Friday, November 16, 2018

ኢሳ

የጉዋጉዋሁለት ውጋጋን ፤
ታላቅ ፍርሃት አሳደረብኝ ፤
ልቤ ተናወጠ ፣ ፍርሃት አንቀጠቀጠኝ።
ትንቢተ ኢሳያስ 21፥4

የጉዋጉዋሁለት ውጋጋን ፤
ታላቅ ፍርሃት አሳደረብኝ ፤
ልቤ ተናወጠ ፣ ፍርሃት አንቀጠቀጠኝ።
ትንቢተ ኢሳያስ 21፥4

Wednesday, November 14, 2018

የክሩስቸቭ ቀልዶች

ይህ እንግዲህ በየቴሌቭዥኑ ይሄ ሁሉ ጄኔራልና ኮሎኔል ሜቴክ እንደዚህ አድርጎ ፤ ጄኔራል ክንፈ እንዲህ ብሎ ሲሉ ፥ የት ነበሩ እኝህ ሁሉ ሰዎች አትሉም ጎበዝ። 

ይሄ ሁሉ ወፈ ሰማይ ጄኔራልና ኮሎኔልና የመንግስት ሹማምንት ሁላ በቲቪ እየቀረበ "ሜቴክ እንዲህ አድርጎ ፥ ክንፈ ዳኜ እንዲህ ብሎ " ፤ ጄኔራሉ በድፍረት ጨረታ አናደርግም ሲል እንኩዋን ለምን ያለ ጋዜጠኛ ኣልነበረም
ዋልታ ቴሌቭዥን ሜቴክ ላይ ሲወርድበት ሳይ አንድ የቀድሞዋ የሶቭየት ህብረት ቀልድ ትዝ አለኝ ፦

የቅድሞዋ ሶቭየቱ አምባገነን ጆሴፍ ስታሊን እ.ኤ.አ በ53 ኣ.ም  ከሞተ በሁዋላ ፥ በእግሩ የተተካው ክሩስቼቭ በስብሰባ ላይ በስታሊን ዘመን የተፈጸሙትን ግፎችንና ወንጀሎችን ይዘረዝራል።

ከመሃከላቸው አንዱ " ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈጸም አንተ የት ነበርክ !! " አለው ድምጽን ከፍ አድርጎ።
ክሩስቼቭም የሰውየውን ማንነት መለየት ስላልቻለ እርሱም መልሶ "ማነው ይህን ያለው? " ሲል ጉባኤተኞቹን በተራው መልሶ ያፋጥጣል። በዚህ ግዜ ለክሩስችቭ መልስ እሚሰጥ ጠፋ ሁሉም ጸጥ ጭጭ አሉ ፥ ደፍሮ መልስ እሚሰጥ ጠፋ ፤ ከእነርሱ መሃል አንዳቸውም መልስ ለመስጠት አልደፈሩም ።

ከአፍታ ቆይታ በሁዋላ ........
ክሩስቼቭም እሚመልስ እንደሌለ ካየ በሁዋላ መልሶ " አያችሁ ያኔም እንደዚህ ነበር የሆነው " አላቸው።

Monday, November 12, 2018

የደራሲዎች ተሞክሮ

ለጀማሪ ጸሃፍት ፦

1) አንባቢዎችህን አሳንስህ አትገምት
never underestimate the audience /the readers

አንድ በፌስ ቡክ እምትፅፍ ጉዋደኛዬ አንዳንድ ግዜ ከእውነታው እያወቀች መረጃን ታሰራጭ ነበር። እና አንባቢዎች ራሳቸው እምትፅፊውን አታውቂም አሉኝ አሉኝ ነበረ። ለምን እውቀቱ እያላት ግን ከእውነቱ ስለተፋታች ነው። 

2) በስፋት አንብብ ፦ ስለምትፅፈው ጉዳይ አቅምህ በፈቀደው መጠን ሰነዶችን አገላብጠህ አንብብ። አቅምህ በፈቀደው መጠን የተሻለ መረጃና ጠለቅ ያለ እውቀት ይኑርህ

