Friday, February 6, 2015

Global Migration & Poverty



ዓለም አቀፉ የህዝቦች እንቅስቃሴና ፍለሰት (Migration)

በአሁኑ ወቅት ስደት ዋነኛ የህዝቦች መንቀሳቀሻ ነው ፡፡ በአረቡ ዓለም ያለው የህዝቦች መንቀሳቀስ ጦርነትን በመሸሽ እንዲሁም በላቲን አሜሪካ ያለውን የቡድን ግድያና ለአደንዛዥ እፅ የሚደረገውን ጦርነት በመሸሽ ምክንያት በአለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የአዳዲስ ህዝቦች እንቅስቃሴና ፍልሰት ይታያል ፡፡
አውሮፓ ህዝቡ እያረጀ በመሆኑ የተሟ የጤና እንክብካቤን ለማግኘት ለታዳጊጉ አገራት ወጣት ወደ አውሮፓ መምጣት እንዳለባቸው ይረዳሉ ፣ ነገር ግን በአብዛኛው ስለ ስደት ያለው አመለካከት አሉታዊ ጎኑ የሚበዛበት ሲሆን እንደ አሜሪካ ያሉ ሃገራት በስደተኞች የተቋቋሙ ናቸው ፡፡ ስደት የህዘብች ስብጥርንና የተለያዩ ህዝቦችን ወደ አንድ ሃገር በመግባት የሃገርን ገጽታ በበጎ ጎኑ የመለወጥ አቅም አለው ፡፡

ድህነት (Poverty)

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት የተነበሩት ሊንደን ቢ ጆንሰን እ.አ.አ. በጥር 8 ቀን በ1964 ዓ.ም. በድህነት ላይ ለኮንግሬሳቸው ባሰሙት አመታዊ ንግግር ላይ ‹‹ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በድህነት ላይ ጦርነትን አውጃለሁ›› ብለው አስታወቁ ፡፡ ጆንሰን በታሪክ የመጀመሪያውን ጦርነት በድህነት ላይ ያወጁ ፕሬዝደንት ናቸው ፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ የዓለማችን መሪዎች እንዲሁም አለም አቀፋዊ ተቋማት እንደ የተባበሩት መንግስታትና አለም ባንክንና የአለም የገንዘብ ድርጅትን ጨምሮ ድህነት ላይ ጦርነትን አውጀናል ሲሉ በተደጋጋሚ ይሰማሉ ፡፡ የፕሬዝዳንቱ አላማ ‹‹የድህነትን ምልክቶችን ለማስታገስ ብቻ ሳይሆን፣ ለማዳንና ለመከላከልም›› ጭምር ነበረ፡፡ ከዚያ ወዲህ የአሜሪካ የፌደራል መንግስት ድህነትን ለመዋጋት ከ19 ትሪሊየን ዶላር በላይ ወጪ አድርጓል ፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁሉ ገንዘብ ምን ውጤት ተገኘ ተብሎ ቢጠየቅ ተገቢነት አለው ፡፡ ከዚህ ይልቅ አንዳንድ ባለሙያዎች በግል እርዳታን የሚያደርጉ እና የግል ኩባንያዎችና ሃብታም ደግ ግለሰቦች የሚሰጡት በመንግስት ከሚደጎመው የማህበራዊ ዋስትና ይልቅ ውጤታማ ሊሆን ይችላል ወይ ብለው ጠይቀዋል ፡፡ ከማህበራዊ ከመንግስት ይልቅ ውጤታማ ናቸው ወይ ብለው እስከ መጠየቅም ደርሰዋል ፡፡
በተመሳሳይም በአፍሪካ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ የአለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ለአፍሪካ አገራት ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ለግሰዋል ፡፡ ነገር ግን አፍሪካ ከድህነት ፈጽሞ በዚህ የእርዳታ ገንዘብ ከድህነት ያልተላቀቀች ሲሆን አፍሪካ ለውጥ ማምጣትና መነቃቃት የጀመረችው ኢንቨስትመንት ስታገኝና ከእርዳታው ይልቅ የንግድ ትስስርን በተለይም ከሩቅ ምስራቅ አገራት እንደ ቻይናና ህንድ ካሉ አገራት ጋር መፍጠር  በጀመረችበት ወቅት እንደሆነ ይታወቃል ፡፡ በእርግጥ አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነፃ ከወጣችበት ባቸው ከ1960ዎቹ እስከ 90ዎቹ ድረስ መረጋጋት ርቋት መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በተበላሸ ወታደራዊ አገዛዝ በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ነግሶ መቆየቱና ይህን ተከትም የእርስ በእርስ ጦርነቶች በበርካታ የአፍሪካ አገራት መቀስቀሱ እንዲሁም አፍሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት የጦርነት አውድማ መሆኗ ለአፍሪካ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ውድቀት አንዱ ሰበብ ሆኖ መቆየቱ አሌ አይባልም ፡፡ ይህ ጉዳይ አከራካሪ ሲሆን በርከታ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየትን ይሰጣሉ ፡፡

