Friday, February 6, 2015

የአሜሪካ የኢራቅ ወረራ



ፖል ብለሬመን አሜሪካ ሆነ ብላ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲን ትከተል እንደነበረ በፃፉት መፅሀፍ አጋልጠዋል ፡፡ አሜሪካና እንግሊዝ የኢራቅን የመከላከያና የፖሊስና የደህንናት ተቋማትን በማፈራረስ ፣ ሃገሪቱን በእጃቸው ካገቡ በኋላ በአገሪቱ ላይ ያደረጉት ጉዳት ከባድ ነው ፡፡  በ 1991 የህዝብ አመፅ በኢራቅ የነበረ ሲሆን አሜሪካውያን ይህንን የህዝብ አመፅ ባልደገፉትም አሜሪካ እንግሊዝ የፈለጉት አልላገኙም ፡፡
አሜሪካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርት ወዲህ በዓለም ዙሪያ 54 መንግስታትን በቀጥታ በራሷ ጣልቃ ገብነት ገልብጣለች ወይንም በተዘዋዋሪ መንገድ በደህንነት ተቋማቶቸዋ እና ከሌሎች ታባባሪዎቿ ጋር ሆና አስገልብጣለች ፡፡
አሜሪካ ለአልማሊኪ መንግስት ኢራቅን ለቃ እንድትወጣና በአለም ግዙፉን ኤምባሲ በማቋቋም ለማካከስ ብትሞክርም አሜሪካ ስትራቴጂያዊ  በሆነችውና የገዘፈ የነዳጅ ክምችት ባላት ኢራቅ ወታደራዊ የጦር ሰፈር መኖሩ እጅግ ይጠቅማት የነበረ በመሆኑ መቆጨቷ ግልፅ ነው ፣ ነገር ግን ኢራቃውያን የአሜሪካንን ወታደራዊ የጦር ሰፈር አንፈልግም በማለታቸው ግን ፕሬዝዳንት ኦባማ ሌላ አማራጭ ስላልነበራቸው ለቀው ለመውጣት ተገደዋል ፡፡
 ከዚህም በተጨማሪ በኢራቅ ምክር ቤት እንዲሁም በሺአ የበላይነት የምትመራው ኢራቅ ወደ ኢራን ማዝመሟ ስላላስደሰታት ኢራቅን ለኢራቅ እጅግ አስፈላጊ የነበረውንና ልትሰጥ የሚገባውን ወታደራዊ የጦር መሳሪያ አቅቦትን አላደረገችም ፡፡ በዚህ ምክንያት ደካማውና አስፈላጊውን ትጥቅ በሚገባ ያላገኘው የኢራቅ ሰራዊት አይ ኤስ ኤስን መቋቋም አልቻለም ፡፡
የእንግሊዝ መሪዎች በተደጋጋሚ ለአሜሪካ ጥቅም ተጋሪ ሆነው አሜሪካ ወረራን ሲፈፅም አብረው የሚሄዱትና ወደ ጦርነት የሚገቡበት ምክንያት አንግዳ ሊሆን ይችላል ፡፡ ነገር ግን እንግሊዝ የአለም ሀያል ቅኝ ገዢ ከነበረችበት ጊዜ ጀምሮ ምንም እንክዋን ወታደራዊ የበላይቷንና በርካታ ግዛቶቿን ብታጣም ከዚያው ከቅኝ ግዛት ዘመኗ የወረሰቻቸው እጅግ ግዙፍ የኢኮኖሚና የንግድ አውታሮች ባለቤት ነች ፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ ሀይሏን ለመከላከልም የአሜሪካንን ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ሃያልነት እንደ ጃንጥላ በመጠቀም ነው የራሷን ጥቅም የምታስከብረው ፡፡
ለምሳሌ በስኮትላምደነንድ ሎከርቢ አየር ላይ የፈነዳው የፓን አም አወረውሮፕላንን በወቅቱ በጋዳፊ የምትመራው የሊቢ የደህንነት ሰዎች አፈነዱት ቢባልም አልጀዚራ የራሱን የወንጀል መርማሪዎችንና ሳይንቲስቶችን በመቅጠር በሰራቸው ጥናታዊ የዘገባ ፊልሞች ግን ትክክለኛው የፍንዳታው አቀናባሪ የኢራን የደህንነት ሃላፊዎች እንጂ የጋዳፊ ሊቢያ አለመሆኗን አረጋግጧል ፡፡ ይህም የሚያሳየው የእንግሊዝ ሆነ የአሜሪካ ባለስልያተጣናት የጉዳዩን ትክክለኛ ገፈፃሚ ቢያውቁም አልሚግራሂ የተባለው የሊቢያ የደህንነት አባል እንዳደረገው ተቆጥሮ ለእስር ተዳርገዋዋል ፡፡፡  
እንግሊዝ በተደጋጋሚ የአውሮፓ ህብረት ጋር ለመተሳርም ሆነ ዩሮን ለመጠቀም ፈቃደኛ የማትሆንበት ምክንያትም አብዛኛው የኢኮኖሚ ጥቅሟ ቀድሞ የቅኝ ተገዢዋ ከነበረችው ከአሜሪካ ጋር ይበልጥ የተሳሳሰረ በመሆኑ ሲሆን ይህንን ጥቅሟንም የምትከላከልላት ግዙፍ የመከላከያ ሃይል ያላት አሜሪካ ስለሆነች አሜሪካ በገባችበት ገብታ ጦርት ውስጥ የምትገባው ፡፡ 

ኢራንና ምእራባውያን

የኢራን ኢኮኖሚ ከሌሎች በመገለል ሊድግ እንደማይችል የኢራኑ መሪ ሃሰን ሮሀኒ አስታውቀዋል ፡፡ ኢራብንና ሩስጠያ ሶርያን በመደገፋቸው ዋጋን ከፍለዋል ይህም የነዳጅ ዋጋ እንዲወርድ መደረጉ እንዲሁም ሩስያ በዩክሬይን ሰበብ ሩስያ የከባድ ማእቀብ ሰለባ ሆናለች ፣ አውሮፓውያን ሳይቀር ተጎጂ በመሆናው ሩስያ ላይ የተጣለው ማእቀብ ሩስያን ይጎዳል ቢሉም አሜሪካ ግን ሩስያ ላይ አምራ ቆይታለች ፡፡
ፍልስጥኤማውያን የአለም አቀፍ የወንጀል ኮሚሽን አባል ለመሆን ያመለከቱ ሲሆን ይህም በፍልስጥኤማውያን ላይ የጦር ወንጀልን ዩፈፀሙ እስራኤላውየን የአይ ሲ ሲ አባል በሆኑ አገራት ጉዞን በሚያደርጉበት ወቅት የመታሰር እጣ የሚገጥማቸው ሲሆን የእስራኤል ባለስልጣናት በጦር ወንጀለኝነት እንዲጠየቁ ያደርጋል፡፡
ሳሂብ ኤራካት የተባሉ የፍልስጥኤማውያን ተደራዳሪ እስራኤል ምንም አማራጭ አልሰጠችኝንም በማለት እስራኤል ፍልስጥኤማውያን ላይ በፈጸመቻቸው ወረራዎችና የጦር ወንጀሎች በሰብአዊ መብት ላይ በተፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ተጠያቂ እንድትሆን ለማድረግ ነው፡፡ 
ይን እንጂ እስራኤልም በበኩላቸው ይህ የፍልስኤማውያን ድርግጊት መልሶ ራሳቸውን ፍልስጥኤማውያንን ይጎዳል ያለች ሲሆን እርሷም በበኩሏ በየወሩ ለፍስጥኤማውያን ማስገባት የነበረባትን 128 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የያዘች ሲሆን አሜሪካ ለፍልስጥኤማውያን የምትሰጠውን ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሆነ ገንዘብንም አሜሪካ እንድትይዝ እየገፋፋች ትገኛለች ፡፡ እስራኤል ወታደሮቿና ባለስልጣናቷ በዓለም የጦር ወንጀለኛ በሚያደርግ የዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀለኝነትን በሚያየው ፍርድ ቤት መቅረባቸው አደጋውን በመረዳት ያሰጋት ሲሆን ለዚህም ይመስላል ሁኔታውን ፍልስጥኤማውያንን መልሶ ይዳል በማት ለማስፈራራት እየሞከረች ያለችው ፡፡
ሁሉንም ሙአባውያን ግደል በሚል መፅሀፍ ቅደስ ላይ የሰፈረውን ለመተግባር ይመስላል የአሁኑ ቤንያሚን ኔታንያሁ እያደረጉ ያሉት ብለው ይተቿቸዋል ፡፡እ.አ.አ. በህዳር 2012 ፍልስጥኤም በተባሩት መንግስተት ውስጥ የታዛቢነት ወንብርን ያገኘች ሲሆን ምንም እንኳን እስራኤል ብትቃወምም የታዛቢነት ወንበሩን አግኝታለች ፡፡