3) አትዋሽም አታዳላም እውነቱን ለማስቀመጥ ጣር። የአድልኦ እንደዚሁም እውነቱን የማምታታት ስራን አትስራ። ይህ በአሁኑ ሰአት በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት እየታየ ነው።

4) በቂ የቃላት ፥ የምሳሌያዊና የፈሊጣዊ አነጋገር እውቀት ይኑርህ። ይህ ሃሳብን ሰፋ አድርጎ በበቂ ለመግለፅ የበርካታ ቃላትንና ትርጉማቸውን ማወቅ ይረዳል።

Sunday, November 11, 2018

ህገ መንግስት ማሻሻል አስፈላጊነት Ethiopian constitution reform or Amendment

የህገ መንግስት (constitution ) ማሻሻያ ፦

በመጀመርያ የህገ ምንግስት ስለሚሻሻልበት እሚደነግገው አንቀጽ መሻሻል አለበት።   ከዚህም ሌላ የህገ መንግስታዊ ፍ/ቤት ማቃዋቃዋም አስፈላጊ ነው።  ለምሳሌ ህገ መንግስት ተርጉዋሚ ነው የተባለው የፌ/ምቤት ክህግ ባለሙያዎች ይልቅ በፖለቲከኞች የተሞላ ስለሆነ በራያ ወልቃይት ወዘተ... የተነሱትን የማንነት ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ ለአመታት ሲዳፈኑና ሲጉዋተቱ ወደ አመፅ ተቀየረ ጥያቄው። ህገ ምንግስታዊ ፍርድ ቤት ቢሆን ግን ጉዳዩን ከፖለቲካ ገለልተኝነት ውሳኔን ያሳልፍበት ነበረ። 

አንዳንድ ከሰብአዊ መብት አንፃር የተቀመጡት የህገ ምንግስቱ ኣንቀፆች advanced ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ከዘመኑ አንጻር ታይተው ሊሻሻሉ የሚገባቸው ናቸው።
የምርጫ ህጉ ለምሳሌ በ (majority vote) ብቻ አሸናፊው የሚለይበት ሲሆን ይህ የምርጫ ህግ ወደ ተመጣጣኝ ውክልና (proportional voting system )እና ወደ የሁለቱም ድብልቅ የምርጫ ውጤት አሰጣጥ ሊሻሻል ይገባል ተብሎ በአቶ ሃይለማርያም ዘመን ተጀምሮ የነበረ ነው። ግን ይህ ህግ በተቃዋሚዎች የሚጠበቅና መጭው ምርጫ በተሻለ ፍትሃዊ ሊያደርግ ቢችልም አልተሻሻለም።
ህገ ምንግስቱ ውስጥ ገብተው መታሰር ያልነበረባቸው ማለትም የሊዝ ህጉና የምርጫ ህጉ ህገ ምንግስቱ ውስጥ ገብተው ሊቆለፍባቸው አይገባም ነበረ። flexibility የሚጠይቁ ስለሆነ እነኝህ ሁለት ጉዳዮች እንዳስፈላጊነቱ የተወካዮች ም/ቤት እና የክልል ም/ቤቶች አዋጅ እያወጣ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ነበረ።

የፍትህ ስርአቱ ልምሳሌ ህግ ተርጉዋሚው አካል ዳኞችን ፍ/ቤቶች ብቻ መሆን አለባቸው። ይህ የፍትህ አተረጋጎም እስካልተሻሻለ ድረስ የፍትህ ስርአቱን ሪፎርም ተደርጎአል ማለት አይቻልም የፌደራል ስርአቱ ለገባበት አጣብቂኝ አንዱ መፍትሄው የህግ ምንግስታዊ ፍ /ቤት ማቁዋቁዋም ነው። 

