ አል ቃኢዳን የመሳሰሉ ለእስልምና መልካም ገፅታን በማጉደፍ በኩል ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ራሳቸው የእስላማዊ ምሁራን የሚያነሱት ጉዳይ ነው ፡፡ በእዝነት ‹ኮምፓሽኔት› አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተው እስልምና አውሮፓም አሜሪካ እስልምናን ይፈራሉ እስላም ኮምፓሽኔት እምነት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ይህንን የእስልምናን ገፅታ ለዓለም በደንብ ማሳየት ይገባናል ባይ ናቸው ፡፡

የቀድሞው የአሜሪካን ፕሬዝደንት የነበሩት ቢል ክሊንተን በህይወት ታሪክ መፅሀፋቸው ላይ ሲፅፉ ‹‹ምንም እንኳን የአሜሪካን ፕሬዝደንት በዓለም ላይ በጣም ሀያሉ ሰው ቢባልም፣ ምንም ማድረግ የማንችልባቸውና አቅመ ቢስ የምንሆንባቸው በርካታ አጋጣሚዎች አሉ›› ብለዋል ፡፡
በምእራባውያንንና በኢራን መካከል የሚደረገው ኢራንን የኒውክየር ጦር መሳሪያ  ግንባታን ለማስተው የሚደረገው ድርድር በአብዛኛው ለአለመተማመኑ መንስኤ የኢራን መሪዎች ለእስራኤል ያላቸው ክፉኛ መጠራጠርና አለመተማመንና ጥላቻ ሲሆን ኢራን የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ብትታጠቅ ስጋቱ ለአሜሪካ ሳይሆን ለእስራኤል መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
አሜሪካኖች የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጃፓን ላይ የተጠቀሙበትን የአቶሚክ ቦምብ የተሰራበትን ህንፃና አካባቢውን ወደ ሙዚየምነት ቀይረውታል ፡፡ በዚህም ‹‹የሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዲያበቃ ያደረጉ›› የሚል ፅሁፍ የተፃፈበት ይሄው ሙዚየም በሚል ታሪካዊ ሙዚየም ሆኖ በአሜሪካ መንግስት ወደ ሙዚየምነት መለወጡ ጃፓናውያንን ቅር አሰኝቷል ፡፡
ኢራን ኒውክሊየርን ለሰላማዊ አገልግሎት ነው የማበለፅገው ትበል እንጂ በተግባር ግን ለቦምብ መስሪያ ነው ለዚህም የደህንነት መረጃ አለን የሚሉት ምእራባውያን የቀድሞው አክራሪው መሪ አህመዲን ነጃድ ከስልጣን ከወረዱ ወዲህ ከአዲሱ መሪ ጋር መልካም ግንኙነትን በመፍጠር ድርድር ጀምራ የቆየች ቢሆንም ከሶስት ወራት በኋላ ዳግም መሪዎቹ ሲገናኙ በኢራን በኩል እብምብዛም የአቋም ለውጥ ባለመኖሩ ምክንያት እንደገና ተጨመናሪ ጊዜን ለኢራን ለመስጠት ምእራባውያኑ ተገደዋል ፡፡
በኢራን አመራር በኩል ምእራባውያኑም ሆኑ እስራኤል ትክክለኛ ጥርጣሬ አላቸው ይሄውም በኢራን በጣም ቀወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በውሳኔን የሚሰጡት አያቶላህ ሲሆኑ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ባለመሆናቸው ምክንያት በሻሆች የምትመራው ኢራን ለዘብተኛ ሆና የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ማበልፀጓንና ምርምሯን ታቆማለች ብሎ ማሰብ ፈታኝ ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ከእስራኤል ጋር ጦርነት ላይ ያሉትን ሃማስንና ሂዝቦላህን በገንዘብና በመሳሪያ የምትደግፈው ኢራን ፣ እንዲሁም በኢራቅ የሺአዎችን