ፍልስምናና መንፈሳዊነት

It is all about the meaning of existence

Tuesday, June 12, 2018

liberalism Ethiopia ethiopian Airline ethio Tel

ከፈረሱ ጋሪው የቀደመው የልማት ድርጅቶን ወደ ግል የማዛወርየ‹‹ሊበራሊዝም››ሂደት

በአሁኑ ሰአት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዋና ዋና የሆኑትን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ ከዚህ ቀደም ገዢው ፓርቲ ያራምድ ከነበረው የተለየ አቋም ሲሆን እነኚህ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል አይዛወሩም በሚል በነሱ አትምጡብኝ የኒኦ ሊበራል ሃይሎች አመለካከት ነው ይሄንን አንቀበልም ሲል የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ብዙዎቹን ምእራባውያኑን ጭምር ያስገረመ የፖሊሲ ለውጥን አድርጓል፡፡ የፖሊሲ ለውጡ ያልተጠበቀ ሲሆን የዘገየና ትንሽ(Too little, Too Late)ፈረንጆቹ እንደሚሉት ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ግን የዚህን ያህል ግዙፍ የፖሊሲ ለውጥን ለማድረግ ከመነሳት በፊት ኩባንያዎቹን ለማስተላለፍና ለውጡን መምራት በህዝብ ዘንድ ተአማኒ በሆነ ሁኔታ ሽግግር እንዲደረግ አስፈላጊ የሆኑት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ነበረባቸው ፡፡
በማንኛውም ሃገር እንደሚደረገው ሁሉ አንድን ተቋም ወደ ግል ለማዛወር እንዲሁም አክስዮኖችን ለህዝብ ለመሸጥ አስቀድሞ የሚያስፈልጉ መዘጋጀት ያለባቸው መደላድል የሚሆኑየገበያ መሰረተ ልማቶች፤ደጋፊ የህግ ማእቅፎችና ተቋማት የሚያስፈልጉ ሲሆን ለምሳሌ ስለ አክስዮን ድርጅቶች የሚደነግገውናከ60 አመት በፊት የወጣው የንግድ ህግ ይሻሻላል ቢባልም ተሻሽሎ አልወጣም ፤ ከዚህ ቀደም ትላልቆቹ የመንግስት ድርጅቶች የቢራ ፋብሪካዎቹን ጨምሮ በዝግ ጨረታ ላሸነፉት የውጭ ኩባንያዎች የተሸጡ ሲሆን ይፋዊ የሆነ የአክስዮን ገበያ ባለመኖሩ ምክንያትእስካሁን ድረስ መንግስት ትላልቆቹን ድርጅቶቹን የመግዛት እድልን ያገኙት የውጭ ባለሃብቶችና እንደ ሚድሮክ ያሉት ናቸው ፡፡እነኚህ ድርጅቶች አክስዮኖቻቸው ለህዝብ ይሸጣሉ ቢባልም በየትኛው የአክስዮን መገበያያ መድረክ እንደሆነ ግልፅ አይደለም ፤ በተደጋጋሚ የንግዱ ህብረተሰብ የአክስዮን ገበያ እንዲከፈት ውትወታ ቢያደርግም በመንግስት በኩል ግን መቆጣጠር አንችልም ፤ ሃገሪቱ ለዚህ ዝግጁ አይደለችም ….ወዘተ በሚሉ ምክንያቶች ፈቃደኝነት አልታየም ፤ ኢትዮጲያ የአክስዮን ገበያ ከሌላቸው በዓለም ላይ ካሉ 40 አገራት ትልቋ መሆኗ የዓለም ሚዲያዎች የዘገቡት ጉዳይ ነው ፤የአሁኑን የመንግስት ድርጅቶችን ለህዝብ አክስዮን እሸጣለሁ የሚለው አቋም በመጀመሪያ የአክስዮን ገበያና ግልፅ የሆኑ የአክስዮን ኩባንያ ድንጋጌዎችና ፤ የንግድ ህግጋት በሌሉበት አክስዮኖቹ እንዴት እንደሚሸጡ ግልፅ ማድረግ ይጠበቃል ፡፡
በመግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው ወደ ግል በሚዛወሩበት ሙስናን ለመከላከልጥንቃቄን እንደሚደረግ አመልክቷል፡፡በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት አባል በሆኑበት ሃገራትና በአሁኗ ራሺያ በቦሪስ የልሲን ዘመን የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል በሚያዛውሩበት ወቅት ከፍተኛ ሙስና በመፈፀሙ ዋና ዋና የሚባሉ ድርጅቶች በግለሰቦች እጅ ገብተው አሁን ቱጃር ኦሊጋርክ የሚባሉት የሃገሪቱን የሀብት ሃብት ምንጭ የሆኑትን ኩባንያዎች በርካሽ ዋጋ በእጃቸው ሊያስገቡ በቅተዋል በዚህም ሩስያና ፤ እንደ ኡክሬን ያሉ ሃገራት በሃብታሙና በደሃው መሀከል ሰፊ የሆነ የሃብት ልዩነት ከሚታይባቸው የዓለም ሃገራት ተርታ ተሰልፈዋል ፤ ብዙዎቹ የአሁኑ የሩስያና ኡክሬይን ቢሊየነሮችም በዚህ መንገድ ሃብትን ያካበቱና ፖለቲካውንና ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር በቻሉ ሰዎች ስለሆነ ዲሞክራሲን ለማስፈንም እንቅፋት ሆኗል ፤ የአሁኑ የሩስያ ፕሬዝደንት ፑቲንም በእነኚህ ዲታ ኦሊጋርኮች ጋር በመሻረክና የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብት በመከፋፈል ሃገሪቱን እየገዙ እንዳለ ይታወቃል፤እነኚህ ባለሃብቶችም ሃገራቸውን ስለማያምኑ ኑሯቸውን በአውሮፓና እንግሊዝ ሲያደርጉ የሃገራቸውን ሃብትም ወደ ውጭ በማሸሽ ኪሳራን ተከትሎም የተዛባ የሃብት ክፍፍል አስከትለዋል፤ እንዲሁም በቻይናም የመንግስትን ኩባንያዎችን እንደ ሩስያ አይሁን እንጂ የኮሚኒስት ፓርቲው አባላትና ዘመዶች ሊከፋፈሏቸው በቅተዋል፡፡
ውሳኔው በገዢው ፓርቲ የተወሰነ ሲሆን ነገር ግን ይህ ቁልፍ ውሳኔ እንደመሆኑ መጠን መወሰን የነበረበት በፓርቲ መዋቅር ነው ወይንስ አስፈጻሚ በሆነው በሚኒስትሮች ም/ቤትና በህግ አውጪው መፅደቅ ነው የነበረበት የሚለው አነጋጋሪ ነው ፤ ጉዳዩ ወደ ፓርላማ ሄዶ ህግ ሆኖ በሚቀየርበት ወቅት ፓርላማው የገዢውን ፓርቲ ውሳኔ ማፅደቅ ይጠበቅበታል ማለት ነው ፡፡ትላልቅና ወሳኝ የሆኑ የኢኮኖሚ አውታር የሆኑ ድርጅቶችን ፤ወደ ግል የማዛወር ሂደት በጥንቃቄ መተግበር ሲኖርበት ከላይ የተጠቀሱትንና የሌሎችን ሃገራትን ልምድን ማስተዋል ያሻል፤ይዛወራሉ ከሚባሉት መሃከል ቴሌን ብንወስድ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ከመደረጉ በፊት ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ክፍት ተደርጎ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ሃብትን እንዲፈጥሩበትና የመወዳደር ብቃታቸውን ለማሳደግ ቅድሚያ እድል ማግኘት የሚገባቸው ሲሆን እነሱ ሲጠነክሩ ለውጭዎች ክፍት መደረግ የነበረበት ቢሆንም ለረጅም አመታት ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ጭምር ክፍት አይደረግም በሚል ግትር አቋም በመንግስት ሞኖፖሊ ለአመታት ተይዞ ቆይቷል፤ የአየር መንግዱም ዘርፍ ከአነስተኛ አውሮፕላንና ከአምቡላንስና ሄሊኮፕተር በስተቀር ለትላልቅ የግል አየር መንገዶች ፈቃድ የማይሰጥ ሲሆን መጀመሪያ ዘርፉን ክፍት በማድረግ የሃገር ውስጥ ትላልቅ አውሮፕላኖችን ለሚያንቀሳቅሱ ክፍት መደረግ ነበረበት ፡፡ አሁን ክፍት ይደረጋሉ የሚባሉት ዘርፎች በሙሉ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ቢፈቀድ ስንት ቴሌና ስንት ትላልቅ የግል አየር መንገዶች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡
የፋይናንሱን ዘርፍ ብንመለከት የግል ኢንሹራንሶችና ባንኮች መጀመሪያ ለሃገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች ክፍት የተደረገ ሲሆን አንዳንዶቹ ተቋማት ከፍተኛ ካፒታልን እስከመፍጠር ደርሰዋል አሁን የዚህ ዘርፍ ችግር ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ክፍት መሆኑና ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት አለመደረጉና ለረጅም ግዜ ዝግ ሆኖ መቆየቱ ደግሞ በዘርፉ በቂ ውድድር እንዳይኖርና የውጭ ምንዛሬን ለማፍራት በራሱ እየፈጠረ ያለው ችግር አለ፡፡ ነገር ግን አሁን ክፍት ይደረጋሉ የተባሉት ዘርፎች ቅደምተከተሉ መሆን ያለበት መጀመሪያ ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ህጎችን ማውጣት የነበረበት ሲሆን በመቀጠልም በሃገር ውስጥ ካፒታልን ከፈጠሩና ከውጭ ባለሃብቶች ጋር መወዳደር የሚያስችል አቅምን በሚፈጥሩበት ወቅት የውጭዎቹ እንዲገቡ ይደረጋል፤ ነገር ግን የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ግን ለውጭም ለሃገር ውስጥም እኩል ክፍት ማድረጉ የተለየ ያደርገዋል ፡፡በኢትዮጲያ የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወር ሂደት ግልፅነት የጎደለውና ለሙስና የተጋለጠ ሲሆን ፤ ብዙዎቹ ትላልቆቹ ለውጭ ባለሃብት የተላለፉ ሲሆን ህብረተሰቡ ከደመወዝተኝነት ውጪ ሌላ ሃብትና ንብረትን እንዳያፈራ ሲያደርገው ከእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ መብት ለመግዛት ምንም እድልን ሳያገኝ የቀረ ሲሆን የአሁኑ ለየት የሚያደርገው ግን ለህዝቡም ድርሻን እሸጣለሁ ማለቱ ነው ይህ መልካም ሲሆን ህዝቡም ተሳታፊ መሆኑ ለግልፅነት አጋዥ ነው፡፡
የገንዘብና / ኢኮኖሚ / ትብብር ሚ/ሩ 59 ቢሊየን ብር በላይ የ2011 ዓ.ም. በጀት ጉደለት ማሳየቱንና ይህንንም ለመሙላት በሃገር ውስጥ የገንዘብ ህትመት ይሸፈናል ማለታው መጪው ግዜ የባሰ የዋጋ ግሽበት የሚታይበትና የዜጎች ኑሮ የበለጠ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገባ አመላካች ነው፡፡ የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት አሁን ካለው አሳሳቢ ከሆነውና አሁንም እየናረ ካለው የዋጋ ግሽበት አንጻር እንደ ከዚህ ቀደም ተጨማሪ ገንዘብን ወደ ኢኮኖሚው ቢለቀቅ የሚፈጥረውን ተጨማሪ ግሽበትን መቋቋም ስለማይቻል እነኚህን ድርጅቶችን መሸጥ አማራጭ የሌለው ሆኖ ተገኝቷል
እንደ ቻይና ያሉ ሃገራትም በተነሳው ብጥብጥና የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ ወደዚህ የሚልኩትን ኢንቨስትመንታቸውን ያዝ ማድረጋቸውም ተሰምቷል ፤ ከውጭ ይገኝ የነበረው ብድር የመቀነስ አዝማሚያን አሳይቷል - በመሸጥ ካልሆነ በቀር እንደ ከዚህ ቀደሙ በብድርም ሆነ በእርዳታ በቀላሉ ከውጪ ገንዘብ ማግኘት እንደማይቻል መገመት ይቻላል ፤ስለሆነም መንግስት ካለበት የእዳ ጫናና ከከፍተኛ የበጀት ጉድለት ለማቃለል የእነዚህን ድርጅቶችን ሽያጭ እንዳሰበው መገመት ይቻላል ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኢኮኖሚውን ለውጭ ባለሃብቶች ‹‹ሊበራላይዝ›› ክፍት አድርግ የሚለውን የምእራባውያንን ግፊት መልስ ለመስጠትና የፖሊሲ ማሻሻያን በማድረግ ሊመጣ የሚችልን እርዳታንና ብድር ለማግኘት ሊሆን ይችላል ፡፡ ሃገሪቱ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንዳትሆን አንድ እንቅፋት ሆኖ የቆየው ይሄው ክፍት አይደረጉም የሚባሉት ዘርፎች ጉዳይ ነው ፤ ይሁንና ወደ ግል ይዛወሩ በተለይም ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ይተላለፉ መባሉ መልካም ቢሆንም ያለውን የሃብት ልዩነትን እንዳያሰፋውና ለማስተካከል በሚያስቸግር ሁኔታ ሃብት በጥቂቶች እጅ መከማቸትን እንዳይፈጥር ጥንቃቄን ማድረግ ያሻል፡፡የልማት ድርጅቶቹ ለረጅም አመታት ሞኖፖሊ በመሆን ባለሃብት አይገባባቸውም መባላቸው በሃገሪቱ እድገት ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅእኖን ፈጥሮ ቆይቷል ፤ ቴሌና አየር መንገድ ድርጅቶች በጣም አትራፊ ስለሆኑ እንደ ኢትዮጲያ አየር መንገድ ያለው በውጭ ምንዛሬ ስለሆነ በተለይም የውጭ ባለሃብቶቹ ትርፋቸውን ወደ ውጭ ማውጣትም ይችላልበዚህም ምክንያት የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ ያስችላል ፤ ነገር ግን ከቴሌ በተለየ ሁኔታ አየር መንገዱ አትራፊና የብሄራዊ መለያ እንደመሆኑ መጠን እርሱን ወደ ግል ማዛወሩ የተቻኮለ ውሳኔ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ እነኚህ የልማት ድርጅቶች በሙስናና ውጤታማ ያልሆነን አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁ ናቸው እንደ ቴሌ ፤ (Shipping Lines) ሺፒንግ ላይንስ ያሉት መንግስታዊ ሞኖፖሊዎች ሲሆን ተወዳዳሪ ኩባንያዎች ቢኖሩ የዋጋና የጥራት ልዩነት ሊመጣ የሚችል ሲሆን ለዚህ የገበያ ውድድር መልካም እድልን ይፈጥራል ፤ከእነኚህ ኩባንያዎች ግልጽ የሆነ የሂሳብ አያያዝ የሚጠይቅ ሲሆን የሂሳብ ሪፖርቶችንም በየሩብ አመቱ በግልፅ ማተምን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ቀደም ለኢትዮያ ዋነኛ አበዳሪ የሆነችው ቻይና የንግድ መርክብ ድርጅት ውስጥ ድርሻ ይሰጠኝ ብላ ጠይቃ የነበረ ሲሆን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ሲደረግ ቻይናና ሌሎች የሩቅ ምስራቅ አበዳሪዎች ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር የሚስችላቸውን ድርሻ ሊይዙ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ መንግስት አብዛኛውን ድርሻ አሁንም ቢሆን እኔ እይዛለሁ ቢልም በሂደት ግን አንዴ መሸጥ ከጀመረ እየሸጠ መውጣቱ የማይቀርና የግል ባለሃብቶቹ ድርሻ እያየለ መምጣቱ አይቀርም ስለዚህ ቋሚ የሆነ የአክስዮን ግብይት በማቋቋም ማንኛውም ሰው ባለው አቅም አክስዮኖችን የመግዛት እድልን ማግኘት አለበት፡፡
የወጪ ንግድ ገቢ የሃገሪቱን ምንዛሬ ፍላጎትን ማሟላት ባቃተው ወቅት ድርጅቶቹን የተወሰነውን ድርሻ መሸጥ እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል ቢችልም በዘላቂነት ግን በሽያጩ ከሚገኘው ገቢ አስተማማኝ ገቢን የሚያስገኝ አቅምን መፍጠር ዋነኛ ተግባር መሆን አለበት፡፡የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለውጡ በዚህ መገታት የሌለበት ሲሆን የሃገሪቱን ሃብት ለረጅም ዘመናት አስረው የያዙና ትርፋማ ያልሆኑ ዘርፎች ለውድድር ክፍት በማድረግ በተሻለ ሁኔታ በግል ባለሃብቶች እንዲተዳደር መደረግ አለበት ፡፡
 