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ ፦

ሕገ መንግሥት አንቀጽ 47 መሠረት ማንኛውም በአገሪቱብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ የራሱን ክልል የመመሥረት መብት አለው፡፡ በዚህ አንቀጽ መሠረት ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆነው የክልል መመሥረት ጥያቄው በብሔሩ፣ ብሔረሰቡ፣ ወይም ሕዝቡ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ማግኘቱ ሲረጋገጥና ጥያቄው በጽሑፍ ለክልል ምክር ቤት ሲቀርብ፣ ጥያቄው የቀረበለት ምክር ቤት ጥያቄውን በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለጠየቀው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ ሲያደራጅ፣ ክልል የመመሥረት ጥያቄው በብሔሩ፣ ብሔረሰቡ ወይም ሕዝቡ ሕዝበ ውሳኔ በአብላጫ ድምፅ ሲደገፍና የክልሉ ምክር ቤት ሥልጣኑን ለጠየቀው ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ ሲያስረክብ እንደሆነና ይህ አዲሱ ክልል የፌዴራል መንግሥቱ አባል እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡

የበርካታ ዞኖች ክልል የመሆን ጥያቄ ምላሽን ይጠይቃል ። ይህ ግን የተዘጋውን pandora box መክፈት ይሆናል። ይሁንና ማንም በቀላሉ እንደሚረዳው የ87 ኣ.ም. ህገ መንግስት ሲፀድቅ ህዝብ ተወያይቶበት ስላልነበረና በርካታ የአተረጉዋጎም  ክፍተቶችና ብዙም የማያራምዱ አንቀፆች የበዙበት ስለሆነ ዶ/ር አብይን ጨምሮ ፖለቲከኞቹም ይህን የፓንዶራ ሳጥን ከፍተው ራሳቸውን ጣጣ ውስጥ መጨመር አይፈልጉም።
ሲጀመርም ያለበቂ የህዝብና የምሁራን ክርክር ያልተደረገበት ከሰብአዊ መብቶች መከበር እውቅና ከመስጠቱ ውጭ አንቀፅ 39ን ጨምሮ አወዛጋቢ በሆኑ አንቀፆች የተሞላ እንደመሆኑ በስልጣን ላይ ያሉ ይህን ህገ መንግስት መነካካት አይፈልጉም። ይሁንና ባገር ደረጃ ግን ህገ መንግስት ማሻሻያን እሚፈልጉ ጉዳዮች ካልተሻሻሉ በስተቀረ የማያባራ ግጭትንና ውዝግብን ሲፈጥሩ መኖራቸው አይቀርም። ለምሳሌ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ብሐዋሳ ከተማ ተደጋጋሚ ረብሻ ሲፈጠር በመጨረሻ ሲዳማ ዞን የክልልነት መብትን እንዲጠይቅ ፈቃድ ሰጠ ። የቱሪስት መስህብ የሆነችው ውቢቱዋ ሐዋሳ ስትረበሽ ፥ቱሪስት መቅረት ሲጀምር በተደጋጋሚ ጉዳዩ ፌደራል መንግስቱን ሲያስጨንቅ ሆነ የክልሉን መንግስት እንዳሳሰበ ግልፅ ነው።

ለባቢሎን ንጉስ የቀረብ ምልጃ ፦

ለባቢሎን ንጉስ የቀረብ ምልጃ ፦

ያለም ጭቁን ህዝቦች ፥
ያለም ዳኛና ፖሊስ እኔ ነኝ ፥
ወደሚለው የባቢሎን ንጉስ ዘንድ ፥
አቤቱታቸውን ይዘው ቀረቡ ፥

የአለም ፖሊስና ዳኛ እኔ ነኝ
ብልሃል አሉ።
"የአለም ፖሊስና ዳኛ ፥
አንተ ነህ ተብሎል ፥
ለዚህ ነው አቤቱታችንን
ወዳንት ይዘን የቀረብነው ፥ " አሉት።