መንግስት የምትረዳው እንዲሁም በአካባቢው ሺአዎች ባሉባቸው እንደ ባህሬን ፣ ሳኡዲ አረቢያና የመን ባሉ የአረብ አገራት ውስጥ ተሰሚነት ያላትና ከሱኒ አረቦች ጋር ታሪካዊ የሆነ የከረረ ውዝግብ ያላት ፣ እንዲሁም በምእራባውያንና በሱኒ የአረብ መንግስታ እየተረዳ ለስምንት አመታት በጦርነት የተገተጋት የኢራቁ ሳዳም ሁሴን የመረረ ትውስታ ያላት ኢራን ኒውክሊየር መታጠቅ ያስፈልገኛል ብትል ከራሷ አንፃር ካለባት ስጋት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡   
ሳኡዲ አረብያ ካላት ዳጎስ ያለ የገንዘብ ምንጭ በመጠቀም የአረብን አለም ለማረጋጋት  ተጠቅማበታለች ፡፡ ለምሳሌ የአል ሲሲን መንግስት ለመደገፍ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በብድርና በነዳጅ ዘይት ስጦታ ለግብፅ የሰጠች ሲሆን ግብፅ የከፋ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ እንዳትገባ ፤ለማገዝ መሆኑ የታወቀ ነው ፡፡ ሳኡዲዎች ወታደራዊውን መንግስት ሲደግፉ በአንፃሩ ትንሽዬዋ ኳታር የግብጽን ወታደራዊ መንግስት አለመደገፍ ብቻ ሳይሆን ያላትን ግዙፉንና ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ያለውን አልጀዚራን በመጠቀም በግብፅ ወታደራዊ መንግስት ላይ ዘመቻ ስታካሂድ በዚህም የበሸቀው የግብፅ የአል ሲሲ መንግስት ሶስቱን በግብፅ ለአልጀዚራ ሲዘግቡ የነበሩትን ጋዜጠኞች በማሰርና የአልጀዚራ ጋዜጠኞችን ከግብፅ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል ፡፡ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን ጉልበት ትበዘብዛለች ተብላ የምትታማው ኳታር
እ.ኤ.አ. በ2014 ዓም በጋዛ በተደረገው ጦርነት ጋዛን እንዳልነበረ አድርጋ ያወደመችው እስራኤል የወደመውን የጋዛ ከተማ እንዲገነባና ቤቶቹም ተመልሰው እንዲሰሩ የሚያስፈልገውን ሲሚንቶ እንዳይቀርብ በመከላከሏ ምክንያት ጋዛን መልሶ ለመገንባት አስርት አመታት ያስፈልጋል ብለዋል ፍልስጥኤማውያን ፡፡
ሳኡዲ አረብያ ለደሀይቱ ጎረቤቷ ለየመንም እንዲሁ በቢሊዮንኖች የሚቆጠር ገንዘብ የለገሰች ሲሆን የመን መረጋጋት ከራቃት ውሎ አድሯል ፡፡ በተለይም የሳኡዲ ሱኒ መሪዎች የሚፈሯቸው የሺአ ሚሊሺያዎች ሰፊ የየመንን ግዛት መቆጣጠራቸው ስላሰጋት እርዳታዋን ለመቀነስም ተገዳለች ፡፡ 
የመካከለኛው ምስራቅ ውዝግብ ዋነኛ ገጽታዎች ሶስት ሲሆኑ አንዱ አረቦች እና ኢራን  ከእስራኤል ጋር ያላቸው የድንበርንና የይገባኛል የቆየ ውዝግብ ሲሆን ፣ ሌላው አክራሪ አረቦች ለምእራባውያን ያላቸው ጥላቻና ምእራባውያን እስራኤልን በመደገፋቸው ያላቸው ቁርሾ ሲሆን ፣ ከዚህም በተጨማሪ በራሳቸው በአረቦች መሀከል ያለው ታሪካዊ የሆኑ የሀይማኖትና የፖለቲካ ልዩነቶች ናቸው - ለዚህም አይነተኛ ማሳያው በሺአዎችና በሱኒዎች መሀከል ያለው ልዩነት በዓለማዊና በአክራራ አረቦች መሀከል ያለ ልዩነት ፣ እንዲሁም ወታደሩ ጠንካራ በሆነባቸው እንደ ግብፅና አልጄሪያን የመሳሰሉ አገራት ከነፃነት ወዲህ ስልጣኑ ከወታደሩ እጅ ሊወጣና የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን መምጣት አለመቻል፣ እንዲሁም በአሜሪካንና