የመካለኛው ምስራቅና ነውጡ

መካከለኛው ምስራቅ ሰላምን ካጣ እጅግ በርካታ አስርት አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን እስራኤል እንደ ሀገር ከተቋቋመችበት ጊዜ ጀምሮ የዓረብና የእስራኤል ውዝብ ግብ የብዙዎቹን ህይወት ሲበላ ቆይቷል ፡፡ ‹‹የእስራኤልን ምርት ፣ እቃና አገልግሎት አትግዙ ፣ እስራኤል ላይ ማእቀብ ጣሉ›› በሚል እስራኤልን ከቀድሞው የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ስርአት ጋር በማመሳሰል እስራኤሎች በበኩላቸው  በበኩላቸው ሲመልሱ እስራኤል በአለም ላይ የብዝሀ ዘረ የሰው ዘሮችን በአገር መሆኗንና ፣ በመካከለኛው ምስራቅ በነፃነት የሚኖሩት አረብ የሆኑት የእስራኤል ዜጎች መሆናቸውንና ሲከራከሩ እንዲሁም እስራኤል ምርትና አገልግሎትን ማእቀብ መጣልና ማግለል ማለት ናዚ ጀርመን በእስራኤል እቃዎች ላይ ያደረገውን እ.ኤ.አ በ1930ዎቹ በእስራኤል ነጋዴዎችና ምሁራን ላይ ካደረገው ማግለልና ማእቀብ ጋራ ያመሳስሉታል ፡፡
እስራኤል በጋዛ ላይ ያደረገችውን ድብደባና ጦርነትን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ፍርድ ቤት ሃማስን ከአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ ሲወስን የእስራኤል መሪዎችን አብግኗል ፡፡
ራሳቸው አንዳንድ አይሁዳውያን ሳይቀሩ ፣ ሜድ ኢን እስራል የሚሉ ሸቀጦችን አንገዛም ማለት የጀመሩም አሉ ፡፡ በአንዳንድ አገራት እንደ ባንግላዲሽ ባሉ አገራት የእስራኤልን ብቻም ሳይሆን የአሜሪካንን እንደ ፔፕሲና ኮካ ኮላ ያሉትን ምርቶችን ላለመግዛት ማእቀብ እስመጣል ደርሰዋል፡፡ ስቴፈን ሀውኪንጊስና ስቲቪ ወንደር እስራኤል የነበረው ኮንሰርት ሲሰርዝ ሀውኪንግስ ከእስራኤላውያን ዘፋኞች ጋ የነበረውን መገናኘትን ሰርዘዋል፡፡ የዚህ አይነት ጉዳዮች የምእራቡ ዓለም ሚዲያ ብዙም የማይዘግባቸው ናቸው  ፡፡
ሳላህዲን እየሩሳሌምን ሲይዝ ምንም ደም ያልፈሰሰ ሲሆን በአንፃሩ ግን የመስቀል ተዋጊዎች እየሩሳሌምን ሲይዙ ግን የመስቀል ተዋጊዎች በርካታ ደም አፍስሰዋል የሚል ክርክርን የዓረብ ታሪክ ጸሀፍት ታሪክን በመጥቀስ  ያወሳሉ፡፡
የዛሬውን አያድርገውና በስፔን እስላሞች ገዢ በነበሩበት ወቅት አይሁዳውያን በነፃነት እንያምኑ ይፈቅዱ ስለነበረ
ስሊሞች የጸሎት አቅጣጫቸውን ወደ አልአቅሳ መስጊድ አድርገው ነው የሚሰግዱት ፡፡ ለሶስቱም እምነቶችም ማለትም ለክርስትናም ፣ለአይሁድና ለእስልምና እምነቶች አልአቅሳ መስጊድ ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡ ነቢዩ ፣መሀመድ ሲያርፉ ከመካ ወደ አልአቅሳ መስጊድ ከዚያም ወደ አላህ ያረጉበት ነው ብለው ሙስሊሞን የሚያምኑበት ቅዱስ ስፍራ ነው ፡፡ እስራኤል በእየሩሳሌም ለመጣ ምንም አይነት ምህረት እንደሌላት በተደጋጋሚ በወሰደቻቸው የጭካኔ እርምጃዎች አሳይታለች ፡፡
የእስላሙ ዓለም ችግር አንድነት አለመኖር ፣ አንዱ ሲሆን ሌላው ምንም እንኳን ሂሳብን ፣ ሳይንስንና አስትሮኖሚንና ህክምናን የመሳሰሉ ጥንታዊ ጥበቦች ያፈለቁትና አውሮፓውያን በጭለማው ዘመን በነበሩበት ወቅት ከግሪኮችና ከሮማውያን የተገኙ ታላላቅ አስተሳሰቦችን የፕሌቶን ጨምሮ ለተቀረው የሰው ልጅ ጠብቀው እንዲተላለፍ ያደረጉት አረቦች ቢሆኑም በዘመናዊ ጊዜ ግን የአረቡ ዓለም በሳይንስና በቴክኖሎጂ ወደ ኋላ መቅረቱ በትምህርት እና በእውቀት ከአይሁዳውያን ጋራ የሚወዳር አለመሆናቸው ሌላው የአረቦች ድክመት ነው ፣‹‹በአላህ ገመድ ላይ በአንድነት ተንጠላጠሉ ፣ አትለያዩ ›› ቅዱስ ቁርአን ላይ የሰፈረ ቢሆንም እስላሞች እርስ በእርስ አንድነት ያላቸው አይደሉም ፡፡
በእስልምና ሃይማኖት የሚደረጉ ቅጣቶች ለምሳሌ በጅራፍ መግረፍ ፣ የመሳሰሉት እስላማዊ ምሁራን በሚከራከሩበት ወቅት እንደሚሉት በምእራቡ ዓለም እንደሚታየው አንድን ሰው በትንሽ ጥፋት አስርት አመታትን በእስር የሚያሳልፍበት ፣ በርካታ ገንዘብ የሚቀጣበት ስርአት ይልቅ ለጥቱ ከተፀፀተ ይቅርታን የሚያደርገው የእስልምና ሃይማኖት የተሻለ ነው የሚል ክርክርን ያቀርባሉ ፡፡
አይሁዳውያን 10 እና 13 በመቶ ድረስ በፒኤች ዲ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን በአረቦች ግን አንድ ከሚሊንም አይገኝም ይላሉ ራሳቸው አረቦች ፡፡ ከዘከ
ከዚህ አንፃር ለክፍለ ዘመናት አይሁዳውያን አንድነታቸው እጅግ ጠንካራ ሲሆን በየትኛውም አገር የሚገኙ አይሁዳውያን ዓለም ዓቀፍ በሆነ ሁኔታ የሚኖሩበት አገር መለያየት የተነሳ ዜግነታቸው እንኳን ቢለያይ በአይሁድነታቸው ግን አንድነታቸውን እንደጠበቁና እርስ በእርስ በመገናኘት የአውሮፓንና የሃያሊቱን አሜሪካን መሪዎችንና ግዙፍ ዓለም ዓቀፍ የንግድና የሚዲያ ተቋማትን በመዳፋቸው በማስገባታቸው ምክንያት አይሁዳውያኑ ያላቸው ዓለም አቀፋዊ ሀይልና አቅም እጅግ ጠንካራና የማይደፈር ነው ፡፡
በምእራቡ ዓለም ያሉ አይሁዳውያያን በእስራኤል ካሉ አይሁዳውያን ጋር ያላቸውን ትስስር እየቀነሰ መጥተዋል የሚሉ ጥናች አሉ ፣ በምእራቡ አለም ያሉ አይሁዳውያን ለፅዮናዊቷ እስራኤል ያላቸው ድጋፍ እየሳሳ መጥቷል ፡፡
አል አቅሳ መስጊድ በሰለሞን የተነገነባ በነቢዩ ሱሌይማን ነው ፡፡ ሙሴ እስላም ነው ፡፡
ቦኮ ሀራምና አይ ኤስ አይኤ አል ቃኢዳን የመሳሰሉ ለእስልምና መልካም ገፅታን በማጉደፍ በኩል ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ራሳቸው የእስላማዊ ምሁራን የሚያነሱት ጉዳይ ነው ፡፡ በእዝነት ‹ኮምፓሽኔት› አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተው እስልምና አውሮፓም አሜሪካ እስልምናን ይፈራሉ እስላም ኮምፓሽኔት እምነት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ይህንን የእስልምናን ገፅታ ለዓለም በደንብ ማሳየት ይገባናል ባይ ናቸው ፡፡