እርሱም ጥያቄያቸውን በአንክሮ ፥
ካዳመጠ በሁዋላ ምላሹን ፥
እንደሚከተለው ሰጠ ፦

የባቢሎን ንጉስ የሰጠው ምላሽ ፦

እባቢሎን ንጉስ ዘንድ ሄደው ከሰሱት ፥
አንተ በላያችን ላይ የሾምክብን ገዢያችን ፥
ሰዋዊ መብታችንን አይጠብቅልንም ፥
ሲፈልግ ያስረናል ፥ ሲፈልግ ይገድለናል ፥
ሃብታችንና መሬታችንን ዘርፎ አዘረፈነ ፥
ያሻውን እያደረገብን ነው።
የአለም ፖሊስና ዳኛ እኔ ነኝ ፥
ብልሃል አሉ ለዚህም ነው ወዳንተ ፥
የመጣነው ሲሉ ክሳቸውን አሰሙ ፥
የባቢሎኑ ንጉስም ባለጉልላታም ከሆነውና ፥
ሃጫ በረዶ ከሚመስለው ቤተመንግስቱ ፥
ምላሽ ሊሰጥ ብቅ አለ።

እርሱም ዘውድ አለመድፋቱና ፥
በእጁ በትረ ሙሴን ካለመያዙ በስተቀረ ፥
ከፈርኦንና ከቄሳር የተለየ አልነበረም።

እርሱም ሲመልስ እንዲህ አለ ፦
እርግጥ ነው ያደረሰባችሁን በደል፥
ሰምቻለሁ ፥ አውቃለሁም ፤
ነገር ግን የኔን ጥቅም ለማስከበር፥
የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ፥
ለዚህ ነው ያደረገባችሁን አይቼ ፥
እንዳላየ የሆንኩት ሲል ፥
ጀነን ኮራ ብሎ ምላሽ ሰጠ። 

እነርሳቸው የድሆች አገር ሰዎችም ፥
እያለቃቀሱ እንባቸውን ወደ ፥
ሰማይ እየፈነጠቁ ወደ የመጡበት ፥
ተበታተኑ። 

Saturday, November 10, 2018

የባቢሎኑ ንጉስ የሰጠው መልስ ፦

የባቢሎን ንጉስ የሰጠው ምላሽ ፦

እባቢሎን ንጉስ ዘንድ ሄደው ከሰሱት ፥
"ሰዋዊ መብታችንን አይጠብቅልንም ፥
ሲፈልግ ያስረናል ፥ ሲፈልግ ይገድለናል ፥
ሃብታችንና መሬታችንን ዘርፎ አዘረፈነ ፥
ያሻውን እያደረገብን ነው"፥
ሲሉ ክሳቸውን አሰሙ ፥
የባቢሎኑ ንጉስም ባለጉልላታም ከሆነውና ፥
ሃጫ በረዶ ከሚመስለው ቤተመንግስቱ ፥
ምላሽ ሊሰጥ ብቅ አለ።

እርሱም ዘውድ አለመድፋቱና ፥
በእጁ በትረ ሙሴን ካለመያዙ በስተቀረ ፥
ከፈርኦንና ከቄሳር የተለየ አልነበረም።

እርሱም ሲመልስ እንዲህ አለ ፦
"እርግጥ ነው ያደረሰባችሁን በደል፥
ሰምቻለሁ ፥ አውቃለሁም ፤
ባካባቢያችሁ እንደሱ ታማኝ አገልጋይ የለኝም ፥
ነገር ግን የኔን ጥቅም ለማስከበር፥
የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ፥
ለዚህ ነው ያደረገባችሁን አይቼ ፥
እንዳላየ የሆንኩት ሲል ፥"