Posted by Unknown at 10:27 AM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Sunday, June 10, 2018

Dr. Abey ethiopian politics

በቁጣ የተነሳሳን ህዝብ በማረጋጋት የተጠመዱት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር

የህዝብን ቁጣ በማስተንፈስ (በአንገር ማኔጅመንት ) ስራ የተጠመዱት  ውስጥ ለዘመናት ፍትህን ያጣና ሲበደልና ሲበዘብዝ በኖረ ህዝብን ለማረጋጋት ወደ ስልጣን የመጡት አዲሱ ጠቅላይ ሚ/ር በአዋሳ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ‹‹የዚህን ያህል ቂም የተያያዝን አልመሰለኝም ነበረ›› ሲሉ የተሰማቸውን እውነቱን ተናግረዋል ፡፡ ታምቆ የቆየውና ለአመታት በሰብአዊ መብትም ሆነ  በዲሞክራሲና በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዘርፍ ተገቢውን ምላሽና ግንዛቤን ያላገኘው ህዝብ በውስጡ ጤናማ ያልሆነ ስሜት መታመቁን መረዳታቸው በራሱ ከእርሳቸው ቀደም ካሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ለየት ያደርጋቸዋል ፤ ይህም የብዙዎቹን ተስፋ አጭሯል ፡፡ ጠቅ / ሚሩ በተለያየ ሃገራት ታስረውና ለአመታት ተረስተው የኖሩትን በማስፈታት በኩል ስራዎችን የሰሩ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ዜጎች ተረስተው እንደነበረ አመላካች ነው፡፡
የቀድሞዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አቶ ሃይለማርያምም ሆኑ አቶ መለስ ዜናዊ ለህዝብ ጥያቄ ቅርበት አላሳዩም ማለት ይቻላል፡፡ ከላይ በሚሰጥ ትእዛዝ ሃገርን የማስተዳደርንና ጨርሶ የህዝብን ጥያቄን አለማዳመጥ በሙስና ፤ በአቅም ማነስ የህዝብ ቅሬታ ይቀርብባቸው የነበሩትን አመራሮችን ከስፍራ ስፍራ መለዋወጥ እንጂ የተሻለ አቅም ያላቸውን ሰዎችን አለመመደብ የህዝብ ጥያቄዎች መፍትሄን ሳያገኙ እየተገላበጡ በእንዲሄዱ ሰበብ ሆኗል ፡፡ ህዝቡ ፍላጎቱን በቅጡ የሚያዳምጠው አካል በለሌለበት ሁኔታ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን የህዝብ ቁጣ ለማስተንፈስና ለማብረድ በተለያዩ የሃገሪቱ አካላት በመገኘት ከህዝብ ጋር ቀጥተኛ ውይይትን ማድረጋቸው ይበል የሚያሰኝ ነው ፡፡ ነገር ግን ጉዳዩ በንግግርና በውይይት ብቻ የሚፈታ ሳይሆን በቀጥታ በፍጥነት ወደ ተግባር መግባትን የሚጠይቅ ሲሆን እንዲሁም ተደጋጋሚ የህዝብ ቅሬታ የቀረበባቸውን ባለስልጣናትን ከሃላፊነታቸው ማንሳትንና በሙስና የማይጠረጠሩ ሃላፊዎችን መሾምን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው በዚህ ዘርፍ ዶ/ር አቢይ ግማሽ ነጥብን ብቻ ሊያገኙ ይችላሉ ለዚህም ምክንያቱ ጥቂቶቹን በጡረታ አሳርፌአለሁ ቢሉም ነገር ግን በህዝብ ዘንድ  የማይወደዱና በብዙ ሙስና የሚጠረጠሩት ሃላፊዎችን መልሰው ቁልፍ በሆኑ ስፍራ መሾማቸው በእርሳቸው ላይ ጥርጣሬን የሚጋብዝ ነው ፤ በቅርቡ በሜቴክ ያደረጉት ሹመት ይህን ጥርጣሬ የሚጋብዝ ነው ፤በአንጻሩ ደግሞ የፖሊስ አዛዦችን መለዋወጣቸውና መከላከያውን በሪፎርም ለማደስ ማሰባቸውን ግልፅ ማድረጋቸው ደግሞ ለለውጥ የቆሙና የህዝብ ድጋፍን ለማግኘት የቆረጡ ሆነው እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡
ሃገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር የህዝብ አመኔታን ለማግኘት ጠቅላይ ሚ/ሩ ከህዝብ ጥርጣሬ የጸዱ አመራሮችን መሰየም የተገባው ቢሆንም ነገር ግን ምክንያቱ በማይታወቅ ሁኔታ የቀድሞዎቹን አመራሮችን ወደ ስልጣን መመለስ የፈለጉበት ምነክንያት አይታወቅም ፤ ምናልባት የቀድሞቹን አመራሮቹን በመሾም ኢህአዴግ ውስጥ ያሉትን ለውጥ ፈላጊ ያልሆኑትን ሃይሎችን ለማስደሰት ‹አፒዝ› ለማድረግ ብለው ከሆነና ለውጥ ፈላጊዎቹን ያስደሰቱትን ያህል ለውጥ የማይፈልጉትንም በማስደሰት መሃል ላይ ስፍራን ለመያዝ ታክቲክ ይሁን ግልፅ አይደለም ፤ ነገር ግን ይህ የጠ/ሚሩ አሹዋሹዋም ነባር የኢህአዴግ አካላትን ሊያስደሰት ቢችልም ከህዝብ ፍላጎት አንጻር ግን የህዝብን ፍላጎትን ማርካቱ አጠያያቂ ነው ፡፡ በዚህም የህዝብን አመኔታን ላለማጣትና ወዳልተረጋጋ ሁኔታ ላለመመለስ ጥንቃቄን ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡
ይህ የአሁኑ ጠ/ ሚር የዶ/ር አቢይ አህመድ ሹመት አሰጣጥ የአሜሪካን ፕሬዝደንት የነበረውን አብረሃም ሊንከንን ያስታውሰናል፤ ሊንከን ፕሬዝዳንት የነበረበት ዘመን በአንድ በኩል የባርያ ስርአትን መቀጠል በሚፈልጉና በሌላ በኩል ደግሞ የባርያ ስርአቱ እንዲያበቃ በሚፈልጉ ሁለት ተቃራኒ ሃይሎች ዙሪያውን ተከቦ የነበረ ሲሆን ሊንከን ሁለቱንም ለማስደሰት ተቃራኒ የሚመስሉ ውሳኔዎችን ይወስን ነበረ ፤ በዚህ በአጭር ግዜ ለውጥ ፈላጊ ያልሆኑትን ሃይሎችን ድጋፍን እንዲያገኝ አስችሎታል፤ ነገር ግን ዋና አላማው የባርያውን ስርአት መለወጥ የነበረ ሲሆን ይህን በማድረጉ ለውጥ ፈላጊ ያልነበሩትን ሃይሎችን ፍላጎት በመጠበቁ ከእነርሱ ሊመጣበት ይችል የነበረንን ለውጥን እምቢታንና ጠንካራ ተቃውሞን ማስቀረትና የማይቀረውን  ለውጥ ማምጣት ችሏል ተብሎ ይታመናል ፤ አንድ ለውጥን እንዲያመጣ የተሰየመ ከፍተኛ ስልጣን ላይ ያለ ሰው ለውጥ እምቢ ባዮችንም ሆነ ለውጥ ፈላጊዎችን በአጭር ግዜ ውስጥ ሊያስደስት የሚችል ፖሊሲን መከተል ሲኖርበት በረጅም ግዜ ግን ለቆመለት ለውጥ ታማኝ በመሆን የህዝብን የለውጥን ፍላጎትን መመለስ ይኖርበታል ፡፡
ራሳቸውን በለውጥ ፈላጊዎችና በለውጥ ተቃዋሚዎች መሃከል ያገኙት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለህዝቡ ታማኝ ይሆናሉ ወይንስ የህዝብን ድጋፍ ላጣውና ስልጣናቸው ከእጃቸው እያፈተለከ ላሉት የፓርቲያቸው ነባር ስልጣን ጠባቂዎች ‹‹ኦልድ ጋርድ›› (old guard) አባላት ታማኝ ይሆናሉ የሚለው ነው ጥያቄው፡፡ የኢትዮጲያ ህዝብ በተደጋጋሚ ለውጥን እናመጣለን በሚሉ መሪዎች የተታለለና ብዙ የችግርንና ውጣ ውረድን በማየት ችግርን ያየ ባስ ሲልም የተዘረፈና የተጨፈጨፈ የተካደ ህዝብ ስለሆነ በቀላሉ መሪዎችን የማመን ዝንባሌን አያሳይም፤ ይህንን የህዝቡን ስነ ልቦና መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትራንስፎርሜሽናል ለውጥ የተማሩ ስለሆነ ለውጥን ለማካሄድ ያሉትን ተፈጥሯዊ ፈተናዎችን የሚረዷቸው ይመስለኛል ፡፡