The Ethiopian Economy & Climate Change



የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ (Climate Change)

የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ የሆነ ዓለማአቀፋዊ ችግር ከሆነ ውሎ አድሯል ፡፡ በአርክቲክ እና በግሪንላንድ በአንታርቲክ አካባቢ የሚገኘው ግዙፍ የበርዶ ግርግር መቅለጥ ለባህር እና ለውቅያኖችሶች ቁመት ከፍታ መጨመርና ለትናንሽ ደሴቶች መዋጥ ፣ ለባህር ጠረፎች በውሀ መጥለቅለቅ ሰበብ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ትናንሽ ደሴቶችና በባህር ዳር የሚገኙ የአፍሪካ አገራትና ደሃ ሀገራት ከባዱ ጉዳት የሚያገኛቸው ይሆናሉ ተብሎ ይሰጋል ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ በአገራት ምጣኔ ሀብት ላይ ጉልህና የሚታይ ጉዳትን ማስከተል ይጀምራል ፡፡ ደሃ ሀገራት በየአመቱ በአየር ንብረት ለውጥ መነሻ በየአመቱ በመቶዎች ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሳራ ያጋጥማቸዋል ተብሎ ይሰጋል ፡፡
የአለም የምጣኔ ሀብት ስርአት በውድድር ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ለተፈጥሮ ሀብት፣ ለገበያ ለመሳሰለው ውድድር የተሞላበት ስሆነ ለሆነ ለተወዳዳሪዬ የበላይትን ይሰጣል በሚል ነው ፡፡ ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአጭር ጊዜ ብዙ ትርፍን ቢዝቁም ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ከመንግስታቱም ጭምር የበለጠ አቅም ቢኖራውም ከእነርሱ በኩል ግን የተሰማ ነገር የለም ፡፡
የተባበሩት መንግስታት በ2014 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ድርጅት የአየር ንብረትን በተመለከተ ምንም ካልተደረገ ጫፉ ላይ ደርሰናል ብሏል ፡፡ ቻይና ቀድሞ ከነበራት ግትርነት በመላቀቅ ታርጌቶችን በማስቀመጥ መንቀሳቀስ መጀመሯ አንድ ለውጥ ሲሆን ራሺያ፣ ብራዚል፣ ህንድና አውስትራሊያና ታርጌት ለማስቀመጥ ፈቃደኞች አይደሉም ፡፡ እኛ በቅርቡ ነው አየር ንብረትን በመከል የጀመርነው ስለዚህ አይመለከተንም የሚሉ የአሁኖቹ እነኚህ በጉልመሳ ላይ የሚገኙ (Emerging) አገራት በተወሰነ ደረጃ እውነት ቢኖራቸውም ፡፡
ለምሳሌ በቻይና ለአየር ንብረት ብክለት ግማሹ ምክንያት የድንጋይ ከሰል ጥቅም ላይ በመዋሉ ምክንያት ነው ፡፡ የድንጋይ ከሰል በወደፊቱ የኢኮኖሚ ዓለም ውስጥ ቦታ እስካለው ድረስ በአየር ንብረት ላይ በካይ መሆኑ ይቀጥላል ፡፡
እንደ ፔሩ ያሉ የላቲን አሜሪካ አገራት በዚህ የሚጎዱ ሲሆን ያላት የአማዞን ደን በከሰል ማክሰል ህገ ወጥ ደን ጭፍጨፋ ደኗን እያጣች ያለችው ይህችው አገር በአለም በሚሊየን ዶላር ህገ - ወጥ ደን ጭፍጨፋን ለመከላከል ወጪ የፔሩን ደን ከጭፍጨፋ ሊያድን አልቻለም ፡፡
በፔሩ በተደረገው ስነ ዓለም ዓቀፍ አየር ንብረትን በተመለከተ በተደረገው ስብሰባ ላይ ለአለም የአካባቢ ሙቀት መጨመር ተጠያቂዎቹ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሃብታም አገራት ነው በሚለው ትችት የተማረሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳሉት ‹‹በአሁኑ ወቅት በአለም ላለው የአየር ንብረት ብክለት ከግማሽ በላይ ተጠያቂዎቹ ታዳጊ አገራት ናቸው›› ብለዋል፡፡   
የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውክሊየር ሱናሚ የሰውን ልጅ የተራቀቀ ቴክሎጂ ባለቤት የመሆንን ተቃርኖአዊ ውጤትን ያሳየ ሆኖ አልፏል ፡፡ ምንም እንኳን የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውከሊየር የሃይል ማመንጫ በጃፓናውያን የተሳራና እጅግ የተራቀቀ ቢሆንም የሰው ልጅ ሊረዳውም ሆነ ሊቋቋመው በማይችለው ሱናሚ ባልተጠበቀ ወቅት በሚመታበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለበት ሰው ሊያውቅና ሊዘጋጅም ባለመቻሉ የደረሰው ውድመት ከባድ ነው ፡፡ የዚህ አይነት ሰው ከሳው ከተራቀቀ ቴክኖሎጂ ጋር አደጋን የሚፈጥሩ ነገሪች ከኒውክሊየር ጦርነት ባልተናነሰ ሁኔታ በአየት ንብረት  ሆነ በራ በሰው ልጅ ህልውና ላይ አደጋም ሊጋርጡ የሚችሉ ናቸው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥም እንዲሁ በራሱ በሰው ልጅ በተራቀቀ ቴክኖሎጂ በሰራው ስራ ሲሆን ነገር ግን የሰውን ለጅም ሆነ የህይወት ያላቸውን ፍጥረታት ህልውና በመገዳደር ላይ ይገኛል ፡፡ 