በምእራባውያን የሚደገፉ የዓረብ ንጉሳውያንና እነሱን እንደ ጨቋኝ በሚቆጥሩ የአረብ ብሄረተኞች መሀከል የአቋም ልዩነቶች አሉ ፡፡ እነኚህ ልዩነቶች ከአረብ ስፕሪንግ ማግስት በብዙዎች የአረብ አብዪት በተካሄደባቸው የአረብ አገራት ውስጥ ሰላምን ለመንሳትና ከነፃነታቸው ወዲህ ታይቶ ለማይታወቅ ለከረረ የእርስ በእረስ ጦርነት የዳረጋቸው ሲሆን ሊቢያ ፣ የመንና ፣ ሶርያና ኢራቅ ፣በመጠኑ ግብፅ (ከሊቢያ ጋር ባለው በድንበሮቿ አካባቢና በሲናይ በረሀ በሚገኘው ግዛቷ ውስጥ) በእርስ በእርስ ጦርነት ሰለባ ሆነዋል ፡፡
በራሳቸው በመካለኛው ምስራቅ አገራት በሱኒዎችና በሺአዎች መሀከል ያለው የቆየ ታሪካዊ ሀይማኖታዊ ልዩነት ራሱ ቀላል የማይባል  ልዩነትን የፈጠረ ሲሆን ለኢራንና ለአረቦች አለመተማመን ዋናው ምክንያትም ነው ፡፡ በተመሳሳይም በየመን ውስጥም አንዱ ለእርስ በእርስ ጦርነት መንስኤ የሆነው ነገር ይሄው የመን ውስጥ ባሉ ሺአዎችና ሱኒዎች እንዲሁም በየመን በሚገኘው አልቃኢዳ ክንፍ መሀከል ነው ፡፡
አንዳንድ ተአቺውቀ ዎደች እንደሚሉት እስራኤል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በናዚ የጦ ካማምፖሰች ውስጥ በጋዝ እየታጠኑ ሲፈጁ በተነመሳሳይም እስራኤል በስዊዝ ካናል ያትን ፍልስጥኤማውያንን የሚያገኛናኙ ቦዮችንና ዋሻዎችን በጋዝ እንደምታጥን የአሁኗ ናዚ ማለት የፅዮናውያን እስተራኤል ነች ይሏታል ፡፡
የዓረብና የእስራኤል ውዝግብ ምን ያህል አደገኛ ደረጃ ላይ እንደደሰረ ለማሳየት ይረዳ ዘንድ እስራኤል የሰባትና የስምንት አመት ህፃናትን ጨምሮ ደረታቸውና ግንባራቸው ላይ በሚያነጣጥር የአልሞ ተኳሽ (Sniper) ጠመንጃ እየተኮሰች የምትገድል ሲሆን ፣ በፈረንጆች አቆጣጠር 2014 ህዳር ወር ላይ የአይሁድ ምኩራብ በመግባት አምስት የአይሁድ ቄሶችን ወይም ራባዮችን በጩቤ ወግተው የገደሉ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ ገዳዮቹ በቁጥጥር ስር ቢውሉም በዚህ ያልረካችው እስራኤል የቤተሰቦቻቸውን መኖሪያ ህንፃ ለማፈራረስ በመወሰን የህንፃውን አገነባብ ስትራክቸር የሚያጠኑ የአፍራሽ ኢንጂነሮችን በመላክ ሌሎችን ቤተሰቦች ጨምሮ የሚኖሩበትን ህንፃ እንደምታፈራርስ ገልፃለች ፡፡
ከዚህ ቀደም የፍስጥኤማውያንን ቤት የማፈራረስ ድርጊቷን ያቆመች ቢሆን የእስራኤል ጄኔራሎች ለበለጠ አመፅ ይገፋል በሚል ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ፣ ነገር ግን የአይሁድ ቄሶች (ራባዮች) መገደልን ተከትሎ ግን ትታው የነበረውን የፍልስጥኤማውያንን ቤት የማፈራስ ተግባር ተመልሳበታለች ፡፡ ይህም የሚያሳየው የሁለቱ ቁርቋሶ ወደ ማይመለስበት ደረጃ መድረሱንና ለተቀረው መካከለኛው ምስራቅም ጭምር አስጊና አደገኛ መሆኑን ነው ፡፡ በዚህ አደገኛ በሆነ አካባቢ አገራት የኒውክሊየር የጦር መሳሪያን ለመታተጠቅ ቢሽቀዳደሙ አስገራሚ አይንም ፡፡
ኢራን የምትገኝበት አካባቢ ከአረቦች ጋር ትይዩ የሆነና በሻጥ አል አረብ በቀን ከ1.5 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ በመርከብ ከሳኡዲ አረቢያ፣ከኩዌት እና ከኢራቅ የሚጓጓዝበት ሲሆን ኢራንም በበኩሏ ጥቃት ከተሰነዘረብኝ ይህን ሰርጥ ኢራን እዘጋለሁ ብላ ዝታ ቆይታለች ፡፡ ይህን ሰርጥ የሚጠብቀው የአሜሪካ ባህር ሀይል ሲሆን በአለም ግዙፉ ከአሜሪካ ውጪ ያለ የባህር ሀይል መደብ አሜሪካ በዚሁ አካባቢ በባህሬን ሲኖራት ፣ባህሬን ላይ በተነሳው የአረብ ስፕሪንግ ፕሬዝዳንት ኦባማ የባህሬንን አመፅ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ሰምተው እንዳልሰማ ሆነዋል ፡፡
