Wednesday, March 13, 2019

የዘርአያቆብ ፍልስፍና ሃቲት

ፈላስፋው ዘርአያቆብ "እስራኤላውያን በእግዝአብሄር የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው የሚለውን" የሙሴን መሠረታዊ አስተምህሮን አይስማማበትም ። መናፍቁ እና ጠርጣራው #Heretic Philosopher ፈላስፋው ዘርአያቆብ የሙሴን መሰረታዊ አስተምህሮቶችን ይጠራጠራል ።

ዘርአያቆብ እግዝአብሄር ለአህዛብ ሚስጥሩን መችልም አይገልጥላቸውም የሚለውን በሙሴ የተጻፈውን የመዝሙረ ዳዊትን ጥቅሥ አይስማማበትም ። ይሁን እንጂ ጸሀፊው የካቶሊክ ቄስ ከሆነ ለአይሁድ ባላቸው ጥላቻን ማንጸባረቁ ሊሆን ይችላል ።

በመዠመር ያዘርአያቆብ ማነው ? ትውልዱስ እንፍራንዜ (ጎንደሬ) ወይስ የአክሱሜ ? ወይስ የካቶሊክ ካህን ?  ። ይሄ መታወቅ አለበት። ማንነቱን ማወቅ አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት ጸሐፊው ኢትዮጲያዊ ላይሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ስላለ ነው። 

ፕሮፌሰር ጌታቸው በጻፉት መጽሀፍ እንፍራንዜ ሲያደርጉት ሌሎች በተረጎሙት ደግሞ በወቅቱ በነበረው በካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች የሃይማኖት ውዝግብ ከአክሱም በሃይማኖት ክፍፍል ምክንያት ሸሽቶ ወደ ጎንደር የተሰደደ ትግሬ ያደርጉታል ።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ዘርአያቆ ትውልድ ስፍራ የትውልድ ስፍራ የራሱን ሃሳብ ሲገልጽ ፦

" የዘርአ ያእቆብ የዓለም ስሙ ‹ወርቄ› ነው፡፡ ‹ወርቄ፣ ብርቄ፣ ድንቄ› የሚሉ የስም አወጣጦች በአማራው አካባቢ እንጂ በአኩስም አካባቢ የተለመዱ ስሞች አይደሉም፡፡ ኡርቢኖ በደብረ ታቦር አካባቢ ሲኖር የሰማውን ስም መሆን አለበት የተጠቀመው፡፡" ይላል በዳንኤል ክብረት እይታ ዘርአያቆብ የጎንደሬ ስም ነው የተጠቀመው ።

ዲያቆን ዳንኤል ሲጠቅሥ " እንዲያውም ‹እንደዚህ ከሀገር ወደ ሀገር ስሄድ ወደ አኩስም እመለስ ዘንደ አልፈቀድኩም፤ የካህኖቿን ክፋት ዐውቅ ነበርና›(ያሬድ፣25) ይላል፡፡ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት እይታ "ዘርአ ያእቆብ በምንም መልኩ አኩስማዊ አይደለም ፡፡ አክሱምን በዚህ መጠን የሚጠላ አኩስማዊም ሊኖር አይችልም፡ በምክንያት የሚያምን ሰው ለዚህ ጥላቻው በቂ ምክንያት አላቀረበም፡፡ ዋና ማዕከላቸውን በአድዋ አድርገው ለነበሩት ካቶሊካውያን አኩስማውያን ቦታ ሊሰጧቸው አልፈቀዱም ነበር፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን መሠረት ሊጥሉ የፈለጉት በአኩስም ነበር፡፡ነገር ግን የአኩስም ካህናት አልፈቀዱም፡፡ይህንን ጥላቻ ነው ኡርቢኖ ያንጸባረቀው፡፡" ይላል።

ሌላው አብዛኛው ዘርአያቆብ እሚጠቅሳቸው ጥቅሦች ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰዱ መሆናቸው ሌሎቹን የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎችን በጥልቀት ያውቃል ወይ ሊያስብል ይችላል።

ዘርአ ያእቆብ ሙሴን ሲወቅስ ‹ወሙሴሰ ይቤ ኩሉ ሩካቤ ርኩስ ውእቱ - ሙሴም ሩካቤ ሁሉ ርኩስ ነው አለ› ይላል(215,9a)፡፡ ነቢዩ ሙሴ ራሱ በጋብቻ ጸንቶ የኖረ ነቢይ ነው፡፡ በምን መልኩ ይህንን ሊል አይችልም፡፡ ሙሴ ይህንን ነገር ለመናገሩ መጽሐፋዊም ትውፊታዊም ማስረጃ የለም፡፡ ዘርአ ያዕቆብ ዳዊት ከማወቅ (እርሱንም ሲደበቅ ደጋግሞ በማንበቡ)፣ ሐዲስን ከማንበብ የዘለለ የብሉይ ትምህርት የለውም ይላል ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡

ከሙሴ ይልቅ ግን ሐዋርያው ጳውሎስን በዚህ ጉዳይ ቢጠቅሥ ይመረጥ ነበረ ልምን ቢባል ጳውሎስ ከቻላችሁ እንደኔ አታግቡ ማለቱ በመልእክቶቹ የሚታወቅ ሲሆን ሐዋርያውም ራሱ ግን በዚህ ሊወቀስ የሚችል አይደለም ይህን ያለው ራሳቸውን በቅድስና ለሚለዩቱ ቅዱሳን ነው ፥ ምክንያቱም እርሱም ቢሆንም ግን የጋብቻን ክቡርነትንና የትውልድ መቀጠልን ነው ያስተማረው። ጌታ እየሱስም ጭምር "አንድ ሴት ለአንድ ወንድ" ብሎ ነው ያስተማረው። ጋብቻ ከሌለ ትውልድ ሊቀጥል እንደማይችል በጥንት ዘመንም የሚታወቅ ቀላል እውነት መሆኑ ይታወቃል ። ስለዚህ ዘርአያቆብ የቱ ቦታ ላይ ነው ሙሴ ሩካቤ ሁሉ እርኩስ እንዳለ ምንጩን አይጠቅሥም። በሙሴ ግዜ እንደውም እስራኤላውያን ህዝቡም ሆነ ነገስታቱ በርካታ ሚስቶችን ያገቡ ነበረ። ሙሴ ለነገስታቶች በሰጠው ምክር "ንጉሡ ሚስቶችን አያብዛ " የሚል ነው። በሃዲስ ኪዳን በአንድ ስለመወሰን ከመደንገጉ በስተቀር በብሉይ ዘመን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደሚቻል ከብሉይ መጽፍሐት መረዳት ይቻላል ። በሙሴ ህግ የሚመሩት የእስራኤል ነገስታት ከአንድ በላይ ሚስቶችን አግብተው በርካታ ልጆችን እንደወለዱ መጽሐፈ ነገስት ያትታል ። ለምሳሌ።ንጉስ ዳትዊንስ የንጉስ ሰለሞን ልጅ ኢዮርብአም በርካታ ሚስቶች እንደነበሩዋቸው ማንበብ ይቻላል ።

ዘርአያቆብ መዝሙረ ዳዊት ላይ ብቻ ትኩረትን ስላደረገ ከብሔረ ኦሪት አሟልቶ መጥቀስ አልቻለም፡፡ የካቶሊክ ሚስዮናውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ቤተ ክርስቲያኒቱን የከሰሱበት አንዱ ክስ ‹ኦሪታዊት ናት› የሚል ነው፡፡ ለእነርሱ በንጉሥ ገላውዴዎስ ዘመን የነበሩት ሊቃውንት መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ዘርአ ያእቆብ የእነርሱ ወገን ካልሆነ በቀር ሙሴን በዚህ መልኩ አይጠቅሰውም፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ዘርአያቂብ ማለት ኡርቢኖ የተባለ የካቶሊክ መነኩሴ ነው።