Ethiopian Eonomy & The Oil Crisis



እ.ኤ.አ በ2014 የነዳጅ ዋና እ.ኤ.አ ከ2009 ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲያዘቀዝቅ እ.ኤ.አ በ2014 ታህሳስ ከ60 ዶላር በታች ሆኖ አዘቅዝቆ ሲያበቃ በጥር 2015 ደግሞ ብሶበት ከ50 ዶላር በታች ወርዷል ፡፡ እንደ ኢራንና ሩስያ ያሉ የመንግስታቸውን ባጀት በከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ላይ የሚመሰረቱ ሲሆን ባጀታቸውን ለመሸፈን ሩስያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ 100 ዶላር ሲሆን እዳዋን ለመክፈልና ባጀቷን ለመሸፈን ያስችለኛል በሚል አቅዳ የነበረ ቢሆን በዩክሬን ጉዳይ ከምእራባውያን ከባድ የማእቀብ በትር ያረፈባት ሩስያ አሁን ደግሞ የነዳጅ ዘይት ዋጋ ማውረድ የመገበያያ ገንዘቧ ከዶላር አንፃር ያለው የምንዛሬ ዋጋ እ.ኤ.አ በ1998 ዓ.ም. ለአይ ኤም ኤፍ እዳ መክፈል አቅቷት በነበረው ደረጃ ደረጃ አቆልቁሎባታል ፡፡
የሩስያ ማእከላዊ ባንክ በአንዴ የወለድ ምጣኔውን ወደ 17 በመቶ ከፍ በማድረግ የገንዘብ ምንዛሬዋን ከመቀነስ ለመታደግ ሞክራለች ፡፡ ነገር ግን የነዳጅ ዋጋ እስከወረደ ድረስ የሩብል የምንዛሬ ዋጋም እየቀነሰ ነው የሚሄደው ፡፡ በዚህ አመት የሩስያ ሩብል በ45 በመቶ ከአሜሪካ ዶላር አንፃር ዋጋው ወርዷል ፡፡ ቭላድሚር ፑቲን ሩስያን በየልሲን ጊዜ ከነበረው ቀውስ ያወጡ ቢሆንም ፣ የምእራባውያንን ማእቀብ ‹‹ህገ ወጥና ወደ አንድ ወገን ያደላ ነው›› ቢሉም የልሲን ገብተውበት ወደ ነበረው አይነት ቀውስ ሩስያ እያመራች ይመስላል ፡፡
ቬንዙዌላ እዳዋን በአብዛኛው ቻይና ላይ ያላትን መክፈል ያቅታታል ሲባል በአንፃሩ ግን በአፍሪካ ባሉ አገራት ግን የባጀት ጫናቸውን ሲቀንስላቸው የቻይና ምጣኔ ሀብት  ይቀዘቅዛል፡፡ ማዳበሪያ ፣ የኬሚካልና የላስቲክ ፋንብሪካዎች የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የመሳሰሉት ነዳጅ ዘይትን የሚጠቀሙ ሁሉ የነዳጅ ዋጋ መውረድ የምርት ዋጋቸውን ይቀንስላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  