ለዚህም ምክንያቱ አሜሪካ በአካባቢው በዚህ እጅግ ግዙፍ በሆነና ለጥቅሟ በሚያስፈልጋት የባህር ሀይል መደብ ምክንያት ሲሆን ሱኒ የሆኑትና በቁጥር ከሚያንሰው የሱኒ ገዢ መደብ የወጡት የባህሬን ነገስታት ድጋፍ ስትሰጥ በአንፃሩ የባህሬን ብዙሀን በሆኑና ነገር ግን በአገራችን ከኢኮኖሚም ሆነ ከፖለቲካ ጥቅም ተገልለናል የሚሉት በቁጥር በዛ የሚሉት ሺአዎች ሲሆኑ ወደ ኢራን ልባቸው ያደላል በሚልና በሱኒዎች ከምትገዛውና ከሳኡዲ አረቢያ ድጋፍን በምታገኘው ባህሬን ጥቅማቸውን  የሚያስከብር ግንኙነት ከሱኒ ገዢው መደብ እያገኙ ባሉት ምእራባውያን ተገቢውን ትኩረት ሳያገኙ ቀርተዋል ፡፡ በተመሳሳይም ሳኡዲ አረብያ ውስጥም በስተምስራቅ ግዛቷ የሚገኙ ሺአዎች አመፅን አካሂደው የነበረ ቢሆንም የነሱም አመፅ ብዙም ሳይራመድ በዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችም የሚገባውን ሽፋንን ሳያገኝ ሲሸፋፈን ተስተውሏል ፡፡
ሀንስ ብሊክስ አኢራን ላይ የተሳሳተ የደህንነት መረጃን ምእራባውያን እንዳይጠቀሙ ሲያሳሰስቡ ምእራባውያን ከዚህ በፊት በኢራቅ ላይ ተመሳሳይ መረጃን በመጠቀማቸው ምክንያት የደረሰውን በማስታወስ ነው ፡፡
ሳኡዲ አረቢያ ትልቋ የጦር መሳሪያ ሸማች ነች ፣ ዩኤኢም እንዲሁ በርካታ የጦር መሳሪያን ከሚያግበሰብሱ አገራት አንዷ ነች በአካባቢው

የሀገራችን ደራስያን



በሀገራችን ደራስያን መፅሀፍ በሚፅፉበት ወቅት ግን ምንጭንና ዋቢ መፅሀፍትን የማይጠቅሱ ሲሆን ቀደምት ደራስያን ስራዎቻውን ልክ ራሳቸው እንደ ወጥ በሆነ ሁኔታ እንደፃፉት አድርገው ይፅፉታል በዚህም ምንም አይት ዋቢ መፅፍ የሌላቸው ሲሆን የአውሮፓውያንን ታሪክ ሲፅፉ ያገኙባቸውን የታሪክ ምንጮችን አይጠቅሱም ፍልስፍናም ሲሆን እንዲሁ የዋናውን መፅሀፍ ምንጭ የማይጠቅሱ ሲሆን  ይህም የሀገራችንን ጸሀፍት የራሳቸው ያልሆነውን ሰራ የራሳቸው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው ያስወቅሳቸዋል እንጂ አያስመሰግናቸውም ፡፡
ለምሳሌ ክቡር ከበደ ሚካኤል በፃፏዋቸው ታላላቅ ሰዎች በተሰኘው መፅሀፍ ላይ ምንም አይነት ምንጭንም ሆነ የታሪክም ሆነ የፍልስፍና መፅሀፍን ያልጠቀሱ ሲሆን ነገር ግን በመፅሀፉ ውስጥ የተጠቀሰው ግን ታሪክና ፍልስፍና ነክ ነገር እንደ መሆኑ ምንጮቹን እና የተጠቀሙባቸውን የማመሳከሪያ መፅሀፍቱ ሊጠቀሱ ይገባ ነበረ ፡፡
በሃገራችን የአድዋ ጦርነት የኢትዮጲያ ብቻ ሳይሂን የአፍሪካና የመላው አለም የነፃነት ተምሳሌትነ የጭቁን ህዝች የነፃነት መሰረት የሆነ ድል መሆኑ አያከራክርም ፡፡ የአድዋን ጦነት አባቶቻችን ያሸነፉት በነበራቸው የጋለ የሀገር ፍቅርና ለሃገራቸው በነበራቸው ተቆርቋሪነት በባዶ እጃቸው በኢንዱስትሪ አብዮት ከተደራጀና ዘመናዊ የጦር መሳሪያን መድፍንና መትረየስን ከታጠቀ ዘመናዊ አውሮፓዊ ሃይል ጋር ነው ፡፡