ሌላው ዘርአያቆብ ስለ ንጉሥ ፋሲለደስ ያለው አመለካከት ነው ። "በዐመሉና በደም ማፍሰስ ጸና፣በጎ ላደረጉለት፣ ቤተ መንግሥትንና ያማሩ ቤቶችን ለሠሩለት፣ በጥበብ ነገር ሁሉም መንግሥቱን ላሣመሩለት ፈረንጆችን ጠላቸው› ይላል " ፋሲለደስ ቤቶችን ይወርስ ነበረ ሴቶችን አብሮአቸው ካደረ በሁዋላ ይገድላቸው ነበረ ሲል ንጉስ ፋሲልን ግፈኛ አድርጎ ያቀርበዋል።

በራሱ አንደበት እንዲህ ይላል " ፋሲለደስ ክፉን ነገር የሚሠራ ሆነ፡፡ ሰዎችን ያለ ፍርድ ይገድል ነበር፡፡ አመንዝራነትም ያበዛ ነበር፡፡ ሴቶችንም ከእነርሱ ጋር ካመነዘረ በኋላ ይገድላቸው ነበር፡፡ ዐመጻን የሚያደርጉ ሠራዊትንም ልኮ የድኾችን ሀገሮችና ቤቶች እንዲቀሙ ያደርግ ነበር፡፡

እግዚአብሔር ለክፉዎች ሕዝቦች ክፉውን ንጉሥ ሰጥቷቸው ነበርና፡፡ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡም ኃጢአት ረሀብና መቅሰፍት መጣ፡፡ ከረሃብ በኋላም ቸነፈር ሆነ፡፡ ብዙዎችም ሞቱ፡፡ ሌሎችም ፈሩ፡፡" ዘርአያቆብ በወቅቱ ለነበረው ማህበረሰብ በጎ አመለካከት አልነበረውም የህዝቡ ክፋት ፋሲለደስ የተባለ ክፉ ንጉስ እንደሰጣቸው አፍርጎ ነው የተረዳው።

ይሁንና ግን ፋሲለደስ በአጼ ሱስንዮስ ዘመን የነበረውን የሃይማኖት ውዝግብን ያስቆመና ፤ግራኝ አህመድን ወረራ ለመመከት መጥተው ነገር ግን ከግራኝ ሽንፈት በሁዋላ የኦርቶዶክስ እምነትን ወደ ካቶሊክ ለመለወጥ የሞከሩትን ፖርቱጋሎችን ያስወጣ ነው።

china port

Marine Gen. Thomas Waldhauser, the top U.S. military officer for Africa, told a congressional hearing last year that the U.S. military could face significant consequences if China took the port in Djibouti.

Monday, March 4, 2019

Ethiopia Debt Sustainability

የገንዘብ ስርአት ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። ከለውጡ በፊት በኢትዮፒያ በኢትዮፒያ ልማት ባንክ በኩል ብድር ቢመቻችም ብድሩ ሳይመለስ #npl ማለትም #የማይመለሱ ብድሮች ይፋዊ በሆነው መረጃ #Non_Performing_Loans #NPL ወደ 40 በመቶ ከፍ ቢልም እስከ 70 በመቶ ይደርሳል በዘርፉ ባለሙያዎች ግምት።ለዚህ ምሳሌ እሚሆነው #Aika_Addis የተባለው የ#ቱርክ #ኩባንያ #አይካ_አዲስ በ8 ቢሊየን እዳ እሳቅፈው ሲሄዱ 29 ሚሊየን ዶላር ማሽን ቢያመጣም 150 ሚሊየን ዶላር እንዳመጣ ተደርጎ ብድር ከልማት ባንክ ተለቆለታል ። ይህም።ልማት ባንኩን አክስሮአል ።
አሁን ግን በዚህ አይነት መንገድ በተለይም ግብርና ዘርፍ እንሰማራለን ብለው ከልማት ባንክ ብድር ወስደው ያልከፈሉ በህግ እንደሚጠየቁ የብሄራዊ ባንክ ገዢ ጠቁመዋል ።

#small & medium eneterprisrs አነስተኛና መካከለኛ ተቁዋማት አበዳሪ
ያጡት በዚህ ምክንያት ነው ።
እሚያበድራቸው የለም ፥ ወጣቱ ስራ ያጣው በዚህ ምክንያት ነው።
አሁን ያለው ለውጥ መደገፍ የምንችለው በኢኮኖሚ ስልት ነው ስራ እድል ለወጣቱ መፈጠር እና ኤክስፖርት #import_Export_Trade #ወጪና_ገቢ_ንግድ መንቀሳቀስ አለበት ፥ ለዚህ ደግሞ መንግስት #ፕላን ማውጣት አለበት። የሀገሪቱ የውጭ ብድርን ጫና የመሸከም አቅም #Debt Sustainability መፈተሽ አለበት።  ከአቅም በላይ ብድርና ክፍያ የውጭ ምንዛሪውን ጠራርጎ እየወሰደው ነው። ሃገሪቱ ብድር ለመክፈል አጠራጣሪ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ እንደነበረ ወይም #Default ልታደርግ እንደነበረ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ጠቆም አድርገዋል በቅርቡ በሰጡት ቃለ ምልልስ።

Sunday, March 3, 2019

Zar’a Ya’aqob Ethiopian philosopher

Zar’a Ya’aqob is not Ethiopian or there was no such philosopher called Zar’a Ya’aqob. The one known as Zara Ya’aqob was a pseudonym used by a 19th Century Freemason European — who penned the treatises as better known as the Hatetas.

Thursday, February 28, 2019

ህገ_መንግስት ኢንሹራንስ ሰምተው ያውቃሉ

ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል ከዚህ መሠረታዊ የፍትሕና ርትዕ መርህ በመነሳት፣ ለየትኛውም ወገን ባለማድላት ተጥሰዋል ተብሎ የቀረበለትን የሕገ መንግሥት መርሆዎች ለማፅናትና ለማስከበር ገለልተኛ መሆን ይገባዋል፤ በዚህ መርህ መሠረትም ተርጓሚው አካል እጅግ ወሳኝ ሚና የሚጫወት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊው ነው፡፡

ሌላው ሕገ መንግሥትን ከመተርጎም አንፃር አዲስ ክስተት ወይም ጽንሰ ሐሳብ የሆነው የሕገ መንግሥት ኢንሹራንስ የሚለውንም አስፈላጊነትን ማንሳት ያሻል፡፡ ሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል በተለይ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በሚከተሉ አገሮች ውስጥ፣ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ዋስትና የሚሰጥ አካል እንደሚሆን ይታወቃል።፡

‹‹የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት የሚከተል የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ፓርቲዎች ይቀያየራሉ፡፡ ስለሆነም አንድ ፓርቲ ከሥልጣን ከወረደ በኋላ ምንም አድልኦ በሌለበት ሁኔታ በሚቀጥለው ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳና ዘመቻ አድርጎ ወደ ሥልጣን እንዲመለስ ዋስትና ያስፈልገዋል፡፡

አማርኛ የAU የስራ ቁዋንቁዋ ሆነ

የአውሮፓ ህብረት #EU ከአስር በላይ የስራ ቁዋንቁዋዎች ሲኖሩት፥ የአፍሪካ ህብረትም አማርኛ ከአረብኛ ከእንግሊዝኛ ከስዋሂሊና ከፖርቱጋል እና ከፈረንሳይኛ ቀጥሎ 6ኛ የስራ ቁዋንቁዋ ይሆን ዘንድ አማርኛ ቁዋንቁዋን ሰይሞአል።  ከአስሩ አፍሪካውያን አንዱ ኢትዮጲያዊ ሲሆን የህዝብ ብዛቱዋ ከአፍሪካ 2ኛ የሆነ ህዝብ መግባቢያ ቁዋንቁዋ የሆነው አማርኛ ቁዋንቁዋ የAU one of the official languages of AU መሆኑ አኩሪ ሲሆን የጠ/ሚሩ ድል ነው።
ይህም ለበርካታ ኢትዮጲያውያን የስራ እድልን ሲፈጥር የኢትዮጲያውያን ደራሲዎች በአማርኛ ብቻ ነው እሚጽፉት በአውሮፓውያን ቁዋንቁዋ እንደ ኬንያ ጋና ወይም እንደ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ ደራስያን  በእንግሊዝኛ ቁዋንቁዋ ቢጽፉ ኖሮ አለም ኣቀፍ እውቅናን ይጎናጸፉ ነበር ለሚለው ምላሽን የሚሰጥ ነው። ምክንያቱም በርካታ ኣፍሪካውያን የአማርኛ ቁዋንቁዋን እሚማሩ ከሆነ የኢትዮጲያ ቁዋንቁዋ ፥ ስነ-ጽሁፍና ባህል ሰፊ የመተዋወቅ እድልን ያገኛክ።