ጀነን ኮራ ብሎ ምላሽ ሰጠ። 

እነርሳቸው የድሆች አገር ሰዎችም ፥
እያለቃቀሱ እንባቸውን ወደ ፥
ሰማይ እየፈነጠቁ ወደ የመጡበት ፥
ተበታተኑ። 

the Republic of plato

"የፕሌቶ ሪፐብሊክ"  ፦

የፕሌቶ ሪፕብሊክን ለመረዳት የሙሴን ህግጋትን ጠንቅቆ መረዳትን ይጠይቃል። ምእራባውያን ከፕሌቶ ሃሳቦች መውጣት አይቻልም ብለው እጅግ ሰፊ ቦታን የሚሰጡት ሲሆን ፥ የምእራቡ ዓለም ፍልስፍና መሠረትም ነው።
ፕሌቶ በሪፐብሊኩ Republic በሚለው ሁነኛ classic ስራው ለሙታን መናፍስቶች አክብሮት መስጠትና ፀሎት ማድረግ ተገቢ ነው ባይ ነው፦ ከሙሴ ህግ ተቃርኖውን ማየት ይቻላል ። ፕሌቶ ሪፐብሊክ በሚለው መፅሃፍ እንደ ሙሴ ሁሉ ለወገኖቹ ህግን ይደነግጋል። እንደ ሙሴ ሁሉ Law Giver proohet ልክ ሙሴ በኦሪት ዘሌዋውያንና ዘህልቁ ህግጋትን እንደሚደነግገው ሁሉ ፕሌቶም በሪፐብሊክ ህግን ይደነግጋል።
ክሌመንት አሌክሳንደር እንደሚለው ግሪኮች እውቀት ከአይሁዳውያን  "በዝርው የቃረሙት ነው " ባይ ነው። ይህም እውነትነት አለው። 
አብዛኛው የታላቁ ግሪካዊው ሌቶና ሌሎችም ግሪካውያን ስራዎች ከግብፅ ሃይማኖቶች እና ፍልስፍናና ክግብፅ ካህናት አስተዳደራዊ ዘዬዎች የተወረሱ ናቸው።

Friday, November 9, 2018

ያፍሪካ ቀንድ የሃይል አሰላለፍና Ethio -Eritrea ወዳጅነት

የመቶ አመት የቤት ሥራ ስጥቻለሁኝ" ፦

ኢሱ - የኤርትራው ፕ/ት ፦

እውነትም ኢትዮፒያውያን በብሄር ልዩነት እየተባሉ ባለበት በዚህ ሰአት በኢኮኖሚም ሆነ በዲፕሎምሲ ከኢትዮፒያ የምታንሰው ኤርትራ የተሻለ አንድነትና ጥንካሬ ላይ ስትገኝ ኢትዮፒያውያን ግን የመቶ አመቱን የቤት ስራ እንኩዋን ሊጨርሱት ገና የጀመሩት ይመስላል። እርስ በእርስ የመከፋፈሉን የቤት ስራ ተግተው እየሰሩ ይመስላል ።
ኤርትራና አማራ ክልል ስትራቴጂክ አጋር።          ( strategic parthner ) ሆነዋል ይባላል ፥ ምክንያቱም ያማራ ክልልን ግዛቶችን በሃይል ቆርጦ ወደ ራሱ ግዛት የቀላቀለው ወያኔ መሃል ላይ ስላለ የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው ይመስላል።  ህወህት ምናልባት ሊተማመንባት የሚችላት ወዳጄ ሊላት የሚችለው ጎረቤት ሱዳንን ቢሆንም ከእርሱዋ ጋር ድንበርን ቀጥተኛ ወሰንን  አይጋራም። ሱዳንም ብትሆን ከተሸነፈ ወይም እየተሸነፈ ካለ ማጣፊያው እያጠረበት ካለ ሃይል ጋር እምታብርበት የስትራቴጂ ምክንያት አይኖራትም።  በህዳሴው ግድብ ዙርያ ከማእከላዊ ፌደራልና ካማራና ቤንሻንጉል ክልል ጋር እየሰራች ሲሆን ፥ ጎንደር ላይ በተደረገው ስብሰባ ላይ ሱዳን አልተጋበዘችም  ።  ሶማሊያ በተጋበዘችበት በዚህ ስብሰባ ቅርብ ጎረቤት ሱዳን አለመጋበዙዋ ዶ/ር አብይ ህወህትን ለመክብበና ወደ ፌደራል መንግስቱ ፍላጎት እንዲመጣ አስበው ይሆናል። ሱዳን ከጎንደር መሬት የወያኔ መሪዎች ቆርጠው ስለሰጡዋት ይህን መሬት ትመልስ ብለው ያማራ ክልል ህብረተሰብና የክልሉ መንግስት ስለጠየቀ ሱዳንን አቶ ኢሳያስና የሱማሌው ፕ/ት በተገኙበት መጋበዝ አላስፈለገም። ያም ሆነ ይህ ግን ዶ/ር አብይ ከፌደራል መንግስቱ ፍላጎት ውጭ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ወያኔንን ከበባ ውስጥ በማስገባት ይህን ስብሰባ ተጠቅመውበታል። እሺ እማይል ከሆነም ከበባ ቀለበት ውስጥ አስገባሃለሁ በሚል ሊሆን ይችላል።