ይህ በጦር ሜዳ ድል የተገኘ ነፃነት በእውቀት ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በአጠቃላይ በእውቀት ታግዞ ልማትንና እድገትን ካላመጣ የሃገሪቱ ህልውና አሁንም አደጋ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል በዘመኑ የነበሩ ምሁራኖች በተለያየ መንገድ መንገድ ሃሳባቸውን ገልጸዋል ፡፡  
በሀገራችን እውቀትን መደበቅና ለራስ ብቻ ማወቅ መፈለግ የተለመደ ሲሆን አዲስ አበባ ዩንቨርሰቲ በነበርኩበት ወቅት አንዳንድ ጠቃሚ የሆኑ መፅሀፍት ያውም በፈተና ሰሞን ይደበቁ የነበረ ሲሆን ከውስጣቸውም ገፃቸው እየተቀደደና እየተቦጨቀ ይወሰድ ነበረ ፡፡
በሃገራችን አዲስ ሃሳብን ለመቀበል ደካሞች ስንሆን አዳዲስ አስተሳሰቦችን እንፈራለን ፣ እንጠራጠራለን ፡፡ አዲስ ሃሳብን ያፈለቀ ሰውን የተወገዘ አድርገን የማየትና ምንም እንኳን ሰውየው ያለው ትክክል ቢሆንም ያንን ለማየትና ለመረዳት ረጅም ጊዜን ይወስድብናል ፡፡ በዚህም በዚያ አዲስ ሃሳብ ለመጠቀም ያለንን እድል ሲያጠብብን ከዚያም ባለፈ ግን ለየት ያለ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች ሃሳባቸውን በአደባባይ እንዳይገልፁና እንዲፈሩ ያደርጋል ፡፡
ቅናትም እንዲሁ በሰፊው በመሀከላችን የሚታይ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ዋናው የእውቀት ምንጭ የሆነው የንባብ ባህላችን ደካማ ነው ፡፡ ከየትኛውም ሚዲንያን ከመከታተል ፣ ወይንም ቴሌቪዥን ከማየትና ሬዲዮ ከመስማት በበለጠ ከማንበብ የበለጠ እውቀት የሚገኝ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የመደማመጥ ባህላችን ራሱ በትኩረት ሊቃኝ የሚገባ ሲሆን የተለያየ አቋም በሚያጋጥም ጊዜ አንዱ ለአንዱ የሚለውን ለማዳመጥ እንኳን እግስት አናሳይም ፡፡

ወጣትነት በዘመን እይታ

ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በታህሳስ 4 ቅፅ 13 ቁጥር 778፣ 2007 ዓ.ም. ከወጣው ያነበብኩት ፅሁፍ ሲሆን አስረስ አያሌው የተባሉ ፀሀፊ ‹‹ወጣቱን በቅኔ›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሁፍ በማየት ነው ፀሀፊው እንዲህ ይላሉ ፤
‹‹የኛ ትውልድ ግራ የተጋባ ነው፡፡ እንደ አያቶቹ አርበኛ ፣ እንደ አባቶቹ ደግሞ አብዮተኛ አይደለም ፡፡ ልግመኛ ነው፡፡ ልግመኛ የሆነው ግን ወዶ አይደለም ፡፡ የሚያግዘው አጥቶ ነው ››
የድሮዎቹ አባቶቻችን ድንበርን በማስከበር ፣ ጦርነት ወራሪን በመከላከል በመሳሰለው  የአርበኝነት ጀብድና ገድል ዘመናቸውን ሲያሳልፉ ፣ ከእነሱ በኋላ የመጣው ዘመናዊ ትምህርትን የቀሰመው አብዮተኛው ትውልድ በበኩሉ ደግሞ እነርሱ ለዘመናት ይዘውት የቆዩትና ሊለውጡት ፈቃደኛ ያልነበሩትን ስርአት ለወደፊቱ አገራችን አይበጅም በሚል ስሜት አብዮትን አስነስቶ የአባቶቹን ስርአት ያፈራረሰና ከዚያም የራሱን ይጠቅማል ያለውን ስርአት ለመተካትና ተግባራዊ ለማድረግ እርሱ በእርሱ በመጫረስም ጭምር መስዋእትነትን የከፈለ ነው ፡፡