Wednesday, February 6, 2019

trade war USA Vs China

የአሜሪካና የቻይና የንግድ ጦርነት #Trade war ወደ ገንዘብ ምንዛሪ ጦርነት # Currency war ይቀየራል ተብሎ ተሰግቶአል። ይህ ደግሞ የሌላውን አገር ሆነ ብሎ# የገንዘብ ምንዛሪን ከፍና ዝቅ እንዲል በማድረግ የዝያን ሃገር ገንዘብ #ማክሰርና ዋጋ ማሳጣት ማለት ሲሆን ይህ በትራምፕ የተቀሰቀሰው የንግድ ጦርነት አለምን በተለይም ታዳጊ ሃገራትን ክፉኛ ሊጎዳ ይችላል። እልኽኛው #Stubbourn ግትሩ # ፕሬዝደንት ትራምፕ ገና ከዚህ የባሰ #ማዕቀብን #በቻይና ላይ ለመጣል እየተዘጋጁ ነው።
አሜሪካ ከዚህ ቀደም ባላንጣ ያለቻቸውን ቱርክንና ሩስያን ገንዘብ ምንዛሪን ዋጋ በማሳጣት የስራ አጥ Unemployment rate #ቁጥሩ እንዲጨምር ፥ #ኤክስፖርት እንዲቀንስና ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስን እሚያስከትልና መንግስታትን እሚያናጋ ነው። ቻይናም የስራ አጥ ቁጥሩዋ እየወነሰ ሲገኝ ይህን የንግድ #ጦርነትን ተከትሎ ለመጀመርያ ግዜ #በ30 አመታት ውስጥ የኢኮኖሚ #እድገትዋ #ቀንሶአል።

Sunday, January 27, 2019

ፋሪድ ዘካራይ ማነው ?

#ፋሪድ_ዘካራይ ማነው ?
በአለም ኢኮኖሚ ፎረም የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም #Word_Economic_Forum
ላይ ተገኝቶ ከጠ/ሚር ዶ/አብይ አህመድ ጋር ሲነጋገር በዚህ ፎቶ የምናየው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ሳይንቲስት ሲሆን# ፓኪስታን አሜሪካዊ ሲሆን በ#newsweek መጽሄት ላይ ቁዋሚ #ኣምደኛ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን የCNN tv #GPS የተሰኘ ስለ አለማችን ወቅታዊ ሁኔታ የተለያዩ መሪዎችን የሚያወያይ ዝግጅት አዘጋጅና አቅራቢ #host ሆኖ ይሰራል። በርካታ መጽሐፍትን የጻፈ ሢሆን በፖለቲካ ትንተና ክህሎቱ የተመሰከረለት ነው። የአለማችን ታላላቅ መሪዎች በእርሱ ኢንተርቪው #interview ላይ መገኘት አጥብቀው ይፈልጉታል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ፥ የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም #Word_Economic_Forum
የ2020 ስብሰባ በኢትዮጲያ እንዲካሄድ ተወስኖአል። 

Sunday, January 20, 2019

የነዳጅ እጥረትና መፍትሄው

የሰሞኑ የነዳጅ መጥፋት የነዳጅ አከፋፋዮች የትርፍ ህዳግ (#profit_margin ) ሲበዛ ማነሱ ዋነኛ ምክንያት ሁኖ ተጠቅሶአል። ይህ የትርፍ ህዳግ ከፍ ይበል ተብሎ በተደጋጋሚ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም ምላሹ ዘግይቶአል። የዶላር ምንዛሬ ሲጨምር የነዳጅ ዋጋ ግን አልጨመረም በአቶ ሃይለማርያም ግዜ ። ይህም በሌሎች ሸቀጦችና ኣገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ ወዲያውኑ #Instantly የኑሮ ውድነትን ያስከትላል ይህ ደግሞ በፈንታው የፖለቲካ ኣለመረጋጋትን ሊያስከትል ይችላል። በኣሁኑ ወቅት በሱዳንና ዚምባብዌ የሚታይርው ህዝባዊ ኣመጽ ሰበቡ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀብ ነው። ነዳጅ ማደያዎች ማደያውን ህንጻ እየገነቡበት ነው ተብሎአል ትርፉ በጣም ትንሽ ስለሆነና አዋጭ ሥላልሆነ ህንጻ ሰርቶ ማከራየትን የቀለለ ሁኖ ኣግኝተውታል። ከዚህም።በላይ ደግሞ ነዳጅ አከፋፋዮችም በዱቤ የወሰዱትን በቢሊየን ዱቤ እየከፈሉ አለመሆኑ ታውቆአል።

Friday, January 4, 2019

12 ሉነበቡ የሚገባቸው የአመራር ጥበብ መጽሐፍት

Bob SuttonProfessor,nally poste
I have been maintaining — and occasionally updating — a list of "Books That Every Leader Should Read" on my old Work Matters' blog since 2011. These are books that have taught me much about people, teams, and organizations — while at the same time — provide useful guidance (if sometimes indirectly) about what it takes to lead well versus badly. This is the 2018 update. I left out many of my favorites — and probably many of yours as well. After all, some 11,000 business books are published in the United States every year.

Many on the list are research based, others tell detailed stories, and only two are quick reads ('Orbiting the Giant Hairball' and 'Parkinson's Law'). That reflects my bias. I lean toward books that have real substance beneath them. This runs counter to the belief in the business book world that people will only buy and read books that are very short and simple — and have just one idea. So, if your kind of business book is 'The One Minute Manager' (which frankly, I like too ... but you can read the whole thing in 20 or 30 minutes), then you probably won't like most of these books.

1. 'The Progress Principle' by Teresa Amabile and Steven Kramer

A masterpiece of evidence-based management — the strongest argument I know that "the big things are the little things."

2. 'Influence' by Robert Cialdini

The classic book about how to persuade people to do things, how to defend against persuasion attempts, and the underlying evidence. I have been using this in class at Stanford for over 25 years, and I have had dozens of students say to me years later "I don't remember much else about your class, but I still use and think about that Cialdini book." I also am impressed with Cialdini's 2016 bestseller, 'Pre-Suasion,' which adds wonderful new evidence-based twists. And while some of the examples in the original book are getting a bit dated, I suggest starting with the classic and then reading the new one.

3. 'Made to Stick' by Chip and Dan Heath

A modern masterpiece, already a classic after just a few years. How to design ideas that people will remember and act on. I still look at it a couple times a month and I buy two or three copies at a time because people are always borrowing it from me. I often tell them to keep it because they rarely give it back anyway. And, for my tastes, it has the best business book cover of all time — the duct tape even looks and feels real.

4. 'Thinking, Fast and Slow' by Daniel Kahneman

Even though the guy won the Nobel Prize, this book is surprisingly readable. A book about how we humans really think, and although it isn't designed to do this, Kahneman also shows how and why so much of the stuff you read in the business press is crap. I also recommend Michael Lewis' 2017 book 'The Undoing Project,' which tells the tale of the complex relationship between Daniel Kahneman and his colleague the late Amos Tversky (who would have shared the Nobel with Kahneman if he had lived).

5. 'Quiet' by Susan Cain

I have long been a fan of this book. The blend of storytelling, Cain's writing voice, and evidence is something to behold. There are three reasons I've moved it to my leadership list. The first is that the influence seems to grow every year; every leader I know now talks about the difference between leading introverts and extroverts. Leaders and future leaders who are introverts now are more confident, and understand better how to blend their style with extroverts. And, from the academic perspective, I believe it is no accident that, since Cain's book was published, there has been a big upswing in research on the virtues and nuances of extroverts — as leaders, group members, romantic partners, and on an on. Second, Cain does an magnificent job of taking down open office designs — which are especially tough in introverts, but undermine productivity, satisfaction, and healthy social interaction for all employees in ways that advocates have denied for decades (despite all the evidence of drawbacks). Cain's book has, I believe, played a substantial role in the current pushback against open offices. Third, and on a more personal level, my wife read 'Quiet' for the first time this year. She is an introvert and has been a successful leader for the past 25 years or so, first at a large law firm, and as CEO of the Girl Scouts of Northern California for the last decade. The book helped her understand why she has been successful and how to fine tune her leadership style depending on whether the staff, adult volunteers, and girls she works with are more introverted or extroverted.