"ዘላለማዊ ወዳጅም ሆነ ዘላለማዊ ጠላት የለም " ፦

ኮ/ል መንግስቱ በገነት አየለ ሲጠየቁ "ዘላለማዊ ወዳጅነትና ፥ ዘላለማዊ ጠላትነት የለም " ሲባል እውነት አይመስለኝም ብለው ነበረ። በሁዋላ ላይ ግን ይህ አባባል እውነት እንደሆነ እውነት እንደሆነ አወቅሁ ሲሉ አመኑ። ህወህትም ይህን መሰረታዊ እውነታ ኮ/ሉ በስልጣን ዘመናቸው እንዳልተረዱት ሁሉ ህወህትም በስልጣን ላይ እያለ ይህን እውነታ ስቶታል። እሁን ሊረዳው ይችል ይሆናል ፥ ከበባ ውስጥ ሥለገባ ።

Wednesday, November 7, 2018

privatisation process in Ethiopia

privatization ወይም የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወር ሂደት ምን መምሰል አለበት ? ፦

ሲጀመር ያክስዮን ግብይትን እሚያቀላጥፍ ተቁዋም በሌለበት ሁኔታ ምንም እንኩዋን
ecx ያክስዮን ግብይት እንዲያካሂድ የተሻሻለው አዋጅ ቢፈቅድለትም እና  የህግ ምእቀፍ ቢዘጋጅለትም ማገበያየት አልጀምረም። ያክስዮን ግብይት የሚዛወሩትን የልማት ድርጅቶችን የሚከታተሉ በርካታ ቦርዶች ቢቁዋቁዋሙም ነገረ ግን  ብቁዋቁዋቃምም ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ቦርድ አልተሾመም ብዙዎቹ ታዋቂ ሰዎችና የፖለቲካ ስዎች ሲሆኑ እነኝህም በየዘርፉ ባለሙያዎች አለመሆናቸው ይታወቃል። ባለሙያዎች አይደሉም። 
ካክስዮን ገበያ በሁዋላ ያክስዮን ግብይት ተቆጣጣሪ መ /ቤት መቃዋቃዋም አለበት ። ቦርድ ላይ የተሰየሙት ፥ይሁንና ግን የፖለቲካ መሪዎቹ ይህንን ዝውውር ለመፈፀም የሚያስችል አቅም ያላቸው አይመስልም አማካሪ ካልቀጠሩ በስተቀረ።  በሌላ ሃገር ቢሆን አማካሪዎችን በዘርፉ መቅጠር አማራጭ ነው የውጭም ሆነ ያገር ውስጥ አማካሪዎችን ቀጥሮ ማሰራት አስፈላጊ ነው ። ሌላው( policy flexibility) አስፈላጊ ሲሆን የዚህን ያህል ግዝፈትና ኣይነት ያለውን ሪፎርም ለማድረግ የተሙዋልስ ወይም።ምሉዕ የሆነ የፖሊሲ ማሻሻያ ማእቀፍን መዘርጋት ያስፈልጋል ግማሹን አሻሽዬ ግማሹን አላሻሽልም ማለት አይቻልም።  ከፊል አሻሽላለሁኝ ከፊሉን ደግሞ በነበረው አስቀጥላለሁ የሚለው የመንግስት ፖሊሲ የሚያስኬድ አይመስልም። ለዚህም ይመስላል ትላልቆቹን የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል አዛውራለሁ ቢልም መንግስት ቀጣይ በምን መንገድ ነው እሚዛወሩት ? ዝውውር ከመጀመሩ በፊትስ የሚያስፈልጉት አዳዲስ ተቆጣጣሪ ተቁዋማት እነማን ናቸው ? መሻሻል ወይም እንደ አዲስ መውጣት ያለባቸው የህግ ማእቀፍስ ምን መምሰል አለበት እሚለው ፍኖተ ካርታ roadmap ያለው አይመስልም።