በማንኛውም ለውጥ ሊደረግበት በሚገባ ተቋም ውስጥ ሶስት አይነት አሰላፎች አሉ፤ አንደኛው ቡድን ከነባራዊው (Status Quo) ሁኔታ ‹‹ስታተስ ኩ›› ተጠቃሚ ሆኖ የኖረና ለውጥ እንዲደረግ የማይፈልግ ቡድን ሲሆን ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ከውጭ ወይም ከውስጥ ያለ ሆኖ ነገር ግን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ያልተጠቀመና ለውጥ በቶሎ እንዲመጣለት የሚፈልገው ቡድን ሲሆን ይህም ብዙሃኑን ህዝብና ወጣቱን ይወክላል ፤ ሶስተኛው ቡድን ደግሞ የለውጥን አስፈላጊነትን በሚገባ የሚረዳ ነገር ግን ለውጥ ይዞት በሚመጣው ጓዝና መዘዝን የሚፈራ አካል ነው ፤ የለውጥ እምቢ ባይነት ‹‹ሪዚስታንስ ቱ ቼንጅ› (Resistance to Change) ሊመጣ ከሚችልባቸው አቅጣጫዎች አንዱ ይሄ ነው ፡፡ ለውጥን ለመተግበር ተቋማት የውጭ አማካሪን እስከመቅጠር ድረስ የሚሄዱበት ግዜ አለ ፤ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ግን ውክልና ባላቸው በራሱ አመራሮች ካልሆነ በስተቀረ የለውጥን ፍላጎት እሚመልስበት እድል የለውም ፤ስለዚህ አመራሩ ራሱ ወቅታዊውን ሁኔታ በመረዳት የለውጡ አካልና ተባባሪ በመሆን ሃገርን ወደሚቀጥለው እርከን የማሻገር ስራን መስራት አለበት፡፡
ጉዳዩ የዘገየና ለውጥ ቀደም ብሎ መምጣት የነበረበት ቢሆንም የዚህን አሳሳቢነት በመረዳት ‹‹ጊዜ የለንም በሚል ስሜት ›› መንግስት ስራውን መስራት እንዳለበት ማሳሰባቸው መልካም ሲሆን ከሁኔታዎች ጫፍ መድረስ አንጻር ሲታይ ግን ወደ ለውጥ መሄድና ፈጠን ባለ ሁኔታ ችግሮችን  በመፍታት ለመጪው ሃገራዊ ምርጫ አስፈላጊ የሆኑትን የመወዳደርያ ሜዳን ከወዲሁ ማዘጋጀት ይገባል፤ ከችግሩ ጥልቅ ከመሆን አንጻር ኢህአዴግ ብቻውን የሚወጣው አይደለም፡፡
የዲሞክራሲ ስርአትን ኮትኩቶ አለማሳደግ ይባስ ብሎም በእኔ አውቅልሃለሁ ልማታዊ መንግስትነት ሰበብ ዲሞክራሲን ሆነ ብሎ ማቀጨጭ ፤ ሃገርን እያስከፈለ ያለው ዋጋ በዚህ ወሳኝ ወቅት በግልፅ የታየ ሲሆን የዲሞክራሲ ስርአትን ማስፈን ጉዳይ ለዚህች አገር ወሳኝ ቢሆንም ነገር ግን በገዢው ፓርቲ በኩል መጀመሪያ አካባቢ የመልካም አስተዳደር ችግር ነው ፤ ቀጥሎም የመልካም አስተዳደር ችግር ነው በሚል ተደጋጋሚ ምላሽን ቢሰጥም ነገር ግን ችግሩ ግን ከዲሞክራሲ ጥያቄም በላይ የሰብአዊ መብት ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል ፡፡ ገዢው ፓርቲ እነኚህን ህዝባዊ ጥያቄዎች ፈጠን ብሎ ምላሽ መስጠት የነበረበት ቢሆንም ምንም አይመጣም በሚል ዝም ብሎ መተኛትን መርጧል ፡፡ ይህም ገዢውን ፓርቲንና ሃገሪቱን በዋጋ የማይተመን ዋጋን አስከፍሏል ፤ እያስከፈለም ይገኛል ፡፡ ይህም በሃገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ትፅእኖን ሲጋብዝ ፤ ለመቶ ሺሆች መፈናቀልን ፤ ለሰብአዊ መብት ጥሰትንና ለከባድ አለመረጋጋት ውስጥ አገሪቱን ሊከታት በቅቷል፡፡
የችግሩን ምንጭ በምንመረምርበት ወቅት የምናገኘው ነገር ከጥቂት አመታት በፊት የምርጫ ውድድር ሰሞን ለችግሩ ከገዢው ፓርቲ ይሰጥ የነበረው ምላሽ የአፈጻጸም ችግር ነው የሚል ነው ፤ ፖሊሲዎቻችን ፍፁም ትክክል ናቸው ነገር ግን አፈጻጸም ላይ ነው ችግር ያለው የሚለው መልስ ለጊዜው ምላሽ ቢሆንም ነገር ግን ከውስጥ ያለውን የባሰውን ችግር ግን መሸፈኛ ሆኖ ለጊዜው አገልግሏል ፤ የአፈጻጸም ችግር ከምንድነው የሚመጣው ለሚለው ጥያቄ አንዱ በቃት ያላቸው አመራሮች በስፍራው አለመመደብ ፤ አመራሮቹን ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር አለመኖርና የፖለቲካ ታማኝነትን ብቻ እንደ ብቃት መስፈርት በመውሰድ የሙስና ችግሮች ስር መስደድ ሲጀምሩ አይቶ እንዳላየ መታለፋቸው መመለሻ ለሌለው የሙስና ደረጃ ላይ ሃገሪቱን አድርሷል ፡፡ ከዚህም ዋነኛው ትክክለኛ ዲሞክራሲ ቢኖርና በዲሞክራሲ መንገድ ህዝብ መሪዎቹን የመምረጥ እድል ቢሰጠው ግን በሙስና የተዘፈቁትን ትቶ የተሻለ አቅም ያላቸውንና በሙስና ያልተነካኩት ይመረጡ ነበረ ፤ በየትም ሃገር መሪዎች እንደ ሰው በሚያጠፉበት ወቅት ጠንካራ ዲሞክራሰ ሲ ያለው ሃር ከሆነ መሪው በህዝብ ድምፅ ከስልጣኑ ይነሳና በሌላ ይተካል ፤ ይሄ ነው ምእራቡ ዓለም አሁን ለደረሰበት ትልቅ ደረጃ የደረሰው በኢኮኖሚም በፖለቲካም ፡፡
ይሁንና ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ከ97 ዓ.ም ወዲህ ያለፉትን ሁለት ምርጫዎችን የተቃዋሚዎችን ድምፅ በፓርላማ አልስማ ያለ በሚመስል ሁኔታ በሃገራዊ ምርጫ ወቅት 96 እና ከዛም በላይ በመቶ ድምፅ አግኝቻለሁ ማለቱና ምንም የተለየ ድምጽን በሚዲያም ሆነ በመንግስት ውስጥ ላለመስማት ዝግ ማድረጉ ገዢውን ፓርቲ በዋጋ የማይተመን ኪሳራን አስከፍሏል፡፡ ነገር ግን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ግረን መከላከያ አዛዦችን ሰብስበው እንደተናገሩት ‹‹ኢህአዴግ ፖለቲካዊ ስራውን መስራት አቅቶት በራሱ ስንፍና የወደቀ እንደሆነ የመከላከያ ሠራዊቱ ሕዝብ ከመረጠው ፓርቲ ጋር መቀጠል የሚችል ሠራዊት መሆን አለበት›› ሲሉ በግልፅ ማስቀመጣቸው መልካም ነው፡፡ይህ አባባላቸው ፓርቲው የህዝብን ድጋፍ ማግኘት ባይችል መከላከያው የወደቀ ፓርቲን ለማዳን መስዋእትነትን መክፈል የለበትም ህዝብ ለመረጠው ፓርቲ ድጋፉን መስጠት አለበት ሲሉ በተዘዋዋሪ ማስረዳታቸው ለዲሞክራሲ መሰረት መልካም ጅምር ሲሆን መከላከያው እንደ ተቋም ህልውናውን ለማስቀጠል የፓርቲ ወገንተኛ አለመሆን መሰረታዊ ጉዳይ ነው ፡፡  
ዲሞክራሲ በሚሰፍንበት ወቅትም የሰብአዊ መብት ጥያቄዎችም በተሻለ ምላሽን ያገኛሉ ፤ ለሰብአዊ መብት ጥሰት ዋነኛው ምክንያት የዲሞክራሲ አለመኖር ነው፤ ዲሞክራሲ ቢኖር ዜጎች ትክክለኛውን ፍትህ ስለሚያገኙ የሰብአዊ መብታቸውና ክብራቸው አይደፈርም፡፡ የህግ የበላይነት በሰፈነባቸው ሃገራት የማንም ዜጋ መብትን ለመድፈር የሚነሳ የለም ፤ ስለዚህ ከሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በምንመለከትበት ወቅት የዲሞክራሲ መስፈን ሊቀድም ይገባዋል ፤ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትርን ዶ/ር አቢይን የመረጣቸው ፓርቲያቸው ነው እንጂ ህዝቡ ወጥቶ አይደለም፤ እስካሁን ድረስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ህዝቡ መሪዎቹን መርጦ አያውቅም ማለት ይቻላል ፤ አዲሱ ጠቅላይ ይህን እድል ሃገሪቱን ወደ ዲሞክራሲ ስርአት ለማሸጋገርና የዲሞክራሲ አባት ለመባል ትልቅ እድል ከእጃቸው ይገኛል ፡፡ 
አሁንም ቢሆን ገዢው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚዎች መጪው ምርጫ ሌሎቹም በርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሳትፈውበት በህዝብ ይሁንታ ብቻ ወደ ስልጣን የሚመጣበትን የፖለቲካ ስርአትን ከመመስረት ውጪ ሌላ አማራጭ የላቸውም ፤ በረጅም ግዜ ሃገሪቱን ሊያረጋጋና ቀጣይ የህዝብ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን መፍጠርና ለወጣቶች የስራ እድልን በመፍጠር የተረጋጋ ሃገርን ለትውልድ የሚተላለፍ ዲሞክራሲያዊ የሆነና የህዝብ ድምፅ የሚሰማበት ስርአተ መንግስትን መገንባት ያሻል፡፡