6. 'Orbiting the Giant Hairball' by Gordon MacKenzie

It is hard to explain, sort of like trying to tell a stranger about rock and roll, as the old song goes. But it is one of the two best creativity books ever written, and one of the best business books of any kind — even though it is nearly an anti-business book. Gordon's voice and love creativity and self-expression — and how to make it happen despite the obstacles that unwittingly heartless organizations put in the way — make this book a joy.

7. 'Creativity, Inc.' by Ed Catmull

One of the best business/leadership/organization design books ever written — this and 'Hairball' are a great pair. I wrote a more detailed review of Ed's wonderful book here. As I wrote in my blurb, and this is no B.S., "This is the best book ever written" on what it takes to build a creative organization. It is the best because Catmull's wisdom, modesty, and self-awareness fill every page. He shows how Pixar's greatness results from connecting the specific little things they do (mostly things that anyone can do in any organization) to the big goal that drives everyone in the company: making films that make them feel proud of one another. I read this book from cover to cover again about a month ago — there is so much there as Ed brings in so much of his amazing life and gleans so many lessons about leadership and life.

I confess that I am biased about this book. I have met Ed several times and swayed by his modesty, smarts and how well he listens. The last time we met, Ed told me a great story. He and his editor were having trouble with the flow of the book. So he asked a couple of the Pixar script writers who worked on the film 'Monsters INC' to read the draft and make suggestions. Ed said they spotted the problem right away and came up with a great solution. Ed has resources that other authors don't! That beautiful cover is a Pixar design too.

8. 'Leading Teams' by J. Richard Hackman

When it comes to the topic of groups or teams, there is Hackman and there is everyone else. If you want a light feel good romp that isn't very evidence-based, read 'The Wisdom of Teams.' If want to know how teams really work and what it really takes to build, sustain, and lead them from a man who was immersed in the problem as a researcher, coach, consultant, and designer for over 40 years, this is the book for you. Oh, and if you want the cheat sheet — although you are missing enough that you are mostly cheating yourself — check out Hackman's HBR piece, the very definition of profound simplicity, a lifetime of wisdom and (I am guessing) the results of 1000 studies summarized in six concise points.

9. 'Give and Take' by Adam Grant

Adam is the hottest organizational researcher of his generation. When I read the pre-publication version, I was so blown away by how useful, important, and interesting that 'Give and Take' was that I gave it one of the most enthusiastic blurbs of my life: "'Give and Take' just might be the most important book of this young century. As insightful and entertaining as Malcolm Gladwell at his best, this book has profound implications for how we manage our careers, deal with our friends and relatives, raise our children, and design our institutions. This gem is a joy to read, and it shatters the myth that greed is the path to success." In other words, Adam shows how and why you don't need to be a selfish asshole to succeed in this life. America — and the world — would be a better place if all of us memorized and applied Adam's worldview. I love this book — I give it to Stanford students and executives all the time, especially when they worry aloud that, to get ahead, their only choice is to be a selfish asshole.

10. 'Parkinson’s Law' by C. Northcote Parkinson

You've probably heard of Parkinson's Law, which he first proposed in The Economist in 1955: "It is a commonplace observation that work expands so as to fill the time available for its completion." I had as well, but I never knew much about C. Northcote Parkinson, nor had I read his 1958 gem of the same name (I didn't even know it existed) until Huggy Rao and I started writing 'Scaling Up Excellence' and my well read co-author pointed me to this collection of essays. Parkinson was quite a guy — a scholar of public administration, naval historian, and author of over 60 books. For our scaling book, I was especially taken with his arguments, evidence, and delightfully polite English sarcasm about the negative and predictable effects of group size and administrative bloat. I am also a big fan of 'The Peter Principle,' which is similar in some ways, (I wrote the forward to the 40 Anniversary Edition), but 'Parkinson's Law' is an even better book.

11. 'To Sell is Human' by Dan Pink

You might ask, what does this have to do with management and leadership? Read the book. Dan does a masterful job of showing how, to lead and motivate others, to protect and enhance of the reputations of the people, teams, and organizations we care about, and to have successful careers as well, we all need to be able to sell people our ideas, products, solutions, and yes, ourselves. Dan's ability as a storyteller is what makes this book stand above so many others — his stories are not only compelling, they make evidence-based principles come alive. To be honest, I had not devoted much attention to this book until my wife picked up a copy and read the whole thing from start to finish in about a day. She then spent the next week raving about all the ways Dan's book would help her as CEO of a non-profit — in everything from fundraising, to inspiring employees and volunteers, to dealing with the media, to convincing new prospects to join her organization's board. Then I read it myself. As much as I admire Malcolm Gladwell, I believe that Dan Pink just might be the most skilled writer we have at translating behavioral science research. His stuff is so fun to read, it doesn't distort or exaggerate findings, and he does a masterful job of teaching us how to apply the lessons in his books.

12. 'The Path Between the Seas' by David McCullough

On building the Panama Canal. This is a great story of how creativity happens at a really big scale. It is messy. Things go wrong. People get hurt. But they also triumph and do astounding things. I also like this book because it is the antidote to those who believe that great innovations all come from start-ups and little companies (although there are some wild examples of entrepreneurship in the story — especially the French guy who designs Panama's revolution — including a new flag and declaration of independence as I recall — from his suite in the Waldorf Astoria in New York, and successfully sells the idea to Teddy Roosevelt).

As my Stanford colleague Jim Adamspoints out, the Panama Canal, the Pyramids, and putting a man on moon are just a few examples of great human innovations that were led by governments. If you want to learn about what world class scaling "clusterfug" looks like, read about how the French messed things up — and if you want to learn about skilled scaling (with some horrible side-effects) and the amazing U.S. President Teddy Roosevelt, find the time to read this rather massive masterpiece.

In addition to these twelve, I was tempted to add 'Collaboration' by Morten Hansen, the best book on the topic ever written and 'The Silo Effect' by Gillian Tett, which is stunning analysis of why — once organizations are broken into specialized groups — all sorts of bad things that undermine the greater good, along with some mighty thoughtful ideas about how to overcome these problems and make the best use of such specialized and isolated "stovepipes." And while I removed 'Who Says That Elephants Can't Dance,' by former IBM Lou Gerstner from my top 12 a couple years ago, it remains the best book on the transformation of a large company that I know of — the first half is especially strong.

Bob Sutton is a Stanford Professorwho studies and writes about leadership, organizational change, and navigating organizational life. His latest book is The Asshole Survival Guide: How To Deal With People Who Treat You Like Dirt.