እንደ ሩስያ ሁሉ በነዳጅ ዋጋ መውረድ ከማእቀብ ጋር የተደራረበባት የኢራኑ መሪ ሩሀኒ በበኩላቸው የነዳጅ ዋጋ መውረድ ‹‹በሙስሊሙ ዓለም ላይ የሚደረግ ሴራ ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከኦፔክ አገራት 700 ቢሊዮን ዶላር ተቀማጭ ያላቸው ሳኡዲዎች የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ እስከ 55 ዶላር ዝቅ ቢል ለተወሰነ ጊዜ መቋቋን ይችላሉ ፡፡ ነገር ግን ለሌሎቹ ነዳጅ አምራች አገራት ግን ጉዳዩ የህልውና ጉዳይ ነው ፡፡
በአለም የነዳጅ ዋጋ ሲወድቅ በአለም የኢመርጂንግ የተባሉት አገራት የገንዘብ ምንዛሬም አብሮ ዘጭ ማለት መጀመሩ ሌላው የሚታይ ሃቅ ሲሆን እንደ ኢንዶኔዢያ ፣ ናይጄሪያና ያሉት አገራትም የዚህ የዋጋ ቅነሳ ሰለባ ሆነዋል፡፡
ኦፔክ የዋጋ መውረዱን ተከትሎ የቀን ምርቱን ከ2 ሚሊየን በርሜል በታች ሲቆርጥ ፣ ሜክሲኮም ሆነች ራሺያ በበኩላቸው እንቀንሳለን ሲሉ የሼል ቡም በአሜሪካ ሲመነጭ የኦፔክ አገራት የምርት አቅርቦታቸውን ቢቆርጡም የኦፔክ አባል አገራት ያልሆነው የሰሜን አሜሪካ ግን ምርቱ ስለሚጨምር ዋጋ ዝቅ ባለበት ሁኔታ የኦፔክ አገራት ምርትን መቀነስ ይበልጥ ይጎዳቸዋል እንጂ አይጠቅማቸውም ፡፡ የሼል ክል ጋዝ መገኘትን ተከትሎ ነዳጅ ላኪ የሆኑ የኢፔክ አገራት 305 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ያደርስባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ ሼል ነዳጅን ማምረት መጀመሩ የአሜሪካ ምርት በሶስት አመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ሲባል በአለም ከፍተኛ የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር አስችሏል፡፡
ዝቅ ያለ የነዳጅ ዋጋ እድገትን ያነቃቃል ወይስ አያነቃቃም የሚለው መሰረታዊ የምጣኔ ሀብት ጥያቄ ነው ፡፡ ያሰነ የነዳጅ ዋጋ በነዳጅና በአማራጭ የሃይል አቅርቦት ላይ ያለውን የመዋእለ ንዋይ እድገትን ይገታል ፡፡ እንደ የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅ አባባል ግን ዝቅተኛ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በሹፌሮች እና በዜጎች እጅ የሚገባውን ገንዘብ ከፍ በማድረግ ኢኮኖሚውን ያነቃቃል የሚል አስተሳሰብ አለው ፡፡