"የስራ ፈጠራ "፦

መንግስት የስራ ፈጠራ ኮሚሽን አቁዋቁማል ይህ መልካም ሲሆን ስራ ፈጠራ በትእዛዝ እሚፈጠር ሳይሆን የፖሊሲ መሳሪያዎችን( policiy) instruments መጠቀምን ይጠይቃል። በተለይም እብዛኛው የሃገሪቱ ሃብት በመንግስት የልማት ድርጅቶች በተያዘበት ሁኔታ እንዲሁም እንደ መብራት ሃይል ያሉት ከመንግስት ባንኮች ከፍተኛ ብድርን በወሰዱበት ሁኔታ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚን  crowed out በማድረጋቸው ወይንም ከውድድሩ ውጭ ማድረጋቸው የግሉ ዘርፍ በበቂ ሳያድግ ለዘመናት እንዲቀጭጭ አድርጎአል።

Tuesday, November 6, 2018

justice system ethiopia



የኢትዮፒያ የፍትህ ስርአት የፍትህ ሥርአት ማሻሻያ  
ፀሃፊው ስሜነህ ተረፈ
የቀድሞው ጠቅላይ / መልካም አስተዳርን ለማስፈን ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በፍትህ ስርአቱ ላይ ትኩረትን አለማድረጋቸው ሳይሳካላቸው እንዲቀር ምክንያት ሆኗል ፡፡ ከዚህ ቀደም በአቶ ለማ መገርሳ የተመራው ኦህዴድ በኦሮሚያ ክልል የፍትህ ስርአቱን መልሶ ያዋቀረ ሲሆን ይህም በፌደራል ቢደገም መልካም ነው ሲባል ነበር ፡፡ የአሁኑ ጠቅላይ / ዶ/ር አብይ የህግ ክፍተቶችን በመድፍን ወደ ስራ በመግባት ነበረባቸው ተብሎ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረ ሲሆን እንደዚሁም መልካም አስተዳደርን ለመድፈን መቼም ቢሆን ከፍትህ ስርአቱ ላይ አይናቸውን መንቀል የለባቸውም ለቀድሞው / ሚር አቶ ሃይለማርያም አስተዳደር አለመሳካትና የህዝብ ቅሬታ ምንጮች በመሆን / ቤቶች ዋነኛ አሉታዊ አውዳሚ ሚናን መጫወታቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው
በፌደራል ደረጃ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፍትህ ስርአት ማሻሻያ እንደተጀመረ / ቤት አመራሮችን በመተካት ተጀምረዋል። እርምጃው የዘገየ ቢሆንም ለውጡ ግን አዋጆችን በማሻሻል መታገዝ አለበት በተለይም የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ሳይውል ሳያድር ሊሻሻል ይገባዋል። ይህ አዋጅ ይሻሻላል ጥፋትን የፈፀሙ ዳኞችን እስከ ወንጀል ድረስ ለመጠየቅ የሚያስችል ነው ተብሎ በአቶ ዳኜ መላኩ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም የት እንደደረሰ አይታወቅም አዋጁ።