2 Attachments
Click here to Reply or Forward
1.41 GB (9%) of 15 GB used
Manage
Terms - Privacy
Last account activity: 3 minutes ago
Details

Posted by Unknown at 12:50 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest
Labels: dr.Abey Ahmed, eprdf, Ethiopia

Tuesday, May 22, 2018

የፖሊሲማሻሻያንየማድረግአስፈላጊነትናየመንግስትዝግጁአለመሆን

የሃገራችንን ምጣኔ ሃብት በተከታታይ አመታት እድገትን እያስመዘገበ የቀጠለ ሲሆን ኢኮኖሚውአሁንባለበትሁኔታእድገቱንለማስቀጠልግንየምጣኔሃብትናማሻሻያንማድረግይጠበቅበታል ፡፡አንድምጣኔ - ሃብት አንድ የእድገትደረጃላይሲደርስከዚያእድገትጋርእሚመጣጠንየፖሊሲማሻሻያዎችንይፈልጋል ፡፡ ለምሳሌቻይናኢኮኖሚዋ እያደገና እየዘመነ (ማቹር) ሲደርግተከታታይየሆኑማሻሻያዎችንእያደረገችትገኛለች ፡፡በተለይምየፋይናንሱ ዘርፍ የዚህ አይነት ማሻሻያዎችን የሚፈልግ ሲሆን እስከ ቴሌኮም ዘርፉ ድረስ የዚህን ዓይነትማሻሻያዎችካልተደረጉለትቀጣዩየኢኮኖሚእድገትባለበትየመቆምባህሪንያሳያል ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ከውጭ የሚመጣቀጥተኛኢንቨስትመንትእያደገመሄድአለበትእንደኢትዮጲያላለበርከትያለየውጭምንዛሪንየሚያስገኝአቅምንገናያልፈጠረ ኢኮኖሚየውጭባለሃብቶችበኢኮኖሚውውስጥበሰፊውተሳትፎማድረጋቸውአስፈላጊነው ፡፡
        በሌላበኩልደግሞመንግስትበጣምወሳኝከሆኑትዘርፎችውጭያሉትወደግልመዛወርያባቸውሲሆንበአብዛኛውበመንግስትስር የሚገኙት የልማት ድርጅቶች የግል ባለሃብቶች እጅ ሆነው ሊቀጥሉ የሚችሉ ናቸው፤ እነኚህን ድርጅቶች ወደ ግል ማዛወር አንድ አማራጭ ሲሆን፤ ነገር ግን ኢህአዴግ መራሹ መንግስትመጀመሪያካደረጋቸውለውጦችወዲህለቀቅየለየኢኮኖሚማሻሻያንለማድረግተነሳሽነትንሲያሳይአይታይም ፡፡ ኢህአዴግ በጣም የሚያደንቃትቻይናበርካታደፋርየሆኑማሻሻያዎችንእያደረገችሲሆንበተለይምበፋይናንስእናበቴሌውዘርፍቀላልየማይባሉለውጦችንአድርጋለችበዚህምየዓለምየንግድድርጅትአባልለመሆንየቻለችሲሆንበዚህምእጅግተጠቃሚሆናለች ፤በኢንዱስትሪምርቶቿሰፊየሆነየዓለምገበያንለመቆጣጠርበቅታለች ፡፡ ገዢውፓርቲኢህአዴግግንዓለምየንግድድርጅትአባልለመሆንየሚያስፈልገውንምጣኔሃብታዊማሻሻያዎችንለማድረግምንያህልፈቃደኛእንደሆነአይታውቅም ፡፡
በተለይምግልፅነትንለመፍጠርሲባልእንደአክስዮንገበያየመሳሰሉትንለመክፈትናካፒታልንእንዲሁምየቦንድገበያንበመክፈትእዚሁካለየሃገርውስጥየፋይናንስምንጭለማሰባሰብእድልንየሚፈጥርየነበረቢሆንምበሃገርውስጥኩባንያዎችስራዎቻቸውንለማስፋፋትየሚያስፈልጋቸውንካፒታልበቀላሉለማሰባሰብያለውንእድልአጥብቦታል ፡፡ለፋይናንስአቅርቦት በውጭ ብድር ላይ ሙሉ ለሙሉ ከመመስረት ይልቅ የሃገር ውስጥ ፋይናንስን ለማሰባሰብ  እድልን ይፈጥር የነበረ ቢሆንም በዚህ ዘርፍ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ሳይደረግ ቀርቷል ፡፡ የውጭ ባለሃብቶችም በቀላሉወደሃገሪቱኢንቨስትአድርገውበሚፈልጉበት ወቅት ገንዘባቸውን መልሰው እሚያወጡበት እድልአለመኖሩናያለአክስዮንገበያበቀጥተኛኢንቨስትመንትብቻእንዲሳተፉመፈለጉበተለይምበኤክስፖርትዘርፍንለማሳደግበሚያስችልመልኩበሚፈለገውደረጃየውጭባለሃብቶችንበማምጣትአልተቻለም ፡፡
        መንግስትበትላልቅየመሰረተልማትግንባታዎችመሳተፉመልካምቢሆንምእነኚህፕሮጀክቶችእንደመሆናቸውበረጅምግዜግንየኢኮኖሚውንመሪነትመያዝያለበትየግሉዘርፍነውፕሮጀክቶችየስራግዜውያቸውንሲጨርሱየሚጠናቀቁእንደመሆናቸውመጠንከፍተኛየመንግስትወጪንማውጣትብቻኢኮኖሚውንለመምራትአዳጋችሲሆንእንደዚሁምለእነኚህትላልቅፕሮጀክቶችየሚያስፈልገውንገንዘብለማሟላትሃገሪቱንእዳውስጥየመንግስትንእዳእያናረውየሚሄድእንደመሆኑኢኮኖሚውንለመምራትየግሉክፍለኢኮኖሚየበለጠሚናንመጫወትያለበትስርአትመዘርጋትአለበት ፡፡ትላልቅፕሮጀክቶችለኢትዮጲያአስፈላጊመሆኑየታወቀሲሆንኢኮኖሚውንበማነቃቃትበኩልከፍተኛሚናንእንዳለውማንምየሚረዳውነው ፡፡
በምእራቡአለምየኢኮኖሚመቀዛቀዝበሚኖርበትወቅትምጣኔሃብቱንለማነቃቃትመንግስትትላልቅፕሮጀክቶችንበመስራትበዚያውምኢኮኖሚውንበማነቃቃትየስራእድልንበመፍጠር፤ገንዘብእንዲሽከረከርናወዲውምከገቡነበትሪሴሽንለመውጣትየሚጠቀሙበትየኬኒዥያንምጣኔሃብትአዋቂዎችየሚመክሩትና በ1930ዎቹ በሩዝቬልትእንዲሁም በ2008 ዓ.ምበነበረውየአሜሪካንሪሰሽንበኦባማአስተዳደደርዘመንተግባራዊየተደረገነው ፡፡በትላልቅፕሮጀክቶችእድገትንማስደገፍየራሱየሆኑጠንካራጎኖችያሉትንያህልድክመትምአለውአንዱከላይእንደጠቀስኩትፕሮጀክቶቹየሚጠይቁትግዙፍፋይናንስማሰባሰብራሱንየቻለፈተናሲሆንበብድርቢገኝእንኳንጋብካልተደረገሃገርንበአጭርግዜውስጥግዙፍእዳውስጥሊከትየሚችልነው ፡፡በሌላበኩልደግሞፕሮጀክቶቹበትክክልከተጠናቀቁለረጅምግዜሃገርንሊጠቅሙየሚችሉመሂናቸውጠንካራጎናቸውነው ፡፡
በተለይምየዋጋግሽበትበሚንበርበትወቅትትላልቅፕሮጀክቶችከፍተኛወጪየሚወጣባቸውእንደመሆናቸውመጠንየዋጋግሽበትንየማባባስናየውጭምንዛሪእጥረትንበማባባስበኩልሚናሊኖራቸውይችላል ፡፡ትላልቅፕሮጀክቶችመንግስታትንበህዝብእንዲወደዱራሳቸውንየሚያሳዩበትእድልንየሚሰጥነው ፡፡ ነገርግንከትላልቅፕሮጀክቶችባሻገርግንምጣኔሃብታዊማሻሻያዎችንበማድረግየበለጠዘላቂእድገትንማፋጠንየሚቻልበትየፖሊሲእድልአለ ፡፡
ምንምእንኳንከወጪንግድገቢአስፈላጊውየዶላርገቢይገኛልተብሎቢታሰብምይህንማሳካትአልተቻለም ፡፡ ከወጪንግድየሚገኘው 3 ቢሊየንዶላርብቻሲሆንነገርግንየሃገሪቱየውጭምንዛሪፍላጎት 16 ቢሊየንዶላርመድረሱአሳሳቢሲሆንበዚህመሃከል ያለው የ13 ቢሊየንዶላርክፍተትንፍላጎትንለመሙላትየወጪንግዱብቻውንሊያሟላውእንዳልቻለመረዳትይቻላል ፡፡ከሌሎችሃገራትልምድእንደምንረዳውየውጭምንዛሪእጥረትለመቅረፍበወጪንግድብቻመተማመንበቂስላልሆነበተለያዩዘርፎችአስተማማኝናቀጥተኛናቋሚየሆነየውጪኢንቨስትመንትመሳብአስፈላጊነው፤ በእርግጥይህኢንቨስትመንትበኢንዱስትሪውዘርፍእንዲሆንናየወጪንግድንእሚያጠናክርመሆንይጠበቅበታል፤ ነገርግንበበቂሁኔታመሳብአለመቻሉየወጭንግዱንበሚፈለገውደረጃላለማሳደግእንቅፋትሆኗል ፡፡ 
ግሽበትንበተመለከተየዋጋውድነትንለመቆጣጠርናብሎምዋጋዎችንለመቀነስያለውበርካታአማራጮችያሉቢሆንምአይኤምኤፍባወጣው መግለጫየኢትየጰዮጲያየውጭእዳ ጫናወደከፍተኛደረጃመድረሱንናይህምመሰረታዊሸቀጦችንወደሃገርውስጥለማስገባት እንደ ስንዴ ፤ ስኳርና ዘይት የመሳሰሉትንለማቅረብአስቸጋሪሁኔታንእንደፈጠረ ተገልጸዋል፡፡ አይኤምኤፍ በበኩሉ ባወጣውመግለጫኢትዮጲያንናታንዛንያንበከባድየእዳጫናውስጥእየገቡእንዳሉአስጠንቅቋል ፡፡
የውጭምንዛሪእጥረትመፈጠርየዋጋግሽበትንበማባባስአሉታዊአስተዋፅኦንአድርጓል ፡፡ይህምየፖሊሲማሻሻያንማድረግአስፈላጊሆኖተግኝቷል ፡፡ነገር ግን በዚህዘርፍፖሊሲአውጪዎችምንያህልዝግጁ ናቸው የሚል አግባብነትያለው ጥያቄ ቢነሳ ተገቢ ነው ፡፡ በፋይናንስ ዘርፍ በተለይም ማሻሻያዎችን ደፈር ብሎ ማድረግ አስፈላጊሲሆንየፋይናንስዘርፉንለውጭባንኮችናየፋይናንስተቋማትበመጠኑከፈትማድረግ አንዱ አማራጭ መሆኑን በርካታ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች እየተናገሩ ይገኛሉ ፡፡ለውጭ ባንኮች ዘርፉ ዝም ተብሎ ባንዴ የሚከፈት ሳይሆን ቀስ በቀስ ለቀቅ እየተደገረገ የሚከፈት ነው ፡፡ ለምሳሌ ቻይና የውጭ ባንኮች ወደ ሃገሯ እንዲገቡ ስትፈቅድ በጀመሪያ ከሃገር ውስጥ ባንክ በጋር የጋራ ሽርክናን በመፍጠር እንጂ የውጭ ባንኩ ብቻውን ሊገባ አይችልም ፡፡ ቀስ በቀስ ግን ቻይና የውጭ ባንኮች ብቻቸውን ወደ ፋይናንስ ዘርፉ እንዲገቡ ፈቅደዋል ፤ በዚህም የምእራባውያንን ድጋፍ አግኝተውበታል ፡፡ በርግጥ የቻይና ሞዴል ሙሉ ለሙሉ ከኢትዮጲያ ጋር ተመሳሳይነውማለትአይደለም፡፡ ቻይናየፋይናንስዘርፍንበሰፊውመክፈትየጀመረችው የፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን ሲመጡ ከቻይና ጋር ያለውን የንግድ ጉድለት አስተካክላለሁ ስላሉ ኢኮኖሚዋን ዝግ አደረገች እንዳትባል ከፈት ማድረግጀምራለች ፤ነገርግንትራምፕበዚህሳይወሰኑበቻይናየአልሙኒየምናበብረትምርቶችላይማእቀብንጥያለሁብለዋል፡፡ነገርግንቻይናየቴሌኮምእናየፋይናንስዘርፏንክፍትማድረጓየዓለምየንገድድርጅትአነባል እንድትሆንና በንግድ እንድትበለፅግና ከፍተኛየውጭምንዛሬ በገቢን በማግኘት መልሳ ለአሜሪካ አበዳሪለመሆንአብቅቷታል ፡፡ ይህ እድል አሁን ቀጥሎ ተጠቃሚይሆናሉ፤ ተብለውየሚጠበቁትእንደኢትዮጲያያሉትየአፍሪካአገራት ናቸው ፡፡ከዚህ ለመረዳት የሚቻለው ስልታዊ በሆነ መንገድ ኢኮኖሚን ክፍት ማድረግ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሚያደርግነው ፡፡በዚህ ዘርፍ ለዘብያለናአሁንካለውወቅታዊከሆነውእንቅቃሴአንጻርበተግባርየሚሰራንፖሊሲመከተልአማራጭመሆኑን ማስተዋልያስፈልጋል ፡፡