የቀድሞው የአሜሪካን ፕሬዝደንት የነበሩት ቢል ክሊንተን በህይወት ታሪክ መፅሀፋቸው ላይ ሲፅፉ ‹‹ምንም እንኳን የአሜሪካን ፕሬዝደንት በዓለም ላይ በጣም ሀያሉ ሰው ቢባልም፣ ምንም ማድረግ የማንችልባቸውና አቅመ ቢስ የምንሆንባቸው በርካታ አጋጣሚዎች አሉ›› ብለዋል ፡፡
በምእራባውያንንና በኢራን መካከል የሚደረገው ኢራንን የኒውክየር ጦር መሳሪያ  ግንባታን ለማስተው የሚደረገው ድርድር በአብዛኛው ለአለመተማመኑ መንስኤ የኢራን መሪዎች ለእስራኤል ያላቸው ክፉኛ መጠራጠርና አለመተማመንና ጥላቻ ሲሆን ኢራን የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ብትታጠቅ ስጋቱ ለአሜሪካ ሳይሆን ለእስራኤል መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
አሜሪካኖች የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ጃፓን ላይ የተጠቀሙበትን የአቶሚክ ቦምብ የተሰራበትን ህንፃና አካባቢውን ወደ ሙዚየምነት ቀይረውታል ፡፡ በዚህም ‹‹የሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዲያበቃ ያደረጉ›› የሚል ፅሁፍ የተፃፈበት ይሄው ሙዚየም በሚል ታሪካዊ ሙዚየም ሆኖ በአሜሪካ መንግስት ወደ ሙዚየምነት መለወጡ ጃፓናውያንን ቅር አሰኝቷል ፡፡
ኢራን ኒውክሊየርን ለሰላማዊ አገልግሎት ነው የማበለፅገው ትበል እንጂ በተግባር ግን ለቦምብ መስሪያ ነው ለዚህም የደህንነት መረጃ አለን የሚሉት ምእራባውያን የቀድሞው አክራሪው መሪ አህመዲን ነጃድ ከስልጣን ከወረዱ ወዲህ ከአዲሱ መሪ ጋር መልካም ግንኙነትን በመፍጠር ድርድር ጀምራ የቆየች ቢሆንም ከሶስት ወራት በኋላ ዳግም መሪዎቹ ሲገናኙ በኢራን በኩል እብምብዛም የአቋም ለውጥ ባለመኖሩ ምክንያት እንደገና ተጨመናሪ ጊዜን ለኢራን ለመስጠት ምእራባውያኑ ተገደዋል ፡፡
በኢራን አመራር በኩል ምእራባውያኑም ሆኑ እስራኤል ትክክለኛ ጥርጣሬ አላቸው ይሄውም በኢራን በጣም ቀወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በውሳኔን የሚሰጡት አያቶላህ ሲሆኑ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ባለመሆናቸው ምክንያት በሻሆች የምትመራው ኢራን ለዘብተኛ ሆና የኒውክሊየር ጦር መሳሪያ ማበልፀጓንና ምርምሯን ታቆማለች ብሎ ማሰብ ፈታኝ ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ከእስራኤል ጋር ጦርነት ላይ ያሉትን ሃማስንና ሂዝቦላህን በገንዘብና በመሳሪያ የምትደግፈው ኢራን ፣ እንዲሁም በኢራቅ የሺአዎችን መንግስት የምትረዳው እንዲሁም በአካባቢው ሺአዎች ባሉባቸው እንደ ባህሬን ፣ ሳኡዲ አረቢያና የመን ባሉ የአረብ አገራት ውስጥ ተሰሚነት ያላትና ከሱኒ አረቦች ጋር ታሪካዊ የሆነ የከረረ ውዝግብ ያላት ፣ እንዲሁም በምእራባውያንና በሱኒ የአረብ መንግስታ እየተረዳ ለስምንት አመታት በጦርነት የተገተጋት የኢራቁ ሳዳም ሁሴን የመረረ ትውስታ ያላት ኢራን ኒውክሊየር መታጠቅ ያስፈልገኛል ብትል ከራሷ አንፃር ካለባት ስጋት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡   
ሳኡዲ አረብያ ካላት ዳጎስ ያለ የገንዘብ ምንጭ በመጠቀም የአረብን አለም ለማረጋጋት  ተጠቅማበታለች ፡፡ ለምሳሌ የአል ሲሲን መንግስት ለመደገፍ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በብድርና በነዳጅ ዘይት ስጦታ ለግብፅ የሰጠች ሲሆን ግብፅ የከፋ የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ እንዳትገባ ፤ለማገዝ መሆኑ የታወቀ ነው ፡፡ ሳኡዲዎች ወታደራዊውን መንግስት ሲደግፉ በአንፃሩ ትንሽዬዋ ኳታር የግብጽን ወታደራዊ መንግስት አለመደገፍ ብቻ ሳይሆን ያላትን ግዙፉንና ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ያለውን አልጀዚራን በመጠቀም በግብፅ ወታደራዊ መንግስት ላይ ዘመቻ ስታካሂድ በዚህም የበሸቀው የግብፅ የአል ሲሲ መንግስት ሶስቱን በግብፅ ለአልጀዚራ ሲዘግቡ የነበሩትን ጋዜጠኞች በማሰርና የአልጀዚራ ጋዜጠኞችን ከግብፅ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷል ፡፡ የውጭ ሀገር ሰራተኞችን ጉልበት ትበዘብዛለች ተብላ የምትታማው ኳታር
እ.ኤ.አ. በ2014 ዓም በጋዛ በተደረገው ጦርነት ጋዛን እንዳልነበረ አድርጋ ያወደመችው እስራኤል የወደመውን የጋዛ ከተማ እንዲገነባና ቤቶቹም ተመልሰው እንዲሰሩ የሚያስፈልገውን ሲሚንቶ እንዳይቀርብ በመከላከሏ ምክንያት ጋዛን መልሶ ለመገንባት አስርት አመታት ያስፈልጋል ብለዋል ፍልስጥኤማውያን ፡፡
ሳኡዲ አረብያ ለደሀይቱ ጎረቤቷ ለየመንም እንዲሁ በቢሊዮንኖች የሚቆጠር ገንዘብ የለገሰች ሲሆን የመን መረጋጋት ከራቃት ውሎ አድሯል ፡፡ በተለይም የሳኡዲ ሱኒ መሪዎች የሚፈሯቸው የሺአ ሚሊሺያዎች ሰፊ የየመንን ግዛት መቆጣጠራቸው ስላሰጋት እርዳታዋን ለመቀነስም ተገዳለች ፡፡ 
የመካከለኛው ምስራቅ ውዝግብ ዋነኛ ገጽታዎች ሶስት ሲሆኑ አንዱ አረቦች እና ኢራን  ከእስራኤል ጋር ያላቸው የድንበርንና የይገባኛል የቆየ ውዝግብ ሲሆን ፣ ሌላው አክራሪ አረቦች ለምእራባውያን ያላቸው ጥላቻና ምእራባውያን እስራኤልን በመደገፋቸው ያላቸው ቁርሾ ሲሆን ፣ ከዚህም በተጨማሪ በራሳቸው በአረቦች መሀከል ያለው ታሪካዊ የሆኑ የሀይማኖትና የፖለቲካ ልዩነቶች ናቸው - ለዚህም አይነተኛ ማሳያው በሺአዎችና በሱኒዎች መሀከል ያለው ልዩነት በዓለማዊና በአክራራ አረቦች መሀከል ያለ ልዩነት ፣ እንዲሁም ወታደሩ ጠንካራ በሆነባቸው እንደ ግብፅና አልጄሪያን የመሳሰሉ አገራት ከነፃነት ወዲህ ስልጣኑ ከወታደሩ እጅ ሊወጣና የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን መምጣት አለመቻል፣ እንዲሁም በአሜሪካንና በምእራባውያን የሚደገፉ የዓረብ ንጉሳውያንና እነሱን እንደ ጨቋኝ በሚቆጥሩ የአረብ ብሄረተኞች መሀከል የአቋም ልዩነቶች አሉ ፡፡ እነኚህ ልዩነቶች ከአረብ ስፕሪንግ ማግስት በብዙዎች የአረብ አብዪት በተካሄደባቸው የአረብ አገራት ውስጥ ሰላምን ለመንሳትና ከነፃነታቸው ወዲህ ታይቶ ለማይታወቅ ለከረረ የእርስ በእረስ ጦርነት የዳረጋቸው ሲሆን ሊቢያ ፣ የመንና ፣ ሶርያና ኢራቅ ፣በመጠኑ ግብፅ (ከሊቢያ ጋር ባለው በድንበሮቿ አካባቢና በሲናይ በረሀ በሚገኘው ግዛቷ ውስጥ) በእርስ በእርስ ጦርነት ሰለባ ሆነዋል ፡፡
በራሳቸው በመካለኛው ምስራቅ አገራት በሱኒዎችና በሺአዎች መሀከል ያለው የቆየ ታሪካዊ ሀይማኖታዊ ልዩነት ራሱ ቀላል የማይባል  ልዩነትን የፈጠረ ሲሆን ለኢራንና ለአረቦች አለመተማመን ዋናው ምክንያትም ነው ፡፡ በተመሳሳይም በየመን ውስጥም አንዱ ለእርስ በእርስ ጦርነት መንስኤ የሆነው ነገር ይሄው የመን ውስጥ ባሉ ሺአዎችና ሱኒዎች እንዲሁም በየመን በሚገኘው አልቃኢዳ ክንፍ መሀከል ነው ፡፡
አንዳንድ ተአቺውቀ ዎደች እንደሚሉት እስራኤል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በናዚ የጦ ካማምፖሰች ውስጥ በጋዝ እየታጠኑ ሲፈጁ በተነመሳሳይም እስራኤል በስዊዝ ካናል ያትን ፍልስጥኤማውያንን የሚያገኛናኙ ቦዮችንና ዋሻዎችን በጋዝ እንደምታጥን የአሁኗ ናዚ ማለት የፅዮናውያን እስተራኤል ነች ይሏታል ፡፡
የዓረብና የእስራኤል ውዝግብ ምን ያህል አደገኛ ደረጃ ላይ እንደደሰረ ለማሳየት ይረዳ ዘንድ እስራኤል የሰባትና የስምንት አመት ህፃናትን ጨምሮ ደረታቸውና ግንባራቸው ላይ በሚያነጣጥር የአልሞ ተኳሽ (Sniper) ጠመንጃ እየተኮሰች የምትገድል ሲሆን ፣ በፈረንጆች አቆጣጠር 2014 ህዳር ወር ላይ የአይሁድ ምኩራብ በመግባት አምስት የአይሁድ ቄሶችን ወይም ራባዮችን በጩቤ ወግተው የገደሉ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ ገዳዮቹ በቁጥጥር ስር ቢውሉም በዚህ ያልረካችው እስራኤል የቤተሰቦቻቸውን መኖሪያ ህንፃ ለማፈራረስ በመወሰን የህንፃውን አገነባብ ስትራክቸር የሚያጠኑ የአፍራሽ ኢንጂነሮችን በመላክ ሌሎችን ቤተሰቦች ጨምሮ የሚኖሩበትን ህንፃ እንደምታፈራርስ ገልፃለች ፡፡
ከዚህ ቀደም የፍስጥኤማውያንን ቤት የማፈራረስ ድርጊቷን ያቆመች ቢሆን የእስራኤል ጄኔራሎች ለበለጠ አመፅ ይገፋል በሚል ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ፣ ነገር ግን የአይሁድ ቄሶች (ራባዮች) መገደልን ተከትሎ ግን ትታው የነበረውን የፍልስጥኤማውያንን ቤት የማፈራስ ተግባር ተመልሳበታለች ፡፡ ይህም የሚያሳየው የሁለቱ ቁርቋሶ ወደ ማይመለስበት ደረጃ መድረሱንና ለተቀረው መካከለኛው ምስራቅም ጭምር አስጊና አደገኛ መሆኑን ነው ፡፡ በዚህ አደገኛ በሆነ አካባቢ አገራት የኒውክሊየር የጦር መሳሪያን ለመታተጠቅ ቢሽቀዳደሙ አስገራሚ አይንም ፡፡
ኢራን የምትገኝበት አካባቢ ከአረቦች ጋር ትይዩ የሆነና በሻጥ አል አረብ በቀን ከ1.5 ሚሊዮን በርሜል በላይ ነዳጅ በመርከብ ከሳኡዲ አረቢያ፣ከኩዌት እና ከኢራቅ የሚጓጓዝበት ሲሆን ኢራንም በበኩሏ ጥቃት ከተሰነዘረብኝ ይህን ሰርጥ ኢራን እዘጋለሁ ብላ ዝታ ቆይታለች ፡፡ ይህን ሰርጥ የሚጠብቀው የአሜሪካ ባህር ሀይል ሲሆን በአለም ግዙፉ ከአሜሪካ ውጪ ያለ የባህር ሀይል መደብ አሜሪካ በዚሁ አካባቢ በባህሬን ሲኖራት ፣ባህሬን ላይ በተነሳው የአረብ ስፕሪንግ ፕሬዝዳንት ኦባማ የባህሬንን አመፅ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ሰምተው እንዳልሰማ ሆነዋል ፡፡
ለዚህም ምክንያቱ አሜሪካ በአካባቢው በዚህ እጅግ ግዙፍ በሆነና ለጥቅሟ በሚያስፈልጋት የባህር ሀይል መደብ ምክንያት ሲሆን ሱኒ የሆኑትና በቁጥር ከሚያንሰው የሱኒ ገዢ መደብ የወጡት የባህሬን ነገስታት ድጋፍ ስትሰጥ በአንፃሩ የባህሬን ብዙሀን በሆኑና ነገር ግን በአገራችን ከኢኮኖሚም ሆነ ከፖለቲካ ጥቅም ተገልለናል የሚሉት በቁጥር በዛ የሚሉት ሺአዎች ሲሆኑ ወደ ኢራን ልባቸው ያደላል በሚልና በሱኒዎች ከምትገዛውና ከሳኡዲ አረቢያ ድጋፍን በምታገኘው ባህሬን ጥቅማቸውን  የሚያስከብር ግንኙነት ከሱኒ ገዢው መደብ እያገኙ ባሉት ምእራባውያን ተገቢውን ትኩረት ሳያገኙ ቀርተዋል ፡፡ በተመሳሳይም ሳኡዲ አረብያ ውስጥም በስተምስራቅ ግዛቷ የሚገኙ ሺአዎች አመፅን አካሂደው የነበረ ቢሆንም የነሱም አመፅ ብዙም ሳይራመድ በዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችም የሚገባውን ሽፋንን ሳያገኝ ሲሸፋፈን ተስተውሏል ፡፡
ሀንስ ብሊክስ አኢራን ላይ የተሳሳተ የደህንነት መረጃን ምእራባውያን እንዳይጠቀሙ ሲያሳሰስቡ ምእራባውያን ከዚህ በፊት በኢራቅ ላይ ተመሳሳይ መረጃን በመጠቀማቸው ምክንያት የደረሰውን በማስታወስ ነው ፡፡
ሳኡዲ አረቢያ ትልቋ የጦር መሳሪያ ሸማች ነች ፣ ዩኤኢም እንዲሁ በርካታ የጦር መሳሪያን ከሚያግበሰብሱ አገራት አንዷ ነች በአካባቢው