አመራር በመለወጥ ብቻ ሳይወሰን 60 አመታት ያህል የቆዩትን የፍትሃ ብሄርና የስ//ህጉ እንዲሁም የወንጀለኛ መቅጫ የስ//ህጉ መሻሻል የሚገባቸው ሲሆን አዳዲስ መውጣት ያለባቸውም ማውጣት ለፍትህ አሰጣጥ አመቺ ያልሆኑ ነባር  ህጎችን መፈተሽ ያስፈልጋል። እንዲሁም ያመራር ለውጡ ወደ ታችኛው /ቤቶች አመራሮች ማለትም የመ/ ድረጃና ከፍተኛ /ቤት አመራሮች በነካ እጃቸው ይለወጡ።
/ሚር / አብይና አዲሲቷ የጠ/ፍ ቤት ፕ/ት በነካ እጃቸው ወደ ታች ያለው የስር ፍርድ ቤት አመራሮችን ማንሳት ይገባቸዋል ። የፍርድ ቤቶች ዳኝነት ተበላሽቶ የከፋ ደረጃ የደረሰው ባቶ ተገኔ ጌታነህ የጠ/ ቤት / በነበሩበት ወቅት ሲሆን በእርሳቸው የፕ/ትነት ዘመን በርካታ ፍርደ ገምድል ውሳኔዎች ተወስነዋል በርካቶችም በሙስና የተነካኩበትና ተጠያቂነት የጠፋበት ሁኔታ ነበረ። ከእርሳቸው በሁዋላ የተሾሙት አቶ ዳኜ መላኩም / ቤቱን ለማሻሻል ጥረትን አድርገዋል የጠ/ ቤቱ ፕሬዝዳንቶቹ ጥቅማ ጥቅምም እጅጉን ተሻሽሎአል ይሁን እንጂ አቶ ዳኜ በርካታ ቅሬታ የሚቀርብባቸውን የስር /ቤት አመራሮችን አልነኩም ስለዚህ የእርሳቸው ጥረት የሚፈለገውን ለውጥ ሳያመጣ ቀርቶአል። የአሁኑዋ / / መአዛ አሸናፊም በቶሎ የስር /ቤት አመራሮችን በማንሳት ስራቸውን መጀመር አለባቸው አለበለዝያ ከላይ የእርሳቸው ጥረት ብቻውን ለውጥን አያመጣም። አዋጆችን ማሻሻል በእጅጉ አስፈላጊ ሲሆን ይሻሻላሉ የተባሉ አዋጆችም በፍጥነት መሻሻል አለባቸው ፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ህግን የመተርጎም እንደ ህገ መንግስታዊ / ቤት ሆኖ ስልጣን የተሰጠው ለፌዴሬሽን / ቤት መሆኑ በራሱ ለህግ አተረጓጎም ችግርን ፈጥሯል ፌዴሬሽን ም/ ቤት ራሱ የአስፈጻሚው የገዢው ፓርቲ አካል ሆኖ መልሶ ከፍ / ቤቶች በላይ ህግ ተርጓሚ መሆኑ ህገ መንግስታዊ ትርጉም ያስፈልጋቸዋል የሚባሉ ጉዳዮች ወደ /ቤቱ የሚሄዱ ሲሆን የህግ አውጭውን የአስፈጻሚውንና የህግ ተርጓሚ የመንግስት አካላት ስራን የሚያደበላልቅ ነው ፡፡ ከዚህም አልፎ ስራውን የጀመረው የህገ መንግስታዊ አጣሪ ኮሚሽን የተባለው ተቋም ስራ መጀመሩ መልካም ሲሆን በርካታ የህግ ክፍተቶች ባሉት የፍትህ ስርአቱ ፍርደ ገምድል ውሳኔ ተወስኖባቸው አጣሪ ኮሚሽኑ ያስተካከላቸው እንዳሉ ይታወቃል ይሁንና ይህ ተቋም የበላይ ሃላፊዎቹ ፍርዱን የፈረደው ተቋም የጠ/ / ቤት ሃላፊዎች መሆናቸው ራሱ ፍርድን የሰጠው ሰው መልሶ ቅሬታውን የሚያየው መሆኑ አሁንም የአጣሪ ኮሚሽኑን ነጻነቱንና ተጠያቂነት አጠያያቂ ያደርገዋል ስለዚህ ይህ ሁሉ ጉዳይ የአዋጆች መሻሻልንና የአዲሲቱዋ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የቤት ስራ ይሆናል ማለት ነው ፡፡