Posted by Unknown at 2:38 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Sunday, April 29, 2018

eprdf , abey justice ethiopia

ፀሃፊው በስሜነህ ተረፈ
የፍትህ ስርአቱ ትኩረትን ይሻል
            መልካም አስተዳር ለማስፈን ዋነኛ መሳሪያ ከሆኑት ተቋማት መሃከል ፍርድ ቤቶች ዋነኞቹ ቢሆኑም ነገር ግን ህብረተሰቡ በሚጠበቅባቸው ደረጃ ላይ አለመሆናቸው የፍትህ አሰጣጡ ያለበትን ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል ፤ ፍርድ ቤቶች ተገቢውን ፍትህ ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸው በአሁኑ ሰአት በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚታየው የስነ ምግባር ውድቀት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ማንም ፍርድ ቤት የሚመላለስ ሰው በቀላሉ የሚያስተውለው ሆኗል ፡፡ በከተማችን በሚገኙት ፍርድ ቤቶች አካባቢ የመዝገቦች መብዛት ፤ የቀጠሮ መርዘምና መደጋገም እንዲሁም የአቅም ማነስና በአጭሩ መቅጨት የሚቻሉ ጉዳዮች አለአግባብ ማንዛዛትና በዜጎች ንብረት መበላሸትና ውድመት እንዲደርስ ማድረግ ፤ የውሳኔዎች ጥራት መጓደል ፤ በተራዘመ ቀጠሮ ንብረቶች በማይገባው ተከራካሪ እጅ ለረጅም አመታት ያለ ውሳኔ መቆየት ፤ አርዝሞ በመቅጠር ማቆየት አንደኛው ወገን ማግኘት የማይገባውን ጥቅም እንዲያገኝ ማድረግና ሌላውን ወገን ተጎጂ ማደርግ አድሎአዊ አሰራር፤ እንደዚሁም የስነ ስርአት ህጎቹ የሚያዙዋቸውን አንቀፆችን አለመጠቀም እና ነገሩን ማሳጠር ሲቻል ነገር ግን ችላ ብሎ በማለፍ ጉዳዩን የሚጓትት አካሄድን መከተል የሚታዩ ጉልህ ጉድለቶች ይሆናሉ
            በአሁኑ ወቅት አንድ ዳኛ በፈለገው ቀን እያስረዘመ ቀጠሮን የሚሰጥ ሲሆን ነገር ግን ያለውሳኔ ለሚያጓትተው ጉዳይ ምንም ተጠያቂነት የለበትም ፡፡ ጠ / ፍ ቤቱ የጉዳዮች አስተዳደር መመርያ ማለትም የመዝገቦች አቀጣጠር መመርያ ይወጣል ቢባልም ወጥቶ ስራ ላይ አልዋለም ፡፡ የፍርድ ቤት ውሳኔ መጓተት ከሃገር ኢኮኖሚ ላይ ውድመትን እያስከተለ ሲሆን ፤ በስር ፍርድ ቤት አመራሮች ዘንድ የሚስተዋለው የስነ ምግባር ችግር በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የበላይ ሃላፊዎች ዘንድ ግንዛቤው ጨርሶ አለመኖር ፤ እንደዚሁም ዳኞችን ከኋላ በስልክ ይታዘዛሉ የሚልም የባለጉዳዮች ጥርጣሬ ያለ ሲሆን በፍትህ ስርአቱ ላይ ከምንግዜውም የወረደ የህዝብ አመኔታ መኖሩ ግን ወዴት እየሄድን ነው ያሰኛል ፡፡ ለዜጎች ፍትህ ያሰፍናል ተብሎ የሚታመንበት ተቋም ዜጎች ፍትህን እንዳያገኙ ዋነኛ ባላጋራ ሆኖ መነሳቱ አሳሳቢ ነው ፡፡ በፍ / ቤቶች ለፍትህ ቆመዋል የሚባሉ ተቋማት እንደመሆናቸው የሚታየው የተበላሸ አሰራር በብዙዎች የአስፈጻሚ መቤቶች እምብዛም የተለመደ አይደለም ፤ ይህም በመንግስት ላይ የአመኔታ እንዲሸረሸርና ህብረተሰቡ የትም ሄጄ መብቴን በትክክለኛው መንገድ ማስከበር አልችም የሚለው አስተሳሰብ በተለይም በወጣቱ ዘንድ ተስፋ መቁረጥን ሲፈጥር ወደ አመፅና ግርግር አገሪቷን ጨምሯል ፡፡  
            ከህዝብ ቅሬታዎችን የመቀበልና መፍትሄ የመስጠት ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ቢሆንም ጉባኤው ከህዝብ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎ በይፋ ምላሽን ሲሰጥ አይታይም ፤ የዳኝነት በደሎች ፤ አድልኦ የመሳሰሉት ባለጉዳዮች ሲያጋጥሟቸው ለጉባኤው ያቀርባሉ ቢባልም ጉባኤው በወር አንዴ ብቻ የሚሰበሰብ ሲሆን አባላቶቹም በርካታ በሌላ መ / ቤቶች ውስጥ ስራ ያላቸው ስለሆነ ዋነኛው ስራቸው አይደለም፡፡ በሃገሪቱ በሞላ የሚቀርቡለትን ጉዳዮችን የሚመለከተው ጉባኤው በወር አንዴ ብቻ መሰብሰቡ በቂ ነው ወይ ሊባል ይችላል ፡፡፡
            በተለይም በፍርድ ቤት ንብረትን ማስለቀቅ በጣም ከባድ ከመሆኑም በላይ ለኪራይ ሰብሳቢነት በርን የከፈተ ሲሆን የመንግስትን ትኩረት የሚሻበት ደረጃ ላይ ደርሷል፤ ያለቀውን ጉዳይ አስከ ሰበር ችሎት ድረስ ያስቀርባል በማለት በተደጋጋሚ አፈጻጸም በማገድ በተደጋጋሚ በማከራከር ጉዳዮችን በማርዘም በባለጉዳዮች ላይ ይሄ ሃገራችን ነው ውይ ብለው እስከሚጠራጠሩ ድረስ ግፍ እየተፈፀመ ይገኛል  ፡፡ የንግድ ቤቶች አከራዮች እዚህ ላይ ጠንቀቅ እንዲሉ ምክሬን እሰጣለሁ በአሁኑ ወቅት የንግድ ቤት ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ከገባ ቀላል የአከራይ ተከራይ ጉዳይ ቢሆንም እንኳን አመታትን ሳይፈጁ በቀላሉ ቤቶቹ የማይለቀቁ ሲሆን የመዝገብ ቤት ፀሃፊዎች ጭምር መዝገቡንና ባለጉዳዩን እንዲለዩት የሚደረግ ሲሆን ከፍተኛ ጉቦ የሚረጭበት ክርክር እንደሆነ በጠበቆች ጭምር በይፋ ይነገራል ፤ በመንግስት ደጋፊዎች በሆኑ ዘንድ ሳይቀር የዚህ አይነት ክርክሮችን ለመርታት ደህና ገንዘብ እንደሚያስፈልግ በይፋ እየተነገረ ይገኛል ፡፡
            በአንድ ወቅት አንድ የህግ ባለሙያ በጋዜጣ ላይ ከሰጡት መግለጫ እንደሰማሁት የዳኞች ሹመት ግልፅ አለመሆንና በጣም ወጣቶች መሆን በራሱ ችግር እንዳለው ሲለግፁ ሁሉም ደካማ ናቸው ባይባልም ነገር ግን የእድሜ ገደብ ቢንስ ወደ 30 አመት ከፍ ቢል ከእድሜ ተሞክሮ የተሻለ ዳኝነት ለመስጠት የሚስችል ሲሆን ባለጉዳዮች ሊያፍሩባቸው የሚችሉ ግለ ጉዳዮች ለምሳሌ የባልና የሚስት የውስጥ ገመና አይነት ክርክሮችን ለመረዳት እድሜ ያበሰለው ሰው ይመረጣል ተብሎ ይታሰባል ፡፡ የትምህርት ዝግጅት ብቻ ሳይሆን የዳኝነት ስራ በባህሪው የእድሜ ተሞክሮ የሚፈልግ ስለሆነ ነው ፡፡  
            ከዚህ ጋር ተያይዞ የዳኞች ደሞዝና ጥቅማጥቅም በመንግስት ጭማሪ እንዲደረግና ይህንንም ለማድረግ የበጀት እጥረት እንዳለ የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዳኜ መላኩ በሚዲያ የገለፁ ሲሆን ጠቅላይ ፍ / ቤቱ የራሱ ቦታ እንደተሰጠው ተሰምቷል የቢሮ እጥረቱን የሚቀርፍለት ሲሆን የዚህ እነኚህ ጅምሮች የሚበረታቱ ናቸው ፡፡ ጠቅላዩ ፍርድ ቤቱ በኮምፒተር መረጃዎችን የመያዝ ፤ መዝገብ የመክፈትና ክፍያዎችን የመፈፀም በተመለከት ማሻሻሉ ፤ በበርካታ መስኮቶች ባለጉዳዮች ያለወረፋ ማስተናገድ መጀመሩ መልካም ቢሆንም  ነገር ግን አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎች አለመውጣታቸው በራሱ ችግርን እንደፈጠረ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሃላፊዎች በሚዲያ የተናገሩ ሲሆን አንድ ጉዳይ ወደ ይግባኝ ሲሄድ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለው ግልፅ የሆነ መመሪያ አለመኖሩ በራሱ ችግርን እንደፈጠረ የስር ፍርድ ቤት በትክክል የፈረዳቸው ማለቅና መቆም ሲገባቸው ያስቀርባል ተብለው ውሳኔዎቹም ላይቀየሩ ነገር ግን የዜጎች ንብረት አፈጻጸም ታግዶ አለአግባብ እንደሚንከራተቱ ይታያል ፤ አንዳንዴ ደግሞ ሊያስቀርቡ የማይገቡ ሆነው ነገር ግን በአድላዊ አሰራር አፈጻጸማቸው ታግዶ ይቆይ ለሰበር ይቅረብ ተብለው ፣ ትክክለኛ የሆነው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔዎች በግፍ ሲሻሩ ይስተዋላል ፤ ሌላ ግዜ ግልፅ ያልሆኑና የተምታቱ ውሳኔዎችን የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት ሲሰጥ ይታያል ፡፡ ይሁንና የሰበር ችሎት የመጨረሻው ይግባኝ ሰሚ ፍ/ ቤት ነው እንጂ ህገ መንግስታዊ ፍ / ቤት አለመሆኑ የሚታወቅ ፤ ነገር ግን በተደጋጋሚ ሰበር ችሎት እንደ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ሆኖ ሲሰራም ይስተዋላል ፡፡ የፌ/ጠ/ ፍ/ ቤት ሰበር ችሎት ለስር ፍ / ቤት አስገዳጅ የሆኑ ሃያ በላይ ቅፆችን ያሳተመ ሲሆን ይህም የሚያሳየው በተለይም የፍትሃ ብሄር ህጉ ውስጥ በርካታ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ስላሉ እነዛ ሰበር ችሎቱ አንዳንድ ግዜም እንደ ህግ አውጭ ፓርላማ ስራን እየሰራ ነው ማለት ይቻላል ነገር ግን ሰበር ችሎቱ በአንድ ወቅት የያዘውን ኣቋም በሌላ ግዜ መለወጥ መቻሉ ነው ከህግ አውጭው የሚለው ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ሰበር አስገዳጅ የህግ ትርጉም የዚህን ያህል መዝገቦች መብዛታቸው በራሱ ህጉ መፈተሸና መሻሻል እንዳለበት አመላካች ነው ፤ ህጎቹ ግልፅ ቢሆኑ ኖሮ የዚህን ያህል የበዙ ጉዳዮች አስገዳጅ የህግ ትርጉም ባልተሰጠባቸው ነበረ ፡፡  