የሀገራችን ደራስያን



በሀገራችን ደራስያን መፅሀፍ በሚፅፉበት ወቅት ግን ምንጭንና ዋቢ መፅሀፍትን የማይጠቅሱ ሲሆን ቀደምት ደራስያን ስራዎቻውን ልክ ራሳቸው እንደ ወጥ በሆነ ሁኔታ እንደፃፉት አድርገው ይፅፉታል በዚህም ምንም አይት ዋቢ መፅፍ የሌላቸው ሲሆን የአውሮፓውያንን ታሪክ ሲፅፉ ያገኙባቸውን የታሪክ ምንጮችን አይጠቅሱም ፍልስፍናም ሲሆን እንዲሁ የዋናውን መፅሀፍ ምንጭ የማይጠቅሱ ሲሆን  ይህም የሀገራችንን ጸሀፍት የራሳቸው ያልሆነውን ሰራ የራሳቸው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው ያስወቅሳቸዋል እንጂ አያስመሰግናቸውም ፡፡
ለምሳሌ ክቡር ከበደ ሚካኤል በፃፏዋቸው ታላላቅ ሰዎች በተሰኘው መፅሀፍ ላይ ምንም አይነት ምንጭንም ሆነ የታሪክም ሆነ የፍልስፍና መፅሀፍን ያልጠቀሱ ሲሆን ነገር ግን በመፅሀፉ ውስጥ የተጠቀሰው ግን ታሪክና ፍልስፍና ነክ ነገር እንደ መሆኑ ምንጮቹን እና የተጠቀሙባቸውን የማመሳከሪያ መፅሀፍቱ ሊጠቀሱ ይገባ ነበረ ፡፡
በሃገራችን የአድዋ ጦርነት የኢትዮጲያ ብቻ ሳይሂን የአፍሪካና የመላው አለም የነፃነት ተምሳሌትነ የጭቁን ህዝች የነፃነት መሰረት የሆነ ድል መሆኑ አያከራክርም ፡፡ የአድዋን ጦነት አባቶቻችን ያሸነፉት በነበራቸው የጋለ የሀገር ፍቅርና ለሃገራቸው በነበራቸው ተቆርቋሪነት በባዶ እጃቸው በኢንዱስትሪ አብዮት ከተደራጀና ዘመናዊ የጦር መሳሪያን መድፍንና መትረየስን ከታጠቀ ዘመናዊ አውሮፓዊ ሃይል ጋር ነው ፡፡
ይህ በጦር ሜዳ ድል የተገኘ ነፃነት በእውቀት ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በአጠቃላይ በእውቀት ታግዞ ልማትንና እድገትን ካላመጣ የሃገሪቱ ህልውና አሁንም አደጋ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል በዘመኑ የነበሩ ምሁራኖች በተለያየ መንገድ መንገድ ሃሳባቸውን ገልጸዋል ፡፡  
በሀገራችን እውቀትን መደበቅና ለራስ ብቻ ማወቅ መፈለግ የተለመደ ሲሆን አዲስ አበባ ዩንቨርሰቲ በነበርኩበት ወቅት አንዳንድ ጠቃሚ የሆኑ መፅሀፍት ያውም በፈተና ሰሞን ይደበቁ የነበረ ሲሆን ከውስጣቸውም ገፃቸው እየተቀደደና እየተቦጨቀ ይወሰድ ነበረ ፡፡
በሃገራችን አዲስ ሃሳብን ለመቀበል ደካሞች ስንሆን አዳዲስ አስተሳሰቦችን እንፈራለን ፣ እንጠራጠራለን ፡፡ አዲስ ሃሳብን ያፈለቀ ሰውን የተወገዘ አድርገን የማየትና ምንም እንኳን ሰውየው ያለው ትክክል ቢሆንም ያንን ለማየትና ለመረዳት ረጅም ጊዜን ይወስድብናል ፡፡ በዚህም በዚያ አዲስ ሃሳብ ለመጠቀም ያለንን እድል ሲያጠብብን ከዚያም ባለፈ ግን ለየት ያለ ሃሳብ ያላቸው ሰዎች ሃሳባቸውን በአደባባይ እንዳይገልፁና እንዲፈሩ ያደርጋል ፡፡
ቅናትም እንዲሁ በሰፊው በመሀከላችን የሚታይ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ዋናው የእውቀት ምንጭ የሆነው የንባብ ባህላችን ደካማ ነው ፡፡ ከየትኛውም ሚዲንያን ከመከታተል ፣ ወይንም ቴሌቪዥን ከማየትና ሬዲዮ ከመስማት በበለጠ ከማንበብ የበለጠ እውቀት የሚገኝ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የመደማመጥ ባህላችን ራሱ በትኩረት ሊቃኝ የሚገባ ሲሆን የተለያየ አቋም በሚያጋጥም ጊዜ አንዱ ለአንዱ የሚለውን ለማዳመጥ እንኳን እግስት አናሳይም ፡፡

ወጣትነት በዘመን እይታ

ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በታህሳስ 4 ቅፅ 13 ቁጥር 778፣ 2007 ዓ.ም. ከወጣው ያነበብኩት ፅሁፍ ሲሆን አስረስ አያሌው የተባሉ ፀሀፊ ‹‹ወጣቱን በቅኔ›› በሚል ርእስ ያቀረቡትን ጽሁፍ በማየት ነው ፀሀፊው እንዲህ ይላሉ ፤
‹‹የኛ ትውልድ ግራ የተጋባ ነው፡፡ እንደ አያቶቹ አርበኛ ፣ እንደ አባቶቹ ደግሞ አብዮተኛ አይደለም ፡፡ ልግመኛ ነው፡፡ ልግመኛ የሆነው ግን ወዶ አይደለም ፡፡ የሚያግዘው አጥቶ ነው ››
የድሮዎቹ አባቶቻችን ድንበርን በማስከበር ፣ ጦርነት ወራሪን በመከላከል በመሳሰለው  የአርበኝነት ጀብድና ገድል ዘመናቸውን ሲያሳልፉ ፣ ከእነሱ በኋላ የመጣው ዘመናዊ ትምህርትን የቀሰመው አብዮተኛው ትውልድ በበኩሉ ደግሞ እነርሱ ለዘመናት ይዘውት የቆዩትና ሊለውጡት ፈቃደኛ ያልነበሩትን ስርአት ለወደፊቱ አገራችን አይበጅም በሚል ስሜት አብዮትን አስነስቶ የአባቶቹን ስርአት ያፈራረሰና ከዚያም የራሱን ይጠቅማል ያለውን ስርአት ለመተካትና ተግባራዊ ለማድረግ እርሱ በእርሱ በመጫረስም ጭምር መስዋእትነትን የከፈለ ነው ፡፡
ለለውጥና አገርን በአዲስ አስተሳሰብና ስርአት ለመቃኘት መነሳሳት በዓለም አገራት ታሪክ ውስጥ ያለና የተለመደ ነገር ነው ፡፡ ለምሳሌ በአውሮፓ የቡርዧ ስርአት የመጣው የፊውዳል ስርአትን በማፈራረስ ነው ፡፡ ነገር ግን ይህ የሆነው በጣም ስር ነቀል አብዮትን በማካሄድ ሳይሆን ዘመናት የፈጀ ጥገናዊ ለውጥን በማካሄድና ወቅቱ ሲደርስም መለወጥ ያለበትን በመለወጥ ነው፡፡ የኢኮኖሚው መሰረት ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ሲቀየር እና የኢንዱስትሪ አብዮት ስር ከሰደደ በኋላ የፖለቲካ ስርአቱንም መለወጥ አስፈላጊነቱን ተረዳው ገዢ መደብ ራሱን ቀስ በቀስ ወደ ቡርዧ ስርአት ማሸጋገር ችሏል ፡፡
አሜሪካንንም ብንወስድ አሜሪካኖች ምንም እንኳን የባርያ አሳዳሪውን ስርአት ለማፈራረስ የተነሱት የኢንዱስትሪው አብዮት በአሜሪካ ሲካሄድ በፋብሪካዎቻው አማካይነት ርካሽ በሆነ ሁኔታ ማምረት ስለሚቻል ያንን የሰው ሃይል ያነሰ ምርታማ በሆነው ግብርናው ዘርፍ ከማሰማራት ይልቅ በኢንዱስትሪው ውስጥ ማሰማራት የበለጠ ትርፍማ በመሆኑና ለዚህ ደግሞ የሚያስፈልገው የሰው ሃይል ያለው ግብርናው ውስጥ በመሆኑ የባርያ አሳዳሪው ስርአት መፈራረስ ነበረበት እንጂ ነጭ አሜሪካውያን ለጥቁሮች አዝነው ወይንም የባርያ አሳዳሪው ስርአት ስነ - ምግባራዊ ስላልሆነ ብለው እንዳልነበረ በርካታ የታሪክና የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይስማማሉ ፡፡ በዚያም አለ በዚህ ግን ስርአቱን መለወጥ አስፈላጊ የእርስ በእርስ ጦርነት ጭምር አካሂደው ለውጠውታል ፡፡   
በአንፃሩ በኢትዮጲያ የተካሄደው አብዮትና ተከትሎት የመጣው እልቂት ወጣቱንና የተማረውን ሀይል ሙልጭ አድርጎ ያጠፋ መሆኑንና አይደለም በአፍሪካ በአለም ደረጃ እንኳን የዚህ አይነት ጥፋትን ያስከተሉ አብዮቶች ቁጥራቸው እምብዛም እንዳልሆኑ ስለ አብዮቶች ያጠኑ የአፍሪካ ምሁራን ጭምር ይመሰክራሉ ፡፡ የኢትዮጲያ አብዮት ውጤት እጅግ የመረረ የሆነበት ምክንያት የሃገሪቱ የምጣኔ - ሃብትና የፖለቲካ ስርአት ለክፍለ ዘመናት ለውጥንና ማሻሻያን ይፈልግ የነበረ በመሆኑና ይህ ግን በገዢዎቹ ታፍኖና ተገቢው ትኩረት ሳይሰጠው ሁኔታው ገነፍሎ ከቁጥጥር ውጪ በመውጣቱ ነው ፡፡ ለምሳሌ እጅግ ኋላ ቀር የነበረውና ከዘመኑ ጋር ፈጽሞ የማይሄደው የመሬት ስሪት ስርአቱ ተጠቃሽ ነው ፡፡  
      ከላይ የተጠቀሱት ጸሀፊው ልግመኛ ያሉት ትውልድ በራሱ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በሱስ የተጠመደ መሆኑን ፣ ስለ አገሩ ደንታ ቢስና ግዴለሽ መሆኑን ነገር ግን ተጠያቂ እንዳይሆን ወዶ አይደለም ፣ የሚያግዘው አጥቶ ነው ብለዋል ፡፡ ካለፉት ትውልዶች የደረሰው እልቂት በተለይም በቀይና በነጭ ሽብር የደረሰው እልቂት መሀል ላይ የሚሸጋግር የትውልድ ማለትም በታላቅየው ወይም በአባትየው ትውልድ እና በታናሽየው ልጅ ትውልዶች መሀል ክፍተት መፍጠሩን በርካታ የስነ - ማህበረሰብ ወይም ሶሺዎሎጂ ባለሙያዎች ይናገራሉ ፡፡ አዲሱ ትውልድ ‹‹እርስ በእርሱ የተገዳደለ ትውልድ›› የሚለው የቀድሞው አብዮተኛው ትውልድ የበዛ መስዋእትነትን በመክፈሉ ምክንያት ከመጪው ትውልል ጋር የሚያገናኘው ጠንካራ ድልድይ እንዳይኖር ቢያደርግም ፣ ይህ መሀል ላይ የተፈጠረ ክፍተት አዲሱ ትውልድ እንደ ታላቅ የሚያየውና የሚያከብረው እንዲሁም እንደ አርአያ የሚቆጥረው ትውልድ እንዳይኖርና ነገሮችን በራሱ መንገድ ብቻ እንዲረዳና እንዲተረጉም ለቀድሞው ትውልድ መልካም ተግባራት ጭምር እውቅናን እንዳይሰጥና ከዚያም ተጠቃሚ እንዳይሆን እድሉን ዘግቶበታል ፡፡
የአሁኑ ትውልድ ግን ሀብትን በማከማቸት ፣ ገንዘብን በመሰብሰብ ሲጠመድ ማየትና መስማት የተለመደ ነው ፡፡ ይህም የዘመኑ ትውልድና የቀድሞው ትውልድ ምን ያህል የተራራቀ የአስተሳሰብ አድማስ እንደነበራቸው የሚያሳይ ነው ፡፡ የዘመኑ ትውልድ ቁጥርና ስታትስቲክስ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ላይ ሲያተኩር የቀድሞው ትውልድ ፖለቲካና ህግ ላይ ትኩረትን ያደርጋል ፡፡ የአሁኑ ትውልድ ገንዘብና ገንዘብ ነክ ጉዳዮች ላይ የበለጠ እውቀት ሲኖረው የቀድሞው ትውልድ ስለ ገንዘብም ሆነ ስለ ምጣኔ ሀብት የነበረው እውቀት ከአሁኑ ጋር የሚወዳደር አይደለም ፡፡ የቀድሞው ትውልድ ለአገሩ ቀናኢ በመሆን የአካልና የህይወት መስዋእትነትን በመክፈል አገሩንና ዳር ድንበሩን አስከብሮ አለፈ እንጂ በአብዛኛው በነበረው ሀብት የተጠቀመ እና በድሎት ተንደላቆ የኖረ አይደለም ፡፡ በአንፃሩ የአሁኑ ትውልድ ከአባቶቹ በወረሰው ድህነት እጅግ መማረሩ ለገንዘብ ከፍተኛ ፍቅር እንዲያድርበት ዋነኛ ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ወደ ውጪ አገር በህጋዊም ሆነ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እሚሰደደው በአብዛኛው ወጣት በኢኮኖሚ ምክንያት ሲሆን በሚችለውም ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ለመለወጥ በትግል ላይ ይገኛል ፡፡
ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ ማለት በተለመደበት ባህል ውስጥ ሁልግዜ የድሮውን ናፋቂ መሆን ከስህተት ላይ እንዳይጥለንና የራሳችንን ዘመን ታሪክ ሳናደንቅም ሆነ በራሳችን ዘመን ታሪክ ተሳታፊ እንዳንሆን እንዳያደርገን መጠንቀቅ አለብን ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን በመጽፈ መክብብ ላይ ምእራፍ 7፣ቁጥር 10 ላይ ‹‹ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አትናገር ፣ የዚህን ነገር በጥበብ አትጠይቅምና ››፡፡

