Friday, February 6, 2015

The Prophet



ነቢይ


የአሲሪያውያና ዋና ከተማ የነበረችው ነነዌ ከታሪክ ገጽ እንደምጥትጠፋ በመጽሃፍ ቅዱስ ተንብዮአል ፡፡ የነነዌ አሸናፊዎች እነ ልክ እነርሱ እንዳደረጓቸው ያደርጓቸው ፡፡አሲሪያ እን አንድ አገርን ስትማርክ ህዝቡን ታሰቃይና ደማቸውን ታንዠቀዥቅ ነበረ ፡፡ ደማቸው በሜዳውና በወንዙ ይፈስ ነበረ ፡፡ ነነነዌ በጎርፍ ፣ በእሳትና በጦር ትሸነፋለች ብሏል ፡፡ እኛ የዓለም ሃያካነብላን ነን ማን ያሸንፈናል ፡፡ 1500 የግንብ አጥሮች በርካታ ከተሞች ፣ በርካታ ከተሞች ብርከታ መቤተመፅሀፍት ፣ ምሽጎች ለሃያ አመታት የሚያዋጋ ምሽግን አዘጋጅተው የነበረ ሲሆን ፡፡ በጎርፍ ወራት የጎፉን አወራደረድ የቀየሩት ሲሆን በክሮኒክል መፅሀፍ ላይ አለ ፡፡ ንጉሱን ከእነ እቁባቶቹ ህዝቡ ሲያቃትላቸው እንዳይማርኩ አቃጥሏቸዋል፡፡ ‹‹ክፉም ቢሆን ወደ ፍርድ ያመጣዋል›› መክ 12፣14

የነነዌ ውድቀት አይቀሬ ነው ብሏቸዋል ፡፡ ትንቢተ ናሆም 612 ቢሲ 1824 በአርኪዎሎጂ እስሚገኙ ድረስ ተቀብረው ቆይተዋል ፡፡

ማህተመ ጋንዲ ‹‹ልክ ነገ እንደምትሞት ተደሰት ፣ ዘላለም እንደምትኖር እውቀትን ፈልግ›› ፡፡ ይሁን እጂ ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹የዚህ አለም ጥበብ በእግዝአብሄር ፊት ሞኝነት ነው›› 1ኛ ቆሮንጦስ ምእራፍ 3፣ ቁ 19፣20 ፡፡

  ነቢይ በሃገሩ አይከበርም የማርቆስ ወንጌል ምእራፍ 6 ላይ ‹‹ይህ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሃገሩ መጣ ደቀመዛሙርቱም ተከተሉት ፤ ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኩራብ ያስተምር ጀመር ብዙዎቹ ሰምተው ተገረሙና ፡- እነዚህን ነገሮች ይህ ከየት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት ? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው ? ይህስ ፀራቢው የማርያም ልጅ የያእቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምኦን ወንድም አይደለምን ? እህቶቹስ በዚህ በኛ ዘንድ አይደሉምን ? አሉ ይሰናከሉበትም ነበር ፡፡ እየሱስም መልሶ ፡- ነቢይ ከገዛ ሃገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው ፡፡ በዚያም በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ከመፈወስ በቀር ፣ ተአምር ሊያደርግ አልቻለም፡፡ ስለአለማመናቸውም ተደነቀ ›› በዚሁ ምእራፍ በቁጥር 10 - 12 ድረስ ደግሞ የሚከተለውን ይላል ፣
‹‹በማናቸውም ስፍራ ወደ ቤት ብትገቡ ከዚያ እስከተክትወጡ ድረስ በዚያው ተቀመጡ ፡፡ ከማይቀበሉአችሁና ከማይሰሙአችሁ ስፍራ ሁሉ ከዚያ ወጥታችሁ ምስክር ይሆንባችው ዘንድ ከእግራችሁ በታች ያለውን ትቢያ አራግፉ፡፡ እውነት እላችኋለሁ ፣ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ በፍርድ ቀን ይቀልላቸዋል አላቸው ››

No comments:

Post a Comment