            ይህ ብቻ አይደለም ህግን የመተርጎም እንደ ህገ መንግስታዊ ፍ / ቤት ሆኖ ስልጣን የተሰጠው ለፌዴሬሽን ም/ ቤት መሆኑ በራሱ ለህግ አተረጓጎም ችግርን ፈጥሯል ፤ ፌ/ ም ቤት ራሱ የአስፈጻሚው የገዢው ፓርቲ አካል ሆኖ መልሶ ከፍ / ቤቶች በላይ ህግ ተርጓሚ መሆኑ ህገ መንግስታዊ ትርጉም ያስፈልጋቸዋል የሚባሉ ጉዳዮች ወደ ም/ቤቱ የሚሄዱ ሲሆን የህግ አውጭውን ፤ የአስፈጻሚውንና የህግ ተርጓሚ የመንግስት አካላት ስራን የሚያደበላልቅ ነው ፡፡ ከዚህም አልፎ በቅርቡ ስራውን የጀመረው የህገ መንግስታዊ አጣሪ ኮሚሽን የተባለው ተቋም ስራ መጀመሩ መልካም ሲሆን በርካታ የህግ ክፍተቶች ባሉት የፍትህ ስርአቱ ፍርደ ገምድል ውሳኔ ተወስኖባቸው አጣሪ ኮሚሽኑ ያስተካከላቸው እንዳሉ ይታወቃል ፤ ይሁንና ይህ ተቋም የበላይ ሃላፊዎቹ ፍርዱን የፈረደው ተቋም የጠ/ፍ / ቤት ሃላፊዎች መሆናቸው ራሱ ፍርድን የሰጠው ሰው መልሶ ቅሬታውን የሚያየው መሆኑ አሁንም የአጣሪ ኮሚሽኑን ነጻነቱንና ተጠያቂነት አጠያያቂ ያደርገዋል ፡፡ 
            ለመልካም አስተዳደር መጠናከር ዋነኛው የፍትህ ስርአቱን መፈተሸና የዳኝነት ስርአቱን በተደጋጋሚ ማሻሻል አስፈላጊ ቢሆንም በከፍተኛ የመንግስት አካላት ሳይቀር ተገቢውን ትኩረት አላገኘም ፡፡ አንዳንዶቹ ህጎች ከወጡ ረጅም አመታት ያለፋቸውና ለአሁኑ ዘመን እንዲያሰሩ በሚገባ መሻሻል የነበረባቸው ቢሆንም ሳይሻሻሉ ለበርካታ አስርት አመታት የዘለቁ እንዲሁም ከህገ መንግስቱ በላይ እድሜ ያላቸውና በስራ ላይ ካለው ህገ መንግስት ጭምር ጋር የሚጣረሱ ሆነው ሳለ ነገር አሁንም እየተሰራባቸው ነው ለምሳሌ ከ60 አመታት በፊት የወጣው የፍትሃ ብሄር ህጉ በርካታ ክፍተቶች ያሉበትና ጉዳዮች በቀላሉ እንዲቋጩ የሚያደርግ ካለመሆኑም በላይ ዜጎች በቀላሉ በፖሊስ ሊያልቁ የሚችሉና የሚታወቁ ነገሮች ላይ አመታት በይግባኝ እንዲጓተቱ የሚያደርግና ለዳኛው ከሚሰጠው ሰፊ ስልጣን አንጻር ለኪራይ ሰብሳቢነት በርን የከፈተ ነው ፡፡ የንግድ ህጉም ቢሆን የቆየ ሲሆንም እሱንም ለማሻሻል ስራ እየተሰራ እንደሆነ በጠቅላይ አቃቤ ህግ የተገለፀ ቢሆንም ተሻሽሎ አልወጣም፡፡ አሁን ሃገሪቱ ካለችበት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት አንጻር ህጎች ከዘመኑ ጋር መሄድ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም ነገር ይህ ሲሆን አይታይም ፡፡
            ፍትህ ስርአቱ የሚወስናቸው ውሳኔዎች በሃገሪቱ የፖለቲካ ጉዞ ላይ መልካምም ሆነ አሉታዊ ተፅእኖ ያለው ሲሆን ቀጥተኛ የፖለቲካ አስተዳደሩን ህልውና በበጎም ይሁን በመጥፎ ይወስናል ፡፡ በሃይለስላሴ ግዜ በ1953 ዓ.ም. ተሞክሮ በከሸፈው የጄኔራል መንግስቱ ንዋይ መፈንቅለ መንግስት ወቅት ጄኔራሉ ለምን መፈንቅለ መንግስት ሊያካሂዱ እንደተነሳሱ ፍ / ቤት ቀርበው በተናገሩት ንግግግር ላይ ህዝቡ በትክል ዳኝነትን እንደማያገኝ እስከ 20 እና 25 አመት ድረስ ፍርድ ቤት ሲመላለስ እንደሚኖር እንደዚሁም በንብረት፤ በመሬት ክርክሮች አስርት አመታትን በሚፈጅ የፍርድ ቤት ሙግት ቤተሰብ እንደሚፈራርስ፤ ልጆች እንደሚበታተኑ እንደዚሁም ለንብረቱ ሲባል በተከራካሪው ወገን ላይ እስከ መገደልና ንብረቱን በህግ ማስመለስ በሚያቅተው ወቅት በሰውየው ህይወት ጭምር አደጋ እንደሚጋረጥ ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን መቁዋጫ በሌለው የአመታት ሙግት ህዝቡ ሲሰቃይ ማየታቸውንና ንጉሰ ነገስቱም ለማሻሻል ጥረት አለማድረጋቸውን ነገር ግን ህብረተሰቡ ለህግ በነበረው አክብሮት ግን ለአመታት ይመላለስ እንደነበረ ተናግረዋል ፡፡ የዙፋን ችሎት ተብሎ ዛሬ እንዳለው የሰበር ችሎት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ችሎቱ ላይ ይቀመጡ የነበሩት ራሳቸው ንጉሰ ነገስቱ ስለነበሩ እርሳቸው ካለባቸው የመንግስት ስራ ጫና የተነሳ ጉዳዩ ዙፋን ችሎት ደረጃ ለመድረስ አመታትን ይፈጅ እንደነበረ መገመት ይቻላል፤ እንደዚሁም ንጉሰ ነገስቱ አስፈጻሚው አካል ሆነው መልሰው ህግ ተርጓሚ ዳኛ መሆናቸው ራሱ የህግ ጥያቄን ሊያስነሳ ይችላል ፡፡ የፍትህ በወቅቱ አለመስፈን የቤተሰብ ብሎም የህብረተሰቡ ሰላም እንደሚያናጋ አሁን በቅርቡ በሃገራችን ያየናቸው አስፈሪ የህዝብ ተወቃውሞ እንቅስቃሴዎች አስረጂዎች ናቸው ፡፡     
            በየትም ሃገር እንደሚደረገው ሁሉ አንድ የፍትህ ስርአት ውስጡ ችግሮች ካሉበት መሻሻል እንዳለበት የታወቀ ሲሆን መንግስታት የህዝብን ጥያቄዎችንና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ለመመለስ በፍትህ ስርአታቸው ላይ ትኩረትን በማድረግ በየጊዜው አዳዲስ ህጎችን በማውጣ ህጎቻቸውን በተደጋጋሚ ሲያሻሽሉ የምንሰማ ቢሆንም በሃራችን ግን አንድ ህግ አላሰራ ማለቱና መሻሻል እንደሚያስፈልገው እየታወቀ ሳይሻሻል ለረጅም ጊዜ እንዲሰራበት በማድረግ ብዙ ችግርን ከፈጠረ በሁዋላ ወደ ማሻሻል ሲገባ ይስተዋላል ፡፡ አንድ መንግስት ስራው አስተዳደር ብቻ ሳይሆን ጥናት እያደረገ ነባሮቹን ማሻሻልና አዲስ ህጎችን ማውጣት ነው በተለይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋነኛው ስራው ህጎቹን ማውጣት ለህግ ተርጓሚው አሻሚ ያልሆኑ ህጎችን መደንገግ ነው ፡፡ ጭራሽ ህችን ካለማውጣት ደግሞ አንድ ህግ ወጥቶ ተሰርቶበት በስራ ሂደት ያለው ድከመት ታይቶ ማሻሻል የበለጠ ተመራጭ ነው ፡፡ እኛ ግን ህግን ለማውጣትም ሆነ ለማሻሻል የምንፈራ እንመስላልን ፤ ምናልባት በመንግስት በኩል እነኚህ ነጻነትን የሚገድቡ ህጎች በቀደሙት መንግስታት ዘመን የወጡ ስለሆነ ነገር ግን ባሻሽላቸው ስልጣኔን የተወሰነው ይቀንስብኛል የሚል ስጋት ሊኖረው ይችላል ብለን ብናስብ እንኩዋን ፤ አሁን ባለው በሃራችን ተጨባጭ ሁኔታ ለመንግስት ስጋት የሚሆነው የመልካም አስተዳር አለመስፈን ስለሆነ የበለጠ ዋጋን እንደሚያስከፍል መረዳት ይቻላል ፡፡ እንደውም መንግስት አሁን ካለው አሳሳቢ ከሆነው የሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በመነሳት ህዝቡ ፈጣን ምላሽንና መሻሻልን የሚጠብቅ በመሆኑ  የህግ ክፍተት ያለባቸውን ህግጋት በባትሪ  ብርሃን እየፈለገ ማሻሻል ያለበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን ፡፡
            ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ ክፍተት ያለባቸውን ህጎች እንደሚያሻሽሉ ፤ እንደዚሁም በተደጋጋሚ የህዝብ ቅሬታ የሚቀርብባቸውን የመንግስት መስሪያ ቤት ሃላፊዎችን እንደ የአመራር ለውጥ እንደሚያደርጉ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን ፍርድ ቤቶች ዋነኛ የህዝብ ቅሬታ ማእከል ከሆኑ ቆየት ብሏል ፤ እንደዚሁም ብሄራዊ ባንክ ቅሬታ የሚቀርብበት ቢሆንም እነኚህ ሁለት ወሳኝ ተቋማት በጠቅላይ ሚ/ሩ የመጀመሪያ ሹመት የአመራር ለውጥ ሳይደረግባቸው ቀርተዋል፡፡
            አንድ ሰሞን ዋነኛ የህግ ክፍተት ከሚታይባቸው ዘርፎች አንዱ የሆነው የአከራይ ተከራይ ፤ የሪል ስቴትና የቤቶች ግዢና መግዛትን የሚመለከት ህግ ይወጣል ቢባልም ሊወጣ ጫፍ ደርሶ ሲያበቃ በማይታወቅ ምክንያት ህጉ ሳይወጣ ቀርቷል ፡፡ መንግስት ለዜጎች ለአመታት ደክመው የሰሯቸውን ቤቶች ንብረት ለድርድር የማይቀርብ የህግ ከለላና ጥበቃ ማድረግ አለበት ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው የፍትሃ ብሄር ህግ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል ካለመሆኑም በላይ አንድ አይነት አለመግባባት ቢፈጠር የዜጎች ውል የመዋዋል መብትንና ከውል የሚመነጭ መብታቸውን ለማስከበር ፤ እንደዚሁም ግዴታዎችን ለማስፈጸም አስቸጋሪና የተንዛዛ የአመታት የፍርድ ቤት ምልልስን የሚፈጥር ነው ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ኮንዶሚኒየም ቤት ቢገዛና ከሻጩ ጋር አለመግባባት ቢፈጠር ነገሩን ለማስተካከል ወደ ህግ ክርክር ከሄደ ውሳኔ ለማግኘት አመታትን የሚወስድ ነው ፡፡ ይህ አዋጅ ለዚህ አይነት ጉዳዮች ፍቱን መድሃኒት ሊሆን የሚችል የነበረ ሲሆን መዘግየቱ ግን ተገቢ አለመሆኑን መረዳት ይቻላል ፤ ይህን በመፍራት ብዙዎች ከመግዛትና መሸጥ ሲታቀቡ ታይቷል ፡፡  በነባሩ የፍትሃ ብሄር ህግ መሰረት አንድ ሰው ተከራይ ሆኖ የሰው ቤት ገብቶ ነገር ግን ካርታና ሰነድ ለውጦ የቤት ባለቤት የሚሆንበት ሰፊ የህግ ክፍተት ያለ ሲሆን እንደዚሁም የሪል ስቴት ኩባንያዎች ቤቶችን ለማስራት ከደንበኞቻቸው ገንዘብን ከሰበሰቡ በሁዋላ አንዳንዶቹ እጅግ ዘግይተው ቤቱን ሰርተው የሚያስረክቡ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ጭራሽ ገንዘቡን በማበባከን ቤት ገዢዎችን በነጻ እንዲወጡ ያደረጉ እንዳሉ በሚዲያ የምንሰማው ጉዳይ ነው ፡፡ በነባሩ የፍትሃ ብሄር ህግ ሪል እስቴት የሚባለው ቃሉ ራሱ የማይታወቅ ሲሆን በአንድ የሪል ስቴት ቤት ገዢና ሻጭ መሃከል አለመግባባት ቢፈጠር በተለይ ቤት ሰርቼ አስረክባለሁ ብሎ ገንዘብ የተከፈለው አካል ተጠያቂ የሚሆንበት የህግ አሰራርም ሆነ የህግ ማእቀፍ ወይም መመሪያም ሆነ አዋጅ የለም ፡፡ በአንድ የሪል ስቴት ኩባንያና በደንበኞቹ መሃከል በተፈጠረ አለመግባባት ላይ አንዱ ደንበኛ ወደ ፍርድ ቤት መሄድ የለብንም ሲል ተሰምቷል ይህም ሪል እስቴት ግልፅ የሆነ አዋጅ ስለሌውና በፍትህ ስርአቱ ላይ አመኔታ ባለመኖሩ ንብረቱ በአፈጻጸም ታግዶ በይግባኝ ለአስር አመታት ሊቀጥል ስለሚችል ባለው ፍራቻ ነው ፤እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ያሉ የህግ ክፍተቶች ናቸው ፡፡