Monday, December 31, 2018

ላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተክርስትያን

#ገናን በላልይበላ እናሳልፍ ።

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙት  ሰሜን ወሎ ዞን ከባህር ዳር ጋሸና 236 ኪ.ሜትር ከጋሸና ላልይበላ 64 ኪሎሜትር ከወልዲያ ሰሜን ምዕራብ 18ዐ ኪ/ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው ከላልይበላ ከተማ ነው፡፡

ውቅር አብያተክርስቲያናቱ በ12ኛው ክፍለ ዘመን በቅዱስ ላልይበላ ከአንድ አለት ተፈልፍለው የታነጹ ሲሆኑ በሶስት ምድብ የተከፈሉ ናቸው፡፡

ምድብ አንድ ፦ ቤተመድሃኒዓለም፣ ቤተ ማርያም፣ ቤተ ሚካኤል / ቤተ ጐለጐታ/፣ ቤተ መስቀል፣  ደብረ ሲና እና ቤተ ደናግል ይገኛሉ።

#ምድብ ሁለት መካከል፦ ቤተ አማኑኤል፣ ቤተ መርቆርዮስ፣ ቤተ ገብርኤል ሩፋኤልና ቤተ አባሊባኖስ ይገኛሉ።

ከሁለቱም ምድቦች ፈንጠር ብሎ የሚገኘው #ቤተ ጊዮርጊስ ደግሞ በምድብ ሶስት ይመደባሉ፡፡

በላሊበላ በርካታ በዓላት አሉ የተለየው ግን ትልቁ ክብረ በአል ታህሳስ 29 ቀን የሚከበረው የገና በአል ነው፡፡

ለበአሉ ታላቅነት ሌላው ተጨማሪ ምክንያት ደግሞ በቅዱስነታቸው የሚታወቁት የቅዱስ ላሊበላ የልደት ቀን ጭምር መሆኑ ነው፡፡

የገና በዓል በላልይበላ በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊ ዝግጅቶች ለበርካታ ቀናት ይከበራል፡፡

በተለይም በገና ዋዜማ በሌሊት የሚከናወነው የቤዛ ኩሉ ሀይማኖታዊ ስርአት እንደእርጥብ ሸንበቆ  ወገባቸው  የሚተጣጠፈውን የደብረ ሮሃ  ካህናት ዝማሜ ማየት እጅግ ያስደስታል፡፡

ጥምቀትም በላሊበላ ሌላው ትልቅ በአል ነው፡፡

የእነዚህን ሁለት ትላልቅ በአላት አከባበር በአካል ለመመልከት  እና ከበዓላት ውጭም ውቅር አብያተክርስትያኑትን የህንፃ ጥበብ ለማየት እና ለማድነቅ ብዛት ያለው ምእመን፣ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጐብኝ ወደ ላሊበላ በየአመቱ ይጎርፋል።

በርካታ ቅርሶችን የያዘ ቅዱስ ላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱትን ሲሰራ የተጠቀመበት መጥረቢያን ጨምሮ በርካታ ቅርሶች በሙዚየም ተደራጅተዋል እንዲሁም ባማረ ህንፃ የተደራጀው የላልይበላ የባህል ማዕከልም የአካባቢውን ወግና ባህል በሚያሳይ መልኩ ሙዚየም  ተደራጅቶ ለጉብኝት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ከ11ዱ ውቅር አብያተክርስትያናት በተጨማሪ በቅርብ ርቀት በርካታ ጥንታዊና ታሪካዊ አብያተ ክርስትያናት ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ይምርኸነክርስቶስ ፣ ገነተማርያም ፣ ናአኩቶለአብ ፣ ብልብላጊዮርጊስ፣ ብልብላ ቂርቆስ ፣ እመኪናመድሀኒዓለም ፣ አሸተን ማርያም ፣ አቡነ ዬሴፍና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡

ውድ የአገር ውስጥና የውጭ ምዕመናን ገናን በላልይበላ በመገኘት እነዚህን ውድ የአገር ሀብትና ኩራት የሆኑትን ቅርሶች በመጐብኘት ደስታችን እጥፍ ድርብ እናድርግ፡፡

የፓርቲዎች ውህደት

"ቅንጅትም አይደለም ፤ ግንባርም አይደለም " ፦
ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች የመሰረቱት ይህ ዜግነትን መሰረት ያደረገ ፓርቲ ከዚህ በፊት በ97ቱ ምርጫ ተሞክሮ ከከሸፈው "ቅንጅት " ትምህርት የተወሰደበት ይመስለኛል። በበፊቱ ቅንጅት አባል የሆኑት ፓርቲዎች እኩል ድምጽ የመበራቸው ሲሆን የራሳቸውን ድርጅታዊ ማንነትንም ይዘው ቀጥለዋል። ኢህአዴግም "ግንባር " ሲሆን አራቱም አባል ድርጅቶች የራሳቸውን ህልውና ይዘው ሲቀጥሉ በህወሃት በሚመራው ኢህአዴግና በአዴፓ በሚመራው ኢህአዴግ መሃል ልዩነቱ የሚታይ ነው። ይህ አሂን ህብረ ብሄራዊ ፓርቲዎች የመሰረቱት ግን "ቅንጅትም " አይደለም "ግንባርም " አይደለም ተብሎአል ይህም ውስጣዊ አንድነቱን ለመጠበቅ የሚያስችለው መላ ነው።
"ቅንጅትም አይደለም ፥ ግንባርም አይደለም ውህደት ነው "።በዚህ ውህደት ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ማክሰሙን ገልጾአል ።ይሁንና ግን አንድነት ሲባል ልዩነት የለም ማለት አይደለም ግን አንድነት ከልዩነት ይበልጣል ነው ሃሳቡ። ይህ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ አዲስ ይዞት የመጣው ሃሳብ በተለይም ምንም አይነት የፖለቲካ ውክልና ለሌለው ከተሜ አማራጭ ሊሆን ይችላል ።
በቦለቲካው ዓለም የአቁዋም ለውጥንና ማሻሻያን ወይም ተሃድሶን ብሎም የአመራር ለውጥን እያደረጉ መቀጠል አዲስ ነገር አይዶለም። ለምሳሌ በአሜሪካን አገር የጥቁር መብት ተከራካሪና ተራማጅ ተደርጎ በአብረሃም ሊንከን በ1860ዎቹ ግዜ የሚወሰደው ሪፐብሊካን ፓርቲው ሲሆን አሁን ደግሞ የሰራተኛውና የጥቁሮች የተሻለ ይወክላል እሚባለው #ዲሞክራቲክ ፓርቲው ነው። #adapt ማድረግ #flexibility ለፖለቲካ ፓርቲዎች ህልውናን ለማስቀጠልና ለአዳዲስ ጉዳዮች ጋር አብሮ ቀጥሎ ዘላቂ የሆነ የህዝብ ድጋፍን ይዞ ለመቀጸል ይረዳል።