በአለም ዙሪያ የአክስዮን ገበያዎችና የገንዘብ ምንዛሬዎችንም መቀነስ ጀምረዋል ፡፡ በተለይም ነዳጅ ላኪ ሃገራት አክስዮን ገበያቸውና የመገበያያ ገንዘባቸው የምንዛሬ ዋጋም እንዲሁ መውረድ መታየቱ ግልፅ ነው ፡፡  የነዳጅ መወደድ አገራት ታዳሽና አረንጓዴ በሆኑ ምርቶች ሃይልን ለማምረት ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ ፍሰት እንዲያደርጉ በማድረጉ የፀሀይን ፣ የንፋስን ሃይል በመጠቀም ሃይል ለማመንጨት ከፍተኛ ፣ምርምርና ኢንቨስትመንት እየፈሰሰ ይገኛል ፡፡ የነዳጅ ዋጋ በሚረክስበት ጊዜ ግን ይህንን ምርመር ሊገታው ይችላል የሚል የኤክስፐርቶች ግምት አለ፡፡ 

ፍራኪንግም (Fracking) ቢሆን ከምንም እንከን የፀዳ አይደለም ፣ የሚጠቀመው በጣም ብዙ ውሀ በአካባቢው የውሀ እጥረትን በመፍጠር ለግብርና ምርት ማምረትን አስቸጋሪ ሲያደርገው እንዲሁም ከዘይት ጋር ተቀላቅለው የሚለቀቁት በካይ ኬሚካሎች የውሀ መበከልና የበዛ የውሃ እጥረትንና የከርሰ ምድር ውሃ መመናመንና መበከልን አደጋን ጋብዟል ፡፡ ነዳጅ ብዙ ውሀን እየበከለ ሲሆን እንደ ካሊፎርኒያ ባሉ ክፍልሀተ አገራት በፍራኪንግ መንገድ ነዳጅን ማውጣት ነዳጅ የበለጠ ሃይል ሲሆን ነዳጅና ውሀ መቀላቀላቸው ለግብርና አደጋን ጋርጧል ፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥን እንዲሁም ብክለትን ያስከትላል የሚባለው ይሄው ፍራኪንግ ነው ፡፡ 

በአለም ዙሪያ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት የተጀመረ ሲሆን ፣ የንፋስ ሃይልን በመጠቀም ኤሌክትሪክን ማመንጨትም ተጀምሯል ፡፡ የኤሌክትሪክ መኪናዎች በአውሮፓ በአሜሪካና በጃፓን ወደ ስራ መግባት ሲጀምሩ ከዚያም አልፎ ሃይድሮጅንን ከውሀ ጋር በመቀላቀል ሀይልን ማመንጨት እጅግ የረቀቀ ቴጀኖሎጂን በመጠቀም መኪኖች ስራ መስራት ሲጀምሩ በነዳጅ ላይ ያለውን ፍላጎት እየቀነሰው እንደሚሄድና ነዳጅ እንደ ቀድሞው ብቸኛው የሃይልን ምንጭ መሆኑ እያበቃ መሆኑን መገመት ይቻላል ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በርካሽ የሃይል ምንጭ ፍለጋ ምክንያት የእርሻ መሬቶች የሸንኮራ አገዳን ለማምረት ኢታኖልን ለማምረት በሚል የምግብ ፣ምርት ይመረትባቸው የነበሩ የእርሻ መሬቶች ወደ ሃይልን ይሰጣሉ የሚባሉ ምርቶችን ለማምረት መዋል መጀመራቸው ራሱ ለአለም የምግብ ዋጋ መናር አንዱ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል ፡፡ በዚህም ምክንያት ምጣኔ - ሀብቱን ለማንቀሳቀስ ሃይልን የተራበው የዓለም ምጣኔ ሀብት የምግብ ማመረቻ መሬቶችን ወደ የሃይል ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉ ሰብሎችን ለማምረት መዋሉ ምክንያት የደኖች መመንጠርና የምግብ እጥረት እንዲባባስ ያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ታዳሽ የሆኑ የሃይልም ምንጮችን መጠቀም ለአለም ምጣኔ ሀብት እድገትና ለምግብ ዋጋ መረጋጋት አስፈላጊ ነው ፡፡  

ምእራባውያን እ.ኤ.አ ከ1973 የነዳጅ ቀውስ ወዲህ በነዳጅ ላይ ያላቸው ጥገኝነት ለምጣኔ ሀብትም ሆነ ለስትራቴጂያዊ ስጋት ውስጥ እንደከተተቻው ይረዱታል ፡፡ በተለይም አብዛኛው የአለም ነዳጅ የሚመረተው በመካከለኛው ምስራቅ መሆኑና አካባቢውም በወታደራዊ ስጋትና በጦርነት ፣ በሃይማኖት ግጭት የሚታመስ ሲሆን አቅርቦቱ በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥና የአለም ኢኮኖሚ ሊናጋ ይችላል የሚለው ስጋት በምእራባውያን ፖሊሲ አውጪዎች ዘንድ ለአስርት አመታት ሲጉላላ የቆየ ጉዳይ ነው ፡፡