ለለውጥና አገርን በአዲስ አስተሳሰብና ስርአት ለመቃኘት መነሳሳት በዓለም አገራት ታሪክ ውስጥ ያለና የተለመደ ነገር ነው ፡፡ ለምሳሌ በአውሮፓ የቡርዧ ስርአት የመጣው የፊውዳል ስርአትን በማፈራረስ ነው ፡፡ ነገር ግን ይህ የሆነው በጣም ስር ነቀል አብዮትን በማካሄድ ሳይሆን ዘመናት የፈጀ ጥገናዊ ለውጥን በማካሄድና ወቅቱ ሲደርስም መለወጥ ያለበትን በመለወጥ ነው፡፡ የኢኮኖሚው መሰረት ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሲቀየር እና የኢንዱስትሪ አብዮት ስር ከሰደደ በኋላ የፖለቲካ ስርአቱንም መለወጥ አስፈላጊነቱን ተረዳው ገዢ መደብ ራሱን ቀስ በቀስ ወደ ቡርዧ ስርአት ማሸጋገር ችሏል ፡፡
አሜሪካንንም ብንወስድ አሜሪካኖች ምንም እንኳን የባርያ አሳዳሪውን ስርአት ለማፈራረስ የተነሱት የኢንዱስትሪው አብዮት በአሜሪካ ሲካሄድ በፋብሪካዎቻው አማካይነት ርካሽ በሆነ ሁኔታ ማምረት ስለሚቻል ያንን የሰው ሃይል ያነሰ ምርታማ በሆነው ግብርናው ዘርፍ ከማሰማራት ይልቅ በኢንዱስትሪው ውስጥ ማሰማራት የበለጠ ትርፍማ በመሆኑና ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገው የሰው ሃይል ያለው ግብርናው ውስጥ በመሆኑ የባርያ አሳዳሪው ስርአት መፈራረስ ነበረበት እንጂ ነጭ አሜሪካውያን ለጥቁሮች አዝነው ወይንም የባርያ አሳዳሪው ስርአት ስነ - ምግባራዊ ስላልሆነ ብለው እንዳልነበረ በርካታ የታሪክና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይስማማሉ ፡፡ በዚያም አለ በዚህ ግን ስርአቱን መለወጥ አስፈላጊ የእርስ በእርስ ጦርነት ጭምር አካሂደው ለውጠውታል ፡፡   
በአንፃሩ በኢትዮጲያ የተካሄደው አብዮትና ተከትሎት የመጣው እልቂት ወጣቱንና የተማረውን ሀይል ሙልጭ አድርጎ ያጠፋ መሆኑንና አይደለም በአፍሪካ በአለም ደረጃ እንኳን የዚህ አይነት ጥፋትን ያስከተሉ አብዮቶች ቁጥራቸው እምብዛም እንዳልሆኑ ስለ አብዮቶች ያጠኑ የአፍሪካ ምሁራን ጭምር ይመሰክራሉ ፡፡ የኢትዮጲያ አብዮት ውጤት እጅግ የመረረ የሆነበት ምክንያት የሃገሪቱ የምጣኔ - ሃብትና የፖለቲካ ስርአት ለክፍለ ዘመናት ለውጥንና ማሻሻያን ይፈልግ የነበረ በመሆኑና ይህ ግን በገዢዎቹ ታፍኖና ተገቢው ትኩረት ሳይሰጠው ሁኔታው ገነፍሎ ከቁጥጥር ውጪ በመውጣቱ ነው ፡፡ ለምሳሌ እጅግ ኋላ ቀር የነበረውና ከዘመኑ ጋር ፈጽሞ የማይሄደው የመሬት ስሪት ስርአቱ ተጠቃሽ ነው ፡፡  
      ከላይ የተጠቀሱት ጸሀፊው ልግመኛ ያሉት ትውልድ በራሱ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በሱስ የተጠመደ መሆኑን ፣ ስለ አገሩ ደንታ ቢስና ግዴለሽ መሆኑን ነገር ግን ተጠያቂ እንዳይሆን ወዶ አይደለም ፣ የሚያግዘው አጥቶ ነው ብለዋል ፡፡ ካለፉት ትውልዶች የደረሰው እልቂት በተለይም በቀይና በነጭ ሽብር የደረሰው እልቂት መሀል ላይ የሚሸጋግር የትውልድ ማለትም በታላቅየው ወይም በአባትየው ትውልድ እና በታናሽየው ልጅ ትውልዶች መሀል ክፍተት መፍጠሩን በርካታ የስነ - ማህበረሰብ ወይም ሶሺዎሎጂ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ አዲሱ ትውልድ ‹‹እርስ በእርሱ የተገዳደለ ትውልድ›› የሚለው የቀድሞው አብዮተኛው ትውልድ የበዛ መስዋእትነትን በመክፈሉ ምክንያት ከመጪው ትውልል ጋር የሚያገናኘው ጠንካራ ድልድይ እንዳይኖር ቢያደርግም ፣ ይህ መሀል ላይ የተፈጠረ ክፍተት አዲሱ ትውልድ እንደ ታላቅ የሚያየውና የሚያከብረው እንዲሁም እንደ አርአያ የሚቆጥረው ትውልድ እንዳይኖርና ነገሮችን በራሱ መንገድ ብቻ እንዲረዳና እንዲተረጉም ለቀድሞው ትውልድ መልካም ተግባራት ጭምር እውቅናን እንዳይሰጥና ከዚያም ተጠቃሚ እንዳይሆን እድሉን ዘግቶበታል ፡፡