Thursday, December 27, 2018

የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሕይወቱ እና ትምህርቱ አጭር ዳሰሳ

                                                                             የቅዱስ አትናቴዎስ ዜና ሕይወት

ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ በ298 ዓ.ም በእስክንድርያ ተወለደ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ በህጻንነቱ በጨዋታ ሜዳ ከህጻናት ጋር እርሱ አጥማቂ እነርሱ ተጠማቂ እየሆኑ ሲጫዎቱ ፓትርያርክ እለእስክንድሮስ አይቶ ወደ መንበረ ፕትርክናው በመውሰድ እንዳሳደገው ሩፊኖስ የተባለው የዚያን ዘመን ታሪክ ጸሐፊ ዘግቧል፡፡
እለእስክንድሮስ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እና ሥርዓት እንዲሁም ሌሎችን የዘመኑ ዕውቀቶች እያስተማረ ካሳደገው በኋላ ለመዓርገ ምንኩስና በቃ፡፡ በቅድስናው፣ በሞያውና በግብረ ገብነቱ እንከን የሌለው ወጣቱ አትናቴዎስ በ23 ዓመቱ ሊቀ ዲያቆን ሆነ፡፡ በዚያ ዘመኑ መዓርግ “ሊቀ ዲያቆን” ማለት የሊቀ ጳጳሱ አፈ ጉባኤ፣ እንደራሴ እንደ ማለት ነበር፡፡ (የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣ አባ ጎርጎርዮስ (ጳጳስ)፣ 1978 ዓ.ም.፣ ገጽ 94)
በአጠቃላይ የአራተኛው መቶ ዓመት የቤተ ክርስቲያን ተጋድሎ ከአርዮሳውያን እና ተረፈ አርዮሳውያን ጋር የተደረገ እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስንም ጎልቶ እንዲወጣ እና ታላቅነቱ እንዲታወቅ ያደረጉት በዚሁ ዘመን የነበረው የአርዮሳውያንና ተባባሪዎቻቸው ሁከትና ሴራ ነው፡፡
አርዮስ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ላይ የክህነት ኃላፊነት ተሰጥቶት ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያስተምር ተሹሞ የነበረ ሊቢያዊ ቄስ ነበር፡፡ በኋላ ግን “ወልድ በመለኮቱ ፍጡር ነው” የሚል ትምህርት እያስተማረ እና የቅዱሳት መጻሕፍትን ንባባት ለዚሁ ትምህርቱ በሚረዳው መልኩ እየተረጎመ ምንፍቅናውን በታላቅ ትጋት በማስተማሩ እርሱ እና መሰሎቹ ቤተ ክርስቲያንን ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አውከዋታል፡፡
በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያውን ዓለም አቀፍ ጉባኤ አድርጋለች፡፡ ይህ ጉባኤ በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ አስተባባሪነት እና በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ በእለእስክንድሮስ መሪነት በ 325 ዓ.ም በኒቅያ (አሁን ቱርክ ውስጥ ባለች ቦታ) ተካሄደ፡፡ በጉባኤው 318 ጳጳሳት ብዛት ካላቸው ቀሳውስት እና ዲያቆናት ጋር ተገኝተዋል፡፡ በጉባኤው የአርዮስን ምንፍቅና በማጋለጥ እና ትክክለኝውን የቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በሚገባ ከገለጡ ሊቃውንት መካከል ለጊዜው በሊቀ ዲያቆንነት እለእስክንድሮስን ተከትሎ የሄደው በኋላ እለእስክንድሮስ ሲያርፍ በእስክንድርያ መንበር በሊቀ ጳጳስነት የተሾመው ቅዱስ አትናቴዎስ ዋናው ነበር፡፡ በተለይ አርዮስን በጉባኤው ፊት ተከራክሮ በመርታቱ እና አርዮሳውያን መሠረቱን ሊንዱት የጣሩትን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ትምህርት በጽሑፍና በቃል በማስተማር በማስጠበቅ ኃላፊነቱን በሚገባ የተወጣ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አባት ነው፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ በአርዮሳውያን ሴራ አራት ጊዜ የተሰደደ እና ብዙ መከራ የተቀበለ ሲሆን ለትውልድ እየተላለፉ ቤተ ክርስቲያንን የሚያለመልሙ ድንቅ የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍትን ጽፏል፡፡ ከነዚህ መካከል “በእንተ ሥጋዌ”፣ “የአርዮሳውያን መቃወሚያ (Against Arians)”፣ “በእንተ ስደት” ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የቅዱስ እንጦንስን ገድል የጻፈው ቅዱስ አትናቴዎስ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ይህ አባት ሌሎች በርካታ መጻሕፍትን እየጻፈ እና ከነገሥታት እና ባለሥልጣናት ሳይቀር የሚመጣበትን መከራ እየተቀበለ ለቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መጠበቅ እስከ መጨረሻዋ ሰዓት ድረስ ታግሏል፡፡ በዚህ ጽናቱም “ዓለሙ አትናቴዎስን ጠልቶታል፤ አትናቴዎስም ዓለሙን  ጠልቶታል” ለመባል በቅቷል፡፡ ዘመን ገጠሙ የነበረው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ “የቤተ ክርስቲያን ዓምድ” ይለዋል፡፡ የግሪክ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ “የኦርቶዶክሳዊነት አባት (Father of Orthodoxy)” ትለዋለች፡፡
ይህ ታላቅ የሃይማኖት አርበኛ በሰባ አምስተኛ ዓመቱ በአርባ ስድስተኛ ዓመተ ፕትርክናው ግንቦት 7 ቀን 373 ዓ.ም ድካምና ውጣ ውረድ የተመላውን የዚህን ዓለም ሕይወት በአስደናቂ ሁኔታ ፈጸመ፡፡
(ከዲያቆን ያረጋል አበጋዝ “ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሕይወቱ እና ትምህርት።      

"ጌታ ለዘለዓለም አይጥልምና፤ ያሳዘነውን ሰው እንደ ይቅርታው ብዛት ይምረዋል" ሰቆቃወ ኤርምያስ ፫ ፥ ፴፩
                                   

Wednesday, December 26, 2018

የጥንቱዋ ኢትዮጵያ ታሪክ

#የጥንቱዋ ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ_#የሱባ ቋንቋ መዝገበ ቃላት_#መጽሃፈ ብሩክ_ዣንሹዋ
#መጽሐፈ ክቡር #መጽሐፈ_ፈውስ #የእውነትን ህይወት_ወደዱ #አፍሪካ_ሁኑ #ጥበብ_ከዕውቀት_ ትምህረት_ከልጅነት #የልቤ_ ወዳጅ_የሰው_ዘር_ልጅ #ምክር_ከእኔ_ስማ_አንተ_ወገኔ ስል የተሰኙትን መጽሐፍት ጨምሮ 24 የሚደርሱ መጻህፍትን ጽፌአለሁ። አብዛኛው ጹሁፎቼ  ደግሞ ስለ ኢትዮጵያ ስለ ዓለም ስልጣኔ ብሎም በጥልቅ ስለማይታወቀው ስላልተመረመሩት
ለሎች ዓለማት ጨምሮ የሚያወሳ ነው።
  #መሪ ራስ ዓማን በላይ ነኝ
መጽሐፎቼን የምጽፋቸው ለህትመት ይበቁልኛል ብዬ ሳይሆን የኢትዮጵያ ታሪክ ትውልድ ሳያውቀው ተከድኖ በመኖሩ ይቆጨኝ ስለነበር ነው። አንድ አንዶች የኢትዮጵያ ታሪክ እንዲሁም መሰረት የሌለው የሚመስላቸው አሉ እንደዚህ አይነት እሳቤዎች በእርግጥም የተሳሳቱ ናቸው። ምክኒያቱም ኢትዮጵያ እነሱን ጨምሮ የእነሱን ዘር ማን ዘር ከመፈጠራቸው በፊት የነበረች ሃገር ናት ። ነጮች ልብስ መልበስ ሳያውቁ በፊት ኢትዮጵያውያን በስልጣኔ በአመራር ጥበብ በህክምና በምህንድስና ሳይቀር ትልቅ ቦታ የነበራቸው ህዝቦች ነበሩ። በነዚህ ጉዳዮችም በተለያዮ መጽሐፍቶቼ ላይ ያካተትኩ ሲሆን ወደ ሃያ አራት (24) የሚደርሱ መጽሐፍቶችን መሳተም ችያለሁ። ሆኖም ለህትመት ያልበቁ ሌሎች ስራዎች አሉኝ። ይህን ሃሳብ ይዤ ነው እንግዲህ የጥንታዊቱዋ #ኢትዮጵያ ትንሳኤ ታሪክ የሚለውን መጽሐፍ የጻፍኩት ። በዚህ መጽሐፍ ውስጥም ማንም ከዚህ ቀደም ስለ ኢትዮጵያ  የማያውቃቸውን ለማመን የሚፈታተኑ ታሪኮች አሰባስቤ የጻፍኩት። እውነት ግን መጪውም ሆነ አሁን ያለው ትውልድ ያሳዝነኛል። እኛ ቀደምቶቹም ብንሆን እውነተኛ ታሪክ ባለማወቅ እውነተኛ ማንነቱ ጠፍቶበት በየሄደበት ታሪኩን ለማግኘት የሚናውዝ በስጋው በነፍሱ የማንነቱ ገናናነት እየታወቀው ዓለም  ሳያውቀው በመቅረቱ ሲያሳንሰው ተደቁሶ  የሚኖር እንደ ግማሽ እብድ የሚያደርገው ስለ ታሪኩ ገናናነት ሲገልጽ ሲሞክር በውስጡ ያለውን አውጥቶ መናገር መግለጽ ስለሚሳነው ዓይኖቹን በማፍጠጥ በቁጣ መንፈስ የሚጋጭ የገዛ ወንድሙን ኢትዮጵያን አገሬን  እንደኔ አታውቃትም አትወዳትም ብሎ የሚደነፋ ነበር። #አሁን ያለው #የማንነት ግራ መጋባት ያናወዘው ነው። የሃገራችን ታሪክ መዛባት ና መጥፋት መነቀፍ የጀመረው ደግሞ ከእኛ ዘመን ቡኃላ በመጣው ትውልድ ነው።
    #የትውልድ ቦታዬም ሆነ ዕድገቴ #ጎንደር_በለሳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው። ገና በልጅነቴ ለትምህርት በሰጠሁት ቦታ ትኩረት ከፍተኛ ነበር። የትምህርት ጥማት ስለነበረብኝ ገና በልጅነቴ ከቤተሰቦቼ ተለይቼ ለዕረጅም ዓመታት ከደብር ደብር እየዘዋወርኩ የቤተክርስቲያን ትምህርት ልቅም አድርጌ ተማርኩ ቤተሰቦቼ ለዘመናት ስለጠፋሁባቸው ጫካ ለጫካ ስሔድ አውሬ በልቶት ይሆናል ብለው እርግጠኛ በመሆን እርማቸውን በለቅሶ ካወጡ ከሰላሳ ከ(30) ዓመት ቡኃላ በህይወት እንዳለሁ አወቁ ። በህይወት አጋጣሚ ብዙ ሃገር ዞሬአለሁ ። በተለይም የማረሳውና ወደ ጥልቅ ጥናት እንዳመራ መንገድ የከፈተልኝን ምስጢር ያገኘሁት ከዛሬ 45 ዓመት በፊት በ19 ዓመቴ ወደ #ሱዳን ኑቢያ ሔጄ በነበረበት ወቅት ነው።  በአንድ ቤተክርስቲያን ግቢ በነበረ የድንጋይ ሳጥን ውስጥ የተገኙ በርካታ የብራና መጻህፍትና ለሃገራችን ታሪካዊ ጥናት አዲስ የምርምር ዕይታ የከፈቱልኝ ነበሩ። በወቅቱ በገዳሙ ውስጥ የነበረኝ ቆይታ እንደ ማንኛውም የሃይማኖት አካልና ተማሪ ነበረ ።
ይሄ ወቅት 1950ዎቹ መጨረሻ የጥንቱዋ ኑቢያ ከነበሩ የጥንት ቤተክርስቲያኖች ፍርስራሽ ውስጥ #የብራና መጻህፍት ማግኘት ችዬ ነበር።
ወደ #ኢትዮጵያ እንደተመለስኩ ብራናዎቹን ለቀዳማዊ አጼ #ኃይለ ስላሴ አሳየዋቸው አጼውም ብራናዋቹን ተመልክተው በጊዜው ለነበሩት የትምህርት ምኒስትር ላኩዋቸው #ምኒስትሩም ብራናዋቹን ተመልክተው አሁን ይህን አሳትመህ ብታቀር  የሚያምንህ የለም።
ዝም ብለህ ጹሁፎቹን እያጠናህ እየተረጎምክ ቆይ ከዛ አመቺ ጊዜ ሲገኝ አሳትመን ለዓለም እናቀርባለን። አሉኝ።   ምክኒያቱን ባላውቀውም የተባለው ቃል ሳይፈጸም ቀረ  ለብቻዬ ሆኜ ከብዙ አመታትና ልፋት ቡኃላ #ብራናዋቹን መተርጎም ቻልኩ።