 ከመካከለኛው ምስራቅ ውጪም ቦሆ ቢሆን ያለው የነዳጅ አምራች አገራት የሆኑት እንደ ናይጄሪያ ፣ ቬንዙዌላና ሩስያም ቢሆኑ ለአሜሪካ እሚመቹ አገራት አይደሉም ፡፡ ሩስያ የተፈጥሮ ጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧውን ሲዘጋ ፣ በናይጄሪያ ቦኮ ሀራም በሚፈጥረው የእርስ በእርስ ጦርነትና ፣ የጋዝ ማስተላለፊያ ሲፈነዳ ፣  በቬንዙዌላም እንዲሁ እንደ ሁጎ ቻቬዝ ያለ ጠንካራ መሪ ወደ ስልጣን ሲመጣ ከአሜሪካ ጋር ውዝግብ ውስጥ ሲገባ አሜሪካ ጠብታ ነዳጅ አታገኝም ብሎ ሲያስፈራራ በመሳሰሉት ምክንያቶች አብዛኛው የአለም የነዳጅ ምንጭ የሚገኝበት አካባቢ በስጋት የሚታመስ ስለሆነ ነዳጅን ለምጣኔ ሀብት ህልውናቸው ሲል ለሚፈልገው በኢንዱስትሪ የበለፀገው የምእራቡ አለም ነዳጅን በሚመለከት ጉዳይ በስጋት ሲናጥ መኖሩ እርግጥ ነው ፡፡ በዚህ የተማረሩት ምእራባውያን ለአስርት አመታት በነዳጅን በሌላ የሃይል ምንጭ ለመተካት ያልተቋረጠ ምርምር ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ይህ ምርምራቸው የኋላ ኋላ ውጤት እየሰጠ የመጣ ይመስላል ፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሮሀኒ በእ.ኤ.አ 2014 ዓ.ም. በታየው የነዳጅ ዋጋ መውረድ አለም አቀፋዊ ሴራ አለበት ያሉት የተወሰነ እውነትነት አለው፡፡ ሳኡዲ አረቢያና አሜሪካ በዚህ ሴራ ውስጥ ዋነኞቹ ተዋንያኖች ናቸው ፡፡ ነዳጅ ለፖለቲካ አላማን ለመሳካት ሲውል ይህ የመጀመሪያው አይደለም ፡፡ በእ.ኤ.አ በ1973 ዓ.ም የግብፁ መሪ የነበሩት አንዋር ሳዳት ከሳኡዲ አረቢያ ጋር የነበራቸውን የተቀራረበ ግንኙነትን በመጠቀም ነዳጅ ላኪ የሆኑ የአረብ አገራት የነዳጅ ምርታቸውን ለመቀነስ በወቅቱ ከእስራኤል ጋር ገብተውት የነበረውን ጦርነት እስራኤልን ያግዙ የነበሩትን አሜሪካንና ከአውሮፓን ከሆላንድ ጋር ለመቅጣት የነዳጅ አቅርቦት አለም በቀነሰበት ወቅት አሜሪካ፣ አወሮፓና ጃፓን ችግር ውስጥ ገብተው የነበረ መሆኑ ይታወሳል ፡፡ 

የአሁኑ ግን ሳኡዲ አረቢያና አሜሪካ ሩስያን ለመቅጣት ሳኡዲ በበኩሏ ሩስያ የኣሳድን መንግስት በመደገፏ ምክንያት እንዲሁም የአሳድ መንገግስት ኳታርንና ሳኡዲ አረቢያን ለመጣል የነዳጅና የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧን ከኢራን በኢራቅ አቋ  ርጦ የሶርያ ወደቦችን በመጠቀም በሜዲተራኒያን ባህር በኩል ለአውሮፓና ለአለም ገበያ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ለማቀቅረብ በ10 ቢሊን ዶላር ወጪ የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ ለመገንባት አቅዶ የነበረ ሲሆን በዚህም ጥርሳቸውን የነከሱት ኳታርና ሳኡዲ አሳድን ለመጣል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ፡፡ ይህ ፕሮጀክት ቢሳካ ኖሮ የሺአዎቹ በአለዋይት ሺአ የምትመራው ሶርያ ፣ በኢራቅ በብዙሀኑ ሺአዎች በምትመራው ኢራቅ በሺአይቱ ኢራን መሀከል የሺአን የኢኮኖሚ የበላይነት በሳኡዲና በኳታር ኪሳራ ሊሳካ ይችል የነበረ መሆኑ ያልጠፋቸው መሆኑ ገልፅ ነው ፡፡