ስነ - ጥበብና አገራችን

ከጣልያን ጦርነት ከማይጨው ጦርነት ከተመለሱ ወዲህ ንጉሰ ነገስቱ ፣ ምንም እንኳ ጣሊያን ትቷቸው የሄዳቸው ጥቂት የመሰረተ ልማቶችና መንገዶች ህንፃዎች ቢኖሩም ሃገሩ ግን በጦርነት መፈራረሱ ግልጽ ነበረ ፡፡ እንደ ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ የጀመሩት የሀገራዊ ስሜትን የሚቀሰቅስ እንቅስቃሴ ነበረ ያም በኋላ መኮንን ሀብተወልድ ይዘውት በሀገር ፍቅር ትያትር ተቋማዊ አደረጃጀትን ይዞ ሲቀጥል ፡፡ በ1950ዎቹ አካባቢ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች ይታያሉ በ1960 ዎቹ እነ ዮሀንስ አድማሱ ፣ ዮናስ አድማሱ እና የመሳሰሉትም እንዲሁ የተለያየ ድርሰቶችን በመስራት አገራዊ ስሜትን ለማነቃቃትና ህብረተሰቡን ለማንቃት ጥረት የተደረገበት ነበረ ፡፡ ገብረ ክርስቶስ ሀዲስ አለማየሁ አፈወርቅ ተክሌን የመሳሰሉ ሽልማት በመስጠትና ለማነቃቃት ጥረት ተደርጓል ፡፡
አብዮቱ ከፈነዳና 1970ዎቹ ወደ ቀበሌ ኪነት ኪነ ጥበብ ሲሰራ ይህ ህዝቡ ለመድረስ ሲያስችል ቀድሞ የነበረው ምሁራዊ የነበረው አቅምና ደረጃ የነበረው ባይሆንም ወደ ህዝብ ግን በቅርበት መድረስ የቻለና በርካታ አቀንቃኞችና ተዋንያን በኋላ ላይ ከቀበሌ ኪነት ታዋቂ ሆነው የወጡበት ነበረ ፡፡ አብዮቱ ሲመጣ ቀድሞ የነበረው የአርቲስቶች ስብስብ ግን አንዳንዶች በሞት ፣ ከአገር በመውጣት ሲበተኑ ገብረ ክርስቶስ ደስታ ከአገር ሰለሞን ደሬሳ ሲወጡ ጸጋዬ ገ/መድህን ፣ መንግስቱ ለማ ፣ተስፋዬ ገሰሰን፣ አባተ መኩሪያን የመሳሰሉት ቀጥለዋል ፡፡ 
የአገራን ደራሲዎች በራሳቸው በአማርኛ ቋንቋ ሲፅፉ ይህ ህዝባዊ ተቀባይትን በአለም ለማግኘት አስቻጋሪ ሲያደርገው ሌሎች የአፍሪካ አገራት ግን በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ የአገራቸውን ስነ - ፅሁፍ ለአለም ለማስተዋወቅ ረድቷል ፡፡
የሼክስፒር ስራዎች በ17ኛው ክ / ዘመን የተሰሩ ቢሆንም አሁንም እንደ አዲስ በየመድረኩ ይሰራሉ በየትያትር ቤቶች በተመሳሳይም የሃራችን ስራዎች ከአሁኑ ሁኔታ ጋር ሊተረጎምና ከአሁኑ ጋር ካለው ሁኔታ ጋር በዛሬ ሁኔታ ላይ ቆመን ስንመለከተው ስለአሁኑ የሚነግረን ይኖራል ፡፡ አውሮፓውያን ከቀድሞው ስራዎቻቸው ብዙ ብዙ ለዘመኑ አንዳመቻቸው ይወስዳሉ ፡፡    
በአገራችን ግን በዚህ አይነት መንገድ ደራሲዎቻችንን ፣ ሰአሊዎችቻችንን ዋጋ የተረዳን አይመስልም ፡፡ በአሉ ግርማ እንዴት እንደሞተ የማይታወቅ ሲሆን እንደ አቤ ጉበኛ ፣  ገብረህይወት ባይከዳኝና ዮፍታሄ ንገሱ እንዴት እንደሞቱ እንኳ አይታወቅም ፡፡
ባህላችንና ታሪካችን ግለሰባዊነትን የሚበረታታ አይደለም ፡፡ ሁሉንም ነገገር ለንጉሰ ለጳጳሱ ወይም ለገዢው ነው የምንሰጠው ፡፡ በዚያ ውስጥ ግን እጅግ በርካታ ባለሙያዎች ሰዎች ያሉ ሲሆን ስለ እነሱ ምንም የሚባል ነረገር የለም ፡፡ ሰአሊዎች በቤተክርስትያን የሚስሉትን ስእሎችን ስንመለከት ንጉሱን ዛፍ አሳክለው ሲስሉ ሌሎቹን ሰዎች ደቃቃ እና ከአይን የማይገቡ አድርገው ነው የሚስሉት ፡፡ የሁሉንም ነገር ማእከልም ፣ መጨረሻውም መጀመሪያው ንጉሱ ወይንም ጳጳሱ አድርገው ነው ፡፡
አውሮፓዊያን በህዳሴው ዘመን ያንሰራሩበት አንዱና ዋናው ምክንያት ቀድሞ የሁሉም ነገር ማእከል የነበረውን መለኮት ላይ ተንጠልጥሎ የነበረውን ወደ ግለሰብ ትይዩ ማለትም ወደ ሰው ደረጃ በማውረዳቸው ነው ፡፡ ለምሳሌ የማክያቬሊ አስተሳሰብ ከህዳሴው ዘመን ዋናው ተደርጎ የሚወሰድበት ምክንያት ቀድሞ ሁሉም ነገር በመለኮት መሪነትና ፈቃጅነት ይደረግ የነበረውንና ከላይ (ቨርቲካል) ከመለኮት ወደ ታች ማለትም ወደ ሰው ይወርድ የነበረውን ግንኙነት ወደ ጎን ማለትም ወደ ሰውና ሰው ፣ ሰውና መለኮት የትይዩ (ሆሪዞንታል) ግንኙነት እንዲኖር ፈርን የቀደደ በመሆኑ ነው ፡፡  
አንድን ስነ የጥበብ ተረድቶና ለማስቀመጥም የመካከለኛው መደብ ያስፈልጋል፡፡ ኢትየጲያ ውስጥ ስእሎችን የመግዛት ነገር አሁን አሁን የሚታይ ነው ፡፡ ብሄራዊ የሳይንስ አካዳሚና ብሄራዊ ሙዚየም ስነ - ጥበብ የሚደግፉና በክብር የሚያስቀምጡ ተቋማት ናቸው፡፡ 