            ነገር ግን ለዚህ ሁሊ መፍትሄ ሊሆን ይችል የነበረው የሪል ስቴት አዋጅን ማውጣት ቢሆንም አዋጁ እንደገና እንዲስተካከል በሚል ሳይወጣ ቀርቷል ፡፡ የቀድሞው ጠቅላይ ሚ/ር መልካም አስተዳርን ለማስፈን ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በፍትህ ስርአቱ ላይ ትኩረትን አለማድረጋቸው ሳይሳካላቸው እንዲቀር ምክንያት ሆኗል ፡፡ ከዚህ ቀደም በአቶ ለማ መገርሳ የተመራው ኦህዴድ በኦሮሚያ ክልል የፍትህ ስርአቱን መልሶ ያዋቀረ ሲሆን ይህም በፌደራል ቢደገም መልካም ነው ማለት ይቻላል ፡፡ የአሁኑ አዲሱ ጠቅላይ ሚ/ ር የህግ ክፍተቶችን በመድፍን ወደ ስራ በመግባት እንደዚሁም መቼም ቢሆን ከፍትህ ስርአቱ ላይ አይናቸውን መንቀል የለባቸውም ፤ ለቀድሞው ጠ / ሚር አስተዳደር አለመሳካትና የህዝብ ቅሬታ ምንጮች በመሆን ፍ / ቤቶች ዋነኛ አሉታዊ አውዳሚ ሚናን መጫወታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው ፡፡
Posted by Unknown at 2:10 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

የፍህ ስርአቱ ሲፈተሽ justice & legal system ethiooia

Posted by Unknown at 2:09 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

የፈፍተትሀህ ሰስረርአተቱ ሰሲፈተሸሸ

Posted by Unknown at 2:08 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Wednesday, December 16, 2015

Ethiopian law constitution

Ethiopian Constitution and Courts Law የኢትዮጲያ ህግና ህገ መንግስት - http://wp.me/p39p0v-8j
Posted by Unknown at 8:34 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest

Saturday, March 14, 2015

Property Rights In Ethiopian Law የኢትዮጲያ ህግና የንብረት ባለቤትነት (Property Right) መብት አፈፃፀም

            አንድ የፍርድ ቤት ሙግት በርካታ ወራትን ብሎም አመታትን የሚፈጅ ሲሆን ይህም ማለት ይህ ጉዳይ ፍርድ   ቤት ይዞታል በሚል ብቻ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ አመታትን መፍጀቱ የንብረት ባለቤትነት መብትን ህጉ በአግባቡ ማስከር ችሏል ወይ ? የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልካም ነው ፡፡ በሃገራችን እንደሚታወቀው የፍርድ ቤት ሙግት በቀላሉ የማያልቅ ሲሆን በቀላሉ ወረዳዎች ወይንም ባስ ካለም ክፍለ ከተማዎች መፍትሄ ሊሰጡት የሚገችሉት ጉዳይ አመታትን ሰዎችን ሲያመላልስ ይስተዋላል ፡፡