ሩስያ የአሳድን መንግስ መደገፏ እንዲሁም በዩክሬን ላይም ያሳረፈችው ተፅእኖ ሃያላኑ በበኩላቸው በሩስያ ላይ ያላቸው የቂም ቋጠሮ ነው ፡፡ ሩስያ በሶርያው የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት ከኣሳድ መንግስት ጋር የጋራ አቋምን በመያዟ ምክንያት እንዲሁም አሜሪካ ሶርያን ልትደብድብ በነበረበት ወቅት ያንን ድብደባ በማስቆሟ ምክንያት እና በሩስያ ላይ ቂም ክፉኛ የቋጠረችው አሜሪካ በዩክሬን ሰበብ ሩስያ ላይ ጫን ያለ ማእቀብን የአውሮፓ አጋራሮቿን አስተብባብራ አስጥላባታለች ፡፡ ውሎ አድሮ ራሳቻው አውሮፓውያን ማእቀቡ ትርጉም የለውም ማለት ቢጀምሩም እንደ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኦሎንድ በሩስያ ላይ የተጣለቸው ማእቀብ ትርጉም አልባ ነው ሲሉ እንደ የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርልክል በበኩላቸው ደግሞ ማእቀቡ ሩስያን ሊነጥልና እንዲሁም በሩስያ ማህበራዊ ቀውስን ሊያስከትልና ያም  ቀውስ ደግሞ ለአውሮፓ ሊተርፍ ይችላል የሚል ስጋት አሳድሮባቸዋል ፡፡ አሜሪካ ግን በሩስያ ላይ አምርራለች ማእቀቡ እንዲላላም ሆነ እንዲነሳ ፍላጎት ያላት አትመስልም ፡፡ 
በነዳጅ መላክ ላይ የተደገፈው የሩስያ ኢኮኖሚ የዛሬ ሃያ አምስት አመታት በፊት ከነበረው ግብርናዋም ሆነ ኢንዱስትሪዋ ያልዘመነ በመሆኑ ኢኮኖሚዋ በነዳጅና በተፈጥሮ ጋዝን በመላክ ላይ ጥገኝነቱ ምንም ያህል ባለመሻሻሉ ምክንያት የነዳጅ ዋጋ መውደቅ ሩስያን ክፉኛ ጎድቷል ፡፡ የሩስያው ፕሬዝዳንት ከዚህ ቀውስ ቀደም ብሎ በአንድ ወቅት ለታይም መጽሄት በተሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ የሩስያ ኢኮኖሚ ከቦሪስ የልሲን ስልጣን መልቀቅ በኋላ በፑቲን የስልጣን ዘመን ያንሰራራው በነዳጅ ዋጋ በአለም ያለው ዋጋ መናር ስለሆነ ነው ተብለው በተጠየቁበት ወቅት የሰጡት መልስ ‹‹ቀንና ሌሊት ለፍተን ሰርተን›› ነው የሚል ነበር ፡፡ 

ነዳጅ ዘይት ውድ በነበረበትና ከአንድ መቶ ዶላር አልፎ በነበረበት ወቅት ነዳጅ ላኪ አገራት ያከማቹት ዶላር ለዚህ የችግር ጊዜ ይረዳቸዋል ተበል ቢታሰብም ከሳኡዲ አረቢያና  ከአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ ኤሚሬት አገራት በስተቀር የተቀሩት እንደ ሩስያ ፣ ናይጄሪያና ኢራን ያሉት ግን ክፉኛ ይጎዳሉ ፡፡ ወደ 900 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ሃገር ተቀማጭ ገንዘብ ያላት ሳኡዲ አረቢያ የነዳጅ ዋጋ እንኳን ከስልሳ ዶላር በታች ቀርቶ ሃያ ዶላርም ቢሆን የምትጎዳ የማትመስለው ሳኡዲ አሳድንና የአሳድ ደጋፊ የሆነችውን ሩስያን እስከጎዳ ድረስ የአለም ገበያን በነዳጅ ለማጥለቅለቅ የወሰነች ይመስላል ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን የነዳጅ ምርታቸውን መጨመር ነዳጅ ላኪ ሃገራትን የሚጎዳ ሲሆን የዋጋው መውረድ ግን ይበልጥ ተጎጂ ያደርጋቸዋል ፡፡     