ኦባማና የሚድ ተርም (Mid Term) ምርጫ



ፕሬዝዳንት ኦባማ በ2014ዓ.ም. በተደረገው የህዝብ አስተያየት መለኪያዎችን እንደሚያመለክቱት እ.ኤ.አ ከ1940ዎቹ ወዲህ የመጀመሪያው ዝቅተኛው የህዝብ ድጋፍ ያላቸው ፕሬዝዳንት ሊሆኑ በቅተዋል ፡፡ ውሳኔን ለማሳለፍ ጥንቃቄን በማብዛታቸው በተለይም ሪፐብሊካን ዘመም የሆኑ በርካታ አሜሪካውያንን ያበገኑት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ኦባማ በ2014 ጥቅምት ወር ላይ በተደረገው የመካከለኛው ዘመን (Mid Term) ምርጫ ወቅት የዲሞክራቲክ ፓርቲው ክፉኛ በተሸነፈበት ወቅት ይህንንም በማየት የራሳቸው የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባላት ጭምር ለመጪው ምርጫ አይረዳንም በማለት ራሳቸውን ከኦባማ ሲያርቁ ተስተውለዋል ፡፡ ይህን ተከትሎም ‹‹ሰምቻችኋለሁ›› ‹‹አድምጫችኋለሁ›› ቢሉም ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ ሆኖባቸዋል ፤ የስልጣን ዘመናቸው እያበቃ በሄደበትና ኮንግሬሱና ሴኔቱ በሪፐብሊካን እጅ በወደቀበት እና አብዛኛውን የስልጣን ዘመናቸውን ባገባደዱበት ሁኔታ ‹‹አድምጫችኋለሁ ፣ ሰምቻችኋለሁ ›› ማለት እምብዛም የሚያመጣው ለውጥ የለም ፡፡
ኦባማ በኢሚግሬሽን ላይ የያዙት አቋም ፣ ከቻይና ጋር የአየር ንብረትን ለውጥን በተመለከተ የያዙት አቋምና ከሀዲ ያስባላቸውን በኩባ ላይ የያዙትን አቋም ከሀዲ እስከመባል ድረስ አድርሷቸዋል ፡፡ በእነኚህ አቋሞቻቸው ከሁለቱም ከዲሞክራትም ከሪፐብሊካንም ፓርቲዎች ትችት አዝንቦባቸዋል፡፡ በተለይ በኩባ ላይ ማእቀቡን ለማንሳት መወሰናቸው ሪፐብሊካኖችን ሲያበሳጭ ፣ ከቻይና ጋር የአየር ንብረትን በተመለከተ የያዙት አቋም ደግሞ ዲሞክራቶችንም ጭምር አበሰጭቷል፡፡
      በእርሳቸው የፕሬዝዳንትነት ዘመን የቀድሞው የሲ አይ ኤው ዳይሬክተርና የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ሊዎን ፓኔታ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ኦባማ ከነገሮች ሸሽተዋል (Disengaged) ወይንም ከእውነታው ራሳቸውን አርቀዋል ብለዋል ፣ ማለትም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ፣ በቶሎ መወሰንና የአሜሪካን ጥቅም በሚስጠብቅ መልኩ መሳተፍ ሲገባቸው ነገር ግን ጦርነትን በመፍራትና ፣ ምጣኔ ሀብቱ ላይ ጉዳት ይደርሳል በሚል እንዲሁም የአገር ውስጥ የህዝብ ድጋፍ አይኖርም በሚል ፍራቻ አሜሪካንን ቁልፍ ከሆኑ ዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች ላይ እንድትገለልና ተሰሚነቷ እንዲቀንስ አድርገዋል ፡፡ የፕሬዝዳንት አሳድ መንግስት በራሱ ህዝብ ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ በተጠቀመበት ወቅት በአውሮፕላን እንዲደበደብ ወስነው ሲያበቁ እንደገና ውሳኔያቸውን አጥፈውታል ፡፡ የህዝብ አስተያየት መለኪያዎችም ያመለከቱት እርምጃ እንዳይወሰድ ቢሆንም ፣ ከአሳድ መንግስት ጋራ ስትራቴጂያዊ ጥቅም ያላቸው የሩስያው ፕሬዝዳንት ጭምር አየር ድብደባቸውን በመቃወም በኒውዮርክ ታይምስ (New York Times) ጋዜጣ ላይ ተቃውሞ እስከመፃፍ ሲደርሱ ኦባማ ውሳኔያቸውን ትተውታል ፡፡ የኦባማ አሜሪካንን ከዋና የዓለም ዓቀፍ ፖለቲካ ተሳታፊነት ውጪ ማድረጋቸው የፈጠረው የሀይል ክፍተት በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ በግልፅ የታየ ነው ፡፡
ፕሬዝዳንት ኦባማ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በአሜሪካውያን መሀከል ያለው የዘር ግንኙነት የተበላሸበትና የበለጠ የዘር ውጥረት የሰፈነበት መሆኑ አስገራሚ ነው ፡፡ በዚህም በርካታ ጥቁሮች በፖሊሶች የተገደሉበትና ይህንንም በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎችና በየከተሞቹም ረብሻዎች የታዩበት ሆኗል ፡፡ እነኚህ ጉዳዮች በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ያስብላሉ ወይስ አያስብሉም በሚል በፍ/ቤቶች ጭምር ቢታዩም ገዳዮቹን ተጠያቂ ባለማድረጋቸው ምክንያት የአፍሪካ አሜሪካውያንን ቁጣ አባብሷል፡፡   
ፕሬዝዳንት ኦባማ አሜሪካን ለመወጥ ‹‹ለውጥ›› በሚል መፈክር ወደ ስልጣን ቢመጡም ወደ ስልጣን ቢመጡም ራሷ አሜሪካ ነች ፕሬዝዳንቱን የለወጠችው ሲሉ የኦባማን የስልጣን ዘመን የተከታተሉ አስተያት ሰጪዎች ይናገራሉ ፡፡
ይህን ተከትሎም በአካባቢው የሀይል ክፍተት መፈጠሩን የተጠቀመው ISIS አይ ኤስ አይ ኤስ የተሰኘው የመካከለኛው ምስራቅ ሶሪያንና ኢራቅን በከፊል የተቆጣጥሮ እያመሰ ያለውን ዓለም ዓቀፍ ታጣቂ እስላማዊ ድርጅት መግታት አልቻሉም ፣ እንዲሁም የሶርያው ጦርነት አውዳሚና አጥፊ ሲሆን እና ወደ ኢራቅ ሲዛመት፣ሊባኖስን ሲከፋፍልና ስጋት ሲደቅን እርምጃን ሳይወስዱ ቀርዋል ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አይ ኤስ አይ ኤስ ላይ እርምጃን ለመውሰድ ኮንግሬስ ድጋፉን ይግለፅልኝ ማለታቸውም እንዲሁ ወሳኝ እርምጃን ለመውሰድ ቁርጠኝነቱ እንደሚያንሳቸው አመላክቷል ፡፡ እንዲሁም በአለም ላይ የኢቦላ በሽታ በአደገኛ ሁኔታ ሲዛመት ተገቢውን ፈጣን እርምጃ መውሰድ አልቻሉም ተብለው ተነቅፈዋል ፡፡
ከዚህ ይልቅ ለኢራኑ ፕሬዝዳንት የሚስጥር ደብዳቤ መፃፋቸው ኢራን የኒውክሊየር መሳሪያን በተመለከተ ከምእራባውያን ጋር በቶሎ መስማማት ከቻለች አሜሪካ ከኢራን ጋር አይ ኤስ አይ ኤስን በመግታት በኩል ለኢራንም ሆነ ለአሜሪካ ጠላት የሆነውን (ISIS) አይ ኤስ አይኤስን ለመግታ አብረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል ፡፡ ይሁን እንጂ ኦባማ በዚህ በኩል ስሌት ስህተት የሰሩ ይመስላል ለዚህም ምክንያቱ በአካባቢው ለምእራባውያንም ሆነ ለእስራኤል በረጅም ጊዜ አስጊ የምትሆነው ኒውክሊየር ልትታጠቅ የምትችልና የበለጠ ጠንካራ የሆነችዋ ኢራን ነች እንጂ (ISIS) አይ ኤስ አይ ኤስ አይደለም ፡፡ እርግጥ ነው ለዚህም ዋናው ምክንያት አይ ኤስ አይ ኤስ ምንም እንኴን የአልቃኢዳ አምሳያ ቢሆንም ውሎ አድሮ ግን (ISIS) አይ ኤስ አይ ኤስ ተሸናፊ መሆኑ የማይቀር ሲሆን ጠንካራዋንና ኒውክየር ለመታጠቅ የምትንደረደረው ኢራን ግን የበለጠ አደገኛ መሆኗ ለምእራባውያን የማይጠፋቸው ሀቅ ነው ፡፡ ከታሊባንና ከናይጄሪያው ቦኮሀራም ጋራ ተመሳሳይ የሆነው (ISIS) አይ ኤስ አይ ኤስ ህልውናው የረጅም ጊዜ እንደማይሆን መገመት ይቻላል ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዝዳንት ኦባማ የስደተኞች ጉዳይን ለብዙ ወራት ኮንግሬሱ እንዲያፀድቁ  ሲማጠኑ የነበረ ቢሆንም ኮንግሬሱ ግን የኦባማን ፖሊሲን ለማፈን በሚመስል ሁኔታ አላፀድቅም ብሎ አንጀታቸውን ሲያሳርረው ከቆየ በኋላ ከሚድ ተርም ምርጫ በኋላ ግን ራሳቸው ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዝን በማውጣት ለእነኚህ ቁጥራቸው ከአምስት ሚሊዮን በላይ ይገመታል ለሚባሉ በህገ ወጥ መንገድ አሜሪካ ይገኛሉ ለተባሉ ሰዎች ምህረትንና ጊዜያዊ የስራና የመኖሪያ ፈቃድን ለመስጠት መወሰናቸው በአለም ዙሪያ በተለይም እንደ ሜክሲኮ ፣ፔሩ ባሉ አገራት ከፕሬዝዳንቶቻቸው ጭምር ይበል የሚያሰኝ ድጋፍን ቢያሰጣቸውም የራሳቸው ኮንግሬስ ግን እከሳቸዋለሁ እስከማለት ደርሷል ፡፡
በህገወጥ መንገድ ወደ አሜሪካን ሃገር ገብተው ከአምስት አመታት በላይ ለኖተሩትና ለክልጆች ላላቸው ከነልጆቻው ለጊዜውም ቢሆን ምህረትን የሚደርገው የኦባማን ኢምግሬሽን አዋጅ እንዲያፀድቀው የተጠየቀው ኮንግሬስ በዝምታ አመታትን በማስቆጠሩ ፕሬዝዳንታዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም ለእነኚህ ሰዎች እፎይታን ያመጣ አዋጅን ማፅደቃቸው በአብዛኛው በተለይም ከላቲን አሜሪካ አገራት በርካቶቹ ስደተኞች ከሚገኙበት ድጋፍን ሲያስገኝላቸው የራሳቸው አገር በተለይም የሪፐብሊካን ፓርቲ ምክር ቤት አባላትን በእጅጉ አንጨርጭሯል ፡፡
በዚህ ፖሊሲ የምክር ቤት አባላቱ ሃሳብ ከተግባር የራቀ ነው ለምን ቢባል አሜሪካ አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ከአገር አባርራለሁ ብላ ብትነሳ በዓለም ውግዘትን የሚያተርፍላት ነው የሚሆነው እንጂ አያስመሰግናትም ስለዚህ የኦባማ ሃሳብ ከተጨባጭ እውነታው ጋር ቅርብ ነው ማለት ይቻላል ፣ ሪፐብሊካን የሆኑ የኮንግሬስ አባላትም ቢሆኑ እነኚህን ሰዎች ሊያባርሩ አይነሱም ፣ነገር ግን እንዲሁ ሰዎቹ ያለ ህጋዊ መኖሪያና ስራ ፈቃድ ሲታሹ  ይኖራሉ እንጂ ጉዳዩ ውሳኔን አያገኝም ነበረ፡፡
እዚህ ላይ የኦባማ ውሳኔ ስሌትን የያዘ ይመስላል ፣ ለምን ቢባል ፓርቲአቸው በሚድ- ተርም ክፉኛ ስለተሸነፈ ፣ የዚህን ሽንፈት ለመበቀልና ለመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የላቲኖችን ድምፅ ሰጪዎችን ድጋፍ ለፓርቲአቸው ለማስገኘት መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ለመጪው እ.ኤ.አ በ2017 ለሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለዲሞክራቶች ይህ ወቅታዊ ውሳኔ የበለጠ ጉልበትን የሚሰጥ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ለዚህም በመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ሚስ ሂላሪ ክሊንተን በትዊተር ገፃቸው ላይ ድጋፍ መስጠታቸው ነው ፡፡ በ2017 ዓ.ም. ለመመረጥ እድላቸው ጠቦ የነበረው ዲሞክራቶች ለመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የቀራቸውን የመጨረሻውን ካርድ ማለትም የኢምግሬሽንን ካርድ መምዘዛቸው መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡
ከኢምግሬሽን (Emigration) በተጨማሪም ኦባማ በኩባ ላይ በተናጠል የአስፈፃነት ስልጣናቸውን በመጠቀም በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ አንስተውታል ፡፡ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኪዩባ ላይ የነበረውን በ እ.ኤኤ ከ 1954 ጀምሮ ተጥሎ የነበረውንንና በኩባ ላይ 1.1 ትሪሊየን ዶላር ኪሳራ ያደረሰውን ማእቀብ ማንሳታቸው ከላቲን አሜሪካን አገራትና ከራሳቸው የአሜሪካ ህዝብም ጭምር እና ከአለም ህዝብም ጭምርን ድጋፍን ሲያስገኝላቸው ፣ አሜሪካ ከሩስያ ጋራ ባለባት ውዝግብ ኩባን እንደ ቀድሞ እንደ ኬኔዲ ጊዜ ወደ ሩስያ እቅፍ እንዳትገባ ነው ፣ ሲሉ አጥባቂ ሪፐብሊካኖች የሰማቸው የለም ፣ እንጂ በኩባ ላይ የተጣለው ማእቀብ መነሳት ያለበት በኩባ ዲሞክራሲ ሲሰፍን መሆን አለበት ብለው ተከራክረዋል ፡፡
ኦባማ በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ ዘመን ያለፈበትና አላፈላጊ ነው በማለት ማእቀቡ እንዲነሳ አዘዋል ፡፡ በሃምሳ አመታት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ለውጥ ነው ሲሉ ነገር ግን ይህ በኮንግሬስ መጽደቅ ያበት ቢሆንም ይሁን እንጂ ኦባማ በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ ማንሳታቸው አንድ ትልቅ የፕሬዝዳንትነታቸው መልካም ውጤት ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን አሁን ባይሆን ፕሬዝዳንት ኦባማ በታሪክ የሚሰጣቸው ስፍራ ወደፊት ከአሁኑ የተሻለ እንደሚሆን መገመት ይቻላል ፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያቱ የአሜሪካንን ምጣኔ ሀብት ከወደቀበት ማንሳታቸው እንዲሁም እርሳቸው ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሶ ከነበረበት ወቅት አንስተው የተሻለ ማድረጋቸው ፣ የስራ አጥ ቁጥሩን ከመጡ በኋላ በእጅጉ እንዲቀንስ ማድረጋቸው ፣ እንዲሁም ከብዙ ትግልና ውዝግብ በኋላ የአሜሪካውያንን የጤና መድህን ሽፋን ለመጀመሪያ ጊዜ ፖሊሲ ማውጣታቸው ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ አዋጁ በርካታ ድክመቶች ቢኖሩትም እነኚህ ተጠቃሽ የሆኑ የኦባማ የአስተዳዳር ውጤቶች ናቸው ፡፡