የአሁኑ ትውልድ ግን ሀብትን በማከማቸት ፣ ገንዘብን በመሰብሰብ ሲጠመድ ማየትና መስማት የተለመደ ነው ፡፡ ይህም የዘመኑ ትውልድና የቀድሞው ትውልድ ምን ያህል የተራራቀ የአስተሳሰብ አድማስ እንደነበራቸው የሚያሳይ ነው ፡፡ የዘመኑ ትውልድ ቁጥርና ስታትስቲክስ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ላይ ሲያተኩር የቀድሞው ትውልድ ፖለቲካና ህግ ላይ ትኩረትን ያደርጋል ፡፡ የአሁኑ ትውልድ ገንዘብና ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀት ሲኖረው የቀድሞው ትውልድ ስለ ገንዘብም ሆነ ስለ ምጣኔ ሀብት የነበረው እውቀት ከአሁኑ ጋር የሚወዳደር አይደለም ፡፡ የቀድሞው ትውልድ ለአገሩ ቀናኢ በመሆን የአካልና የህይወት መስዋእትነትን በመክፈል አገሩንና ዳር ድንበሩን አስከብሮ አለፈ እንጂ በአብዛኛው በነበረው ሀብት የተጠቀመ እና በድሎት ተንደላቆ የኖረ አይደለም ፡፡ በአንፃሩ የአሁኑ ትውልድ ከአባቶቹ በወረሰው ድህነት እጅግ መማረሩ ለገንዘብ ከፍተኛ ፍቅር እንዲያድርበት ዋነኛ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ወደ ውጪ አገር በህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እሚሰደደው በአብዛኛው ወጣት በኢኮኖሚ ምክንያት ሲሆን በሚችለውም ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥ በትግል ላይ ይገኛል ፡፡
ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ ማለት በተለመደበት ባህል ውስጥ ሁልግዜ የድሮውን ናፋቂ መሆን ከስህተት ላይ እንዳይጥለንና የራሳችንን ዘመን ታሪክ ሳናደንቅም ሆነ በራሳችን ዘመን ታሪክ ተሳታፊ እንዳንሆን እንዳያደርገን መጠንቀቅ አለብን ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን በመጽፈ መክብብ ላይ ምእራፍ 7፣ቁጥር 10 ላይ ‹‹ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አትናገር ፣ የዚህን ነገር በጥበብ አትጠይቅምና ››፡፡

ስነ - ጥበብና አገራችን

ከጣልያን ጦርነት ከማይጨው ጦርነት ከተመለሱ ወዲህ ንጉሰ ነገስቱ ፣ ምንም እንኳ ጣሊያን ትቷቸው የሄዳቸው ጥቂት የመሰረተ ልማቶችና መንገዶች ህንፃዎች ቢኖሩም ሃገሩ ግን በጦርነት መፈራረሱ ግልጽ ነበረ ፡፡ እንደ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ የጀመሩት የሀገራዊ ስሜትን የሚቀሰቅስ እንቅስቃሴ ነበረ ያም በኋላ መኮንን ሀብተወልድ ይዘውት በሀገር ፍቅር ትያትር ተቋማዊ አደረጃጀትን ይዞ ሲቀጥል ፡፡ በ1950ዎቹ አካባቢ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች ይታያሉ በ1960 ዎቹ እነ ዮሀንስ አድማሱ ፣ ዮናስ አድማሱ እና የመሳሰሉትም እንዲሁ የተለያየ ድርሰቶችን በመስራት አገራዊ ስሜትን ለማነቃቃትና ህብረተሰቡን ለማንቃት ጥረት የተደረገበት ነበረ ፡፡ ገብረ ክርስቶስ ሀዲስ አለማየሁ አፈወርቅ ተክሌን የመሳሰሉ ሽልማት በመስጠትና ለማነቃቃት ጥረት ተደርጓል ፡፡