The Prophet



ነቢይ


የአሲሪያውያና ዋና ከተማ የነበረችው ነነዌ ከታሪክ ገጽ እንደምጥትጠፋ በመጽሃፍ ቅዱስ ተንብዮአል ፡፡ የነነዌ አሸናፊዎች እነ ልክ እነርሱ እንዳደረጓቸው ያደርጓቸው ፡፡አሲሪያ እን አንድ አገርን ስትማርክ ህዝቡን ታሰቃይና ደማቸውን ታንዠቀዥቅ ነበረ ፡፡ ደማቸው በሜዳውና በወንዙ ይፈስ ነበረ ፡፡ ነነነዌ በጎርፍ ፣ በእሳትና በጦር ትሸነፋለች ብሏል ፡፡ እኛ የዓለም ሃያካነብላን ነን ማን ያሸንፈናል ፡፡ 1500 የግንብ አጥሮች በርካታ ከተሞች ፣ በርካታ ከተሞች ብርከታ መቤተመፅሀፍት ፣ ምሽጎች ለሃያ አመታት የሚያዋጋ ምሽግን አዘጋጅተው የነበረ ሲሆን ፡፡ በጎርፍ ወራት የጎፉን አወራደረድ የቀየሩት ሲሆን በክሮኒክል መፅሀፍ ላይ አለ ፡፡ ንጉሱን ከእነ እቁባቶቹ ህዝቡ ሲያቃትላቸው እንዳይማርኩ አቃጥሏቸዋል፡፡ ‹‹ክፉም ቢሆን ወደ ፍርድ ያመጣዋል›› መክ 12፣14

የነነዌ ውድቀት አይቀሬ ነው ብሏቸዋል ፡፡ ትንቢተ ናሆም 612 ቢሲ 1824 በአርኪዎሎጂ እስሚገኙ ድረስ ተቀብረው ቆይተዋል ፡፡

ማህተመ ጋንዲ ‹‹ልክ ነገ እንደምትሞት ተደሰት ፣ ዘላለም እንደምትኖር እውቀትን ፈልግ›› ፡፡ ይሁን እጂ ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹የዚህ አለም ጥበብ በእግዝአብሄር ፊት ሞኝነት ነው›› 1ኛ ቆሮንጦስ ምእራፍ 3፣ ቁ 19፣20 ፡፡

  ነቢይ በሃገሩ አይከበርም የማርቆስ ወንጌል ምእራፍ 6 ላይ ‹‹ይህ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሃገሩ መጣ ደቀመዛሙርቱም ተከተሉት ፤ ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኩራብ ያስተምር ጀመር ብዙዎቹ ሰምተው ተገረሙና ፡- እነዚህን ነገሮች ይህ ከየት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት ? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው ? ይህስ ፀራቢው የማርያም ልጅ የያእቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምኦን ወንድም አይደለምን ? እህቶቹስ በዚህ በኛ ዘንድ አይደሉምን ? አሉ ይሰናከሉበትም ነበር ፡፡ እየሱስም መልሶ ፡- ነቢይ ከገዛ ሃገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው ፡፡ በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር ፣ ተአምር ሊያደርግ አልቻለም፡፡ ስለአለማመናቸውም ተደነቀ ›› በዚሁ ምእራፍ በቁጥር 10 - 12 ድረስ ደግሞ የሚከተለውን ይላል ፣
‹‹በማናቸውም ስፍራ ወደ ቤት ብትገቡ ከዚያ እስከተክትወጡ ድረስ በዚያው ተቀመጡ ፡፡ ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባችው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ፡፡ እውነት እላችኋለሁ ፣ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል አላቸው ››