የአሜሪካጣኔ ሐብት

የአሜሪካ ምጣኔ ሀብት ችግር ያለበት የተወሳሰበ ችግር ያለበት ሲሆን ከ1970 ዎቹ ወዲህህ አሜሪካ ኢንዱስትሪዎቿ ከጃፓን ኢንዱስትሪዎች ጋር መወዳደር እያቃታት ወዲህ ችግሩ በጊዜ በውስጥ እየተባባሰ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ጃፓን ብቻ ሳትሆን የጃፓን ጎረቤት የሆኑ የእስያ ሀገራት እንደ ደቡብ ኮርያ ፣ ታይዋንና ግዙፏ ቻይናም ጭምር የአሜሪካንን ኢንዱስትሪዎች የመወዳደር አቅም በእጅጉ እየፈተኑ ይገኛሉ ፡፡
ይህ ብቻ ሳይሆን አሜሪካ ከመስረም 11ዱ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ በኢራቅና በአፍጋኒስታን የገባቻቻው ጦርነቶች ትሪሊዮኖች ዶላሮቿን እሳት ያየው ቅቤ ሲያደርግ ፣ሀገሪቱ በእዳ መዘፈቋ ሳያንስ ጦርነቱ ይባስ ብሎ አገሪቱን አክስሯል ፡፡

ኩባ ላይ የተጣለው 54 አመት ማእቀብ መነሳት

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ኦባማ ከኮንግረስ ጋር አብረው በመስራት ኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ እንዲነሳ እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡ ዲፕሎማሲ ግንኙነትን እንደሚመሰርቱ ፣ ኢምባሲ እንደሚከፍቱ እና የጉዞ ማእቀብን እንሚያላሉ ተናግረተዋል ፡፡ ኩባ በቀድሞው በቻቬዝ ቬንዙዌላ ትደገፍ የነበረ ቢሆንም ቬንዙዌላ ኢኮኖሚዋ ሲቀዘቅዝ ወደ አሜሪካ ማእቀቡ መላላቱ ለኩባ ጠቃሚ ነው ፡፡ ሪፐብሊካን ሴናተሮች የቬንዙዌላ ኢኮኖሚ በቀዘቀዘበት በአሁኑ ወቅት ቬንዙዌላ ኩባን መደገፍ በተሳናት በዚህ ወሳኝ ወቅት ማእቀቡ መነሳት የኩባን አምባገነናዊ መንግስት እጅግ ይጠቅመዋል ብለው ተከራክረዋል ፡፡
ኩባ ኢንተርኔትን መጠቀም ስትጀምር ፣ እንዲሁም የተባበሩት ምግስትታትና ከቀይ መስቀል ጋር ግንኙነቷን አሻሽላለች ፡፡ የሮማው ካቶሊክ ፖፕ ሸመገሉት በተባለው በዚህ የማእቀብ መላላት ኩባም ወዲያው አንድ አሜሪካዊ እስረኛን በመልቀቅ ደስታዋን ስትገልፅ በአሜሪካ ያሉ ኩባውያንም ደስታቸውን ገልፀዋል ፡፡ ቀጥሎም ኩባ ወደ 53 የሚሆኑ አሜሪካ የፖለቲካ እስረተኛ ስትል ትጠራቸው የነበሩ እስረኞችን ለቃለች ፡፡
በኩባ ላይ የተጣለውን ማእቀብ ለማንሳት የኮንግሬሱን ድጋፍ የሚጠይቅ ሲሆን ኤምባሲ መክፈትና ግንኙነትን ማሻሻል ፣ የጉዞ እገዳዎችን ማላላት የመሳሰለው ፕሬዝዳንቱ በስልጣናቸው ሊያደርጉት ሲችሉ የኢኮኖሚ ማእቀብ ማንሳት ግን የኮንግሬሱን ድጋፍ ካልታከለበት ውጤት አይኖረውም ፡፡
የቀዝቃዛው ጦርነት ካበቃ ወዲህ ፕሬዝዳንትት ሬገንና እሳቸውን ተከትለው የመጡ የአሜሪካ መንግስታት ለሶቭየት ህብትረት ማእቀብን ሲያላሉና ሲያነሱ በኩባ ላይ ግን በተከታታይ ወደ ስልጣን የመጡ ፕሬዝዳንቶች እንኳን ማእቀብ ሊያነሱ ቀርቶ በኩባ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰው ቆይተዋል ፡፡ የአሜሪካ ጠላቶችን በተመለከተ በወጣው አዋጅ መሰረት (America Enemies Act) በሚለው ድንጋጌ መሰረት አሜሪካውያን ኩባን ረግጠው ቢመጡ እና ፓስፖርታቸው ላይ የኩባ ቪዛ የተመታበት ማህተም ቢታይባቸው እስከ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ቅጣትና እስር ይጠብቃቸው ነበረ፡፡  
ሪፐብሊካን የፕሬዝዳንቱ ተቺዎች በበኩላቸው እንደሚሉት ፕሬዝዳንቱ ብዙ ሰጥተው ምንም አላገኙም በሚል ተችተዋቸዋል፡፡ የሰብአዊ መብትን ለሚጥስ መንግስት ሽልማት እንደመስጠት ነው ብለዋል ፡፡ አንዳንድ ኩባ አሜሪካውያን ሲደግፉ ሌሎች ተቃውመዋል ፡፡ ራሳቸው ኩባ አሜሪካውያን በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙ ሪፐብሊካኖቹም ሆኑ ዲሞክራቶቹ ውሳኔውን ሲነቅፉ ተስተውለዋል ፡፡ ፕሬዝዳንቱ ንግድንና ጉዞን ኢንቨስመንትን ከሰብአዊ መብት አስበልጠዋል ተብለው ሲተቹ ፡፡ ሽብርተኝነትን ከሚደግፉ አገራት መዝገብ ዝርዝር ውስጥም አሜሪካ ኩባን መሰረዝ ይጠበቅባታል ፡፡
ኩባ እዳ በመክፈል 173ኛዋ ሃገር ስትሆን ከሰሜን ኮርያ በአንድ ደረጃ ከፍ በማለት በዚህ ደረጃ የምትገኘው ኩባ እዳዋን በማትከፍለው በዚህች አገር ብድር የማግኘት እድሏ ጠባብ ነው ፡፡
አሁን ይህ ማእቀብ ሊነሳ የተፈለገበት ምክንያት በኩባ የደም መፋሰስንና አብዮትን ለመከላከል ነው ፣ የተገለሉት ጄኔራሎች እንዲሁም የኩባ ኢኮኖሚ በመውደቁ ኩባን በነዳጅ አቅርቦት በመሳሰለው ኩባን ስታግዝ የነበረችው ከቬንዙዌላ ኢኮኖሚ መንኮታኮት ወዲህ በኩባ የዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲኖር በሚል ሊሆን ይችላል ፡፡ ሰላማዊ ሽግግር እንዲኖርና የኩባ ጄኔራሎች ጥቂት ኦክስጅንን ወደ ኩባ ለመልቀቅ ነው ፡፡
አሜሪካ በኩባ ላይ ማእቀብን ያነሳችበት ምክንያት ኩባ ወደ ሩስያ እንዳትሄድ ነው ቢባልም ነገር ግን በላቲን አሜሪካ ለአሜሪካ ጥቅም ጠንካታራ ባላጋራ የሆነችው ቬንዙዌላ ነች እንጂ ኩባ አለመሆኗ አሜሪካ አታጣውም ፡፡ ትልቋና የነዳጅ ዘይንት የበለፀገችው ሃብታሟ ቬንዙዌላ በድፍረት የአሜሪካንን ጥቅም በአለካባቢው ስትቃረን በመቆየተዋ ሲሆን ቬንዙዌላ ኩባን በነዳጅ አቅርቦትና በገንዘብ ድጋፍ ስትደግፋት ቆይታለች ፡፡ ይን እንጂ ሁጎ ቻቬዝ ከሞቱና ከቅርበ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የነዳጅ ዋጋ ከተንኮታኮተ ወዲህ ከነዳጅ የምታገኘው ገቢ የቀነሰባት ቬንዙዌላ በሃገራ የዋጋ ንረት በማሻቀቡ የምጣኔ ሃብት አቅሟ ሲዳከም እንደ ቀድሞው ኩባን ለመደገፍ አቅም እያነሳት መሄዱ ግልፅ ነው ፡፡ አሜሪካ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ኩባን ከቬንዙዌላ ወደ ራሷ ለማምጣት ተጠቅማበታለች ፡፡   