ጹሁፎቹ የተጻፍት በጥንቱ #ሱባ ቋንቋና በጥንቱ የመሮ ፊደላት እናም በግዕዝ ልሳናት ነበረ። እነዚህን ለመተርጎም እረጅም ጊዜ ፈጀብኝ ሁለቱን ቋንቋዎች ለመተርጎም በቂ እውቀት ያለው ሰው ማግኘትና እንዲመጥን አድርጎ መተርጎም ከባድና ፈታኝ ነበር። በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያ ያልተነገሩ  ሚስጥራትን ለማወቅ ከጠቅላይ ግዛት ወደ ጠቅላይ ግዛት እየተዛወርኩ  #ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጋር እየተገኛኘሁ ስለ #ኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ መመራመርና ማወቅ ችያለሁ። የተለያዩ ቦታዎች  ያሉትንም ብርቅ መጻሕፍት ለማወቅ ዕድል አግኝቻለሁ ።   እነዚህን መጻህፍት አሰባስቤ መጻህፈ_ሱባዔ የተባለውን የመጽሐፉን ንድፍ ጽፌ ለወዳጆቼ ሳሳያቸው ከዛም አማን_በላይ ብለው በስሜ የባለቤትነት መብት አያይዘው ይሰጡኛል። ከዛም በጣም በረጃጅም ዐርፍተ ነገር የጻፍኳቸውን ጹሁፍ ሳላስተካክል የላኩላቸውን እነሱ በበኩላቸው ለአንባቢ እንዳያሰለች በአጭር በአጭሩ እየከፋፈሉ እንዲመች አድርገው እያዘጋጁ ያስደስቱኝ ነበር።

በዚህ መልኩ ያሰባሰብኩዋቸውን ጹፎች ወደ መጻህፍት መቀየር ብዙ አላስቸገሩኝም ነበር።
እንደ ነገርኳቹ አብዛኛው የምጽፋቸው ጹሁፎች  በሰው ልጅ በጥልቀት ስላልተዳሰሱ ስለ ዓለማት ሚስጥር ነው። በተለይም መጻህፈ_ብሩክ_ዣንሽዋ መጻህፈ_ክቡር የተባሉ መጻህፍቶቼ ከኢትዮጵያ በአሳሹ ጀምስ_ብሩስ ተሰርቀው ከወጡት ታላላቅ የሚስጢራት  አንዱ በሆነው መጻህፈ_ሄኖክ ዙሪያና አልበርት_አንስታይን ሳይቀር ተመራምሮ ሊፈታቸው ስላልቻለው ስለ ሌሎቹ ዓለማት ሚስጢራትና እኛ ስለምንኖርባት ምድር ትልቅ ሚስጢሮች ነው። እኔም ኢትዮጵያን የእነዚህን ድንቅ ሚስጥራት የያዙ
መጻህፍት ባለቤት እንደመሆናችን  የማወቅ መብት አላቸው ብዬ ስለማምን ሁሉንም ሳይሆን ለንባብ ይመጥናሉ ያልኳቸውን ለንባብ ።

Friday, December 21, 2018

joseph cabkla

ካቢላ በመጨረሻም እጅ ሰጡ ። የቀድሞዋ ዛተር የእድሁንዋ DRC #president በመሆን አባታቸው ሲገደሉ ካባታቸው ስልጣን በመረከብ በ29 አመታቸው ወደ ስልጣን የመጡት ካቢላ መካሄድ የነበረበትን ምርጫን አራዝመው ስልጣንን የሙጥኝ ብለው ቆይተዋው ነበረ አሁን ግን እ.ኤ.አ በ2019 ምርጫውን በማድረግ ስልጣን ለማስረከብ መወሰናቸውን ተናግረዋል።
በማእድን ሀብቱዋ እጅግ ሃብታም የሆነችውና የቆዳ ስፋትዋም #ትልቅ ሲሆን ፥ ይህችው ሃገር #ጆሴፍ ካቢላ ካባታቸው የወረሱትን ስልጣን ወደ 18 አመታት ያኽል ቆይተውበታል የበዛ ሃብትም አካብተውበታል ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው እስክ 6 ቢሊየን ዶላር ይገመታል -የራሳቸውና የቤተሰባቸው ሃብት። በብዙ ቢዝነስም በሃገሪቱ ተሳታፊዎች ናቸው እርሳቸውም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው።በቀድሞው #ሞቡዩ ሴሴሴኮ በርካታ #ቢሊየን ዶላር የተመዘበረችው የቀድሞዋ ዛየር ያሁነና #DRC ሰላም ከራቃትና ብጥብጥ መመለስ ከጀመረች ቆየች። የኦቦላ ወረርሽኝም ሌላው ፈተናዋ ነው።
DRC #የኮባልትሽየአለም 90 በመቶ ምንጭ ስትሆን የቆዳ ስፋትዋም በአፍሪካ ትላልቅ ከሚባሉ አገራት አንዱዋ ነች።

ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ በኢትዮጲያ

እንድ የህግ ምሁር #ህገ መንግስታዊ አጣሪ ፍርድ ቤት ይቁዋቁዋም ሲሉ ፥ ህገ-መንግስት አጣሪው የፌዴሬሽን ም/ቤት መሆኑ የህግ አተረጉዋጎም ላይ ችግርን እንደፈጠረ መረዳት ይቻላል።
አስፈጻሚው ይህን ከባድ ህግን የመተርጎምን ስልጣን በ#ህገ_መንግስታዊ #ፍ/ቤት አማካይነት ለነጻ #ዳኞች መስጠት #ስላልፈለገ ቀስ ብለን መጀመርያ አጣሪ ፍ/ቤት ይቁዋቁዋም እሚለው ሃሳብ ዞሮ ዞሮ አሁንም የፌ/ም/ቤት የመጨረሻው ስልጣን #ከም/ቤቱ እጅ አይወጣም ይኽም #ህገ መንግስቱን ማሻሻልን እሚጠይቅ ነው።
#አቶ_ ሌንጮ ለ#Nahoo_ TV በሰጡት ቃለ ምልልስ #ህገ- መንግስቱን የ84ዓ.ም ቱን ቻርተር ማለታቸው ነው ያረቀቅነው እኔ መለስና "ህወህት ሻእብያና ኦነግ ሆነን "ነው  ብለዋል :: ይህ #ህገ-መንግስት #አማራው" አይወክለኝም፥አገር አልባ አድርጎኛል "  ሲል ትግራይ ክልል ደግሞ እስቲ "ከህገ መግስቱ አንድ አንቀጽ ይነካና" እያለ ያሳስባል። ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው በማንንነትና የአስተዳደራዊ ድንበር ኮሚሽን ይቁዋቁዋም ተብሎ በጠ /ሚ/ሩ ሲወሰንና በፓርላማ ሲጸድቅ የህውሃት አክቲቭስቶች #daniel-birhaneን ጨምሮ አምርረው ሲቃወሙ በአማራ ክልል በተደረጉ እንድ ሰልፍ ደግሞ #ህገ-መንግስቱ# ይህንን የድንበርንና የማንነት ጥያቄን ሊፈታው ስለማይችል# "ፖለቲካዊ_ መፍትሄ _ያስፈልገዋል " ብሎ #ህዝብ ሰልፍ ነው የወጣው።
ወደ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ፤  #internally_displaced ወይም የሃገር ውስጥ ተፈናቃይ #ህዝብ ያለ #ሲሆን ለዚህም አንዱ ምክንያት# የፌደራል አከላለሉ #ያለጥናት መካሄዱና #የአማራና #የኦሮሚያ_ ክልሎችን ሆን ተብሎ ለማጥበብ የተደረገ ነው ብለው እሚተቹት አሉ።ለምሳሌ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል #ካማራና ኦሮሚያ ክልሎች ተቀንሶ አለአግባብ ሰፊ እንዲሆንና #የአጎራባች #ክልሎችን #ግዛት አላግባብ #እንዲጠቀልል ተደርጎአል።
ይህም በፈንታው እንደ #እስራኤል ዙሪያዬን ተከብብልአለሁ የሚል የ( #seige mentality) በህወህስት ዘንድ እንዲደጠር አድርጎአል።# ዶ/ር_ ደብረጽዮንም ሁለት የተምታታ #መልእክትን ባንድ #በኩል ወጣቱ ለምናደርግለት ጥሪ #ይዘጋጅ ብሌልሳ በክክል ደግሞ #ከፌደራል መንግስቱ ጋር በጋራ እንሰራለን የሚሉ ንግግሮችን #አድርገዋል።

Friday, December 14, 2018

usa,china,russia africa relations in africa

#US አሜሪካ የአፍሪካ #ፖሊሲዋን ልትፈትሽ ነው
ብዙ ግዜ ያሜሪካ ፖለቲከኞች አፍሪካን የዘነጋ ፖሊሲን ይከተላሉ ይባላሉ ። ያሁኑ ፕሬዝደንት ትራምፕ ፖሊሲ "prosper Africa " ይሰኛል። አሜሪካ የዘነጋቻት አፍሪካ የሩስያና የቻይና ተጽእኖ እየሰፋ መሄድ አሁን እያሳሰባት ይመስላል። ለምሳሌ በጣም ቁልፍ በሆነችው ጅቡቲ ቻይና የጦር ሰፈር ሲኖራት ሁለት ተፎካካሪ ሃያላን ማለትም ቻይናና አሜሪካ በአንድ ሃገር የጦር ሰፈር ጎን ለጎን ሲኖራቸው በታሪክ የመጀመርያው ነው። ጅቡቲ ለጦር ሰፈር ኪራይ ከሁለቱም በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር ክፍያን ታገኛለች። አሜሪካ ቻይና ጅቡቲ ላይ ያላት ተጽእኖን ባለመውደድዋ ኢትዮፒያ 95 በመቶ የገቢና ወጭ ንግድ እምታስተናግደውን ጅቡቲን ትታ ወደ ኤርትራና ሶማልያ ወደቦች ፊትዋን እንድታዞር ትሻለች። በዚህም ተሳክቶላት ኢትዮ-ኤርትራን በኤሚርቶችና ሳኡዲዎች በኩል ማስታረቅ ችላለች።  ጅቡቲ ደግሞ ከግብጽ ጋር ሞቅ ያለ ግንኙነትን ጀምራለች። ይህ ሁሉ አሜሪካ አምባገነኖችን በአፍሪካ መደገፍዋ የፈጠረው ክፍተት ለሩስያ በተለይም ለቻይና አመቺ ሁኔታን ፈጥሮአል.። USA ከቻይና ጋር በገባችው የንግድ ጦርነትም ካአፍሪካ ሃገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላትን ቻይናን ማድከምና ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ ማምጣት አልቻለሽም።
አሜሪካ ከአፍሪካ ጋር ያላት ግንኙነት #በጸረ-ሽብር ርግል ዙሪያ ብቻ የተቃኘ #መሆኑ ሲጎዳት አሁን በዚህ ዘርፍም ሶማልያን ጭምር በመተው ሊቢያና #ማሊ ላይ ብቻ ትኩረትን ለማድረግ ወስናለች።

This administration will not allow hard-earned taxpayer dollars to fund corrupt autocrats, who use the money to fill their coffers at the expense of their people, or commit gross human rights abuses,” said #Mr. Bolton.የፕሬዝደንቱ የደህንነት አማካሪ። #አሜሪካ ቻይና በብድር እዳ አፍሪካን ማስመጥዋንም አልወደደችውም።
The predatory practices pursued by China and #Russia stunt economic growth in Africa, threaten the financial independence of African nations, inhibit #opportunities for U.S. investment, interfere with U.S. military operations and pose a significant threat to U.S. #national security interests,” #John Bolton,# Mr. Trump’s national #security adviser, said

joseph cabkla

ካቢላ በመጨረሻም እጅ ሰጡ ። የቀድሞዋ ዛተር የእድሁንዋ DRC #president በመሆን አባታቸው ሲገደሉ ካባታቸው ስልጣን በመረከብ በ29 አመታቸው ወደ ስልጣን የመጡት ካቢላ መካሄድ የነበረበትን ምርጫን አራዝመው ስልጣንን የሙጥኝ ብለው ቆይተዋው ነበረ አሁን ግን እ.ኤ.አ በ2019 ምርጫውን በማድረግ ስልጣን ለማስረከብ መወሰናቸውን ተናግረዋል።
በማእድን ሀብቱዋ እጅግ ሃብታም የሆነችውና የቆዳ ስፋትዋም #ትልቅ ሲሆን ፥ ይህችው ሃገር #ጆሴፍ ካቢላ ካባታቸው የወረሱትን ስልጣን ወደ 18 አመታት ያኽል ቆይተውበታል የበዛ ሃብትም አካብተውበታል ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው እስክ 6 ቢሊየን ዶላር ይገመታል -የራሳቸውና የቤተሰባቸው ሃብት። በብዙ ቢዝነስም በሃገሪቱ ተሳታፊዎች ናቸው እርሳቸውም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው።በቀድሞው #ሞቡዩ ሴሴሴኮ በርካታ #ቢሊየን ዶላር የተመዘበረችው የቀድሞዋ ዛየር ያሁነና #DRC ሰላም ከራቃትና ብጥብጥ መመለስ ከጀመረች ቆየች። የኦቦላ ወረርሽኝም ሌላው ፈተናዋ ነው።
DRC #የኮባልትሽየአለም 90 በመቶ ምንጭ ስትሆን የቆዳ ስፋትዋም በአፍሪካ ትላልቅ ከሚባሉ አገራት አንዱዋ ነች።