          አንዱ መዋእለ ንዋይን ለማበረታታት ከሚመከሩት የተመቻቹ ሁኔታዎች አንዱ የንብረት ባለቤትነት (Property Right) መብትን ማስከበር ሲሆን በምእራባውያን የምጣኔ - ሐብት ባለሙያዎወች እንደተጠናው ከሆነ ለአፍሪካ ኢንቨስትመንትን አግባቡና  በበቂ ላለመሳቧ ዋነኛው ምክንያት የንብረት ባለቤትነት መብት በበቂ አለመከበሩ ነው ይላል ፡፡

          አንድ መዋእለ ንዋይ አፍሳሽ አንድ የውጭ ሃገር ሄዶ ገንዘቡን ሲያፈስ የሚያፈሰውን ገንዘብ ሲፈልገው መልሶ ማውጣት ሚፈልግበት በማንኛውም ሰዓት ላይ ማውጣትን የሚፈልግ ሲሆን የንብረት መብት (Property Right) በአግባቡ የማይከበርባቸው ሃገራት የውጭ መዋእለ ንዋይን የማግኘት እድላቸው በጣም ጠባብ ነው የሚሆነው ፡፡  ይህም አወዛጋቢ በሚሆንበት ወቅት የሚከበር ፍርድ ቤቶች አማካይነት በተፋጠነና በተከራካሪ ወገኖች ላይ የማያስፈልግ ወጭንና ኪሳራን በማያስከትል ሁኔታ በአንዱ ኪሳራ ሌላኛው አለአግባብ በማይጠቀምበት ሁኔታ መሆን አለበት ፣ የነገሩ መንዛዛት አንደኛው ወገን በአንደኛው ኪሳራ አለአግባብ እንዲጠቀም የሚያደርግ ሲሆን ፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ በሁለቱም ወገኖች ላይ ከባድ ኪሳራንና መጓተትን ያስከትላል ፡፡ ለምሳሌ በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰው ሶማልያን እናስብ ፤ አንድ የውጭ ሃገር ኢንቬስተር ሶማልያ ሄዶ መዋእለ ንዋዩን እንደማፍሰስ ብለን ብናስብ አንድ ባለሃብት እርዳታ አድርጎ ቢሰጠው ይሻለኛል ፣ ዝም ብዬ ሄጄ ገንዘቤን ከማፈስና ከምነጠቅ ብሎ ነው እሚያስበው ፣ ስለዚህ ሶማልያ መዋእለ ንዋይ የማግኘት እድሏ አነናሳ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡

          በአፍሪካ የንብረት ባቤትት መብት በአግባቡ የማይከበር ሲሆን ለኢንቨስትመንት አስፈላጊ የሆነ መሬት ያለ በቂ ሰነድ የሚያዝ ሲሆን መዋእለ ንዋይን ለማፍሰስና ለማሳደግም ሆነ ለማሻሻል አስቸጋሪ ሲሆን አድርጎታል ብለው የውጭ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ ከዚህ ተጨማሪ ግን ፍርድ ቤቶች ጠንካራ ሆነው የንብረት ባለቤት ህጉን ለማስከበር ፈጣንና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መፍታት ካልቻሉ ረጅም ግዜን መውሰዱ መዋእለ ንዋይን ከማረታታት አንፃር አሉታዊ ጎን ይኖረዋል ፡፡ ለምሳሌ አከራይና ተከራይ መሐከል ያለ ክርክር አመታትን ሊወስድ ይችላል በዚህም ምክንያት አከራዩ ፣ ክርክሩ ቤቱ ተይዞት ከሆነ የሚካሄደው ቤቱን እስከሚያስለቅቅ ድረስ የሚደርስበትን ኪሳራን ከውል ውጭ ጉዳት ደርሶብኛል በሚል ሌላ መዝግብ በመክፈት ድጋሚ ከሶ ብቻ ነው ማስከፈል የሚችለው ፡፡ ይህ ራሱ ደግሞ ከውል ውጭ ምን ያህል ነው የደረስብህ ኪሳራ የሚለው ለዳኝነት ቁልጭ ያለ ባለመሆኑ ምክንያት አሻሚ  ስለሚሆን ከውል ውጭ ጉዳት ለደረሰበት ወገን አርኪ ላይሆን ይችላል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪም ጉዳቱ ለደረሰት ወገን የደረሰበት ጉዳት ሌላ ተጨማሪ ወጮጪን ፣ የጠበቃ አበልን የሚያስወጣው ሲሆን ጉዳቱ የበዛ ነው የሚሆነው ፡፡

          የኢንቨስትመንት አዋጁ እንደሚደነግገው ከዚህ ቀደም አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ ኢትዮጲያ ውስጥ ቤት መግዛትም ሆነ መስራት የማይችል ሲሆን ነገር ግን የዚህ አዋጅ መሰረት ግን ኢንቨስተሩ ቤት ለመስራት ይፈቀድለታል ፡፡ ለምሳሌ በ2004 ዓ.ም. የወጣው የሊዝ አዋጁን ብንወስድ አዋጁ የወጣትበት ዋነኛው ምክንያት የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ማሳካት የሚል ሲሆን ፣ የግል የንብረት ባለቤትነት መብትን ይጋፋል በሚል በህግ ባለሙያዎች የተተቸ ሲሆን ነገር ግን አዋጁ የወጣበት አላማ ግን መንፈሱን መረዳት ይቻላል ፡፡
Posted by Unknown at 6:22 PM No comments:
Email ThisBlogThis!Share to XShare to FacebookShare to Pinterest
Newer Posts Older Posts Home
Subscribe to: Posts (Atom)

Economy and Philosopy

  • December (3)
  • January (1)
  • February (9)
  • March (36)
  • April (12)
  • May (6)
  • August (7)
  • October (1)
  • February (28)
  • March (1)
  • December (1)
  • April (3)
  • May (1)
  • June (2)
  • July (2)
  • August (1)
  • September (1)
  • October (5)
  • November (57)
  • December (44)
  • January (7)
  • February (3)
  • March (8)
  • April (13)
  • May (2)
  • July (8)
  • August (4)
  • September (1)
  • October (1)

The Books I like

  • The Secret

Blog

This is about Philosophhy

Labels

  • Addis Ababa (1)
  • corruption (3)
  • dr. Abey Ahmed (4)
  • dr.Abey Ahmed (1)
  • economic policy (1)
  • eprdf (3)
  • Ethiopia (4)
  • ethiopian constitution amendement or rsform (1)
  • metec (1)
  • tplf (1)
  • ኢትዮፒያ ኢኮኖሚ (1)
Powered By Blogger

Do You Like the Post?

Send me Your Feelings

I would like to hear from You

Popular Posts

  • Prospects & Challenges of Private Commercial Banking in Ethiopia
    PROSPECTS AND CHALLENGES OF PRIVATE COMMERCIAL BANKS IN ETHIOPIA BY: SIMENEH TEREFE                                       ...
  • ሰው ለሰው
    የህይወት ጥያቄዎች አንድ ሰው ለምንድነው የሚኖረው ? የህይወት ፈተናዎች ምንድናቸው ?  ሰው መሆን ጥበብ ይብዛም ይነስም ማንኛውም ሰው የሚመራበት የራሱ የሆነ የህይወት ፍልስ...
  • የመግባባት (Communication Skill) ችሎታ
    የመግባባት ችሎታ ለመሪነት ብቻም ሳይሆን ለአንድ ሰው የህይወት ስኬት እጅግ ቁልፍ ከሆኑ ክህሎቶች አንዱና ዋነኛው ነው ። እንኳን መሪ ይቅርና አንድ ሰው በህይወት ...
  • ጥበብ እና ፍልስፍና
    ስኬታማ ለሆነ ኑሮ ተግባራዊ የሆነ የህይወት ልምድ ያስፈልጋል ። በተለይም በርካታ ችግሮችን ያሳለፈ ሰው ችግሮች አስቀድመው ሊፈጠሩ ሲሉ አስቀድሞ ማየት ይችላል ። በአለም ላይ ...
  • የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሕይወቱ እና ትምህርቱ አጭር ዳሰሳ
                                                                                 የቅዱስ አትናቴዎስ ዜና ሕይወት ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ በ298 ዓ.ም በእስክንድርያ ተወለደ፡፡ ...
  • ፍትሀ ነገስትና ዘመናዊ የኢትዮጲያ ህግ
    ፍትሀ ነገስት ለሃገራች ህግ መሰረት ሲሆን ይሄው ፍትሀ ነገስት መሰረት የሚያደርገው መፅሐፍ ቅዱስን ነው ፡፡ ከቅዱሳን መፅሀፍት ለህግ ልዩ ትኩረትን ይሰጣሉ ፡፡ ማንኛውም ሃይማኖት አንዱ ክፍል የሚሆነው ህግ ነው ...
  • የምጣኔ ሀብት አስተዳደር
    አሁን የምንኖርባት አለማችን በየቀኑ እየተለወጠችና እየጠበበች በመምጣት ላይ ትገኛለች ።በብዙ ዘርፎች ከፖለቲካና ከቴክኖሎጂ ለውጥ ጀምሮ ቴክኖሎጂ እያደገና የንግድ ልውውጦች እየተስፋፉ በሄዱ ቁጥር የእርስ በእር...
  • የወሲብ ስሜትን «በማፈን» የተገኘው ስልጣኔ
    ሲግመን ፍሮይድ ይህ የሠው ልጅ ስልጣኔ የሰው ልጅ « የወሲብ ስሜቱን በማፈን ያገኘው ነው » ሲል እንዲሁም ፍሬደሪክ ኒችም ይህ ስልጣኔ « ራስን በማሰቃየት የተገኘ ነው » ሲል ገልጿል ። ለዚህ የኒች አባባል ...
  • Human Psycholgy ማመዛዘንና ማነፃጸር
    የስነ - አእምሮና የስነ - ማህበረሰብ ጥናት ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት የሰው ልጅ አእምሮ ነገሮችን በማመዛዘንና በማነፃፀር እንደሚሰራ ተረጋግጧል ፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት የመኪና መንዳት ልምምድ ያስተምረን በክፍ...
  • የክስ አቀራረብና ስነ - ስርአት
    አንድ ሰው ፍርድ ቤት ሲሄድ በክስ ማመልከቻው ላይ በሚያቀርብበት ወቅት በግልፅ ችሎቱ የማየት ስልጣን አለው ስለዚህም ፣ ይፈረድብኝ ወይንም ይፈረድልኝ ብሎ ምሎ ነው ፡፡ የክስ ማመልከቻውን በሚያቀርብበትም ጊዜ መጀ...

Translate

Total Pageviews

Subscribe To

Posts
Atom
Posts
All Comments
Atom
All Comments

A blogger residing in Addis

Unknown
View my complete profile

Search This Blog

Simeneh Terefe Demissie All rights Reserved . Simple theme. Theme images by carlosalvarez. Powered by Blogger.