አሜሪካንና የፑቲንና ሩስያ

      የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለምእራባውያን የማይጨበጥ የጋለ ፍም ብረት ሆነውባቸዋል ፡፡ ምንም እንኳን ምእራባውያንና ዓልም አቀፍ የሚዲያ ተቋማቶቻቸው በፑቲን ላይ በርካታ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን ቢያደርጉም ፑቲን በሙስና የተዘፈቀች ሩስያን ነው እሚመሩት ፣ ራሳቸው ፑቲን ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የደለበ ሃብትን አካብተዋል ፣ የሚሉና ለሌሎቸ በአንድ ወቅት በአንድ ከተማ የቼቼኒያ አማፅያን እንዳደረጉት በማስመሰል ፈንጂ እንዲፈነዳ በማድረጋቸው የህዝብ ቁጣ በቺቺኒያ አማፅያን ላይ ያን ተከትለው ዘመቻን አካሂደዋል የመሳሰሉት ክሶችን ሃሳቦችን አቀውርበዋል ፡፡
ፒቢ ኤስ የተሰኘው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ማሰራጫ ተቋም በፑቲን ላይ በሰሯቸው ጥናታዊ የዘገባ ፊልሞች ላይ የፑቲንን አነሳስ ሲዘረዝር እንዲሁም ፑቲን አርባ ቢሊዮን ዶላር ሃብት አካብተዋል ሲል ባደረኩት ምርመራ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡
ይሁንና ፑቲን ይህ ሁሉ እርሳቸው ቢባልም በሩስያ ጥቅም ላይ የሚደራደሩ አለመሆናቸውና በአገራቸው ጥቅም ለመደራደርም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ግን ምእራባውያኑን ያሳርራል ፡፡ ፑቲን ሩስያ ሶርያ አሳድ የኬሚካል ጋዝን በዝህዝቧ ላይ በተጠቀመችበት ወቅት አአሜሪካኖች ሶርያን ሊደበድቡ በነበረበት ወቅት ፑተን በመከላከላቸውና በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ድብደባውን በመቃወም ፅሁፍን ማውጣታቸው በአሜሪካኖችና በሱኒ አረብ መንግስታት ጥርስ አስነክሶባቸዋል ፡፡
ሩስያ አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ኢኮኖሚዋን ከቀዝቃዛው ጦነት ወዲህ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣበት ባለማድረጓ ለተደጋጋሚ የምእራባውያን የፋይናንስና የምጣኔ ሃብት ማእቀብ ተጋላጭ አድርጓታል ፡፡ ይህም በተፈጥሮ ማእድናት የበለፀገችው ሩስያ ከአውሮፓ ሃገራት ርካሽ የፋይናንስ አቅርቦትንና ብድርን የምታገኝ ሲሆን አውሮፓውያንም የሩስያን ማእድናትና ነዳጅ ዘይነትና የተፈጥሮ ሃብትን በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተው ኢኮኖሚያቸው ሲሉ ይፈልጉታል ፡፡
በዚህም ምክንያት በዩክሬይን ምክንያት ምእራባውያን በሩስያ ላይ በጣሉት ማእቀብ የተነሳ ሩስያ በትቂ ጥቂት ወራት ውስጥ መንኮታኮቷ ራሳቸውን አውሮፓውያኑን ጭምር አስደንግጧል ፣ ይህም ሩስያ የምጣኔ ሃብትንና የማህበራዊ ቀውስ ውስጥ ከገባች ዳፋው ለአውሮፓም ይተርፋል የሩስያ መንኮታኮት ለአውሮፓም ጭምር ስጋትን ሊደቅን ይችላል በሚል ሰስጋት ሲገባቸው በአንፃሩ አሜሪካኖች ግን ሩስያ በደንብ እንድትቀጣላቸው ነው እሚፈልጉት ፡፡
ከቻይናም ሆነ ከሌሎች የብሪክስ አገራት በተለየ ሁኔታ ሩስያ ከውጭ እንደምትታየው ውስጣዊ ጥንካሬ ያላት አገር አይደለችም ፡፡ የሩስያ ፖለቲካ በሙስና የተዘፈቀና ግልፅነት የሌለው ሲሆን ኩባንያዎቿም እንዲሁ በሙስና የተዘፈቁ ሲሆን የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎም ወደ ግል ሲዛወሩ አብዛኞቹ በጥቂት ኦሊጋርኮች ቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡ ክሌፕቶክራሲና ክሮኒዝም የተንሰራፋባችት ሩስያ አስፈሪ አገር ነች ሲሉ የምእራባውያን መዋእለ ንዋይ አፍሳሾች የሚፈሯት ሃገር ሰትሆን በአንፃሩም የሩስያ ገዢ መደብ ‹‹ኤሊት›› ሃገራቸውን ለመጪው ውድድር አለማዘጋጀታቸው ፣ የሃገራቸውን የተፈጥሮ ሃብት በመላክ ያገኙትን ገንዘብ ወደ ውጪ ሃገራት ባንኮች ማሸሻቸው ሳቢያ በምእራባውያን ላይ የበዛ የምጣኔ ሀብት ጥገኝነት ላይ የተመሰረተው በመሆኑ የሩስያ ኢኮኖሚ ምንም እንኳን እውሮፓውያኑ ራሳቸው በማእቀቡ ሳቢያ ጉዳት ቢደርስባቸውም የበለጠ ግን ሩስያ ተጎጂ ነች ፡፡
አውሮፓ በቆዳ ስፋት ጠባብ ሲሆን በአንፃሩ ሩስያ ግን እጅግ ሰፊ የሆነ መሬት ባለቤት ስትሆን በመሬቷ ውስጥ ያሉት ማእድናትን እንደ አልሙኒየም ፣ ኮባልት ፣ ኮፐርና ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ እና የሌሎችንም የበርካታ ማእድናት የደለበ ሃብት ባለቤት ነች ፡፡ ሩሥያ ይህ ብቻም ሳይሆን በሳይቤሪያ እና በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ አካባባ ከሚገኘው ግዛቷ ሰፊ የማእድናት ክምችት ያላት አገር ነች ፡፡ አውሮፓ ጠባብ አህጉር ቢሆንም ለክፍለ ዘመናት ያደገ ኢንዱስትሪ ባለቤት ሲሆን ሩስያኖች ይህንን የአውሮፓውያንን ፍላጎት እምብዛም አይረዱትም ፡፡
ምእራባውያን በብዛት የሩስያ የፖለቲካ ስርአት ተመችቷቸው አያውቁም ቢባል ማጋነን አይሆንም ፡፡ ምእራባውያን የሩስያን የፊውዳሉን ዘመን ደራሲያንና ፀሀፍትን አብዘተው የሚያደንቁ ሲሆን ከዚያ ውጪ ብዙም ሩስያን በደግ አያነሱም ፡፡ አውሮፓውያን ሩስያን ለማስገበር በርካታ ግዜ ሞክረዋል ለምሳሌ የፈረንሳዩ ጀብደኛው ንጉሰ ነገስት ናፖሌዎን ቦናፖርቴ ሩስያን የወረረ ሲሆን በከባዱ የክረምት ‹ዊንተር› በረዶ አብዛኛው ሰራዊቱ በአርበኞቹ ሩስያውያን ተመቶ አልቆበት ሩስያን ለቆ ወጥቷል ፡፡ የጀርመኑ የናዚዎች መሪ አዶልፍ ሂትለርም ሩስያን ወሯል ነገር ግን እርሱም ሰራዊቱ ተመቶ አልቆበት በሽንፈት ተመልሷል ፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን በቀዝቃዛውም ጦርነት ዘመን ጭምር ምእራባውያን ሩስያን በቀጥታ መውረር አደጋ እንዳለው በመረዳት በኦኮኖሚ መክበብ ፣ ተደጋጋሚ ማእቀብ መጣል ፣ በኔቶ መስፋፋት ሩስያን አጣብቂኝ ውስጥ መክተትን አማራጭ አድርውት ቆይተዋል ፡፡ በቀዝቃዛው ጦርነት ሩስያ የተሸነፈችው በኢኮኖሚ ከምእራቡ ዓለም ጋር መወዳደር ባለመቻሏ ሲሆን እንኳን ከአሜሪካ ይቅርና ከአውሮፓውያኑ ጋር እንኳን የሚወዳደር የኢንዱስትሪም ሆነ የፋይናንስ አቅም ስላልነበራት ከሰባ አመታት በኋላ እጅ ለመስጠት ተገዳለች ፡፡