አብዮቱ ከፈነዳና 1970ዎቹ ወደ ቀበሌ ኪነት ኪነ ጥበብ ሲሰራ ይህ ህዝቡ ለመድረስ ሲያስችል ቀድሞ የነበረው ምሁራዊ የነበረው አቅምና ደረጃ የነበረው ባይሆንም ወደ ህዝብ ግን በቅርበት መድረስ የቻለና በርካታ አቀንቃኞችና ተዋንያን በኋላ ላይ ከቀበሌ ኪነት ታዋቂ ሆነው የወጡበት ነበረ ፡፡ አብዮቱ ሲመጣ ቀድሞ የነበረው የአርቲስቶች ስብስብ ግን አንዳንዶች በሞት ፣ ከአገር በመውጣት ሲበተኑ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ከአገር ሰለሞን ደሬሳ ሲወጡ ጸጋዬ ገ/መድህን ፣ መንግስቱ ለማ ፣ተስፋዬ ገሰሰን፣ አባተ መኩሪያን የመሳሰሉት ቀጥለዋል ፡፡ 
የአገራን ደራሲዎች በራሳቸው በአማርኛ ቋንቋ ሲፅፉ ይህ ህዝባዊ ተቀባይትን በአለም ለማግኘት አስቻጋሪ ሲያደርገው ሌሎች የአፍሪካ አገራት ግን በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ የአገራቸውን ስነ - ፅሁፍ ለአለም ለማስተዋወቅ ረድቷል ፡፡
የሼክስፒር ስራዎች በ17ኛው ክ / ዘመን የተሰሩ ቢሆንም አሁንም እንደ አዲስ በየመድረኩ ይሰራሉ በየትያትር ቤቶች በተመሳሳይም የሃራችን ስራዎች ከአሁኑ ሁኔታ ጋር ሊተረጎምና ከአሁኑ ጋር ካለው ሁኔታ ጋር በዛሬ ሁኔታ ላይ ቆመን ስንመለከተው ስለአሁኑ የሚነግረን ይኖራል ፡፡ አውሮፓውያን ከቀድሞው ስራዎቻቸው ብዙ ብዙ ለዘመኑ አንዳመቻቸው ይወስዳሉ ፡፡    
በአገራችን ግን በዚህ አይነት መንገድ ደራሲዎቻችንን ፣ ሰአሊዎችቻችንን ዋጋ የተረዳን አይመስልም ፡፡ በአሉ ግርማ እንዴት እንደሞተ የማይታወቅ ሲሆን እንደ አቤ ጉበኛ ፣  ገብረህይወት ባይከዳኝና ዮፍታሄ ንገሱ እንዴት እንደሞቱ እንኳ አይታወቅም ፡፡
ባህላችንና ታሪካችን ግለሰባዊነትን የሚበረታታ አይደለም ፡፡ ሁሉንም ነገገር ለንጉሰ ለጳጳሱ ወይም ለገዢው ነው የምንሰጠው ፡፡ በዚያ ውስጥ ግን እጅግ በርካታ ባለሙያዎች ሰዎች ያሉ ሲሆን ስለ እነሱ ምንም የሚባል ነረገር የለም ፡፡ ሰአሊዎች በቤተክርስትያን የሚስሉትን ስእሎችን ስንመለከት ንጉሱን ዛፍ አሳክለው ሲስሉ ሌሎቹን ሰዎች ደቃቃ እና ከአይን የማይገቡ አድርገው ነው የሚስሉት ፡፡ የሁሉንም ነገር ማእከልም ፣ መጨረሻውም መጀመሪያው ንጉሱ ወይንም ጳጳሱ አድርገው ነው ፡፡
አውሮፓዊያን በህዳሴው ዘመን ያንሰራሩበት አንዱና ዋናው ምክንያት ቀድሞ የሁሉም ነገር ማእከል የነበረውን መለኮት ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን ወደ ግለሰብ ትይዩ ማለትም ወደ ሰው ደረጃ በማውረዳቸው ነው ፡፡ ለምሳሌ የማክያቬሊ አስተሳሰብ ከህዳሴው ዘመን ዋናው ተደርጎ የሚወሰድበት ምክንያት ቀድሞ ሁሉም ነገር በመለኮት መሪነትና ፈቃጅነት ይደረግ የነበረውንና ከላይ (ቨርቲካል) ከመለኮት ወደ ታች ማለትም ወደ ሰው ይወርድ የነበረውን ግንኙነት ወደ ጎን ማለትም ወደ ሰውና ሰው ፣ ሰውና መለኮት የትይዩ (ሆሪዞንታል) ግንኙነት እንዲኖር ፈርን የቀደደ በመሆኑ ነው ፡፡  
አንድን ስነ የጥበብ ተረድቶና ለማስቀመጥም የመካከለኛው መደብ ያስፈልጋል፡፡ ኢትየጲያ ውስጥ ስእሎችን የመግዛት ነገር አሁን አሁን የሚታይ ነው ፡፡ ብሄራዊ የሳይንስ አካዳሚና ብሄራዊ ሙዚየም ስነ - ጥበብ የሚደግፉና በክብር የሚያስቀምጡ ተቋማት ናቸው፡፡